ወደ ቅሊንጦ እስርቤት ያመሩት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እስረኞችን እንዳይጠይቁ ተከለከሉ

UDJ PR
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ አቶ አስራት ጣሴ፣ አቶ ሙላት ጣሰው እና አቶ ዳንኤል ተፈራ ሚያዚያ 1 ቀን 2005 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከከተማ ውጭ ወደሚገኘውና መንገዱ እጅግ አስቸጋሪ ወደ ሆነው ቅሊንጦ እስርቤት  እስረኞችን ለመጠየቅ ቢሄዱም ተፈትሸውና መታወቂያ አስይዘው ወደ ውስጥ ገብተው ለ45 ደቂቃ የሚሆን እንዲጠብቁ ተስፋ ከተሰጣቸው በሁዋላ ሃላፊው የሉም ለስብሰባ ስለወጡ ስልክ አያነሱም በሚል ተራ ሰበብ እንዳይገናኙ መደረጋቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አስታውቋል፡፡

የህዝብ ግንኙነቱ እንደገለፀው አመራሩ ወደ እስርቤቱ በር እንደደረሱ መታወቂያ ከጠየቋቸው የእለቱ ሰራተኞች፡- ‹‹መጠየቅ ምትፈልጉት ግንቦት ሰባቶችን ነው ወይ?›› የሚል አስደንጋጭ ጥያቄ ቀርቦላቸዋል፡፡ አመራሮችም ‹‹አይ እኛ የምንጠይቀው ግንቦት ሰባቶችን ሳይሆን የፖለቲካ እስረኞችን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ብላችሁ መጥራታችሁ ትክክል አይደለም›› በማለት አነጋገራቸውን እንዲያርሙ አሳስበዋል፡፡ ሰራተኞችም፡- ‹‹እኛ ሁልጊዜም ግንቦት ሰባቶች ነው የምንላቸው›› ካሉ በኋላ መታወቂያ ይዘውና ፈትሸው ወደ ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡

አራቱ ከፍተኛ አመራሮች ወደ ቂሊንጦ እንዲያመሩ ያደረጋቸው በተደጋጋሚ በፖለቲካ እስረኞች ይደርሳል የሚባለውን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት እንዲሁም ግፍና በደል ይደርስብናል የሚል ጥቆማ ከእስረኞች በመድረሱና እሱንም ከእስረኞች ለመስማትና አጠቃላይም ስላለው አያያዝ ለመወያየት እንደሆነ የህዝብ ግንኙነት ክፍል አስታውቋል፡፡ ነገርግን የሚመለከታቸው አካላት ማነን መጠየቅ እንደሚፈልጉ ከመዘገቡ በሁዋላ ጠብቁ በማለት እንደምንገምተው እላይ ካሉ ባለስልጣናት ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በሁዋላና ብዙ ከጠበቁ በሁዋላ መጠየቅ እንደማይችሉ፣ ምክንያቱም ሃላፊው በመውጣታቸውና ስልክ ባለማንሳታቸው እንደሆነ የሚል ሰበብ በመናገር የአንድነት አመራሮች ጊቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ካልገደሉ አያቆሙንም – ሃብታሙ አያሌዉ (የአንድነት አመራር) ሰልፉን በተመለከተ

ይህ ድርጊትም አሁንም ገዥው ፓርቲ መሰረታዊ የሆኑ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማፈን ለመቀጠል መቁረጡን ከሚያሳዩ ሁነቶች አንዱ ነው በማለት የህዝብ ግንኙነት ይገልፃል፡፡

 

1 Comment

  1. Can you believe this? The woyane bandits function in the same style they functioned in the bush. How is this possible. the visitors were searched and stripped and were told to wait outside. then the woyane told them the boss is gone to a meeting. I thought the visitors wanted to see the prisoners, not the boss.

    Ethiopia is ruled by stupids like these woyanes must be a world record.

Comments are closed.

Share