“ሕገ መንግሥቱ” ይከበር ዘንድ የሚጠይቀው “የትግራይ መከላከያ ኃይል” ቃል አቀባዩ ጌታቸው ረዳ – አቻምየለህ ታምሩ 

አቻምየለህ ታምሩ

ጌታቸው ረዳን የማውቀው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ አስተምር ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ነው። በወር አንድ ቀን የሚገባበት ቢሮው ከኔ ቢሮ ጀርባ ነበር። ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከመባርሩ በፊት የቅዬው ልጅና የወቅቱ የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝደንት ዶክተር ምትኩ ኃይሌ ጌታቸው ለምን እንደማያስተምር፣ ቢሮ ለምን እንደማይገባና ክፍል ለምን እንደሚቀጣ ተማሪዎች በተሰበሰቡበት ጠይቀውት ነበር። ለዚህ የዶክተር ምትኩ ጥያቄ የጌታቸው መልስ « ደመወዜ አይበቃኝም፤ በደመወዜ ማስተማር የምችለው አንድ ሳምንት ብቻ ነው፤ በየወሩ መጀመሪያ አንድ ሳምንት ብቻ አስተምሬ ለሶስት ሳምንታት ከግቢ የምጠፋው ቀሪውን ሶስት ሳምንታት የሚያኖረኝን ሳንቲም ፍለጋ መንደር ለመንደር እየተንከራተትሁ ነው።» የሚል ነበር።

ጌታቸው ጫት የሚበላበትና ካቲካላ የሚገዛበት ገንዘብ ለሰጠው ሰው ጥቁሩን ነጭ ነው ብሎ ከመከራከር የማይመለስ ፍጥረት ነበር። ስለብርቱካን ሜዴቅሳ እሱና ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ በአዲስ ነገር ጋዜጣ ያደረጉትን ክርክር ብዙ ሰው የሚያስታውሰው ይመስለኛል። ዶክተር ዳኛቸው የጌታቸውን ድንቁርና በአደባባይ ያሳዩ የመጀመሪያው ሰው ናቸው። ጌታቸው በፋሽስት ወያኔ የነፍስ አባት “በአቦይ ስብሃት” ዐይን የገባው ያኔ በአዲስ ነገር ጋዜጣ ዶክተር ዳኛቸው ወደር የማይገኝለት ዋሾ መሆኑን «በመሰከሩለት» ወቅት ነበር። በምርጫ ዘጠና ሰባት ጌታቸው የቅንጅት ደጋፊ፤ በተለይም የብርሀኑ ነጋ አምላኪ ነበር። በብርሃን ፍጥነት ከቅንጅት አምላኪነት ወደ ወያኔ ሎሌነት የገባው ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ከተባረረ በኋላ ጫትና ካቲካላ የሚገዛበት ገንዘብ የሚሰጠው ሰው ባለማግኘቱ ከችጋር የተነሳ ነው።

ጌቾ የብዙ ሱስ ባለቤት ስለሆነ ደሞዙ አይጠቅመውም ነበር። ጌታቸው መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሳለ መንደር ለመንደር ገንዘብ ፍለጋ ይንከራተት የነበረው፤ በመጨረሻም ከዮኒቨርሲቲው እንዲባረር ያደረገው ይህ የሱሱ ጦስ ነው። ይህን ሱሱን ለማርካት ከሚያውቃቸው የመንግሥት ሰራተኞች እስከ ድሆቹ ተማሪዎቹ ድረስ ገንዘብ ይበደር ነበር። ካገር እስክወጣ ድረስ የጫትና ካቲካላ መግዣ ገንዘብ ተበድሮ ያልመለሰላቸው ሰዎች ቁጥር በርካታ ነበር። ከአገር ከወጣኹ በኋላ የተበደረውን የጫትና ካቲካላ መግዣ ገንዘብ ስለመመለሱ መረጃው የለኝም።

አንድ ጊዜ ተጨማሪ ክፍያ ለመውሰድ ሒሳብ ክፍል ፊት ለፊት ሰልፍ ይዘው ተራቸውን ይጠባበቁ የነበሩ ባልደረቦቻችን ጌታቸው ሒሳብ ክፍል ገብቶ «ክፍያው አነሰኝ» በማለት ረዥም ጊዜ ከገንዘብ ከፋይዋ ሴትዮ ጋር እየተጨቃጨቀ ቢቆይባቸው «በሩን ክፈቱና ጫት አሳዩት፤ ያኔ ጫቱን ሲያይ ከሴትዮዋ ጋር የሚያደርገውን ክርክር ርግፍ አድርጎ ትቶ ተሽቀንጥሮ ይወጣል» ሲሉ ቀልደውበት ነበር። የጫት ቤት ጓደኞቹ ደግሞ «ጌታቸው እስኪመረቅን ሳይሆን እንኪደክም ይቅማል፤ እስኪሰክር ሳይሆን እስኪያቅረው ይጠጣል፤ እስኪጠግብ ሳይሆን ሆዱ እስኪፈነዳ ይበላል» ይሉት ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል

የፋሽስት ወያኔው ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በትናንትናው እለት ካድሬዎቹን ሰብስቦ ባሰማው ዲስኩር ወርረው በቅኝ ግዛታቸው ስር ይዘውት ስለኖሩት ወልቃይት “ዝም እያላችሁ ነው” የሚል አውጫጭኝ እንዲጠይቁት አድርጎ ነበር። ጌታቸው ረዳ በየቀኑ ካድሬዎቹን ሰብስቦ በሚቀረደድበት መድረክ ሁሉ ወርረውት ስለኖሩት ወልቃይት ያልደነፋበት ወቅት ኖሮ አያውቅም። እውነታው ይህ ቢሆንም ቅሉ ስለ ወልቃይት ተንፍሶ እንደማያውቅ ሆኖ ዝም እያላችሁ እየተባለው ነው የሚል አውጫጭኝ እንዲቀርብለት አድርጓል።

ጌታቸው ስለ ወልቃልት እንዲጠይቁት ስላደረገው አውጫጭኝ በሰጠው መልስም ስለ ወልቃይት ዝም እንዳላሉ፤ ዝም የማይሉትና ወልቃይትን ለድርድር የማያቀርቡትም የአማራ ልኂቃን ከትግራይ አልፈው ደቡብ ክልል ጉራፈረዳ ውስጥ የአማራ ዞን ይቋቋምልን ስለሚሉና ይህን ደግሞ አገር ስለሚያፈርስ ጭምር ነው ብሏል። ጌታቸው እንዲህ ሲሳለቅ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ብለው የተዋደቁት የራያው አርበኛ ደጃዝማች አበራ ተድላ እንጂ ኢትዮጵያ ለማፍረስ ሲዖልም ቢሆን እንወርዳለን ያለውና አማራ ክልል በሚባለው ውስጥ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን፣ የአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ የዋግ ብሔረሰብ ዞን፣ የአርጎባ ብሔረሰብ ዞንና የቅማንት ልዩ ወረዳን የመሰረተና እያንዳንዱ መንደር ውስጥ የሚኖር ማናቸውም ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ “ራሱን በራሱ” ያስተዳድር ዘንድ ሕጋዊ መሰረት የጣለው ድርጅት ቃል አቀባይ አይመስልም።

ግብዙ ጌታቸው ረዳ አማራ በወልቃይት ላይ ያነሳውን ሕጋዊ፣ ታሪካዊና ሰብዓዊ ጥያቄ የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በዐይነ ቁራኛ እንዲያየው ለማድረግ ሲኳትን ያሰበው ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ አማራው የሚያነሳቸውን ማናቸውንም ጥያቄዎች በጥርጣሬ እንዲያይ ማድረጉን እንጂ በየትኛውም አካባቢ የሚኖር “ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብ” “ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር” ሕገ መንግሥት የጻፈው እሱ የተወከለበት የፋሽስት ድርጅት መሆኑን ረስቶታል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በኢትዮጵያ አሁን ለሚታየው ውጥንቅጥ መፍትሄው ፖለቲካዊ ብቻ አይደለም (ድጋፌ ደባልቄ)

አማራ ክልል በሚባለው ውስጥ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን፣ የአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ የዋግ ብሔረሰብ ዞን፣ የአርጎባ ብሔረሰብ ዞንና የቅማንት ልዩ ወረዳ እንዲመሰረት የፈቀደው የፋሽስት ወያኔ ሕገ አራዊት ደቡብ ወይም ኦሮምያ በሚባሉት ክልሎች ውስጥም የአማራ ልዩ ዞን፣ የጉራጌ ልዩ ዞን፣ የትግሬ ልዩ ዞን፣ የዎላይታ ልዩ ዞን፣ የሶማሌ ልዩ ዞን ወዘተ እንዲቋቋም ይፈቅዳል።

አማራ ሲያነሳው ብቻ ሐጢያት ነው ካልተባለ በስተቀር የፋሽስት ወያኔ ሕገ አራዊት ፈቅዷል ተብሎ አማራ ክልል በሚባለው ውስጥ የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን፣ የአዊ ብሔረሰብ ዞን፣ የዋግ ብሔረሰብ ዞን፣ የአርጎባ ብሔረሰብ ዞንና የቅማንት ልዩ ወረዳ ከተቋቋመ ደቡብ ክልል ጉራፈረዳ ውስጥ የአማራ ልዩ ዞን ይቋቋም ብሎ ጥያቄ ማንሳት ለምን ሐጢያት ይሆናል? የቱ ላይስ ነው የሕገ መንግሥት ተብዮው ጥሰት?

የፋሽስቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረ ሕገ መንግሥት ተብዮው ይቅር ከተባለ ከሕገ መንግሥቱ በፊት የአማራ ክልል ስላልነበረ ወልቃይት የአማራ ክልል አይሆንምም ብሏል። ይህንን የጌታቸውን ውንብድና ሌሎች ቀጣፊዎችን ሲያነሱት ይሰማል። እነዚህ ደናቁርት አማራ ክልል የሚባለው እንጂ አማራ በ1983 ዓ.ም. እንዳልተፈጠረ የተገነዘቡ አይመስልም። ሲባል የሰሙትን እንደ በቀቀን የሚደግሙ ካድሬዎች ስለኾኑ ስለ አማራ ጥንታዊነት አማራና ቤጃ የሚባሉ ነገዶች አደረጉት ስላሉት ጦርነት በ5ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አገራችንን የጎበኙ አረቦች ስለጻፉት ታሪክ አላነበቡም ወይ ብዬ በመጠየቅ አዋቂ ላደርጋቸው አልሻም።

የኾነው ሆኖ ወልቃይት በሕገ መንግሥት ተብዮውም ሆነ በሽግግር መንግሥት ቻርተር ተብዮው መሰረት ወደ ትግራይ አልተካተተም። ወልቃይት ወደ ትግራይ የተካተተው ፋሽስት ወያኔ በ1968 ዓ.ም. ባወጣው ማኒፌስቶ መሰረት ነው። ነውረኛው ጌታቸውን ግን ታሪክ እንደማይደግፈው ስለሚያውምቅ በወረራ የወሰዷቸው የወልቃይትና ራያ ጉዳይ የሕገ መንግሥት ጉዳይ አድርጎ ሕገ መንግሥት ተብዮው ይከበር ዘንድ አሳስቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ህዝብ አይሰሳትም   

ሕገ መንግሥት ተብዮው እንዲከበር የሚጠይቀው ጌታቸው ረዳ የሕገ መንግሥት ተብዮውን ጥርስ ራሱ እያረገፈ ነው። በሕገ መንግሥት ተብዮው መሰረት መከላከያ ሠራዊት [Defense Force] የሚኖረው የፌዴራል መንግሥቱ ብቻ ነው። በወልቃይት ጉዳይ ሕገ መንግሥቱ ይከበር ሲለን የሚውለው ጌታቸው ረዳ ሕገ መንግሥት ተብዮውን አርግፎ እሱ ራሱ የትግራይ መከላከያ ኃይል [Tigray Defense Force]ቃል አቀባይ ሆኖ ነው። ሕገ መንግሥት ተብዮውን የማያካብሩትና ባፍጢሙ የደፉት እነሱ ራሳቸው ኾነው ሌላውን ግን ሕገ መንግሥቱን ያክብሩ ይላል። አንባቢ የሚባለው ጌታቸው ረዳ እንጥፍጣፊ የሎጂክ እውቀት ቢኖረው ኖሮ የትግራይ መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ሆኖ ሕገ መንግሥቱ ይከበር እያለ የሌላውን ንቃተ ኅሊና ዝቅ አድርጎ ለማሰብ አይዳፈርም ነበር።

ባጭሩ ታሪክንና እውነትን ትተን ጥሩንባው ጌታቸው የሚያጭበረብርበትን ሕገ መንግሥትም ሆነ የሽግግር መንግሥት ቻርተር ተብዮዎችን ብንወስድ እንኳ ወልቃይትና ራያ የአማራ ክልል ወይም የክልል ሶስት ተብዮው እንጂ ፈጽሞ የትግራይ ክልል ሊሆን አይችልም። “ብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መስተዳደሮችን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ” በሚል ጥር 5 ቀን 1984 ዓ.ም. በነጋሪ ጋዜጣ ታትሞ የወጣው አዋጅ ቁጥር 7/1984 ወልቃይትና ራያ ወደ አማራ ክልል ወይም ወደ ክልል ሶስት እንዲካለሉ ይደነግጋል። ፋሽስት ወያኔ ግን ራሱ ያወጣውን የሽግግር መንግሥት ቻርተር ጥርሱን አርግፎ በ1968 ዓ.ም. ያወጣውን ድርጅታዊ ማንፌስቶ በማንበር ወልቃይና ራያን ወደ ትግራይ ክልል ወይም ክልል 1 እንዲጠቃለሉ አድርጓል።

ታሪክና እውነት ቀርቶ ሕገ መንግሥቱም ሆነ የሽግግር መንግሥት ቻርተር ይከበሩ ከተባለ እንኳን ወልቃይትና ራያ መካከል ካለባቸው ወደ አማራ ክልል ወይም ክልል ሶስት እንጂ ወደ ትግራይ ክልል ወይም ክልል አንድ አይደለም። “ብሔራዊ ክልላዊ የሽግግር መስተዳደሮችን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ” በሚል የታወጀው አዋጅ ቁጥር 7/1984 አንቀጽ 4 እና ይህንን ሕጋዊ ያደረገው ሕገ መንግሥት ተብዮው የሚደነግጉት ይህንን ነው።

© አቻምየለህ ታምሩ

ስቶክሆልም :- ሐምሌ 28/2014 ዓ.ም

2 Comments

  1. እናመሰናለን መጥፋትህ አሳስቦን ነበር ስለዚህ ነሆለል እንኳን ብዙ ሰምተናል አንተንም ማስረጃ ለማግኘ ምድከም አልነበረብህም፡፡ ረብ ያለው ሰው አይደለም፡፡ ሰውዬው ቅልቅል የሌለው ራያ መሆኑን አብሮ አደጎቹ በየጊዜው እየተናገሩ ነው እንዳልከው ሱሱን መግዛት አቅቶት ማንነቱን ሲለወጥ ምን ይባላል? አቦይ ስብሃትም ስሙኒ እየሰጡ እንደ በቀቀን ያስጮሁታል እንጅ ለወገኖቹ ያልሆነ ለነሱ ይሆናል ብለው አያምኑትም፡፡ ትግሬዎች አንድ ቀን እንደሚበሉት ጥርጥር አይኖርም እንደው ከዛ አካባቢ እንደ ሰው የሚያስብ ጠፋ ማለት ነው? ገብሩ አስራት፤አብረሃ ደስታ፤አረጋዊ በርሄ፤ግደይ ዘራጽዮን፤ተወልደ ገ/ማርያም እያለ ይቀጥልና ፈንግል ነው ፈንቅል ከሚሏቸው ውርጋጦች ላይ ይጥልሃል አሁንስ ኢትዮጵያዉያን አይደለንም የሚሉት ተስማምቶኛል እንደነሱ አይነት ኢትዮጵያዊ የለም፡፡ ባንዳነት ባህላቸው ሁኗል ያጎረሳቸውን እንደነከሱ እንዳረዱ አሁን ድረስ አሉ፡፡ እንገንጠል ሲሉ መንገዱን እንደማመቻቸት በጀት መመደብ፤ከወንጀለኛ ዝርዝር መሰረዝ፤ቢሊዮን ብር ኢትዮጵያን እንዲሰድቡበት በአንቶኖቭ ጭኖ እግር ስር ወድቆ መስጠት፤ሲጠቁ ምቱን አቁሙ ማለት ምን የሚሉት ነው? የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረድ

  2. ከጠጃሙ ጌቾ የምንዝናናበት አንድን ቁም ነገር አስትውለናል፡፡
    ወያኔ “”ድልድይ አፍራሽ”ወንበዴ”” ሆና በነበረችበት ጊዜ ምእራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ የምትላቸውን ለም የአማራ መሬቶች ማለትም ወላቃይት፣ ጠገዴ፣ ራያና አካባቢውን አሁንም የባለይዞታ መብት አለኝና አለም ይፍረደኝ እያለች እየጮሀች መሆኑን ነው፡፡
    እነዚህ መሬቶች እጅግ ለም የሆኑ የአማራ ርስቶች ናቸው፡፤ በጉልበት ወስደዉት ነበር፡፡ አማራ የደም ዋጋ ከፍሎ በጉልበት አስመልሷቸዋል፡፡
    መሬቶቹ በእርግጥም እጅግ በጣም አጓጊ የሆነ ሰፊና ፈጣን ልማት ሊካሄድባቸው የሚችሉ እጅግ አመቺና ለም የሆኑ መሬቶች ናቸው፡፡ ወያኔ ይህንን እውነታ አሳምሮ ስለሚያውቅ ነው የማይገባውን እንደ ትንሽ ልጅ የሚያላዝነው፡፡
    ሰፋፊና ያለቀላቸው የአግሮ ኢንዱስትሪ ልማት፣ የክብት ሀብትና ተዋጽኦ ልማትና መስኖ ልማቶች ጥናቶች ተካሂደው ቁጭ ብለዋል፡፡ትግራይ ተገንጥላ አገር በመሆን እነዚህን ርስቶቿ እስከምታደርግ ድረስ ጥናቶቹ ይፋ እንዳይወጡ ተደርገውም ታሽጎባቸዋል፡፡
    የእነዚህ መሬቶች ባለመብቱና ባለርስቱ የአማራ ህዝብ በራሱ ትክክለኛ ልጆች መመራትና መተዳደር ሲጀምር በራሱ መንገድ ወደልማቶቹ ይገባል፡፡ የእነዚህ አካባቢወች ሁለገብና የተደጋገፈ ዘመናዊ ልማት የአማራን ህዝብ አልፎ ዘልቆ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለጎረቤት አገሮች ጭምር የሚትረፈረፍ እንደሚሆን ጥናቶቹ ይጠቁማሉ፡፡
    ስለዚሁ ጉዳይ የማያገባቸው አሜሪካና የኤውሮጳ ህብረት የሚያደሩትን የተንኮል ጸረ አማራ ድር እኛ አማራወች ማወቅ፣ መከታተል፣ነቅተን መጠበቅና ማክሸፍ አለብን፡፡ ለነገሩ አሜሪካም ሆነች የኤውሮጳ ህብረት በፈለጉት ቅኝት ጉዳዩን ቢቃኙትም 46 ሚሊዮኑን የአማራ ህዝብ ጨርሰው አጥፍተው መሬቶቹን ለወያኔ ሊያሰጡት አይችሉም፡፤ አማራ ጠሉ አብይ አህመድም ቢሆን በድርድርም ሆነ በምክክር ሰበባ ሰበብ አማራን ከርስቱ ላይ ነቅሎ ለወያኔ የሚሰጥበት አግባብ በሚገባ የተነቃበት ስለሆነ አያዋጣውም፡፡ ይህንኑም በሚገባ ተረድቶታል፡፡
    በነገራችን ላይ እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ አብይ አብይ አህመድም የአማራ ህዝብ ቁጥር ከሁሉም የበለጠ መሆኑን አይቀበልም፡፡ ሲጀመር የአማራ ህዝብ 27 ሚሊዮን እንጅ 46 ሚሊዮን ነው የሚለውን ማመን አይፈልግም;፡፡ ምክንያቱም ባለው አሰራር የበጀት ድልድል፣ የድምጽ ቆጠራና ሀብት ክፍፍል መሰረቱ ይህ የህዝብ ብዛት ቆጠራ ዉጤት ስለሆነማ እውነቱ ከወጣ በቂጡ ቁጭ ስለሚል ነው፡፡ የሚደነቅ ፍራቻ ነው፡፡ እርሱና ተረኛው ኦሮሙማ በስልጣን እስካሉ ድረስ አብይ አህመድ ይህንን እውነታ አምኖ አይቀበልም፡፡ ተአማኒ ቆጠራ አድርጎ ለማረጋገጥም አይደፍርም፡፡
    ማጭበርበሩን ጊዜና ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ ዉጤት ወደፊት ይፈታዋል፡፡
    ጌቾ ይህንን ቢያውቅም የወያኔ አፈጣጠሩ ስለሆነ ህገ መንግስቴ ብሎ ያቀረበውን የጫካውን የወያኔ ማኒፌስቶ አያከብረውም፡፡ ከውስጡ የሚጠቅመውን እየመረጠ ሲጠቀምበት ይከበርልኝ ሲል በጎን ከዚያው ህገ መንግስት የማይጠቅመውን እየመረጠ ውድቅ ያደርገዋል፡ ይጥሰዋል፡፡ ፡ ይህ ነው ወያኔ ማለት፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share