የባህልና የእምነት ጣራ ሲያፈስ ክህደት፣ ቅጥፈንትና ሌብነት እንደ ዶፍ ሳያቋርጥ ይወርዳል!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ከትናት ወዲያ ክህደት! ትናንት ክህደት! ዛሬም ክህደት! ውሸት! ቅጥፈት! ከሀዲዎችና ቀጣፊዎች በክህደት ብዛትና በውሸት ጋስ ተወጥረው እንደ ፊኛ ፈንድተው ሳያልቁ፤ ተከጅዎችና ትሉሎችም በክህደትና በመታለል ጦር ልባቸው ቆስሎና ህሊናቸው ናውጦ ከሀዲና ቀጣፊን እስከመጨረሻው እንቅር አርገው ሳይተፉ አዙሪት ቀለበቱ ቀጥሏል፡፡

“የተናገርኩት ተሚጠፋ የወለድኩት ይጥፋ” የሚለው የመንፈስ ልዕልና ሚዛን በኢትዮጵያ ሰማይና ምድር የሰው ልጅ መለኪያ ነበር፡፡ አባቶቻችን ተከሀዲ፣ ተሌባና መዋሸት ተማይታክተው ከንቱ እንኳን አብሮን መኖርን በመንገድ መተላለፍን ይፀየፉ ነበር፡፡ የትግሬ ነፃ አውጭና እንደ አፍንጫ መጥረጊያ መሀረብ ሲጠቀምበት የኖረው ይህ አድግ በአገሪቱ እንደ ተምች ከወረዳበት ወዲህ ግን “የተናገርኩት ተሚጠፋ የወለድኩት ይጥፋ” የሚለው “ከርሴ ከሞላ የአሁኑም ሆነ መጪው ትውልድ እንጦሮጦስ ይግባ” በሚል ተአህያ ባነሰ ሥነ ምግባር ተቀይሮ በእምነቱ የጸና፣ የማይክድና የማይሰርቅ ተቤተ እምነቱምና ተቅየው እየተገፋ ወደ ከርቸሌ ሲወርድ ከሀዲው፣ ቀጣፊውና ሌባው ወደ ስልጣን ሲወጣ ይውላል፡፡

የትግሬ ነፃ አውጪና ይህ አድግ በቁሳዊ ብሔራዊ ሐብት ላይ ካደረሱት ታይቶ ተሰምቶ ከማይታወቅ ውድመት በላይ በብሔራዊ መንፈሳዊ ሐብት ላይ አድርሰዋል፡  የውጪ ተላላኪው የትግሬ ነፃ አውጪና የተላላኪዎች ተላላኪ ይህ አድጎች ወራሪዎች ለሺህ ዓመታት ሞክረው ያልተሳካላቸውን ካርታ ተመሬት ያነጠፉትና፣ ነባራዊና መንፈሳዊ ቅርስንም ወራሪዎችም ከተለሙት በላይ ያወደሙት በሚከተሉት ሶስት መንገዶች እንደሆነ እንኳን ህሊና ያለውና ያስተዋለ ህሊናውን ገሽልጦ በልቶ ለመሞት የተፈጠረ አሳማም ያውቀዋል፡፡

 

አንደኛ፦ ባንዳዎች ነፃ አውጪ ነን እያሉ “ምሁር” ተብዮውን እንደ ባህር ላይ  ኩበት አንከርፈው ለፍቶ አዳሪውንም አታለው ተወንበር ከተቀመጡ በኋላ ሌቦችን፣ ዘራፊዎችን፣ ቀጣፊዎችን፣ ከሀዲዎችን፣ የትምህርት ቤት ውዳቂዎችን፣ ከርሳሞችን፣ አድርባዮችንና በክፉ ባህሪያቸው በህብረተሰቡ የተተፉትን እየመረጡ በእየርከኑ ተስልጣን የአንባሻ ምጣድ እንደተጣደበት ጉልቻ ጎለቷቸው፡፡ እነዚህን ጉልቻዎች ሆዳቸውን እንደ ቅሪላ እየሞሉ በእርኩስ ባህሪያቸው የጠላቸውን ሕብረተሰብ በመደዳ እንዲፈጁ፣ እንዲያሰቃዩ፣ ድምጡን እንዲያፍኑና የገሃነብ ኑሮ እንዲኖር አደረጉ፡፡

 

ሁለተኛ፦ “ተምረዋል፣ ዲግሪ ጭነዋል፣ ተመራምረዋል!” የሚባሉትን እንደ ክፍሌ ወዳጆ፣ እንድርያስ እሼቴ፣ ነጋሶ ጊዳዳ፣ ሽመልስ ከማል፣ ገነት ዘውዴ፣ ስንታየሁ ወልደሚካዔል ወዘተርፈ  ያሉትን ጉዶች ደሞ “በህገ መንግስት አርቃቂነት በትምህርት ሚኒሲተር፣ በዩንቨርሲቲ አመራርና በሌሎችም ቦታዎች እንደ ቶፋ እየጣዱ የክህደትና የተንኮል ንፍሮ ቀቀሉባቸው፡፡ ከእነዚህ ሺህዎች ተሚቆጥሩት የተማሩ ሰንኮፎች የክህደትና የተንኮል መቀቀያ ቶፋ እንደነበር ተናዞ የሞተው ነጋሶ ጊዳዳ ብቻ ነው፡፡ ኑዛዜው ከልቡ ከነበረ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በካልጋሪ ከተማ የኮፈሌ ሰመአትን ለማሰብ በተደረገው ዝግጅት ላይ የቀረበ ማራኪ ግጥም - - በእዝራ ዘለቀ

 

ሶስተኛ፦የኢትዮጵያና የአማራ ጥላቻ ያላቸውን የታሪክ ጉዶች በተዋህዶ ቤተከርስትያንና በእስልምና ሃይማኖት መሪነት አስቀምጠው በተለይም የተዋህዶ ቤተክርስትያንን የትምህርትና የክህነት  ቦጫጨ ፡፡  ለሺህ ዘመናት ፀንቶና ተጠብቆ የኖረውን የቤተክርስቲያኗን አጥር አፍርሰው ውሾች “ዲያቆንና ቄስ ነን”፣ አሳሞች “ቆመስ፣ መነኩሴ፣ ጳጳስና ፓትሪያሪክ ነን” እያሉ  እንዲገቡ አድርገው የቤተክርስትያኗን ዶግምና ቀኖና የሚተገብሩ፣ የምዕመናኑን ደህነትና ሰላም የሚጠብቁ፣ ለእግዚአብሄር የሚታዘዙ ቅዱሳን ሳይሆን ካድሬዎች ሆነው ሕዝብን በመደዳ የሚፈጁ ባለስልጣናትን የሚያገለግሉ ከይሁዳም የከፉ ከሀዲዎች እንዲሆኑ አደረጉ፡፡

 

የትግሬ ነፃ አውጪ ተወንበር የጎለታቸው በአምሳሉ የተሰሩት ወሮበሎች፣ የተንኮልና የክህደት ንፍሮ መቀቀያ ሆነው ያገለገሉትን ካርሳም “ምሁሮች”፣ እግዚአብሔርንና በአስራት የሚያስተዳድራቸውን ሕዝብ ክደው ለሕዝብ ጨፍጫፊ ባንዳዎች ያደሩ የሃይማኖት “መሪዎች” ወደር በሌለው የኢትዮጵያ እምነትና ባህል ላይ ታሪክና ትውልድ ይቅር የማይለው ዘግናኝ በደል ከሰላሳ ዓመታት በላይ ፈጥመዋል፡፡

 

የባህልና የእምነት ጣራ ሲያፈስ የሰው አይምሮና ገላ በክህደት፣ በውሸት፣ በቅጥፈትና በሌብነት ዶፍ ይጨቀያል፤ ይበሰብሳል፡፡ አገር ተረካባዊው ወጣት ይህንን እውነታ  ልብ ሊለው ይገባል፡፡ ታማኝነት፣ ቁርጠኝነትና ጀግንነት ከአካል ወይም ከጡንቻ ሳይሆን ከእምነትና ከባህል እንደ ዓባይ ወንዝ ሲፈልቅና እሳት ሲተፋ ይኖራል፡፡

 

ከባህሉ ያፈነገጠ ማህበረሰብ ከባህሩ እንደሸሸ አሳ በህልውናው አደጋ ይጋረጥበታል፡፡ አማራ በጀግና አፍላቂ ባህሩ በሚዋኝበት ዘመን ከዱር አራዊት አንበሳና ነብርን፤ ከሰው አራዊትም ቅኝ-ገዥዎችንና ተስፋፊዎችን አንድ ለአምስት የሚገጥሙ ጀግኖችን እንደ ብርቱካን እያንዠረገገ ሲያፈራ ኖሯል፡፡ ከባህሩ ባፈነገጠባቸው ግማሽ ክፍለ ዘመናት ወዲህ ግን በክብሩ ብቻ ሳይሆን በህልውናውም አደጋ ተጋርጦበት ይገኛል፡፡

ወጣት ሆይ! ስንዴ ጉዛም እስተ ሆድ ዕቃው በርቅሶ ታረሰው ለም መሬት ተዘርቶና ታርሞ እንደሚያፈራው ጀግናም በጀግንነት መንፈስ ከለማ የባህል ማሳ ሲተከልና ሲኮተኮት ፍሬው ይጎመራል፡  ጠላትን እንደ ፍልጥ ተርክከውና እንደ ማገዶ አንድደው ድል ስልነሱ የምትዘፍንላቸውና የምትኮራባቸው አርበኞችህ በተፈጥሯቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህን ሰዎች ከአላህ በቀር ማንንም የማይፈሩ ጀግኖች ያደረጋቸው ሲወለዱ የተነቀሩበት በጀግንነት ባህል የታሸ ቅቤ ሲያድጉም የበሉት በጀግንነት መንፈስ የተቦካ የባህል እንጀራ ነበር፡፡

በጀግንነት ባህል የተቦካ እንጀራን ጀግና አፍሪነት የተገነዘቡ ምዕራባውያን ከአምስቱ ዘመን ዳግም ሽንፈታቸው በኋላ ባህልህን በተለያዬ መንገድ ማጥቃት ጀመሩ፡  ብፁእ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ  እንዳሉት ያገራቸው ባህልና ታሪክ ያልተቀዳበትን የጭንቅላት ቶፋ ይዘው ወደ ምዕራብ የተላኩትን ተማሪዎች በምዕራባውያን ርዕዮተ ዓለም እያጠመቁ የራሳቸውን ባህል እንደ አተላ እንዲደፉት አደረጉ፡፡ እነዚህ የራሳቸውን ባህል እንደ አተላ የደፉ “ስልጡን” ተማሪዎችም ጠጉራቸውን እንደ ጫጉላ ሙሽራ እየከፈከፉ በባህላቸውና በሃይማኖታቸው ዘመቱ፡፡ ጀግና እንደ ደን የሚያፋፉ ቀረርቶዎችና ፉከራዎችን እንደ አልሰለጠነ ባህል ቆጥረው “ዘመናዊ” በሚሉት የምዕራባውያን ዳንስ እንደ ጋማ ከብት መራገጥ ጀመሩ፤ እርግጫቸውን ለሌሎችም አስተማሩ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አራጅ ሆይ! ላንተም ቢሆን ኦርቶዶክስ ትሻልሃለች (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

እነዚህ የዳንስ እርግጫ ወረርሽኝ ተጠቂዎች ቅረርቶንና ፉከራን በዳንስ ኮቴ ስብርብር ከማድረግም አልፈው የቅኔን ፍልስፍና ማስተማሪያ የሆኑትን የባህል ዘፈኖች እያጠፉ የምዕራባውያንን ሙዚቃና ሲኒማ አስፋፉ፡፡ በእነዚህ ወራሪ ሙዚቃዎችና ሲኒማዎች ወጣቱን እያነፈዙ ለአገሩ ባህል ባይተዋር አደረጉ፡፡ በዚህም ምክንያት የቆንጆ ወንድ መለኪያው ጀግንነት መሆኑ ቀረና ሱሪን ከጪን ታጥቆ መዥገር እንደ ሸበባት ግታም ላም እየተውለደለዱ መራመድ ሆነና አረፈው፡፡

ይህ ጀግና አምራች ባህል ከአምስቱ ዘመን ድል ማግስት ጀምሮ በምዕራባውያን የባህል ጎርፍ እንደ ዓባይ ሸለቆ ዳገት መሸርሸር ቢጀምርም ጭራሹን የተጠረገው አማራን በጠላትነት የፈረጀ የወንበዴዎች አገዛዝ ከመጣበት ሶስት አስርተ ዓመታት ወዲህ ነው፡  ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቀረርቶና ፉከራ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን በሰፈርና በመንደርም እንዳይሸለል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተከለከለ፡፡ በዚህ ክልከላ ምክንያትም ይህ ጀግናን እንደ አሳ ገንዳ የሚያራባው ባህር እንደ ጣና በእምቦጭ ተመጦ እንዲደርቅ ትልቅ ሴራ ተሸረበ፡፡ በዚህ ሴራም አዲሱ ትውልድ በቀረርቶና በፉከራ አይምሮንን በጀግነት እንዳያንፅ በምዕራባውያን አጉል ሱስ ተጠምዶ በባህል ሸቀን እንዲቆሽሽ ተደረገ፡፡

ወጣቱ እንደ አያቶቹ በጀግንነት እንዲታነፅ ይህ የባህል ቆሻሻ በሕዝባዊ ዘመቻ መጠረግ ይኖርበታል፡፡ የባህል ቆሻሻው በበረኪና ታጥቦ ወጣቱ በራሱ የባህል ባህር መዋኘት ሲጀምር እንደ አያቶቹ እንኳን ራሱን ሌሎችንም ኢትዮጵያውያን በጎርፍ ከመጠረግ ያድናል፡፡ ከሸረኞች ደባ የፀዳ ባህል እንደ አያቶችህ ቆራጥ፣ ታማኝና ሩህሩህ ጀግኖችን ያፈራል፡፡ ባህልህ ከቆሻሻ ሲፀዳ በእግዚአብሔር ሚዛን የሚፈርዱ ሽማግሌዎችና ዳኞችን ይፈጥራል፡፡ ከተንኮለኞች ሸቀን የፀዳ ባህል ሲኖርህ እንደ ጥንቱ ለቆባቸው የሚያድሩ ሼሆችና መነኩሴዎች ይኖሩሃል፡፡ ከባህል እድፍ የፀዳ ባህል ሲኖር የሰው የማይነካ የራሱንም የማይሰጥ ኩሩና ሙሉ ትውልድ ይገነባል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጫልቱ እንደ ሄለን ከቡርቃ ዝምታ የቀጠለው መርዛማ ብዕር

ወጣት ሆይ! ስለዚህ ለህልውናህም ሆነ ለክብርህ ወደ ባህልህ መመለስ ይኖርብሃል፡፡ ሱሪህን ከጪንህ ከፍ አድርገህ ከወገብህ በቀበቶ ማጥበቅ ይጠበቅብሃል፡   በባዕዳን ዳንስ እንደ ማይክል ጃክሰን እንደ ጥንዚዛ መፈናጠሩን ትተህ እንደ በፊቱ ድረስ አንተነህ እንደ አሁኑ ሞላ ሰጥአርጌ በሽለላና በፉከራ መንጎራደድ ይኖርብሃል፡፡

ወጣት ሆይ!  አገርህን በነጣነት ጠብቋት የኖረ እምነትህና ባህልህ ነው፡፡ የራስህን ጠማማዎች እጀታ አድርገው በአያቶችህ የተሸነፉ ወራሪዎች በባህልህና በእመነትህ የመጡ ይኸንን ስልተረዱ ነው፡  ስለዚህ እንደ ጀግና አያቶችህ ወደ ባህልህ! እንደ መንፈስ መጋቢ አያቶችህ ወደ እምነትህ! ሽለላና ፉከራ የጀኛ መፍለቂያ መንፈስ ነው! ሽለላና ፉከራ የስልጣኔ ምልክት ነው! ያለመሰልጠን ምልክት ነጣነትን ማጣት፣ አገር አልባ መሆንና መገዛት ነው! ስለዚህ ሳትገዛ በስልጣኔ ለመኖር ሽለላና ፉከራን ምግብህና መጠጥህ አድርገው! ከክህደት፣ ከውሸት፣ ከቅጥፈትና ከሌብነት እንዲጠብቅህ የአያቶችህን እምነትና ማተብ ጠበቅ አርገህ እሰረው፡፡

ወጣት ሆይ!  የአያቶችህን እምነት፣ ቤተክርስትያንና መስጊድ ይህ አድግ ለቂጣ መጠፍጠፊያነት እንደ ብረት ምጣድ በጣዳቸው ፓትሪያሪኮች፣ ጳጳሳትና ሼሆች መለካት ፀያፍና በሰማይም የሚያስተይቅ  ነው፡፡ የአያቶችህ እምነትና ቤተክርስትያን የእነስረስ የኔሰው፣ የእነ ተዋናይ፣ የእነ መምህር ኤርሚያስ፣ የእነ መምህር አካለ  ወልድ፣ የእነ አራት አይናው ጎሹ፣ የእነ አቡነ ጴጥሮስ፣ የእነ አቡነ ሚካዔል፣ የእነ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ የእነ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ፣ የእነ አቡነ ጎርጎሪዎስ ወዘተርፈ እምነትና ቤተክርስትያን ነው፡፡ የአያቶችህ እምነትና ቤተክርስትያን ምዕመናን ተሚሞቱ እኔ ልሰዋ አሰኝቶ ክሀዲንና ክፉን በጸሎትም በጉልበትም እንደ ይሁዳና ሳንጥናኤል የሚያንበረክክ ነው፡፡

ወጣት ሆይ! አሁንም ልብ በል! የባህልና የእምነት ጣራ ሲያፈስ ክህደት፣ ቅጥፈንትና ሌብነት እንደ ዶፍ ሳያቋርጥ ይወርዳል! ይህም በመሆኑ በአለፉት ሰላሳ ዓመታት የኢትዮጵያ ምድሯ ብቻ ሳይሆን አይምሮዋም በክህደት፣ በውሸት፣  በቅጥፈትና በሌብነት ዶፍ በስብሶ ጥንብት ብሏል፡፡ ይህም በመንሆኑ ዛሬም በነጋ በጠባ  የምንሰማው ክህደትና ቅጥፈት ሆኗል፡፡ ይኸንን ለማዳን ወይም ለማከም ወጣት ሆይ ወደ አያቶችህ እምነትና ባህል መመለስ ይኖርብሃል፡፡ በአንድነት ቆመህ ከሀዲን፣ ቀጣፊን፣ ውሸታምን፣ ሌባንና ሆዳምን ከቤተ መንግስት፣ ከቤተክህነትና ከቤተ መስጊድ ጠርገህ አስወጥተህ አገርህን መልሰህ የአያቶችህ አገር ማድረግ ይጠበቅብሃል፡፡ ቆርጠህ ከተነሳህ መለኮትና የመለኮት አገልጋይ ቅዱሳን መላእክትም ይረዱሃል፡፡ አሜን፡፡

 

መስከረም ሁለት ሺ አስራ አምስት ዓ.ም.

 

2 Comments

  1. በውነት ኢትዮጵያን እና አፍሪካን ላስተዋለ ህዝቡ በጣም የሰለጠነና አርቆ አሳቢ ነው፡፡ ያለ መሪ በተፈጥሮ ህግ የሚኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ፡፡ባለፈው 50 አመት ያለምንም መሪ የኖረ ነው፡፡ ከዚህ በተሻለ በሰላም ይኖር ነበር ሰላሙን የሚኒሱት ብቃት የሌላቸው መሪዎቹና ተማርን የሚሉ ዜጎቹ ናቸው፡፡ ሹመኞቹ በጣም ከህዝቡ አስተሳሰብ ዝቅ ያሉ ናቸው አእምሮዋቸው በታላቅ ልቀት ስላልተቃኘ ወምበሩ ላይ ሲቀመጡ ምን እንደሚሰሩ አያውቁም፡፡ እድገታቸው ያለፈ ኑሮዋቸውን የሚያውቅ አንድም የለም፡፡ ግማሹ ቁማር ሲጫወት፤ ጫት ሲበላ፤ ሲሰርቅ፤ ሲጠጣ ኑሮ በአጋጣሚ ወይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ይዞ አንድ ዲፕሎማ ያገኛል ወይም የአንዱ ጎሳ አፈቀላጤ ይሆናል አሁን አሁን ደግሞ ዲፕሎማ ይገዛል ምሁር ሳይሆን ምሁር የሚል ቅጥያ ይሰጠዋል፡፡ ከዛ በኋላ አንድ ምሁራዊና ምርምር የሚጠይቅ ስራዎች ላይ አናገኘውም ሲጠሩት የትምህርቱ ቅጥያም ካልታከለ ይቆጣል፡፡

    የኢትዮጵያ አምላክ ያሳያችሁ ብርሃኑ ነጋ፤ዳውድ ኢብሳ፤አረጋዊ በርሄ፤ዲማ ነጋዎ፤ቀጀላ መርዳሳ፤ሀዝቀኤል ጋቢሳ፤ታከለ ኡማ፤አዳነች አቤቤ፤ሽመልስ አብዲሳ፤መራራ ጉዲና፤እንድርያስ እሸቴ፤አገኘሁ ተሻገር፤ አለምነው መኮንን፤ሽፈራው ሽጉጤ፤ሌንጮ ለታ/ባቲ፤በትምህርት ቤት ደጃፍ ያለፉ ይመስላሉ እንደ ትክል ድንጋይ ዘምንና ወጣት ቀድሞዋቸው ሲሄድ ቁመው ይንገዛገዛሉ መስራት አይችሉ ሌላውን አያሰሩ አእምሮዋቸው ምንም ሃሳብ ሊያፈልቅ አይችልም ካፈለቅም ተንኮልን ነው፡፡ ነጋሶ ጊዳዳ ሙተዋል ብዬ ነው ያለፍኳቸው ባሉበት ጤና ይሁኑ፡፡ አሁን ከዚህ በላይ ያሉትን ጉዶች ዶ/ር ኢንጅነር ብየ መጥራት ይጠበቅብኛል? እናንተው ፍረዱኝ ፡፡ ምሁር ማለት ያነበበ፤የተመራመረ፤የምርምሩን ዉጤት ለትውልድ ያስተላለፈ፤አዲስ ነገር ያስተዋወቀ፤ ትውልድን በእውቀት በየጊዜው ያነጸ ነው፡፡ ይህ መስፈርት ከላይ ላሉት ሰዎች ለአንዱ ይመጥናል? ሌላውን ብንተወው ብርሃኑ ነጋን እባክህ ከልደቱ ጋር ቀርበህ በተለያዩ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ሃሳብህን ስጥ ቢባል ካራ ባንገቴ እንዳለ ልደቱም ወጥቶ ቀረ ብርሃኑም ነብሱ ሃሴት አደረገች ልደቱም ከዛ ሁኖ ትግሬዎች በሚቆርጡለት አበል አገር ያምሳል ብርሃኑም ከአገር ቤት ያምሳል፡፡ አንድ ፕሮፌሰር ካላላችሁኝ ብሎ መከራ የሚያበላ ከአንድ ደቂቅ ዜጋ የማላውቀው የለም በሚለው በራሱ ስልጠና ቀርቦ ማስረዳት ካቃተው አገኘሁት የሚለው ወረቀት ከአባዱላ ዲግሪ በምን ይለያል? ጎበዝ ይህ ነገር ቀላል አይደለም፡፡ እኔ ሃሳብ የገባኝ የድንቁ ደያስ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ሰጥቶ ዶ/ር ብሎ አስመርቆ እነዚህ ሰዎች ወደ ስራ ከገቡ ነው፡፡እግዚኦ የዚች አገር ችግር እግዚኦ የትግሬ ክፋት ነገሩን ሁሉ ብልሽትሽቱን አወጣው አሁን ደግሞ የብልጽግና ባለስልጣናት ተምበርክከው እባክህ ተደራደር እያሉ እየለመኑት ነው፡፡ ትግሬ በክብር ከተመለስ የሚቀጥለው የኢትዮጵያ ውጊያ ከአስመራ ጋር ይሆናል እስቲ የረገበ ነገር ያቅርብልን፡፡ እንደው ዶ/ር አብይ ከነዚህ ሰዎች የተሻለ ሰው ከ130 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ አጥቶ ነው?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share