ግስላው የአማራ ልዩ ኮማንዶ በዛሬው ዕለት ተመርቆ በማየቴ ደስ ብሎኛል! – ~ አሸናፊ ገናን

ጠላቶቻችንን እግር በእግር እንቅስቃሴያቸውን ለመገደብ የራስን ሃይል ማጠናከር አስፈላጊ ነው።

የአማራ ህዝብ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ራሱን መከላከል የሚችልበት አዋጭ መንገድ ልክ እንደ # አዳኞቹ ሰልጥኖ ወትሮ ዝግጁ የሆነን ሃይል አጠናክሮ መገንባት ከቻለ ብቻ ነው።

ህዝባችን ከምንም በላይ ባለፉት ዓመታት ከባድ የሆነ ሰው ሰራሺ ችግሮችን ማሳለፉ የሚታወቅ ነው።

ስለሆነም የአማራ ልዮ ኮማንዶ በዚህ ደረጃ ሰልጥኖ ለህዝቡና ለሃገሩ በቆመ ጊዜ ጠላቶቻችን አሰላለፋቸውን የሚቀይሩ መሆኑ እሙን ነው።

ዓለም ላይ የሃይል ሚዛን የሚለካው ሃገሮች ባለቸው ወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ነው።

ስለሆነም የአማራ ህዝብ እና አመራርም ከአሉታዊ አጀንዳዎች በመውጣት ለህዝባችን የሚሆነውን ነገር እንድሰሩ አበረታታለሁ።

የአማራ ልዩ ሃይል ባለፉት ሁለት ዓመታት ሃገር እና ህዝብን በጀግንነት የጠበቀበት መንገድ እጅግ የሚደንቅ ነበር።

በታሪክ ሺሚያው ላይ ብዙ ስውር እና ያልተገቡ ደባዎች ቢፈፀሙበትም እናት ሃገሩን በሚገባ አፅንቶ ቆይቷል።

የዛሬዎች አዲኞች ደግሞ ለነባሩ ጦር ታላቅ ደጀን በመሆናቸው የግዳጅ አፈፃፀማቸውን በተለየ ሁናቴ የሚያጠናክረው መሆኑ ግልፅ ነው።

ለሁሉም አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች እና መላው የአማራ ህዝብ እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

አመራሮቻችን አንዳንድ ጊዜ እንድህ የመሬት ላይ ስራ እየሰራችሁ ስታሳዩን ልናመሰግናችሁ እንወዳለን።

ህዝባችንን ከአላስፈላጊ መዘናጋት እንዲወጣና ወትሮዝግጁ ሆኖ እንዲጠብቅ ማድረግ ተፍጥሮአዊ ግደታ ነው።

ስለሆነም ከጠላታችን ብዛት አንፃር የልዩ ኮማንዶው ስልጠና ተጠናክሮ ይቀጥል።

ወቅቱ መሰልጠን፣መታጠቅ እና በሃሳብ አንድ መሆንን ይጠይቃል።

አማራው በሃገረ መንግስቱ ህልውናውና ክብሩ ተጠብቆ እንዲኖር ካስፈለገ መውጫ መንገዱ ወታደራዊ አቅምን መገንባት ብቻ ነው።

ከዚህ ውጭ አማራውን በብሔር እና በሃይማኖት እያጋጩ እርስ በእርሱ እየተታኮሰ እንዲኖር በሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ የሆነ ስሜት መኖሩ ግልፅ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Ibrahim Jeilan defeats Mo Farah to win the Mens 10,000m in Daegu World Championships

ስለሆነም አማራ ሆይ ከጫጫታ፣ከወቀሳ እና ከትችት ወጥተህ በመሬት ስራው ላይ ተገለፅ!!

ሃገር የምታተርፈው በተግባር ሰሪዎች ውጤት ነው።ስለዚህ ልክ እንደ አዳኞቹ የተግባር ስራዎች ይቅደሙ።

ጥንቃቄ እና ዝግጁነት የሁሉም ነገሮች አሸናፊዎች ናቸው።

© አሸናፊ ገናን

3 Comments

  1. As one of my compatriots who do wish for the best of the struggle for the realization of real freedom and justice in the Amhara regional state in particular and in all parts of the country in general, I wish it could be the case you are wishing for ! However, to be so essentially requires a well trained and organized force that could not be under the criminal ruling elites of Amhara in particular and in Ethiopia in general! I strongly argue that this special force of the Amhara regional state will never make any radical or significant change of a democratic system within the Amhara in particular and within Ethiopia in general as long as it stays under the deadly command or control of the deadly criminal ruling elites in Bahir Dar and in Addis Ababa! I sincerely believe that any struggle short of bringing about a truly democratic change from the grass root ( local ) to the federal ( national) level is noting but serves the same political system of deadly ethno-centrism of Abyi and his company !! I know this sounds frustrating .But this is the very bitter reality we have to face as far as our very ineffective political game is concerned!

  2. They just graduated. They have not been tested in war. You are already calling them “Gissila”. You don’t even know if they are trained to protect Amhara or protect Amhara’s lords from Amhara. The dangers of Ethnic politics!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share