የሳምንቱ ወሬ አንዱ እና ከፍተኛዉ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን አስተላለፉት በተባለዉ የፅሁፍ መልዕክት የዓማራ ህዝብ በኢትዮጵያዊነት እና ሉዓላዊነት ጉዳይ የማይታማ እና ለዚህም የአገር መስራችነቱ እና ባለሟልነቱ ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን ባለዉለታ መሆኑን በግልፅ መስክረዋል ፡፡
ይሁን ባለስልጣኑ በሰጡት አስተያት የተለያየ መረዳት እና አስተያየት እንዳላቸዉ ይስተዋላል ፡፡
የኤርትራን ከዕናት አገር ኢትዮጵያ ለመለየት በተጀመረዉ የነፃነት ትግል ጥሪ ተቀባይነት በማግኘት ትግሉን በሚፈለገዉ መንገድ ለመምራት እና ከግብ ለማሳካት ኢትዮጵያዊነት የዓማራ ህዝብ የአገዛዝ ስርዓት መሰረት መሆኑ እና በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የማይለወጥ እና የማይናወጥ አቋም የነበረዉ መሆኑን ነዉ ፡፡ ይህም በኢትዮጵያ አንድነት እና ሉዓላዊነት ላይ የኤርትራን ከዕናት አገር ኢትዮጵያ መለየት በዓማራ ህዝብ /ኢትዮጵያዉያን በዋዛ የማይታይ መሆኑን በመረዳታችን በኤርትራ ህዝብ እና የኤርትራን መለየት ለሚደግፉ አጋሮች የዓማራ ህዝብ እና ኢትዮጵያዊነት ርዕዮተ ዓለም የአገዛዝ እና የጨቋኝነት ታሪክ እና ስርዓት መሆኑን በማስረፅ የነፃነት ትግል በማድረግ ከጂምር እና አስከ አገር መመስረት ለቅስቀሳ እና ወቀሳ (ፕሮፖጋንዳ) ፍጆታ ተጠቅመናል ብለዋል ፡፡
ይህም ዕዉነታዉን ተናገሩ እንጂ ይህ ከላይ ዓማራ ጨቋኝ እና ግዥ በመሆኑ ምክነያት ኤርትራ ከኢትዮጵያ እንድትለይ ዕዉነተኛ መንስዔ እንዳልነበር ስሁት ትርክት ስለመሆኑ በማያወላዳ አገላለፅ መስክረዋል ፡፡
ለዚህም በ1955 ዓ.ም ኤርትራ ከእናት አገሯ እንድትቀላቀል ከፍተኛዉን ሚና የተጫወቱት ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ የነበራቸዉ በኤርትራ የነበሩ ኢትዮጵያዊ ፤ ኤርትራዊ ነበሩ ይህም ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለመለየት የነበረዉን የትግል ዕንቅስቃሴ ለማፋፋም አይነተኛዉ መንገድ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ከኤርትራ ነፃነት ጋር በተቃርኖ ማሳየት ግድ ይል እንደነበር ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ወይም ሞት የሚል አስተሳሰብ የነበራቸዉ በአንድም በሌላም ኢትዮጵያዊነትን ታሪክ የሚከተሉ እና የሚያቀነቅኑ ስለመሆናቸዉ የቅኝ ግዛት ተስፋፊዎች ምዕራባዉያን የሄዱበት ኢትዮጵያን የማፍረስ ኢትዮጵያዊነት ሉዓላዊነት እና ጥንታዊነት ክዶ ለማስካድ እንዲቻል የጥንት ሊቃዉንትን፣ የኢትዮጵያዊነት /ዓማራ አስተሳሰብ ፣ የቤተ ክርስቲን የቀደመ አቋም የማጥላላት ዘመቻ የዉስጥ ባንዳዎች እና ተላላኪዎች ይህን ከፋፋይ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ አስከምንገኝበት ዕለት አገር የማጥፋት ተልዕኮ እየተፈፀመ ነዉ ፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ ዕምብርት ዉስጥ ሆኖ የኢትዮጵያን ህዝብ እያሳደዱ እና እያዋረዱ የሚገኙት የኢትዮጵያን አንድነት በማናጋት እና ዜጎችን በማንነት መግደል ከምዕራባዉያን ሆነ ከኤርትራ ኃይሎች የወሰደዉ የአጥፍቶ መጥፋት ልማድ ነዉ ማለት ስህተት ብቻ ሳይሆን ፍፁም የማይገናዘብ ነዉ ፡፡
ምዕራባዉያን ለህዝባቸዉ እና ለአገራቸዉ የጋራ ዕድገት እና ብልፅግና እንዲሁም ኤርትራም ለኤርትራ ህዝብ በዓላማ አንድነት እና ፅናት የትግል መስመር መሆኑን መገንዘብ የሚቻል የአደባባይ ሚስጥር ነዉ ፡፡ ነገር ግን ወደ አገራችን ስንመለስ ኢትዮጵያ ምድር እየኖሩ ፀረ-ኢትዮጵያ ፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት ፣ ፀረ-ዓማራ ዘመቻ ላለፉት ግማሽ ክ/ዘመን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዉያን ለማጥፋት በጥምረት የሚሰሩት ኢህአዴግ ፣ ትህነግ እና ኦነግ ይህን በራሳቸዉ አገር እና ህዝብ ላይ የመከራ ቋጥኝ የሚንዱበት እና የሚጭኑበት ከኤርትራ የተማሩት ነዉ የሚሉትን ትተን ወደ ዉስጥ ችግር እና መፍትሄ መመልከት ነዉ የሚበጂ ነዉ ፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ሁነኛ የዓመታት ችግር ምንጭ ቀንደኛ ታሪካዊ ጠላቶች እነማን እንደሆኑ የሚያዉቅ ሠፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የዓማራ ህዝብ ቁጭ ብሎ የሚያከብረዉን ፤ ቁሞ የሚንቀዉን የሚያዉቅ መሆኑን ተረድተን ዠላለማዊ ጠላትም ሆነ ወዳጂ የለም እና እንኳንስ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀዉ አይደለም ከኢትዮጵያ እና የዓማራ ህዝብ ጎን በመሆን የኢትዮጵያን አንድነት እና የህዝቦች የዓመታት የጭቆና ቀንበር አስሽቀንጥሮ ለመጣል ከኤርትራ ህዝብ ጋር በአዲስ የወንድማማችነት መንፈስ መቆም እና መተባበር ጊዜዉ አሁን ነዉ ፡፡
“የታጣዉን ለመመለስ ፤የራቀዉን ለማቅረብ ጥላቻ ማንበር ሳይሆን መተባበር ነዉ ፡፡ ”
“አንድነት ኃይል ነዉ ”
NEILOSS-Amber