ሹፌሩ ሳያውቅ መሪው መዞር አይችልም ። አውቶማቲክ እና እጅግ ዘመናዊ መኪና እንኳን በመጀመሪያ በተቀነባበረለት ፕሮግራም መሠረት እንጂ በደመ ነፍስ አይጓዝም ። አንድ የአገር መንግሥትም የጠራ እና ዜጎችን ያቀፈ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ መንገድ ይኖረዋል ። ፕሮግራም ና ፖሊሲ ይባላል ። በወጉ በተሰነዱ ፣ ፖሊሲዎቹና ፕሮግራሟች ነው ፤ መንግሥት አገርን የሚያሥተዳድረው ። ህዝብንም የሚመረው ። ህዝብንም ይህንን በመረዳት ነው ከጎኑ የሚሰለፈው ። ወዴት እንደሚወሥድህ ከፖሊሲው አንፃር እያወቅህ “ አንድ የጋራ ማህበረሰብ መፍጠር “ ይቅር እና ሥልጣን አገርቶ ሥልጣኑንን በኃይል የቀማውን ክልል መቆጣጠር ሲያቅጠው ዜጋ ምን ይላል ?
የብልፅግና መንግሥት አሪፍ አሪፍ የኢኮኖሚ ፣የውጪ ጉዳይ ፣ የግብርና ፣የከተማና የገጠር የተለያዩ ፖሊሲዎች ፣ እና የሚኒሥትር መሥሪያ ቤቶች ደንብና መመሪያዎች እንዳሉት ዜጎች ያውቃሉ ።
( ይኼ የጠላቶቻችንን ኦሮሞ ፣ አማራ፣ትግሬ እያሉ መከፋፈል ወዲያ አሽቀንጥረህ ጣለው ። በኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ያለው የማይበላለጥ ዜጋ ነው ። ኢትዮጵያዊ ዘጋ ። የሰው ስብስብ ። …)
እርግጥ መንግሥት የሌለው የክልሎች የፖለቲካ አካሄድን መቆጣጠሪያ መንገድ ነው ። ይህ መንገድ ለፊደራል መንግሥት በግልፅ አልተሠናደለትም ። የለውም ማለትም ይቻላል ። የፊደራሉ መንግሥት በእነዚህ ክልሎች ፣ ፖሊሲዎቼን ላንሸራሽር ካለ የሚያንሽራሽረው ሃሳብ መሪ አልቦ ነው ። እናም በዕውር ድንብሩ ሲያሽከረክር ገደል ቢገባ አይገርምም ።
ዳር ሆነን እንደምንታዘበው ፣ ለመንግሥት የተቀናጀ እና ተመሳሳይ የሆነ የቅጥፈት ሪፖርት በየጊዜው ይደርሰዋል ። የፀጥታና የሠላም መሥፈን ሪፖርትም ለፊደራሉ መንግሥት በየቀኑ ይላክለታል ። የፊደራል መንግሥቱም አገር ሠላም ነው ብሎ የልማት ሥራ ላይ ያተኩራል ። የሚሠራው ትሪሊዮን የወጣባቸው ሥራዎች ግን እንዲወድሙ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ትሪሊዮን ዶላር በየክልሉ ለግጭትና ለሽብር እየበተኑ ነው ። በየክልሉ የሚደረገውን ለመቆጣጠር የሚያሥችል መንገድ የፊደራል መንግሥቱ የለውም ። ያለመንገድ ሃሳቡን ለማንሸራሸር እንዴት ይችላል ? መሪው ለአገር እና ለህዝብ ጠቃሚ ሃሳቡን እንዴት ማስረፅ ይችላል ?
የውጪ ጠላቶቻችን ግን መንገድና መሪ በየክልሉ አላቸው ። በመሪዎቻቸው ተጠቅመውም ፣ በጊዜ የተቀመረ ፣ በቦታ እና በሁኔታ የታጀበ ሽብር እና ቀውስ ለመፍጠር ሌት ተቀን በሚሥጢር ይሰራሉ ። ሃሳባቸውንም ያሰርፃሉ ። ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች በመንግሥት አፍንጫ ሥር በመሪያቸው ተጠቅመው ቀየቀኑ እሣት ይጭራሉ ። የሚሪው ተላላኪ ወጣትም ረብጣ ብር ተሰጥቶታል እና ሌላው ተማሪ ተማረ አልተማረ ደንታ ቢሥ ነው ። በአዲስ አበባ ፖሊሥም ውሥጥ የግብፅ ተከፋይ ፖሊሶች እንደተሰገሰጉ ከኑሮቸው አንፃር መጠርጠር ይቻላል ። በአዲሥ አበባ ዙሪያ ለመመደብ አንድ የኦሮሚያ ፖሊሥ 50 ሺ ብር ይከፍላል ። ይባላል ። ለኃላፊው ። ለአዘዋዋሪው ። ገንዘቡን ግነ ኬት ያመጣል ?
እንግዲህ እነዚህ ናቸው ያልሆነ የውሸት መረጃ ለአብይ ሹክ የሚሉት ። በሃሰት ፈጠራ ያናድዱታል ። ብሬን ወሽ ያደርጋሉ ። የዜግነት ነፃነትን የሚጋፉ ማአት ያበዱ ፖሊሶች በከፍተኛ አመራር ላይ እንደተቀመጡ ማወቂያ መንገዱን ይዘጉበታል ። እናም ከአራጆቹ ጋር በፀጥታ ይጓዛል ።
ዜጋ ግን ያውቃል ። ሥለ አገር እንጂ ሥለ እና ሃያቶላ ደንታ የለውም ።
ዶ/ ር አብይ አህመድ እንደ አገር መሪነታቸው ሥለ አገር እንጂ ሥለ ጠባብ እብድ የፖለቲካ ሰዎች እና ሥለባንዲራቸው የሚጨነቁበት ጊዜ ያለፈ መሆኑንን ዛሬ የሚገነዘቡ ይመሥለኛል ። ….
አሜሪካ እንደ ቀድሞዋ ሶቬት ህብረት ኢትዮጵያን ለመከፋፈል እንደ ጎርቫቾቭ ዶ/ር አብይን ትጠቀማለች ብዬ ማሰብ እጅግ ይከብደኛል ። ይሁን እንጂ ሱሉልታ ኦነግ ሸኔ ቀረጥ ከሰበሰበ የአሜሪካ ዕቅድ እየተሳከ ነው ማለት እችላለሁ ። …
መንግሥት ፣ ማወቅ ያለበት “ ከአንተ በፊት እኔን ያሥቀደመኝ ። “ በማለት “ በፉገራ “ የተካኑ ተልከሲሶች ከፍትህ እያራቁት ነው ። ከሴትና ከሥጋ ውጪ የማይታያቸው ቱባ ባለሥልጣኖች በየክልሉ እና ከአጠገቡ ተቀምጠዋል ። የ 1 % ቱ ጥጋብ የጠቅላለው ደሃ ህዝብ ( የ99% ) የሚመሥላቸው ትላንትን የረሱ ግብዞች መዓት ናቸው ።…
ለእነሱ ፣ አንድ ታላቅ አገርን ማሥተዳደር ማለት ፊውዳልና መኳንንት መሆን ማለት ነው ። በየቀኑ አሥረሽ ምቺው ማለትን ለምደዋል ። በየቀኑ ለህዝብ ሠላም እና ደህንነት መጠበቅ ብሎ የሚሰዋው የመከላከያ ኃይል ፣ የፊደራል ፖሊሥ እና የየክልሉ ልዩ ፖሊሥ ከቶም አይቆጫቸውም ።
እንዴ ! እነዚህ ሰዎች ከደረግ በባሰ አብዮት መጥፋትን ይፈልጋሉ እንዴ ? ማንም ይሁን ማን ሊተርፍ የማይችልበት አብዮት ፀጥ ባለው ፤ ከጠባብ የኦሮሞ ፖለታከኞች ውጪ ባለው ፤ ፖለቲከኛ እና ህዝብ ነገ የሚከሰትበትን መንገድ እነ “ የግብፅ ጉዳይ አሥፈፃሚዎች “ እየጠረጉ ነው ። ነገ በአሰቃቂ መልኩ በራሳቸው ላይ ሰቆቃ እንደሚመጣ ግን የተገነዘቡ አይመሥልም ። እየታረደ ዝም የሚል ፍጡር የለም ። …
ከሀገር የሚበልጥ የለም ። ዛሬ ያለመሪ በየክልሉ እየተጓዘ ያለው የፊደራሉ መንግሥት ፣ ነገ የአንድ ዘመናዊ ሉአላዊ መንግሥት ትክክለኛው አቅጣጫ ፣ ዜግነት ተከብሮ በዜጎች ቅቡል ሃሳብ መመራት እንጂ የ18 ክ/ዘ ኋላ ቀር አሥተሣሠብ መዘመር እንደማያዋጣ እንደሚገነዘብ አሥባለሁ ። መሪው በአጠቃላዩ ዜጋ ሃሳብ እና ፈቃድ መጓዝ ማምን ሲጀምር ፣ ሁሉም “ ናዚስቶች “ ፣ በሰፈሩት ቁና ይሰፈርላቸዋል ።