October 7, 2022
21 mins read

አንዳርጋቸው ጽጌ ሣይቀር የሚሣለቅበት አማራ ይህችን የጨለማ ዘመን ካለፈ ምንም አይል – ሥርጉት ካሣሁን (አዲስ አበባ)

Angargachew

ይሄ “እንደሠራ አይገድል” የሚባል አማርኛ አንዳርጋቸው ጽጌን የመሳሰሉ የታሪክ ዝቃጮችንና በሞቀበት ዘፋኞችን ለመግለጽ ምንኛ ክርክም ያለ ውብ ገላጭ መሰላችሁ! ብዙ ነገሮች አጀማመራቸው ቢያምር አጨራረሳቸው አያምርም፡፡ ለዚህም ነው እንዳማሩ መሞት የለም የሚባለው፡፡ ይሄ የፈረደበት አማራ እንዲህ የማንም ሞልፋጣ አፍ መክፈቻና መጫወቻ ሆኖ ይቅር ግን? የዚህን ሰው ብልግና ሰምቼማ ዝም ማለት የለብኝም በሚል ብዕር አነሳሁ፡፡ የፈለገው ይምጣ እንጂ እስከዶቃ ማሰሪያው እነግረዋለሁ፡፡ ባለጌን ባለጌ ካላሉት ደግ የሠራ ይመስለውና ቅርሻት ብስናቱን በስፋት መቀጠሉ አይቀርም፡፡ እንደአማራ የሚያሳዝን አሁን አሁን የለም፡፡ ሁሉም እየተነሳ ያልተገራ መደዴ አፉን በነገር የሚያሟሸው አማራን በመሳደብ ነው፡፡

በቅድሚያ ግን ወደ ደርግ ዘመነ መንግሥት ልውሰዳችሁና ስለመንጌ አንድ ነገር ላጫውታችሁ፡፡ መንጌ አንድ ወቅት ሚኒስትሮቹን ሰብስቦ “ብታምኑም ባታምኑም እናንተ የት እንደምታመሹ፣ ምን እንደምትበሉና እንደምትጠጡ፣ ከማን ጋር እንደምትዝናኑ፣ ምን ምን ሀብትና ንብረት እንዳላችሁ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚገባ ያውቃል!…” አላቸው (ዘመኑ ራቅ በማለቱ በትክክል ባልጠቅስ ይቅርታ)፡፡ ለምን ትዝ አለኝ መሰላችሁ – የኢትዮጵያ ሕዝብ ያኔም ሆነ አሁን የሚጠቅሙትንና የሚጎዱትን፣ የሚያላግጡበትንና ከምር አለሁልህ የሚሉትን፣ ጨዋዎችንና ዋልጌዎችን፣ እውነተኞችንና አስመሳዮችን … ለይቶ በሚገባ ያውቃቸዋል … ለማለት መፈለጌን ለማጠየቅ ነው፡፡ ብዙው ፖለቲከኛ ከአልባሌ ቦታ እየመጣ ፖለቲካን እንደብቸኛ አማራጭ ወስዶ ሕዝብ ጫንቃ ላይ እንደሙጫና እንደመዥገር ስለሚጣበቅ ይሉኝታና ሀፍረት ብሎ ሲያልፍም አይነካው፤ ፖለቲካ እንጀራ እንጂ ሙያ መሆኑ ቀርቷል፡፡ አብዛኛው ፖለቲከኛ አንድም በሌላ ሙያ ቢሰማራ ችሎታ እንደሌለው በማመን ወደ ፖለቲካው ይገባና ያጨመላልቀዋል፡፡ አንድም በሥልጣን አራራ በመናወዝ ወደዚያው የፈረደበት ፖለቲካ ይገባና ዝናንና ታዋቂነትን አትርፎ በዚያ ለመኮፈስ በሀብትም ይበልጥ ለመክበር ይገባል፡፡ የአማራጭ-የለሾች መሰባሰቢያም እንደሆነ ይነገራል፡፡ በዚህም ሳቢያ የኛን ፖለቲከኞች ስናይ ከሙያ አንጻር እንኳን ጥቁር ሠሌዳና ጠመኔ የሰለቻቸው መምህራን ወይም አካፋና ዶማ ያንገላታቸው የቀን ሠራተኞች ወይም የቢሮ ጉዳይ አስፈጻሚ የነበሩ አውደልዳዮች እንጂ በሕዝብ አስተዳደር ዲግሪ ይቅርና ሰርቲፈኬት እንኳን ያላቸውን ለማግኘት እንቸገራለን፡፡ የኛ ሀገር ፖለቲካ ደግሞ በሩ ለማንም ዋልጌና ስድ ክፍት በመሆኑ እንደከተማ አውቶቡስ ማንም ዘው እያለ ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት ቅርሻቱን ይለቅብናል፡፡

አንዳርጋቸው ጽጌም – ይቅርታ ይደረግልኝና – ከነዚህ ልቅ አፎችና መደዴዎች አንዱ ነው፡፡ ይህ ሰው የጭቃ እሾህ መሆኑን ለመረዳት ጊዜ ቢወስድም አሁን ላይ ብዙዎቻችን አወቅነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ውለታቢሶችን በዝምታ ማለፍ ለሌሎች ባለጌዎች በር እንደመክፈት ነውና አካፋን አካፋ ማለት ነውር የለበትም፡፡ አንድ ሰው ከመናገሩ በፊት ደጋግሞ ማሰብ አለበት፤ ዕብሪት የትም አያደርስም፡፡ በወያኔ ዘመን ታስሮ ብዙ ስቃይ ያየበትንና ከልጅነቱ ጀምሮ መከራ የቆጠረበትን የሀገር ነፃነት ትግል በአንዴ በዜሮ የሚያባዛ ንግግሩን ከዚህ በታች እንመልከትለትና ወደተጨማሪ ማብራሪያ እናምራ፡-

የመከላከያን ጭራ እየተከተልክ ያሸነፍክ ሲመስልክ .. ጀግናው ልዩ ሀይላችን ትላለህ ስትቀጠቀጥ ደሞ መከላከያ የታለ ለኔ ወግኖ ሌላ ኢትዮጲያዊን ይውጋ ትላለህ፡፡ በ‹ሆሏ ለድል ሽሚያ መሯሯጥህ አይቀርም officially declare “ወያኔ ከአቅማችን በላይ ነው

ይህ ያላንዳች ለውጥና አርትዖት(editing) በቀጥታ ከምንጩ የተገለበጠ ጽሑፍ የአንዳርጋቸው ጽጌ መሆኑ በአስተማማኝ ማስረጃ ተደግፎ በፌስቡክ ሲዘዋወር የተገኘ ነው፡፡ “ከርሱ እንዲህ ያለ ቅሌት አይወጣም” በሚል በመጠራጠሬም ሁነኛ ሰው ጠየቅሁ፤ ግን እውነት ነው፡፡ ይህ ሰው አብዷል፡፡ ጠበል ውሰዱት፡፡

ይህ ፀረ-አማራ ዝቃጭ ንግግር በ@ardii_africa ላኪ አድራሻ ለ@HabtamuAyalew21 ተቀባይ አድራሻ የተላከ ሲሆን የሚሣለቀው በአማራ ላይ ስለመሆኑ እያንዳንዱ ቃል አፍ አውጥቶ ይናገራል፡፡

አማራን ለመሳደብ አንዳርጋቸው ይህን ያህል መቃተት ለምን እንዳስፈለገው ለመግለጽ ግንቦት ሰባት ድረስ መሄድ አያስፈልግም፡፡ እዚያ ድረስ ቢኬድ ብዙ ገመና ይወጣል፡፡ ምክንያቱም ያ የኢዜማ እርሾ የሆነ የአየር በአየር ቀፋላ ድርጅት ፀረ አማራ መሆኑን በብዙ አቅጣጫዎች ያስመሰከረ በመሆኑ ወደዚያ ገብቶ መዳከር ጊዜ ማባከን ነው፡፡ እንጂ አማራን በገዛ ሀገሩና በገዛ ቀየው “መጤ ነው” ሲል በቅርቡ የተናገረውን የድርጅቱን የዕድሜ ይፍታህ ፕሬዝደንት ካሙዙ ባንዳ ብርሃኑ ነጋን ማውሳት በተቻለ ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን ስታዘበው በእጅጉ ያባልጋል፡፡ እዚያ ላይ ሲወጡ አፋቸውን ምን እንደሚበላቸው አይገባኝም – ማን አይዟችሁ እንደሚላቸውም እንደዚሁ፡፡ የዕብሪትና ጥጋባቸው መንስዔ የሀብት ብዛት ይሁን፣ የዝነኝነት ብዛት የሚያስከትለው ሥነ ልቦናዊ ልክፍት ይሁን፣ የዕውቀት ብዛት ይሁን፣ የአስተዳደግ ጉድለት ይሁን … ምሥጢሩ ምን እንደሆነ ሳይገባኝ አንዳንድ ሰዎች አንደበታቸውን መግራት እየተሳናቸው በተደጋጋሚ ሲቀሉ አስተውላለሁ፡፡ ደግነቱ “እባብ ልቡን አይቶ እግሩን ነሳው” እንደሚባለው ይህን መሰሉን ቅምድምድነታቸውን እያዬ ይመስላል ፈጣሪም እዛው ባሉበት ድውይ አድርጎ ያስቀራቸዋል፤ ሊጨብጡት የሚፈልጉትን ነገር በማየት ብቻ ያረጃሉ፤ይሞታሉም፡፡ ላይ ወጡ የሚባሉትም መጨረሻቸው ሳያምር አንድም ለሞት አንድም ለስደት ይዳረጋሉ፡፡ አዎ፣ “እንደሠራ አይገድል” ብሎ ብሂሉ አስቀድሞ አስቀምጦታላ፡፡ ትኅትና ማንን ገደለ? ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን ምን በላው? ይሉኝታ ወዴት ሸፈተ? የመማርና የማወቅ ትርጉሙስ ምንድን ነው?

አንዳርጋቸው ጥጌ ልክ እንደአለምነህ መኮንን አማራን ለመዘርጠጥ ይህን ያህል የደፈረው ማንን ለማስደሰት እንደሆነ በመሠረቱ ግልጽ ነው፡፡ እንደመረገም ሆኖብን ካለፉት 30 ዓመታት ወዲህ የኢትዮጵያን ፖለቲካ እንዳሻው የሚጋልበው በመለስ ዜናዊ ተቀርፆ ከ1983 ወዲህ ሥራ ላይ የዋለው አማራ ጠሉ የጎሣ ፖለቲካ ዘይቤ ነው፡፡ መለስ ቢሞትም ተረካቢው ግራኝ አህመድ ማነው አቢይ አህመድ የዘር ፖለቲካውን በሚገባ አጠናክሮ እያስቀጠለው ነው – “ካለበት የተጋባበት” ይባላል ዱሮውንም፡፡ በዚህ ፖለቲካ አንዳች ጥቅምና ሥልጣን ለማግኘት የሚቋምጥ ደጅ ጠኚ ሁሉ ታዲያ አማራን ካላንጓጠጠና ካልተሳደበ በባለጊዜዎቹ ተረኛ ዘረኞች ዘንድ የሚወደድ ስለማይመስለው ቀጭን ሰበብ እየፈለገ ሁሉም የሥልጣን ተስፈኛ አማራ ላይ ሲለፋደድ ይታያል፡፡ በሥልጣን ዙሪያ ይሉኝታ እንደሌለ ደግሞ ግልጽ ነው፡፡ ዛሬ የምትለው ነገር ከትናንቱ መቃረኑ አያሳስብህም፡፡ ጭንቀትህ ተረኛውን ኃይል ማባበልና ማስደሰት በመሆኑ ትኩረትህ ሁሉ ገዢው የሚጠላውን ወገን በስድብ ለመሞለጭ ቀን ከሌት የስድብ ክምችትህን ማደስና በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የፈረደበት ባለተራ ተሰዳቢ ላይ መትፋት ነው፡፡ አንዳርጋቸውና ብርሃኑም ከነቢጤዎቻቸው እያደረጉት ያለው ይህንኑ ነው፡፡ ዕድሜ እማያለዝበው ትምክህት!

“አማራ ምን አድርጓችሁ ነው በተስኪያን እንደገባች ውሻ እንዲህ ጠምዳችሁ የያዛችሁት?” ተብለው ቢጠየቁ አንድም መልስ የላቸውም፡፡ “ያው የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደሚስቱ ሮጠ” እንደሚባለው ዓይነት ነው፡፡ ተጠሪ ያላቸውን ነገዶች ቢሳደቡ የሚደርስባቸውን ያውቁታል፡፡ እግዜር አይበለው እንጂ ሌሎችን ለመሳደብ አፋቸውን ቢያሞጠሙጡ ሥጋቸው በአንድ ኩርቱ ፌስታል፣ አጥንታቸው በአንድ ሌላ ኩርቱ ፌስታል ተጠቅሎ በየደጃፋቸው እንደሚጣል እነሱም ሸኔዎችም እኛም እናውቃለን፡፡ እርግጥ አማራ ለጊዜው ወኪል የለውም፤ ቢኖረውም ወደ ውራጅ የብቀላ አዙሪት እንደማይገባ ተሳዳቢዎች ሳይቀሩ ይረዳሉ፡፡ ለዚህም ነው ሁሉም በዚህ ሕዝብ ስድብ የሚለማመደው፡፡ አሁንና ዛሬ ደግሞ በገዛ ሀገሩም በየማዕዘናቱ ተወጥሮ የሚገኝ ሕዝብ ሆኗል፡፡ እንደፍቅር እስከመቃብሩ ጀግና እንደአበጀ በለው የራሱን የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በየአካባቢው ካልተደራጀና ጠላቶቹን በጋራ ካልተጋፈጠ አማራን ካላጠፉ ሰላም የሚያገኙ የማይመስላቸው አንዳርጋቸዎች አያኖሩትም፡፡

ከፍ ሲል የተቀመጠውን የአንዳርጋቸውን መልእክት ትንሽ ልተቸው፡፡ በምሣሌም ላሳይ፡-

አንድ ሰው ታስረው የተቀመጡ ዕብድ ውሾች አሉት እንበል፡፡ እነዚያን ውሾች ፈትቶ ቢለቃቸውና ጎረቤቶቹን ቢነክሱ ተጠያቂው ማን ነው? ተጠያቂው አርፈው የተቀመጡ ውሾችን ፈትቶ ጃዝ ብሎ የለቀቃቸው ወገን ነው፡፡ ስለዚህ ለ30 ዓመታት ለጦርነትና በጦርነት የተዘጋጁ ዕብድ ወያኔዎችን አውዳሚ የጦር መሣሪያዎችን ከነሙሉ ስንቅና ትጥቅ ሰጥቶ በአማራ ገበሬ ላይ መልቀቅ ፍትኃዊም ሞራላዊም አይደለምና “ወያኔን አልቻልነውምና መንግሥት ይድረስልን” የሚል ዐዋጅ የሚያስነግር ጉዳይ አይደለም፤መሆን ያልነበረበት በመሆኑ፡፡ ከሃዲው አንዳርጋቸው ይህን ሊያውቅ ይገባል፤ ለነገሩ ልቦና ካለው ይህን እውነት አያጣውም፡፡ ለጦርነት ያልተዘጋጀውና በወያኔና በቀጣዩ የአቢይ መንግሥትም ከበፊቱ የከፋ ግፍና በደል እየደረሰበት የሚገኘው የአማራ ሕዝብ በፌዴራሉ ሁለንተናዊ እገዛ ትህነግ እንዲወረው መንግሥትን አልጠየቀም፡፡

ትህነግ ላይ ጦርነት ያወጀው የፌዴራል ተብዬው መንግሥት እንጂ የአማራ ክልል አለመሆኑ ደግሞ ይታወቃል፡፡ አማራ ያደረገው ብቸኛ ነገር የተቀማ ርስቱን ጊዜው ሲፈቅድ በደሙ ማስመለሱ ነው፡፡ አዲስ ነገር አይደለም – በጉልበት የወሰዱት በጉልበት ተመለሰ፡፡ ለአብነት ቦርሣህን ቀምቶ የሚሮጥን ቀማኛ ሌባ ስታሳድድ ቆይተህ ሌባው ድንገት ወለም ቢለውና አንድ ቦታ ቆም ቢል ዕቃህን ነጥቀህ መመለስ እንጂ በህግና በሥርዓት ያልወሰደውን ንብረትህን በህግና በሥርዓት ካላስመለስኩ ብለህ ከርሱ ጋር እንድትጓተት – እንድትጃጃል ማለትም ይቻላል – የሚመክርና የሚፈልግም ወገን ካለ መቼም የሌባው ተባባሪ መሆን አለበት፡፡ እውነቱን እያወቁ እንዲህ ባይ ፍርደ ገምድል ወገኖች አስቂኝ የአማራ ጠላቶች ናቸው፡፡ ፌዴራሉ እንደተባለው የጥሞና ጊዜ ለመስጠትና የእርሻ ወቅትን እንዲጠቀሙበትም ይሁን በሌላ ምክንያት የተኩስ አቁም ከወሰነ መከላከያው ከትግራይ ክልል ወጥቶ በትግራይ ድንበሮች መሥፈርና ሌሎች ክልሎችን ከወያኔ ጥቃት መከላከል ነበረበት እንጂ በሽሽት ሽምጥ ሊጋልብ ባልተገባው ነበር – ለዚያውም ከባድ የቡድንና የተናጠል ሜካናይዝድ የጦር መሣሪያዎችን እየተወ፡፡ መከላከያው በተናጠል ተኩስ አቁም ሰበብ ትግራይን በመልቀቅ ሌሎች ክልሎችን ለወያኔ ጥቃት ዳርጎ ከሸሸ እነአንዳርጋቸው የሚያውቁት ሌላ ጉዳይ አለ ማለት ነው እንጂ አንዱ የጀመረውን ጦርነት ሌላው እንዲቀጥል የሚደረግበት አግባብ የለም፡፡ ጦርነት በውርስ የሚተላለፍ የሰንበቴ ጽዋ ማኅበር አይደለም፡፡ ለማንኛውም አቶ አንዳርጋቸውም ሆነ ግብረ አበሮቹ የኢዜማ አንዳንድ ሰዎች ይህን ምሥኪን አማራ ለቀቅ አድርጉት፡፡ ጥላቻችሁንም ገደብ አብጁለት፡፡ ነገ እንዳንተዛዘብና ቡና እንኳን መጠራራት እንዳይከብደን ይህ ጨለማ እንደሚያልፍ ቆም ብላችሁ አስቡና አደብ ግዙ፡፡ መረጋገሙ ዋጋ እንደሌለው ከመረዳት አኳያ ሆን ብለን ተውነው እንጂ አማራን የምትጠሉና ገዢዎችንም ሆነ የስንኩል ተፈጥሯችሁን የተንሻፈፈ ሥነ ልቦና ለማስደሰት ስትሉ ዘወትር አማራን የምትሳደቡ ወገኖች “ልጅ አይውጣላችሁ፤ ጥቁር ውሻም ውለዱ!” ብለን መራገም አቅቶን አይደለም፡፡ አንድን ግለሰብ መሳደብ ተገቢ ባይሆንምና ባይመከርም መሳደብ ግን ይቻላል፡፡ አንድን ማኅበረሰብ ካላበሳው መወረፍ ግን ነውር ብቻ ሣይሆን ወንጀልም ሃይማኖት ካላችሁ ደግሞ ኃጢኣትም ነው፡፡ አማራን ከወደቀ ግንድ ጋር አመሳስላችሁት ከሆነ ደግሞ ተሳስታችኋልና በቶሎ ታረሙ፡፡ የአቢይ ኦሮሙማ እንደሆነ አማራን መሳደብ ቀርቶ ብትገድሉለትም እንደውለታ አይዝላችሁም፤ ከፍላጎቱ አንዳች ነገር ብታፋልሱ – እናንተም ታውቁታላችሁ – ተራችሁን ጠብቆ ገቢ ያደርጋችኋል፡፡ ለማንም የሚራራ አንጀት ኢንቀብዱ፡፡ ለሰላማዊው ታጋይ ለእስክንድርና ጓደኞቹ ያልተመለሰ ብዔልዘቡል ለእናንተም የሚመለስ አይደለም፡፡ የጎንደርንና የወሎን አማራ በጅምላ አጥፍታችሁ ለሽልማት ብትቀርቡ በሸኔው ይቆላችኋል፡፡ አማራንና አማርኛን ብትጠሉትም በተረት እንደጀመርኩ በተረት ልጨርስ – “አገባሻለሁ ያለ ላያገባሽ ከባልሽ ሆድ አትባባሽ፡፡” ተግባባን?

 

 

 

9 Comments

  1. አዎ! እንደ አንዳርቸው አይነት ግለሰቦች ከእንዲህ አይነት እጅግ አሳዛኝ (very tragic) ከሆነ ሁለንተናዊ የሰብእና ውድቀትና ውርደት ጋር ቀሪ የጥቂት ጊዜ እድሜያቸውን ለመኖር ሲወስኑ ምንም አይነት የህሊና ወቀሳ የማይሰማቸው ግለሰቦች በመከረኛ ህዝብ (በአገር) ላይ ለመሳለቅ ሲቃጣቸው ከነውርነትም አልፎ ወንጀል ነውና በቃችሁ ሊባሉ ይገባል!

    አዎ! የእራሳቸውን (የግላቸውን) ታሪክ በለየለት ቆሻሻ ላይ መጎተት መብታቸው ቢሆንም ይህንኑ ግትልትልና መርዘኛ ቆሻሻቸውን በመከረኛው ህዝብ (በአገር) ላይ ማራገፋቸውን እንዲያቆሙ በግልፅና በቀጥታ ሊነገራቸው ይገባል!

    አዎ! አያሌ ንፁሃንን አራት ዓመታት ለዘለቀና አሁንም ሳያቋርጥ ለቀጠለ ለመግለጽ የሚያስቸግር የግፍ ግድያና የቁም ሰቆቃ ሰለባዎች ላደረገና በማድረግ ላይ ለሚገኝ የህሊና ቢሶችና ጨካኞች አገዛዝ እራሳቸውን (ነፍስንና ሥጋቸውን) አሳልፈው የሰጡትንና የሚሰጡትን እንደ አንዳርጋቸው አይነት የቁም ሙቶች መፀየፍና በማያሻማ ሁኔታ በቃችሁ ማለት ካልቻልን እንደ አሸን የሚፈሉ ቢጤዎቻቸው (አምሳያዎቻቸው) የሚያስከትሉት እጅግ አስከፊና አስፈሪ የመከራና የውርደት ዶፍ ሰለባዎች ሆነን እንደምንቀጥል ለማወቅ ብዙ ማሰብን አይጠይቅም!
    ስለሆነም ከምር መቆጣትና በቃ ማለት አነስተኛው የፖለቲካና የሞራል ግዴታ ነውና ይህንኑ ላለማድረግ ምንም አይነት ሰበብ መደርደር አያስፈልገንም!

  2. መረጃ ቢስ የሆነ ሃሳብ በማሰራጨት ለምን ችግራችን ታባብሳላችሁ? በየትኛው መስፈርት ነው አቶ አንዳርጋቸው የአማራ ጠላት የሆነው? ለመሆኑ ሰውን ጥላሸት ከመቀባትና አነካኪና አቆራቋሽ የሆኑ ነሲባዊ ነገሮችን መለጠፍ የምናቆመው መቼ ነው? ለዶ/ር እከሌ ምላሽ ለምላሹ ምላሽ ስንጽፍ ለምን እድሜአችን ይሮጣል? የአማራ ጠላት ራሱ የአማራ አመራር ነው። ከዚያ ባሻገር ለይቶለት ሂሳብ ለማወራረድ ለ 3ኛ ጊዜ ወረራ የከፈተውና በወያኔ የሚሾፈሩት ኦነግ ሸኔና ሌሎች የሩቅ የሾፌሮቹ ሾፋሪዎች ናቸው። ከዚህ ውጭ ያለው ሁሉ ቃና የለሽ ጫጫታ ነው። ፍትህ ርትዕ በሃበሻ ምድር አለ ወይም ለወደፊት ይኖራል ብሎ መከራከርም ከንቱነት ነው። ዛሬ ላይ በእስራት ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች የፓለቲካ ተወዛጋቢዎችና ሌሎችም በወያኔ ጊዜ ዘብጥያ የወረድ ናቸው። የመደመሩ ሂሳብ ወደ መቀነስ ተለውጦ ይኸው አቦይ ስብሃትን የፈታው የብልጽግና መንግስት ለሃገር አንድነትና ለወገን እኩልነት የሚፋለሙትን እየሰወረ ይገኛል።
    በቅርቡ The Heritage foundation የወያኔውን ጄ/ጻድቃንን ቃለ መጠየቅ ለማድረግ አቅራቢው ሲያስተዋውቅ የተጠቀመባቸውን ቃሎች ለመረመረ ነጩ ህዝብ ለብሶ አብዷል ያሰኛል። ግን ግባቸው አንድ ነው። ሃገር መናድና ማፍረስ። ቃለ መጠይቁ ላይ ጄ/ሉ/ድርድር እንደማያስፈልግ ሲናገር መስማት የቱን ያህል ጭንቅላታቸው በዘር ፓለቲካ እንደ ተያዘ ያሳያል። ወያኔ በቀድሞዋ አልባኒያ የኮሚኒዝም ስልት እየተመራ ማሌሊትን ካቋቋመ በህዋላ በውስጣቸው ነገሩ ልክ አይደለም ያሉትን ሁሉ አፈር እየመለሰና እያሳደደ ዛሬ ላለበት አጣብቂኝ ደርሷል። ነጩ አለም አንዴ የትግራይ መንግስት፤ ሌላ ጊዜ የትግራይ መንግስት ሰራዊት ወዘተ እያሉ የሚያምታቱት ሆን ብለው ጉዳዪን ለማመቻቸት እንጂ ትክክል አለመሆኑ ጠፍቷቸው አይደለም። እናቶች፤ አባቶች፤ ቀሳውስትና የእስልምና እምነት ወንድምና እህቶች እያለቀሱ ሲለምኗቸው አሻፈረኝ ብለው አሁን ሰላም ፍለጋ ደቡብ አፍሪቃ ድረስ ለመሄድ ማሰብ ርካሽነት ነው። ለነገሩ ገና ከጅምሩ እንደማይሳካ የታወቀ ነበር። የአሜሪካ እጅ የገባበት ነገር ሁሉ ይፈራርሳልና። የአሜሪካ ተቀጣይ ጅራት የሆነው የአውሮፓ ህብረት ያወጣውን መግለጫ እጅግ የሚያሳዝን ነው። ግን ይህም ሆን ተብሎ የሚደረግ ነው። የተመድ የዝግ ስብሰባም ከዚሁ ከክፋት ኮሮጆ ጋር የተዛመደ ነው። እንግዲህ ይህን ሁሉ የውጭ ክፋትና የሃገር ውስጥ ተንኮልን የሚገነዘብ ወገን እንዴት በጥቃቅን ጉዳይ ጭቃ ይቀባባል? ማንም ሰው በሁሉ ነገር መስማማት አይችልም። ፍጽም ዝምታና መስማማት ያለው መቃብር ስፍራ ብቻ ነው። ስለሆነም ለምላሽ ምላሽ ስንሰጥ፤ ያንም ይህንም ቆርጠን ስናሳጥር፤ ይሄ የዚህ ህዝብ ጠላት ነው እያለን ነገር ስናቀብል ለወገን ለሃገር መፍትሄ ያፈላለግን ከመሰለን ተሳስተናል። ነገርን እየመረጡ ማለፍ አንድ ጥበብ ነው። የህዝብና የወገን ጠላትንም ለይቶና አልሞ በደረጃ ማስቀመጥ አዋቂነት ነው። ከሁሉ ጋር ትግል፤ ከሁሉ ጋር ፉክክር ለማንም አይጠቅምም። በቃኝ!

    • Tesfa የአንዳርጋቸውን መጽሃፍ “ትውልድ አይደናገር እኛም እንናገር” የተባለውን አንብበሃል? ጸሃፊው ስህተተኛ ሁኖ አንተን ፍጹም የሚያደርግህ አመንክዮ ምንድነው? እንዳንተ ምክር ከሆነ መለሰንም፤ስብሃት ነጋንም፤ስዩም መስፍንንመ ሌሎች አጋዚዎችንም ማውገዝ ጥቅም የለውም:: እሽ እንታዘዛለን

  3. ስርጉት ጉብዝናሽና ያየሁት ጽሁፍሽን ስትጨርሺ ነው፣ እሱ ላይ ቀጥይበት፣ ተረቱ ላይ ማለቴ ነው። በተረፈ ጽሁፍሽ ይዘቱም ቅርጹም እጅ እጅ ይላል

  4. ጌትነት እጅ እጅ ያለህ ምናልባት የማንበብ ልምድህ እየዳኸ ሊሆን ይችላል፡፡ ልምዱ ከሌለህ በፓራግራፍ እየከፋፈልክ አንብበው ለማንበብ አዲስ ከሆንክ እርግጥ ነው ይሰለቻል መዳበሩ ግ ን አይቀርም ሳትሰለች አንብብ፡፡ እንዲህ ያለ ግ ንዛቤ ለሚጠይቅ ጽሁፍ እንግዳ ከሆንክ የነ ዶ/ር በፍቃዱና ሃይሌ ላሬቦ አቻምየለህ ታምሩ አገር አስጥሎ ሊያበርህ ስለሚችል ሳቅ ጨወታ የበዛበት ጽሁፍ እየመረጥክ አንብብ እንጂ አትተው፡፡

  5. Who deleted my response to Getnet Sileshi? I saw it posted but it was removed after a while. I don’t see any fairness with this move of any body.

  6. Sergut I dont think it is intentional, when thier page was down by the providers they were unable to fix it again. Myself and Dr Fekafu has also complained about it. Expect more wrong things to come for the children of Ethiopia. Apart from that I dont thing they are professionally equipped with knowledge finance and experience, with all that they provide us excellent service we have to help them they too have to listen to us. Keep up u r trying ur best.

  7. By I_Mognu

    One Shegitu Dadi, A Very Forward Looking Oromo Woman Has The Following To Say On Confederation. I’m Copying And Pasting Her Write-Up Without Her Authorization Hoping That She’ll Not Mind.

    “Here Is How To Save Amharas, Oromos And The Country.

    Once Again In Our Recent History, Amharas Have Emerged As The Holders Of The MASTER Key To Solve Ethiopia’s Multifaceted Problems . How? By Opting For Confederation.

    Amharas Have No Choice But To Move For Confederation Simply Because Federation In The Ethiopian Context Does Not Work.

    As A Polirized Multi-Ethnic Country, Ethiopia Will Not Have A Fair And Free Election Without The Opression Of One Or Another Ethnic Group. Hence, Democracy Is An Illusion That Cannot Be Realized. The Way Oromo Rose To Power And Now Control The Entire Country Through Proxy Regional Governments Is The Proof. Tigreans Did It For The Last Thirty Years And Oromos Have Stepped In Tigreans Shoes To Impose Similar One Ethnic Group Rule. With Their Number And Size Of Their Region, Oromo Opressive Rule Will Be Much Worse Than Tigrean`S. Give Another Ten Years To Oromo Rule, Ethiopia Will Be The Tail Of The World By All Standards Of Measure.

    So, It Is Time For Amharas To Exercise Their Constitutional Right To Self-Determnation And Vote On Confederation. If They Adopt Conederation, It Will Give Them The Opportunity To Attract Direct Foreign Investment Since Confederation Will Enable Them To Have Economic Diplomats And Even Have Embasies Abroad Cutting The Oromo Controlled Foreign Ministry Diverting Foreign Investment To Oromia And Other Favoured Regions. Amharas Can Also Have A Defense Force Which Will Protect Them From Foreign Invaders Including Ethnic Oromo Organizations.

    The Belgian Model Of Confederation Which Appears To Hep Advance Amhara Interests Is Something To Explore.

    In Any Event, Ethiopia Needs Vast Decentralization Resembling Confederation Since The Federalism The Country Has Adopted Is Notheing Other Than Unitarism In Disguise. Controlled From The Centre, It Has Miserably Failed To Develop The Country Let Alone Prosper And Ensure Safety And Security Of Its Citizens. The Chaos We See In The Country Right Now Has Much To Do With Lack Of Development (In All Sectors) And Security. Both Have Proven Beyond The Capacity Of The Federal Government To Provide.Change Of Government At Federal Level Is Not The Answer For These Problems.

    Tigreans Have Floated The Idea Of Confederation, Amharas Must Follow. Tigreans Know That They Will Not Be Fairly Treated Under Oromo Rule; As A Result, Their Choice Of Confederation Appears Just. Amharas Must Seize The Opportunity To Decide Their Destiny Via Self-Determination As Well Without Wasting Another Decade Under Incompetent Oromo Rule. Despite All The Atrocities They Have Committed, Tigreans Are Being Heard And Embraced By The Oromo Rule Since Oromos Now Feel Tobe The Savours Of Ethiopia.

    Folks! Don’`T Be Fooled!. Oromos Pretend To Be “Savours” Only If They Rule The Entire Country As One Piece. Like Any Other Ethnic Group That Aspire To Oppress And Dominate , They Are After Resources. If Amharas Want To Be Heard And Embraced As Tigreans, They Have To Go For Confederation. If Confederation Does Not Work, They Have To Say Good Bye To The Ethiopian State.

    It Is Outdated For Amharas To Hang On “Mama Ethiopia” Cry Since Nobody In The Country Is Interested In It Any More. What Amharas Got From This Cry Is Atrocotoes, Redicule And Shame. All These On Amhara Because They Gave Oromos And Other Ethnic Groups A Country Which They Are Not Ready And Willing To Let Go. If Amhara Insist On Confederation, Oromos Might Call The Army On It To Protect The Unity Of The Country! That Will Make Them A Laghing Stock Since They Were In The Forefront To Weaken The Unity Of The Country. Now They Cannot Be Alllowed To Reverse Gear.

    Amhara! Wake Up And Smell The Coffee. Tell Oromos That You Want Confederation – If Not Confederation Then Separation. Oromo Crack Down Will Soften Even Disappear As It Did For Tigreans If Amara Opt For Confederation. But The Idea Is Not To See Oromo Softening On Amhara, It Is To Seek Real Confederation As A Wayout From Decades Long Quagmire. Oromo Softeneing Does Not Take Amharas Anywhere.

    Try It! It Will Work And Catapult Amhara Development And Growth To The Sky And Ensure Their Security. It Will Eventually Liberate Oromos Too From Their Bloody Distructive Path Poised To Takie Everybody Else Down With Them.

    For Us, Oromos, Conederation Is Also The Answer. ”

    GREAT!

  8. I mognu, if Oromos are willing to take DNA test what % of oromos are natural Oromo taking sample from Balea elders?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

177327
Previous Story

በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለው የዘር ፍጅት | Welega | Amhara

salt
Next Story

ጨው ለራስህ ስትል አትጣፍጥ! – በላይነህ አባተ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop