December 8, 2022
18 mins read

አዶልፍ ሂትለርና ይሁዶች፣ ጭራቅ አሕመድና አማሮች – መስፍን አረጋ

መከራህ ለጊዜው ቢመስልህም ጎጅ
ያጠነክርሃል ድል አያርግህ እንጅ፡፡
ብረት ወርቅ ተብሎ የሚከብረው ገ(ን)ኖ
ካለፈ ብቻ ነው በሳት ተፈትኖ፡፡

Abiy Ahymed

መከራ የሚመጣው ወይ ሊቀብር ወይ ሊያጠነክር ነው፡፡  ወይም ደግሞ ፈረንጆቹ እንደሚሉት አበሳ የሚመጣው ወይ ሊጥል ወይ ሊያነሳ ነው (what doesn’t kill you makes you stronger)፡፡  ባበሳው መውደቅ ወይም መነሳት ደግሞ ያበሰኛው ሳይሆን የተበሰኛው ምርጫ ነው፡፡  አልሸነፍም ያለን ሕዝብ ማንምና ምንም አያሸንፈውምለጊዜው ሊጎዳው ቢችልም፡፡

አዶልፍ ሂትለር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ይሁዲወችን በዘግናኝ ሁኔታ በመጨፍጨፍ በይሁዲወች ላይ ወደር የለሽ ጥፋት አድርሷል፡፡  በኅሊናቸው ላይ ደግሞ መቸም የማይረሱት ዘላለማዊ ጠባሳ ጥሎባቸው አልፏል፡፡  በሌላ በኩል ግን አዶልፍ ሂትለር የፈጸመባቸው ወደርየለሽ ወንጀል ይሁዲወችን በሰባት መሠረታዊ መንገዶች ጠቅሟቸዋል፡፡

  • ሂትለር የጨፈጨፋቸውና ወደፊትም ሌላ ሂትለር ቢነሳ ሊጨፈጭፋቸው የሚሞክረው በማንነታቸው(ይሁዲ በመሆናቸው) ስለሆነ፣ ይሁዲነታቸውን ከማናቸውም ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል፣ ከብረት የጠነከረ ይሁዳዊ አንድነት ፈጥረዋል፡፡
  • ርስት በሺ ዓመቱ ለባለቤቱ ነውና፣ በጦርነት ተሸንፈው የተቀሙትን ያባታቸውን የዳዊትን ግዛት ከሺ ዓመታት በኋላ ባንድም በሌላም መንገድ አስመልሰው፣ የቀረውን ደግሞ በሂደት እንደሚያስመልሱት ለራሳቸው ቃል ገብተው፣ ይሁዲነት የነገሰባት ይሁዳዊት አገር(እስራኤልን) እንዳዲስ መሥረተዋል፡፡
  • የሂትለር ዓይነት ጭፍጨፋ መቸም አይደገምም(never again) የሚል ጽኑ ውሳኔ ወስነው፣ ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም በሚለው ብሂል በቋሚነት እየተመሩ፣ ለሕልውናቸው የሚያሰጋ ማናቸውም ፀረይሁዲ ገና ብቅ ሲል ጭንቅላቱን ብለው ባጭሩ የሚያስቀሩበትን ፍቱን አደረጃጀት ፈጥረዋል፡፡
  • ደም የሚጠራው በደም ነውና፣ በሂትለራዊ ጭፍጨፋ ላይ የተሳተፉትን ዋና ዋናወቹን ናዚወች (በተለይም ደግሞ ጀርመናዊ እና ዩክሬናዊ ናዚወች) አፈንፍነው እየፈለጉ፣ ከተደበቁባቸው ጉሬወች ማንቁርታቸውን ይዘው በማውጣት፣ ለሁሉም ፀረይሁዲወች መቀጣጫ ይሆኑ ዘንድየሚረሸኑትን ረሽነው የሚሰቀሉትን ሰቅለዋቸዋል፡፡
  • ወንጀለኛ በወንጀሉ ማትረፍ የለበትምና፣ የጀርመን መንግስትና ሕዝብ ይሁዲወችን በመጨፍጨፍና ሐብትና ንብረታቸውን በመዝረፍ ያገኙትን የወንጀል ትርፍ፣ በሺ እጥፍ እንዲከፍሉ አድርገዋቸዋል፡፡
  • የጀርመን መንግስትና ሕዝብ በይሁዲወች ላይ የፈጸሙትን ጭራቃዊ ድርጊት መቸም አይረሱት ዘንድ ጭራቃዊ ድርጊታቸውን የጀርመን ታሪክ ዋና አካል አድርገው ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ በማስገደድ፣ በጭራቃዊ ድርጊታቸው ሁልጊዜም እንዲሸማቀቁና ይሁዲወችን ቀና ብለው እንዳያዩ አድርገዋቸዋል፡፡
  • እንዳዲስ የገነቧትን ይሁዲነት የገነነባትን ይሁዳዊ አገራቸውን እስራኤልን፣ ይሁዲወች ሁሉ የሚኮሩባት፣ ጠላቶቿ የሚፈሯት፣ ወዳጆቿ የሚያከብራት የታፈረችና የተከበረች አገር አድርገዋታል፡፡ ቋንቋቸውን ዕብራይስጥንደግሞ ከሞት አንስተው፣ ሕይወት ዘርተው ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያንሰራራ በማድረግ በመላው እስራኤል ላይ አስፍነውታል፡፡

 

ወደ አማራ ሕዝብ ስንመለስ ደግሞ፣ ይህ ሕዝብ በጭራቅ አሕመድ ኦነጋዊ ዘመን የገጠመው ያሁኑ የሕልውና ፈተና ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት በግራኝ አሕመድ ዘመን ከገጠመው የሕልውና ፈተና እጅግ የከፋ ነው፡፡  ያሁኑን የሕልውና ፈተና እጅግ የከፋ ያደረገው ደግሞ በአማራወቹ ነገስታት በነ አጤ ልብነድንግል እና አጤ ገላውዲወስ ከፍተኛ ተጋድሎ የሉባ ጭፍጨፋ እንዳይደርስበት ከተደረገው ከትግሬ ሕዝብ አብራክ የወጣው ወያኔ፣ ከዘመናችን ሉባ (ጭራቅ አሕመድ) ጋር እጅና ጓንት ሁኖ የአማራን ሕዝብ ከጀርባው እየጨፈጨፈውና እያስጨፈጨፈው መሆኑና፣ አማራ መስለው አማራን የሚጨፈጭፉና የሚያስጨፈጭፉ የደመቀ መኮንን እና የተመስገን ጡሩነህ ዓይነት የአማራ ለምድ የለበሱ ፀራማራ ተኩላወች እንዳሸን የፈሉ መሆናቸው ነው፡፡

በሌላ በኩል ግን ሳይደግስ አይጣላምና  ወይም ደግሞ ፈረንጆቹ እንደሚሉት ሁሉም ደመና ጸዳል አለውና (every cloud has a silver lining)፣ ጭራቅ አሕመድ በጭራቃዊ ድርጊቱ የአማራን ሕዝብ ካምሳ ዓመታት በላይ ድብን ብሎ ከተኛበት አዚማም እንቅልፉ ቀስቅሶ፣ ምን ጉድ መጣብኝ ብሎ ክፉኛ ደንግጦ፣ በርግጎ እንዲነሳ አድርጎታል፡፡  ይሁዲወች ሂትለር ሊቀብራቸው አስቦ የጣለባቸውን የመከራ ቀንበር ይበልጥ ለመተሳሰርና ለመጠንከር እንደተጠቀሙበት ሁሉ፣ የአማራ ሕዝብም ጭራቅ አሕመድ ሊቀብረው አስቦ የጣለበትን የመከራ ቀንበር፣ ይበልጥ ለመተሳሰርና ለመጠንከር እንዲጠቀምበት የሚያስችል ትልቅ እድል ተፈጥሮለታል፡፡  የመከራው ቀንበር አስተሳስሮት ጠንክሮ የሚወጣው ደግሞ በሚከተሉት ሰባት መንገዶች ነው፡፡

  • ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ እየጨፈጨፈ ያለውና ወደፊትም ሌላ ኦነጋዊ ወይም ወያናዊ ጭራቅ አሕመድ ቢነሳ የአማራን ሕዝብ ሊጨፈጭፍ የሚሞክረው በማንነቱ (አማራ በመሆኑ) ስለሆነ፣ አማራነቱን ከማናቸውም ጥቃት ለመከላከል የሚያስችል፣ ከብረት የጠነከረ አማራዊ አንድነትመፍጠር አለበት፡፡
  • የወያኔና የኦነግ ልሂቃን እንወክለዋለን በሚሉት የትግሬና የኦሮሞ ሕዝብ ላይ (በተለይም ደግሞ በወጣቱ ትውልድ ላይ) የነዙበት በማንነት ላይ የተመሠረተ የአማራ ጥላቻምክኒያት አልባ ጥላቻ ስለሆነ እየከረረ የሚሄድ እንጅ መቸም ሊወገድ የማይችል ጥላቻ መሆኑን በመገንዘብ ቁርጡን አውቆ፣ መቸም በማይድን ያማራ ጥላቻ ከተመረዘው ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ ጋር ባንድ አገር ውስጥ በመከባበርና በመተባበር እኖራለሁ የሚለውን እንቶ ፈንቶ እርግፍ አድርጎ ትቶ፣ በሉባ ተስፋፊ የተነጠቃቸው ግዛቶች አንዳቸውም ሳይቀሩ ሁሉም የሚጠቃለሉበትና በቀድሞ ስማቸው የሚጠሩበት ካርታ ሰርቶ፣ ስሟ ጦቢያ፣ ባንዲራዋ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ፣ አርማዋ ጥቁር አንበሳ የሆነ የራሱ የአማራ አገር የሆነች አማራነት የገነነባት፣ አማራዊት ጦቢያን ለመመሥረት ቆርጦ መነሳት አለበት፡፡  በዚህ ረገድ ደግሞ በሉባ ተስፋፊ የተነጠቃቸውን (ባዲሱቱ አማራዊት ጦቢያ ካርታ ውስጥ ያጠቃለላቸውን) ያባቶቹ ዐጽመ ርስቶች፣ አንዳቸውም ሳይቀሩ ሁሉንም፣ የፈጀውን ጊዜ ቢፈጅም በውድም በግድም ወደ አማራዊት ጦቢያ እንደሚያስመልሳቸው በይፋ የሚገልጽበት ልፈፋ አማራ (Amhara manifesto) ማውጣት አለበት፡፡  በልፈፋው (manifesto) ላይ ደግሞ በደማቸው አማራ ሁነው ሳለ አማራዊ ማንነታቸውን በሞጋሳና በጉዲፈቻ አማካኝነት ተነጥቀው ኦሮሞ ሳይሆኑ ኦሮሞ ነን እንዲሉ የተደረጉትን እልፍ አእላፍ አማሮች፣ አማራነታቸውን አውቀው፣ የተለጠፋባቸውን የኦሮሞ ስም አውልቀው፣  ወደ ቀድሞ እውነተኛ ማንነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው እንዲመለሱ ለማበረታታት አጥብቆ እንደሚሠራ መግለጽ አለበት፡፡
  • የጭራቅ አሕመድ ዓይነት ኦነጋዊ ወይም ወያናዊ ጭፍጨፋ መቸም አይደገምም(never again) የሚል ጽኑ ውሳኔ ወስኖ፣ ይቺ ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም የሚለውን ብሂል ቋሚ መመርያው አድርጎ፣ ለሕልውናው የሚያሰጋ ማናቸውም ፀራማራ ገና ብቅ ሲል ጭንቅላቱን ብሎ ባጭሩ የሚያስቀርበትን ፍቱን አደረጃጀት መፍጠር አለበት፡፡
  • ደም የሚጠራው በደም ነውና፣ ባማራ ጭፍጨፋ ላይ የተሳተፉትን ዋና ዋናወቹን ፀራማሮች (በተለይም ደግሞ ወያኔወች፣ ኦነጎችና ብአዴኖች) አፈንፍኖ እየፈለገ፣ ከተደበቁባቸው ጉሬወች ማንቁርታቸውን ይዞ በማውጣት ለሁሉም ፀራማሮች መቀጣጫ ይሆኑ ዘንድየሚረሸኑትን መረሸን የሚሰቀሉትን መስቀል አለበት፡፡
  • ወንጀለኛ በወንጀሉ ማትረፍ የለበትምና፣ወያኔወች፣ ኦነጎችና ብአዴኖች የአማራን ሕዝብ በመጨፍጨፍና ሐብት ንብረቱን በመዝረፍ ያገኙትን የወንጀል ትርፍ፣ በሺ እጥፍ እንዲከፍሉ ማድረግ አለበት፡፡
  • የማንነቱ ጠላቶች ከሆኑት ከወያኔወችና ከኦነጎች ጋር ያለው ምርጫ ወይ እነሱን ማጥፋት ወይ በነሱ መጥፋትብቻ ነውና፣ የሞት ሽረት ትግል አድርጎ ወያኔወችንና ኦነጎች ድምጥማጣቸውን ለማጥፋት ቀበቶውን አጥብቆ፣ ወኔውን ሰንቆ፣ በሂወቱ ቆርጦ መነሳት አለበት፡፡  ወያኔወችንና ኦነጎችን የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ ከፍሎ ካጠፋቸው በኋላ ደግሞ፣ የወያኔንና የኦነግን ጭራቃዊ ድርጊት  መቸም አይረሱት ዘንድ ለትግሬወችና ለኦሮሞወች (በተለይም ደግሞ ለወጣቶቹ) ሳያሰልስ በማስተማር ትግሬወችና ኦሮሞወች ካብራካቸው በወጡት ጭራቆች ለዘላለም እንዲያፍሩባቸው ማድረግ አለበት፡፡
  • እንዳዲስ የሚገነባትን፣ ሁሉንም የአማራ ግዛቶች በካርታዋ የምታጠቃልለውን፣ አማራነት የገነነባትን አዲሲቷን አማራዊት ጦቢያን፣ አማራወች ሁሉ የሚኮሩባት፣ ጠላቶቿ የሚፈሯት፣ ወዳጆቿ የሚያከብሯት የታፈረችና የተከበረች አገር ለማድረግ ማድረግ ያለበትን ሁሉ እንደሚያደርግምሎ መገዘት አለበት፡፡  በዚህ ረገድ ደግሞ ወያኔወችና ኦነጎች የአማራን ሕዝብ ባማራነቱ የሚጠሉበት አንዱና ዋናው ምክኒያት የአማረኛ ቋንቋ መሆኑን ተረድቶ፣  አማረኛ ባዲሲቷ አማራዊት ጦቢያ ውስጥ እንግሊዘኛን ሙሉ በሙሉ እንዲተካ አድርጎ፣ ልጆቹን እስከ ከፍተኛ ደረጃ ድረስ ሙሉ በሙሉ ባማረኛ በማስተማር፣ እንደ ጃፓንና ኮርያ አገሩን በፍጥነት የሚያሳድግ ትውልድ በፍጥነት ለመፍጠር በቁርጠኝነት መነሳሳት አለበት፡፡  የሺ ኪሎሜትር መንገድ የሚጀመረው ባንድ እርምጃ ነው፡፡

 

ማጠቃለያ

ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ ለዘላለም እቀብራለሁ ብሎ የመከራ ዶፍ እያወረደበት ይገኛል፡፡  የአማራ ሕዝብ ግን አሻፈረኝ አልቀበርም እስካለ ድረስ በጦር ገበሬነት ከግሩ ጥፍር የማይደርሱት መንጋወቹ ወያኔወችና ኦነጎች ቀርቶ ልዕለ ኃያል የሚባሉትም ሊቀብሩት አይችሉም፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሕልውናውን በተመለከተ ሁለት ምርጫወች ብቻ ቀርበውለታል፡፡  አንደኛው ምርጫ በበላዔ አማራው በጭራቅ አሕመድ ተበልቶ ማለቅ ነው፡፡  ሁለተኛው ምርጫ ደግሞ የይሁዲወችን ፈለግ በመከተል፣ ጭራቅ አሕመድ በሕልውናው ላይ የጋረጠበትን ከባድ ፈተና ፊት ለፊት ተጋፍጦ፣ አስፈላጊውን መስዋዕትነት ከፍሎ ፈተናውን ባሸብራቂ ውጤት በማለፍ፣ የጭራቅ አሕመድን ሕልም አብንኖ፣ የራሱን ራዕይ አውኖ፣  በወያኔና በኦነግ መቃብር ላይ አማራ ባማራነቱ የሚገንባትን አዲሲቷን አማራዊት ጦቢያን መገንባት ነው፡፡  ከነዚህ ከሁለቱ ምርጫወች ውስጥ የትኛውን መውሰድ እንዳለበት የሚወስነው ደግሞ ሌላ ማንም ሳይሆን ራሱ የአማራ ሕዝብ ነው፣ የሚጥመውን የሚያውቀው እሱ ራሱ ነውና፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop