November 18, 2022
18 mins read

‹‹መዋቅራዊ ማሻሻያ መርሃ-ግብር!!!›› ከዓለም ባንክና አይኤምኤፍ  ሆድቃ፣ ዶላር ፍለጋ በጨረቃ!!! (ክፍል 1) – ሚሊዮን  ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

ኢት-ኢኮኖሚ             /ET-  ECONOMY
በ2022እኤአ የኢትዮጵያ ጂዲፒ 112 ቢሊዩን ዶለር ወይም  6.222  ትሪሊዮን ብር መድረሱ የኢትዮጵያ የብር ምንዛሪ መሽመድመዱን ያሳያል!!!

Worldbank and IMF
 ዶላር ፍለጋ በጨረቃ!!! ላም አለኝ በሠማይ፣ ወተቷንም አላይ!!!

በ2022እኤአ የኢትዮጵያ ጂዲፒ (GDP) መቶ አስራ ሁለት ቢሊዩን ዶለር ሲሆን በኢትዮጵያ ብር ስድስት ትሪሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ቢሊዮን ብር መድረሱ የኢትዮጵያ የብር ምንዛሪ መርከሱን ያሳያል!!!

የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ባንክ ያዘዘላትን መዋቅራዊ ማሻሻያ መርሃ-ግብር ‹‹ስትራክቸራል አጀስትመንትን›› የፖሊሲ ምክረ ሐሳብ ተቀብላ እየተገበረች እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ የዓለም አቀፋዊ ትስስር (ግሎባላይዜሽን) ዓለማችንን ከመካከለኛ መንደርነት ወደ ትንሽ መንደርነት የቀየራት ዓለምአቀፋዊ ንግድ፣ የካፒታል ዝውውር፣ የሰው ኃይል ዝውውር፣ በተለይ መዋለንዋይን ከአህጉር ወደ አህጉር፣ ከአገር አገር ብሔራዊ ድንበር ተሸግሮ ኢንቨስት አድርጎ የመስራት ነፃ ኢኮኖሚ የገበያ ሥርዓት በውድድር ላይ የተመሠረተ የኢኮኖሚ ፖሊሲን መከተል የታዳጊ አገሮች እጣ ፈንታ ብቸኛ አማራጫቸው ሆኖል፡፡ በዚህም መሠረት ዓለም ባንክና አይኤምኤፍ የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦችን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲተገብር ተፅዕኖ በማድረግ እጅና እግሩን ተብትበው ካሰሩት አመታት ተቆጥሮል፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም ባንክ መዋቅራዊ ማስተካከያ (ስትራክቸራል አጀስትመንት) ፕሮግራም ተቀብላ እየተገበረች እንደሆነ በዚህም መሠረት የብርን የመግዛት አቅም ማዳከመ ( Devaluation) የመንግሥትን ወጪ መቀነስ

የታክስ መሠረቱን ማስፋት፡ የአገሪቱን የታክስ መሠረት ያሰፋሉ ተብለው እየተተገበሩ የሚገኙ አዳዲስ የታክስ ዓይነቶችም የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ያዘዛቸው የፖሊሲ አቅጣጫዎች ውስጥ የሚመደቡ መሆኑ ተጠቆመ፡፡

ሊብራላይዜሽን (ኢኮኖሚውን ክፍት ማድረግ) በኢኮኖሚው ውስጥ ያለውን ግዙፍ የመንግሥት ሚና ወደ ግሉ ዘርፍ ማሻጋገር ባለመቻሏ  እና መንግሥት የሚያደርገውን ኢኮኖሚያዊ ድጎማ ማቆም የዓለም ባንክ ፈጣን ስትራክቸራል አጀስትመንት እንድትተገብር ማዘዙን፣ ይህንንም የኢትዮጵያ መንግሥት ተቀብሎ በመተግበር ላይ እንዳለ የሰሜኑ የትግራይ ጦርነት ተጀመረ፡፡

 (1) የውጭ ምንዛሪ ተመንና የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም

የውጭ ምንዛሪ ተመንና የብርን የመግዛት አቅም ማዳከም (Devaluation) በአገር ሃብት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረውና በኢኮኖሚው ውስጥም በከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ማስከተሉ እውን ሆኖል፡፡ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ከአመት ወደ አመት እየረከሰ መሄድ ማለትም፣ የአንድ ዶላር የብር ተመን በ1991 እኤአ 2.05 ብር የነበረ ሲሆን፣ ከ1992 እስከ 1994 እኤአ ወደ 5 ብር፣ ከ1995 እስከ 1999 እኤአ 5.88 ብር፣ ከ2000 እስከ 2004 እኤአ 8.15ብር፣ ከ2005 እስከ 2008 እኤአ 8.65 እስከ 9.67 ብር አንድ አሃዝ እየረከሰ ሄድ፡፡  ከ2009 እስከ 2015 እኤአ የአንድ ዶላር የብር ተመን ወደ ሁለት አሃዝ እየረከሰ ከ12.39 ብር ወደ 21.83 ብር፣ ከ2016 እስከ 2022 እኤአ ከ22.39 ብር ወደ 51.00 ብር  የብራችን የመርከስና የብር የመግዛት አቅም መውደቅ ዋና ምክንት የተደላደለና የረጋ የውጭ ምንዛሪ ተመን አለመኖሩን በቀላሉ ለመረዳት ይቻላል፡፡

ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እድገት በተለይም  በ2022እኤአ ብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (GDP) 112,000,000,000 (መቶ አስራ ሁለት) ቢሊዩን ዶለር ሲሆን በኢትዮጵያ ብር 6,222,000,000,000 (ስድስት ትሪሊዮን ሁለት መቶ ሃያ ሁለት ቢሊዮን ) ብር መድረሱ የኢትዮጵያ የብር ምንዛሪ በመርከሱ የተነሳ የመጣ የቁጥር ግዝፈት (አንድ ዶላር በሃምሳ አንድ ብር) በመመንዘሩ የተገኘ ስሌት ሲሆን የኢኮኖሚ እድገትን አያሳይም የኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ ሆና አንድ ነጥብ ሰባት ትሪሊዮን ብር የመሠረተ-ልማቶች ኪሳራ፣ ስምንት መቶ ሽህ ወጣቶች ህይወት መርገፉን፣ ብዙ ሽህዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው፣ ብዙ መቶ ሽህዎች ቀያቸውን ለቀው በሰፈሩበት ወዘተ ኢኮኖሚው ተመነደገ ማለት አላዋቂነት ነው፡፡ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ‹‹ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ ተንከባለለ እንደ ሙቀጫ!!!›› ተብሎለታል፡፡ በጥቁር ገበያ አንድ ዶላር ከ82 እስከ 84 ብር ብሎም 112 ብር ድረስ ተመንዝሮ ነበር፡፡

“The Zimbabwean 50 billion-dollar note is worth just 33 U.S. cents…….10 trillion Zimbabwean dollars , which is worth about $8 on the black market. Jan 16,2009.”………………….….(1)

በዚንባብዌ የኢኮኖሚ ቀውስ ዘመን የሃምሳ ቢሊዮን ዶላር ኖት ዋጋው ሠላሳ ሦስት የአሜሪካ ሳንቲም ነበር፡፡ በተመሳሳይ አሥር ትሪሊየን የዚንባዌያን ዶላር ኖት ስምንት የአሜሪካ ዶላር ዋጋ በጥቁር ገበያ ዋጋ ነበረው፡፡ ኢትዮጵያ ከዚንባዌ ብትማር፣ አብይም ከሙጋቤ ቢማር ይመረጣል!!!

የብር መንዛሪ የመርከስ ሁኔታ በዓለም አቀፍ ንግድ ገበያ የኢትዩጵያ ብር የመሸጥና የመግዛት አቅም እንደተሸመደመደ ያሳያል፡  አገሪቱ በውጪ ንግድ የምትልካቸው ምርቶች ዋጋ መቀነስን አስመዝግቦል፡፡ እንዲሁም አገሪቱ በገቢ ንግድ የምታስገባቸው ካፒታል ጉድስ እቃዎች ዋጋ በመጨመሩ የዶላር  የመግዛት አቅም  በመጨመሩ ሃገሪቱ በገቢ ንግድ ተጎጂ ሆናለች ማለት ነው፡፡ በመሆኑም የብሄራዊ አማካይ ጠቅላላ አመታዊ ምርት (GDP) ከቢሊዩን ብር ወደ ትሪሊዩን ብር እምርታ ማሳየቱ የኢኮኖሚ እድገትን አያመላክትም፣ የብር መርከስንና የመግዛት አቅም መቀነስን ነው የሚያሳየው፡፡

እንደ ዋስ ኮንሰልቲንግ በዊል ኮንሰልታንት የተደረገው ጥናታዊ ዶሴ መሠረት የአማካሪ ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ይርጋ ተስፋዬ በጥናት የተዳሰሰው የውጭ ምንዛሪ ቀውስና አዙሪትና መፋትሔዎቹ  እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡…………………………(2)

‹‹ ዲቫሉዌሽን ኤክስፖርትን አላሳደገም፡- በተለይ የውጭ ንግድን ለማበረታታትመንግሥት የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም (ዲቫልዩ) ማድረጉ ምንም ዉጤት ያላመጣ መሆኑን አመልክቷል፡፡ የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም ማድረግ ኤክስፖርትን የረታታል የሚል ጽንስ ሃሳብ የለም ያሉት አቶ ይርጋ ብርን በማዳከም ኤክስፖርን አበረታታለሁ በማለት መንግሥት የወሰዳቸው እርምጃዎች እንዳልሠሩ ጠቁመዋል፡፡ በጥናታቸው መገንዘብ እንደቻሉትም እኤአ ከ2008 በፊት በዓመት 2500 ላኪዎች ፈቃድ ወሰዱና ያደሱ ሲሆን በ2019 ቁጥሩ ወደ 6000 ማደጉን በ2021 ላይ ደግሞ ፈቃድ የወሱት ላኪዎች ቁጥር 16000 መድረሱን አመላክተዋል፡፡ ይህ የሆነበትም ምክንያት የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ዕድል የሚኖረው የኤክስፖርት ፈቃድ ሲኖረው ነው የሚል አስተሳሰብ በመፈጠሩ ነው፡፡ ይህም የንግዱ ማህበረሰብ የኤክስፖርት ንግድ አትራፊ ይሁን አክሳሪ መገምገም ሳያስፈልገው የውጭ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ሲል ብቻ የኤክስፖርትንግድን እንዲያማትር ሊያደርግ ይችላል፡፡››

በመደበኛው የባንክ አገልግሎት ከባንክ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ያልቻሉ ኤክስፖርተሮች ወደ ጥቁር ገበያና የጠረፍ አካባቢ ዶላር ፍለጋ በመሄድ አንድ ዶላር እስከ 78 ብር (ቆይቶም እስከ 112 ብር) በመክፈል ከባንክ ከሚመነዘርበት ዋጋ በላይ ዶላር እንደሚገዙ በጥናቱ ተረጋግጦል፡፡ በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ብዙ ፋብሪካዎች መዘጋታቸውንና ከፊሎቹም አምራቾች ከአቅማቸው በታች በማምረት ላይ እንደሚገኙ ጥናቱ አረጋግጦል፡፡ በጣም ድጋፍ የሚደረግላቸውና ተለምነው  በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ሼድ ተሠርቶላቸው የገቡ ኤክስፖርተሮች ጥሬ የምርት ግብዓት ለማስመጣት 136 ዶላር ወስደው ያመረቱትን ምርት ኤክስፖርት አድርገው የተገኘው ገቢ ግን 100 ዶላር ብቻ ነው፡፡

‹‹የታመመው ሙሉ ኢኮኖሚው በመሆኑ መታከም ያለበት ሙሉ ኢኖሚው ነው፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የአገሪቱ ሰላምና መረጋጋትም ወሳኝ በመሆኑ፣ ሰላም እስካልሰፈነ ኢኮኖሚው ጥሩ ሊሆን እንደማይችል፣ኢኮኖሚው ጥሩ ካልሆነ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ችግር ሊፈታ እንደማችል አመልክተዋል፡፡››

‹‹የውጭ ምንዛሪ እጥረቱን ለመፍታትም ሆነ አጠቃላይ የአገሪቱ ኢኮኖሚን ለማሳደግ መንግሥት ለኢኮኖሚውና ለንግድ እንቅስቃሴው ከሌሎች በተለየ ቅድሚያ መስጠት እንደሚኖርበት ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ለመዋጋትም ሆነ የህዳሴ ግድቡን ለመጠበቅም ዶላር ያስፈልጋል፡፡ ለእያንዳንዱ ጥይት ዶላር ያስፈልጋል፡››

‹‹የግብርናው ዘርፍ የአገሪቱ ዋነኛ የውጭ ንግድ ገቢ አመንጪ ሆኖ ሳለ ባለፈው አሥር ዓመታት በአማካይ ከጠቅላላ ወደ አገር ከገባው የካፒታል ዕቃ ግዢ ውስጥ የግብርና ካፒታል ዕቃ ድርሻ ሁለት በመቶ ብቻ እንደሆነ በመጥቀስ ግብርናው መደገፍ እያለበት ያልተደገፈ ዘርፍ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡››

‹‹በአንፃሩ ግን የኢንዱስትሪ የካፒታል ዕቃዎች ግን ከ 20 እስከ 25 በመቶ በየዓመቱ እንዲገባ መደረጉ ይህ ያስገኘው ውጤት ግን የውጪ ንግዱ ላይ አለመታየቱን በመጠቆም፣ ይህ ጉዳይ እንዲፈተሸ ጠይቀዋል፡፡ ››

‹‹በአጭር ጊዜ ዕቅድ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መከፋፈል ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ብቻ ማስገባት የሚለው አንዱ መፍትሔ ነው፡፡››በማለት ጥናቱ ይደመድማል፡፡

 

‹‹የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቌም (አይኤም ኤፍ)እኤአ የ2023 የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት 5.7 (አምስት ነጥብ ሰባት) በመቶ እንደሚያድግ ተንብዩ የነበረ ቢሆንም አዲስ ባወጣው የዓለም ምጣኔ ሀብት ዳሰሳ ሪፖርት ትንበያ በ0.4 ቀንሶ 5.3 በመቶ አደረገ፡፡ ››…………..(3)

‹‹አይ ኤም ኤፍ በ2022 እኤአ አስራአንደኛ ወር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 3.8 በመቶ እንደሚያድግ ትንበያውንም አስቀምጦል፡፡ ተቆሙ በ2027 እኤአ የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት በሰባት በመቶ ያድጋል ብሎል፡፡››

‹‹አይኤም ኤፍ በ2022 እኤአ የኢትዮጵያ የንግድ ሚዛን ጉድለት የጥቅል አገራዊ  ምርቱን 4.3 በመቶ እንደሚሆን አስቀምጦል፡፡ ››

‹‹አይኤምኤፍ በ2022 እኤአ የሸቀጦች ዋጋ ንረት 34.5 በመቶ እንደሚሆን ገምቶ ሲሆን ወደ 33.6 በመቶ ዝቅ አድርጎታል፡  በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ከሐምሌ 2013 እስከ ሰኔ 2014 ዓ/ም የነበረው ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት አስመልክቶ ካወጣው 33.7 በመቶ የሚል ቁጥር ጋር ተቀራራቢ ነው፡፡››

በማጠቃለያ በኢትዮጵያ የጦርነት ኢኮኖሚ  የሸቀጦች ዋጋ ንረት በተለይ በትግራይ ውስጥ ኩንታል ጡፍ 17000 (አስራሰባት ሽህ ብር)፣ የመኪና ነዳጅ በሊትር 300 (ሦስት መቶ ብር)፣ የምግብ ዘይት 2200 (ሁለት ሽህ ሁለት መቶ ብር)፣ አንድ ቢራ 250 (ሁለት መቶ ኃምሳ ብር)፣ሳፍት 150 (መቶ ኃምሳ ብር)፣ ኪሎ ጨው 200 (ሁለት መቶ ብር)፣ ክብሪት 20 (ሃያ ብር)፣ ወዘተ ጦርነት ክልልህ ውስጥ እንዳይገባና ህዝብ እንዳይሰቃይ ከትግራይ ህዝብ ተማሩ፡፡ ጦርነት ጥቂት ሰዎች የሚከብሩበት ንግድ ነው፡፡

ጦርነት መቼም የትም አይደገም!!!

ምንጭ፡-

(1) https://www.nytimes.com>africa

(2)በጥናት የተዳሰሰው የውጭ ምንዛሪ ቀውስ አዙሪትና መፍትሔዎቹ/ሪፖርተር ጋዜጣ 12 ቀን ጁን 2022

(3) አይኤም ኤፍ የኢትዮጵያን የ2023 ምጣኔ ሃብት ትንበያ ወደ 5.3 በመቶ ዝቅ አደረገ/ ሪፖርተር ጋዜጣ ኦክቶበር 12 ቀን 2022

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
Go toTop