ችግርን ከነ ምንጩ ማለባበስ እና ማሳነስ ከኢትዮጵያ ምድር ይደምሰስ !

ከረጂም ዓመታት የኢትዮጵያ ምስቅልቅል  ዘመናት ጀምሮ ያለፈዉን እና የነበረዉን በማዉገዝ እና በመደለዝ ፍሬ ቢስ የጥላቻ ስብከት አገሪቷን እና ህዝቧን ከድጡ አዲስ ጎጂ ሠሪ በማድረግ በተመሰቃቀለ የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ወጥመድ ዉስጥ አስገብቷል፡፡

ከአራት ዓመት( ፬) ዓመት በፊት የነበረዉ ቀዳሚ ኢህአዴግ  አገሪቷን እና ህዝቧን ከቀደሙት ስርዓቶች ጋር ፍርኃት እና የበታችነት ስሜት የወለደዉ ጥላቻ መንፈስ ለሰላሳ ዓመታት ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያዉያን እና የቀደሙት መንግስታት ወቃሽነት ተጠምዶ ስለነበር ኢህአዴግ በአገር እና ህዝብ ላይ ያደረሰዉ ወደር የለሽ ግፍ እና መድሎ ሊታየዉ አልቻለም ነበር ፡፡

አበዉ “ራስ ሲመለጥ ፤ ቃል ሲያመልጥ አይታወቅም ” እንዲሉ  የነበረዉ የዓመታት ድርብርብ ብሄራዊ በደል በኢህአዴግ  በጥላቻ የማናገር እንጂ በተጠያቂነት እና በኃላፊነት ህዝብን የመስማት ጠባይም ሆነ ልምድ ስላልነበረዉ በጥላቻ ተፀንሾ  በጥላቻ ፈራርሶ  ግን አሁንም በማንአለብኝነት ተኮፍሶ የሚገኝ ነዉ ፡፡

ይህም የሆነዉ ለዛሬዋ ኢትዮጵያ በመከራ አዉድማ ላይ መገኘት ችግሩም ሆነ መንስዔዉ ብቸኛዉ እና ዋነኛዉ ኢህአዴግ መሆኑ በተለያየ መንገድ በሽፍንፍን መታለፉ ነዉ፡፡

ዛሬ ላይ ኢህአዴግ ካለፉት ረጂም ዓመታት ከሰራዉ የአገር እና ህዝብ በደል አዲስ እና የተለየ ነገር የለም ፡፡ የሚለይ ነገር ቢኖር ቀደም ሲል በህዝብ እና ሠባዊ ክብር ላይ የሚደርሰዉ አድሎ እና መድሎ እንዲሁም በአገር ሉዓላዊነት ላይ የሚያሳስበዉ አደጋ በግለጭ እና በማን አህሎኝነት ከዉስጥ እና ዉጭ ጠላቶች ጋር የሚከወን መሆኑ ነዉ ፡፡

ዛሬ በኢትዮጵያዉያን ላይ በማንነት ላይ ያተኮረ የዘር ማጥፋት፣ ስደት ፣ ዕንግልት እና ዉርደት ፣ በኢትዮጵያ የግዛት አንድነት ላይ የሚደረግ ክህደት እና ቅርምት …. ላለፉት ፴ ዓመታት ከነበረዉ የሚለይበት ቢኖር ይህን ያህል በአገር እና በህዝብ ላይ የሠባዊ እና ብሄራዊ ጥፋት እና ክህደት የፈፀሙት በወንጀላቸዉ ሳይጠየቁ ዛሬም በድርጊታቸዉ እንዲገፉበት በራሱ በኢህአዴግ ፈቃድ ያገኙ መሆናቸዉ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  “ኋላ-ቀር አስተሳሰብ ባላቸውና በአረመኔዎች የሚመራ ምስኬን ህዝብና አገር” ትችት መልስ! - ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

ለዓመታት ኢትዮጵያዊነት ደመኛነት ፣ ኢትዮጵያዊ ማንነቶች ወንጀሎች ፣ የኢትዮጵያን ግዛት እና የባህር በር ኣሳልፎ ለጠላት መስጠት እና ህዝብን  ጋት በማይሞላ መሬት ማጋደል ፣ ኢትዮጵያዊነት ባይተዋርነት …..በማድረግ ኢትዮጵያ በታሪክ ገጥሟት የማይታወቅ የዜጎች ሞት እና መፈናቀል፣ የመልካም አስተዳደር ዕጦት ፣ድህነት  የመሳሰሉት የተከሰቱት በኢህአዴግ የአመራር ድክመት እንጂ በኢትዮጵያዉያን ኃጢያት አለመሆኑ ይታወቃል ፡፡

ሆኖም ኢህአዴግ ራሱ የዚህች አገር ችግር እና የችግር ምንጭ  መሆኑን የሚነግረዉም ሆነ የሚነገረዉን አስቀድሞ በጠላትነት ፍረጃ ባለዉ ፍርኃት ወለድ ጥላቻ ከኔ በላይ ላሳር በሚል ልክፍት ዛሬም በዚህች አገር እና ህዝብ ላይ ለሚደርሰዉ የመከራ በረዶ  ችግር እና ምንጭ ወደ ኋላ እና ወደ ዉጭ ይልጥፋል ፡፡

የምንም ነገር በሽታ እና መንስዔ የሚነሳዉ ከዉስጥ እንጂ ከዉጭ ሆኖ አያዉቅም ፡፡  በከብቶች በረት የሚገኙ ዕንስሶች ጥቃት የሚጀምረዉ ከዉስጣቸዉ በሚከሰት የአብሮነት ትስስር ሲሰረሰር ብቻ ነዉ ፡፡ ለዚህ ነዉ አህአዴግ ትናንት ኢትዮጵያን በደም እና በአጥንት መስርተዉ እና ጠብቀዉ ያቆዩትን ኢትዮጵያን ሲኮንን ጨልሞበት ዛሬ  “ሌባሲሰርቅ ይስማማል  ሲከፋፈል ይጣላል ” እንዲሉ አባት እና ልጂ የሚያስጨንቃቸዉ የዚህች አገር የግዛት አንድነት እና የህዝቦች ሉዓላዊነት ሳይሆን የስልጣን እና የጥቅም ግጭት መሆኑን በማዳፈን  ረመጡ በሚያቃጥላት አገር  በጭለማ  ዉስጥ ሆነዉ በህዝብ እና አገር መስዋዕትነት የራሳቸዉን ብርኃን ይናፍቃሉ ፡፡

ለሁላችንም እንደ ህዝብ አገር በጋራ ጎጆነቷ እንድትቀጥል  ይህችን አገር ለዘመናት በጥፋት ቋያ ረመጥ ዉስጥ እንድትነድ ምክነያት የሆነዉ ኢህአዴግ በአገር እና በህዝብ ላይ ላደረሰዉ መጠነ ሰፊ ጥቃት እና ክህደት ይቅርታ እንዲጠይቅ ፣ በጥፋቱም እንዲጠየቅ እስካልሆነ ጊዜ ድረስ ችግርን ወደ ሌላ መግፋት እና ዕዉነትን በማክፋፋት  ማለባበስ እና መድበስበስ ለተዉልድ እና ለአገር ፋይዳ ሳይሆን ባልበላዉ እና ባልኖረበት ከፋይ  እንዲሆን  ዕዳ ማስተላለፍ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያውያን ሴቶች ለምን በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ በብዛት አይሳተፉም

የአገራችንን ጥንታዊ ብሂል“ ነገርን ከስሩ ፤ ዉኃን ከምንጩ ” መሆኑን ተገንዝበን እንደ አገር  ችግራችንን ፣ ምንጩን እና መድኃኒቱን  ከእኛ በላይ ሠማይ ብቻ መሆኑን በመረዳት እና በመረዳዳት መርህ ካለፈዉ ተምረን ፤ዛሬ ተባብረን ፤ በዓላማ እና በግልፅ መኖርን የኢትዮጵያዊነትን  ህማም መከተል ይኖርብናል ፡፡ እንደ አገር ለዘመናት ከተጣባን ፈርጀ ብዙ ችግር እና መከራ የምንፋታዉ ችግሩን ከመነስዔዉ በመንቀስ ፣መዉቀስ እና መደምሰስ እንጂ ወደሌላ በመግፋት እና በማጥላላት ማለፍ ብሶት እንጂ ትሩፋት አያስገኝም ፡፡

“የአገር አንድነት፣ሉዓላዊነት  እና  ነጻነት ያለህዝባዊ  ተሳትፎ  ህልም ነዉ ፡፡”

“አንድነት ኃይል ነዉ” !!!

NEILLOSS Amber

2 Comments

  1. ገጣሚና ከያኔው፤ ዘፋኝና ሸላዪ አልቃሽና አስለቃሹ ግጥምና ዜማ እየቋጠሩ ለዘመናት ሃገራችን ኢትዮጵያን ሲያወድሷት፤ አልፎ ተርፎም በየጊዜው የቤተመንግስት ተረኞች የሆኑትን ግፈኞች ሲወርፉበት ኖረዋል። አሁንም ይህኑ ቅኔ፤ ሰምና ወርቅ፤ ተረትና ምሳሌና ሌላም ነገር ተላብሶ በማንበብና በመስማት ላይ እንገኛለን። ጊዜው ረዘመ እንጂ አንድ ልጅ ጠበንጃ ባነገቱ የግፍ ሃይሎች ይገደልና ይሞታል። ታዲያ አስለቃሽ ተቀጥሮ፤ ሰው ደረቱን እየደቃ ስለተሰናበተው ልጅ እየተገጠመ እየተተኮሰ እየተፎከረ ይለቀሳል። በዚህ መካከል አስለቃሿ ከመሃል ሆና እንዲህ አለች። “ያን ማዶ ተራራ እርጥቡ ጋረደው ገብቶ የነደደው ደረቅ ደረቁ ነው”። ሰው ከፍርሃቱ የተነሳ አንዳንድ ከለቅሶው ሽልክ እያለ ወደ ቤቱ ሄደ ሌላው ደግሞ የአስለቃሿን ነጠላ ጎንተል አርገው ተይ ፓለቲካ ነገር አትናገሪ ሲሏት ” አስለቅሺ ብላችኋል እያስለቀስኩ ነው” በማለት ያዋከቧትን ረስታ ቀብሩ በሰላም ተከናወነ። ይህ ከላይ ካለው መጣጥፍ ጋር ምን አገናኘው ይል ይሆናል አንባቢ። እኮ በሉ ረጋ። “ችግርን ከነምንጩ ማለባበስና ማሳነስ ከኢትዮጵያ ምድር ይደምሰስ”። ስንደመስስ፤ ሲጨፈልቁን እንደገና ስንቆም፤ ቆመንም ስንገዳገድ ይኸው ዛሬ በዘር አፓርታይድ ፓለቲካ ተጠፍረን ሰለጠን አወቅን ብለን ወገናችን መጤ ነህ በማለት በማረድ ላይ እንገኛለን። እጅግ የሚያሳዝነው ተምረናል አውቀናል መጥቀናል በማለት ዶ/ር፤ ፕሮፌሰር፤ እንጂኒየር ወዘተ የሚሉ ተስፋ የለሽ የስም ቅጥያን የያዙ የምሁር ድውያኖች የዘር ፓለቲካን ሲያቀነቅኑ ከመስማት የበለጠ ሞት የለም። ራሳቸው ዝንቅ በሆነ ህብረተሰብ (Pluralistic Society) ውስጥ እየኖሩ ወገን በሃገር ቤት እንዲገዳደል በሃሳብና በገንዘብ የሚያግዙ የቁም ሙታኖች አስገራሚ ፍጥረቶች ናቸው። በመሰረቱ መደምሰስ ያለበት በዘርና በቋንቋ ተጠፍሮ የተያዘው የአስተሳሰብ ስልታችን ነው። ግን ይቻላል ወይ?
    ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም እንዲሉ ትላንት ያለቀሱ አይኖች ዛሬም ካነቡ፤ ፍትህ ያጡ ወገኖቻችን ዛሬም ፍትህን ፍለጋ ሲፋለሙ በሃሰት ተወንጅለው ዘብጥያ ከወረድ የመደመር ስሌቱ ተጣርሷል ማለት ነው። ለእኔ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ማለት የጠገበን አውርዶ ሌላ የተራበን በወረፋ ማስቀመጥ ማለት ነው። ሌላው ሁሉ የጊዜው የከበሮ ድምጽ እንጂ ፍሬ የለውም። በመሰረቱ የሃበሻው ምድር ጠላቶች 90% እኛው በእኛው ስንሆን ቀሪውን ደግሞ ነጩና አረቡ ነዳጅ የሚያርከፈክፉበት ጭድ ነው። በቅርቡ የተመድ ዋና ሰው ስለ ትግራይ የተናገረውን ሃሳብ ለፈተሸ ሰው እነዚህ ሰዎች የእኛን ያለ ማቋረጥ መገዳደል እንደሚፈልጉ ቁልጭ አርጎ ያሳያል። በአሜሪካ የሚዘወረው ተመድ ሸፋፋ አስተሳሰብን ያዘለ የአሜሪካና የአውሮፓ ተወካይ እንጂ ሌሎችን ሃገሮች አይወክልም። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ተመድ እንደተሰበሰበው ጊዜና ብዛት፤ የመግለጫው ጋጋታ፤ የአሜሪካው ስቴት ዲፓርትመንት የወያኔ ጠበቃ መሆን ሁሉ ሲደመር የሚያሳየው አንድ ነገርን ብቻ ነው። ተመድም ሆነ አሜሪካና አውሮፓ እፎይ የሚሉት ሃገሮች ሲፈራርሱ ብቻ ነው። ለምን ተመድ ስለ ሶሪያ፤ ኢራቅ፤የመን፤አዘርባጃንና አርሜኒያ ወዘተ ከደርዘን በላይ አልተሰበሰበም? እፎይ የሚሉት ሃገሮች እንደ ሊቢያ ፍርስርሳቸው ሲወጣ ብቻ ነው። ስለዚህ ነገርን ከምንጩ ለማድረቅና የአጥፊዎችን ክፋት በበጎ ተግባር ለመተካት ራስንና አስተሳሰብን መለወጥ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል። ዛሬ ሰው ሁሉ በወሰለተበት ዘመን ላይ እንገኛለን። ግን ራስን ከዚህ የክፋት ግርግር አርቆ ዘርና ጎሳን ሃይማኖትና ቋንቋ ተገን ሳያረጉ ሰው ለሆነ ሁሉ ሰው ሆኖ ለመቆም ለእኔ፤ የእኔ የሚለውን የአራዊት አስተሳሰብ ከራስ ማራቅ ይኖርብናል። ይደምሰስ ስንል ደምሳሽና ተደምሳሹ ማን ነው? ሃሳቡ/ የሃሳቡ አፍላቂዎች/ችግራችን/ኸረ ስንቱ የምድሪቱ አሸንክታብ ብዙ ነው። አንድ ሲላላ ሌላው ይጠብቃል። የጠበቀው ሲፈታ ሌላው ቋጠሮ ያፈተልካል። አታድርስ ነው። የጎጃም ገበሬ እንዲህ ብሎ ነበር።
    “አባይ በጣና ላይ እንዴት ቀለደበት ለአንድ ቀን ነው ብሎ ዘላለም ሄደበት”። እኮ እስቲ ተናገሩ ሊመጣ ያለውን አሁን ላይ ተቀምጦ የሚነግረን አለ? በጭራሽ፡ በመጨረሻ ከሃገር ቤት በስልክ በተነገረኝ አንድ ነገር ልዝጋ። ልጅቷ ሁሌ ያመኛል ትላለች። ህመሟ ግን ጭራሽ አልታወቀም። ታዲያማ አንድ ነብይ ነኝ ከሚል ሰው አዲስ አበባ ይወስዷታል። ከዚያም ከሆዴ ነፍስ ያለው እባብ ወጣልኝ ብላ ስትነግረኝ። ለጊዜው ደንገጥ አልኩና የቀረ እንዳይኖር ተመልሰሽ ሂጂ ስላት በቁጣ ስልኩን ዘጋችብኝ። ህዝብን የምናታልለው እንዲህ እያደርግን ነው። የወስላታ መንጋ! በቃኝ!

  2. እንዴት ሁኖ ነው ችግር የሚደመሰሰው ሹመኞቹ ዋና ችግር ሁነው። ብርሀኑ ነጋ፣አብረሀ በላይ፣አረጋዊ በርሄ፣ቀጀላ መርዳሳ፣አገኘሁ ተሻገር፣ሽመልስ አብዲሳ፣ሽፈራው ሽጉጤ፣ታከለ ኡማ፣ አዳነች አቤቤ፣ ሱሌማን ደደፎን የመሳሰሉ እንኩቶዎች ሀገር እንዲያፈርሱና ልምድ እንዲያገኙ እየተሾሙ በየት በኩል አገር ይረጋጋ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share