በኢትዮጵያ የህዝብ ቆጠራ የማይደረግበት ዋና ምስጢር (እውነቱ ቢሆን)

የአገሪቱ ችግሮች የሚመነጩት ወያኔ በኦነግ ትከሻ ላይ ተረማምዶ ካቋቋመው ህገ መንግስት መሆኑተደጋግሞ ተገልጿል፡፤ ከሽህ አመታት በፊት ተፈጥራ ለዘመናት አንዴ ስትሰፋ አንዴ ስትጠብ የኖረችውን ኢትዮጵያን ወያኔ መራርጦ ያደራጃቸው ብሄር ቤረሰቦች ተስማምተው በፈቃዳቸው የፈጠሯት  ነው ይላል ህገመንግስቱ፡፤

አገር የሚመራውም ሆነ የሚተዳድረው በስምምነት ላይ ተመስርቶ መሆኑ አለም አሁን የደረሰበት እውነታ ያረጋግጣል፡፡ ስምምነቱ ግን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፤ በእኩልነት ላይ ለሚካሄድ ስምምነት ግልጽ የሆነ መስፈሪያ ያስፈልገዋል፡፤ ከነዚህ መስፈሪያወች ውስጥ አንዱ ትክክለኛ ውክልና ነው፡፤ ይህም ውክልና መሰረቱ የህዝብ ብዛት ነው፡፡ የህዝብ ብዛትን መሰረት ያላደረገ ስምምነት በጉልበት ለጊዜው ካልሆነ በስተቀር ዘላቂነት  ሊኖረው አይችልም፡፡

በፊት የወያኔ አሁን ደግሞ የኦሮሙማ የተሳሳተ አመራር ከፈጠረው እልቂት የተረፈው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት አሁን ላይ ከ116 እስከ 120 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ ይገመታል፡፡ ይህንኑ  ግምት የሚያረጋግጥ የህዝብ ቆጠራ ዉጤት ግን በተጨባጭ የለም ሳይሆን ትክክለኛና ተአማኒ የህዝብ ቆጠራ እንዲደረግ አይፈለግም፡፡ በጭራሽ??

በህዝብ መራር ትግል ከስልጣን የተባረረው ወያኔ ያደርግ እንደነበረው ሁሉ ተረኛው ገዥ ፓርቲም ያንኑ እያደረገ ነው፡፤ በነገራችን ላይ አሁን ያለው ገዥ ፓርቲ ተብየው “ብልጽግና ፓርቲ” ሁሉንም ያካተተ ነው ይባላል እንጅ በተግባር ግን የኦሮሞ የበላይነት የነገሰበት “የተረኞች” ፓርቲ ነው፡፡ ሌሎቹ ማናጆና ተለጣፊወች ናቸው፡፡ በሴራ ፖለቲካ የተካነው አብይ አህመድ አስቦና አቅዶ ያደራጀው ይህ የዘረኞችና የተረኞቹ ኦሮሙማወች መፈንጫ የሆነው ፓርቲ ግልጽና ተአማኒ የሆነ የህዝብ ቆጠራ ቢደረግ መሰረቱን የሚያናጋው መሆኑን አሳምሮ ስለሚያውቅ የህዝብ ቆጠራ መደረጉን እንደ ጦር ይፈራዋል፡ለአንድ አገር ሁለንተናዊ እድገት የህዝብ ቆጠራን ማድረግና የተፈጥሮ የሀብት ክምችት ለይቶ ለማወቅ ለዉጤታማ ዘመናዊ አስተዳደር ወሳኝነት አለው፡፡

አሜሪካ ነጻነቷን እንደ ኤውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1776 ያወጀች ሲሆን ብሄራዊ የህዝብ ቆጠራ እንዲደረግም በህገ መንግስቷ ቆጠራው በየአስር አመቱ እንድደረግ በህግ ደንግጋለች፡፡ ይህ ማለትም አሜሪካ የህዝብ ቆጠራ የማድረግ አስፈላጊንትን በህገመንግስቷ ያወጀችው የባቡር ተሽከርካሪ ወይንም ብሄራዊ መዝሙር ሳይኖራት በፊት ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ ምን ያህል የሰው ሀብት ቁጥርን በትክክል ማወቅ ለልማት፣ ለዲሞክራሲ፣ ለምርጫ፣ ለስልጣን ውክልና፣ ለሀብት ክፍፍልና  ወዘተ ምን ያህል ጠቃሚና አስፈላጊ እንደሆነ በግልጽ ያሳያል፡፤ ብዙ አገሮች የህዝብ ቆጠራን በአዋጅ አስደንግገው በተግባርም ሀቀኛ ቆጠራን አድርገው ይገለገሉበታል፡፤ ይህም ለዲሞክራሲ መጎልበትና  ለአገራቸው ሁለንተናዊ እድገት ዋና ቁልፍ መሳሪያ ሆኖ እያገለገላቸው ይገኛል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የፕሪቶሪያ ስምምነት:- ውጫሊያዊ ወይስ አልጄርሳዊ? (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

እኛስ አገር??  እኛ አገርማ ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ እንድደረግ አይፈቀድም፡፤ ቆጠራው ይደረግ ከተባለም የእጅ ስራ ተሰርቶ የሚቀርበው የተጭበረበረ የህዝብ ቆጠራ ዉጤት ነው የሚሆነው፡፡

ወያኔ አንድ ወቅት ያደረገው የይስሙላ የህዝብ ቆጠራ ዉጤት በአሳፋሪነቱ ወደር አልተገኘለትም፡፡ በዚያ አሳፋሪ ቆጠራ ዉጤት መሰረት የአማራ ህዝብ ከአመታት በፊት ከነበረበት ቁጥር በሁለት ሚሊዮን አንሶ ተገኘ ተብሎ የቆጠራ ሪፖርት ቀርቧል፡፡ ይህም ድርጊት  ምን ያህል የሚያሸማቅቅ ተንክልና ሴራ በአማራው ላይ እንደተሰራ ቁልጭ አድርጎ አስይቷል፡፤ አማራው በምንም ጉዳይእስካሁን ድረስ  ትክክለኛ  የሆነ የራሱ ተወካይ ስለሌለው እንደ ሌሎች ጉዳዮች ሁሉ ይህም የአማራ ህዝብ ቁጥር በፊት ከነበረበት በሁለት ሚሊዮን አንሶ የመገኘት ጉዳይ ተድበስብሶ ቀርቷል፡፤ ምክንያቱም የአማራ ወኪሎች ተደርገው የተቀመጡት ሆዳሞችና ትርፍ አንጀቶች በፊት ለወያኔ አሁንም ደግሞ ለተረኛው ለሮሙማ አጎብዳጅ አሽከሮች ስለሆኑ ነው፡፡

ወሳኝ ወደሆነው ተአማኒ የህዝብ ቆጠራ ርእሳችን እንመለስ፡፡ ተረኛው ኦሮሙማ ጠቅልሎ የያዘው መንግስት ይህ እንዲፈጸም ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ያለው የአብይ አህመድ ኦሮሙማ አገዛዝ እንኳን የህዝብ ቆጠራ ሊያስብ ይቅርና በሁሉም አቅጣጫ ኢትዮጵያዊነት እየነቀለ በቦታው  ኦሮማዊነት እየተከለ ነው የሚገነው፡፡  ይህ እስከመቼ ይቀጥላል?? አይታወቅም፡፡ ጊዜና የግፉ ሞልቶ የመፍሰስ መጠን ይፈታዋል፡፡

በአገሪቱ ውስጥ ህዝቡ ተሳስቦና አንዲነቱን አጠናክሮ በሀቀኛ ፌደራላዊ አስተዳደር እንዳይተዳደር በአለም ላይ ተሞክሮ በከሸፈ በዘር ላይ በተመሰረት ፌደራሊዝም  መደራጀቱን በፊት ወያኔ አሁን ደግሞ  የአብይ አህመድ ኦሮሙማም  የሙጥኝ ብለው ተያይዘውታል፡፡ ይህ ሁሉንም ይጎዳል እንጅ  ማንንም እንደማይጠቅም ይታወቃል፡፤ዙሮ ዙሮ የአገር ውድቀትን ብቻ ነው የሚያመጣው፡፡ ለጊዜው ሊመስላቸው ይችላል እንጅ አንዱ ተነጥሎ የላቀ ተጠቃሚና ሰላም የሚሆንበትን ዘላቂ መንገድን ፈጽሞ አያመጣም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአቋም መግለጫ - ኢትዮጵያን የዘመናችን ጽንፈኞችና ጎሰኞች እንዲያፈርሷት አንፈቅድም!

ባለጊዜወቹ ከገፉበት ዘንድ ግን ትክክለኛ የሆነ የህዝብ ቆጠራ ተደርጎ ሁሉም ዘር በዚያ ቆጠራ ዉጤት ላይ ብዛቱ ይታወቅና ልማቱም ውክልናውም የበጀት ድልድሉም የድምጽ አሰጣጡም በዚሁ ሁሉም ተስማምቶ ባመነበትና በሚጸደቀው በውጭ ታዛቢወችም  በኩል በተረጋገጠው ትክክለኛ የህዝብ ቆጠራ ዉጤት ላይ ይመስረት የሚለውን ሀሳብ ተረኞቹ ኦሮሙማወች ፈጽሞ አይቀበሉትም፡፤ በአጎራባች ያሉትን ሁሉ አማራውንም፣ ጉራጌውንም፣ ሶማሌውንም ደቡብ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦችንም “” እኛ ኦሮሞ ነህ ብለንሀል ተቀበል”” ነው ጉዳዩ፡፡ ይህ አያስኬድም፡፡

በወያኔ አሰራር የተካለሉትን ክልሎች  ብንወስድ  ከአማራው፣ ከጉራጌው፣ ከአፋሩ፣ ከሶማሌው ከደቡብ ልዩ ልዩ ብሄር ብሄረሰቦች አሁን ተረኛው ኦሮሙማ ግዛት እያስፋፋና  እየጠቀለላቸው ያሉ መሬቶችና በመሬቶቹ ላይ ያሉት ህዝቦች በሙሉ ትክክለኛ ቆጠራ ከተደረገ ማንነታቸው ገሀድ ስለሚወጣ ኦሮሙማ አቀንቃኙ የአብይ አህመድ አገዛዝ ራቁቱን ይቀራል፡፡

ይሄውም የቆጠራ ውጤቱ ተአማኒና ሀቀኛ በሆነ መንገድ ከተካሄደ የት የቆጠራ ቦታ ላይ ማን የበለጠ የህዝብ ቁጥር አለው የሚለውን ራሱ  ዉጤቱ ቁልጭ አድርጎ ስለሚያሳይና በዚያ ቆጠራ ዉጤት ላይም ተመስርቶ ያ ህዝብ በቆጠራ ዉጤቱ መሰረት በራሱ ሰወች የመተዳደር መብትን ስለሚያጎናጽፈው የአብይ አህመድ ተስፋፊ የኦሮሙማ አገዛዝ አለቀለት ማለት ነው፡፡

ይህ እውነታ እንደሚፈጠር አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች ምሳሌ በናዝሬት፣ ሀረር፣ ድሬዳዋ፣ ደብረዘይት፣ አዋሳ ጅማ፣ ወዘተ ቁልጭ ብሎ መሬት ላይ ያለ ሀቅ ነው፡፡

አብይ አሁን ይህንን የሚያስብ ጭንቅላትም ግዜም የለውም፡፡ የህዝብ ቆጠራው ለእርሱ ቀልድ ነው፡፤

አብይ አህመድ አሁን በአራት ነገሮች ላይ ህልምና ቅዠት ውስጥ ነው ያለው፦ እነርሱም፦

1ኛ)   ፋኖን አጥፍቼና አማራን ራቁቱን አስቀርቼ ከወያኔ ጋር በገባህት ድብቅ ውል መሰረት እንዴት አድርጌ ነው ራያንና ወልቃይትን ለወያኔ አስልፌ የምሰጠውና ስልጣኔን የማስቀጥለው?

ተጨማሪ ያንብቡ:  እሽሩሩ ማሞ - በ አሥራቴ ወርቁ

2ኛ) በተካንኩበት ውሸት ህዝቡን ሸውጄ እንደት አድርጌ ነው የአገሪቱን እድሜ ጠገብ የእስልምና ሀይማኖት በእነ አህመድን ጀበል ተዋንናይነት አበጣብጬ የማጠፋውና አመራሩንም በኦሮሞወች እጅ የማስገባው፡፡ ኦርቶደክስን እንዴት አድርጌ ልፈረካክሰውና እርባና ቢስ ላድርገው??

3ኛ፣ የዙፋኔን መቀመጫና የዘረፋ ማእከሌ የሆነችውን ስድስት ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባትን አዲስ አበባ ከተማንና ኗሪውን አዲስ አበቤን ሸውጄ በሀገ መንግስቱ ራሷን ከቻለች መስተዳድርነት አውጥቼ እንደት በኦሮምያ ስር ላድርጋት??

4ኛ)  አገሪቱ እንዲህ ስትታመስ ኢትዮጵያዊነት በጀመርኩት ዘዴ በቶሎ ተነቃቅሎ ኦሮማዊነትን እየተከልኩ እንዴት በቶሎ ፍሬ እንዲያፈራ ላድርገው?

በጣም አጭር አስተያየትና ምክር፦

አብይ ሆይ አትችልም፡፡ አንዱንም ሳታሳካ የህዝቡ ብሶት የወለደው ጎርፍ እየሞላ ስለሆነ ጠራርጎ ይወስድሀል፡፤ አንተ በወንጀልህ የሚገባህን ፍርድ ስታገኝ በዙሪያህ ያሉት ሆዳሞቹ የአማራ አስከሮችህና ተረኞቹ የኦሮሙማ ተጠቃሚወችም ከፍርድ አያመልጡም፡፤ የሚያሳዝነው ልጆችህና የልጅ ልጆችህወደፊት በአንተ እንዴት እንደሚሸማቀቁብህ አለመረዳትህ ብቻ ነው፡፤

አስራ አንደኛው ሰአት ላይ ነህ፡፡ በቶሎ ከኦሮሙማ ድሪቶ ውጣና የኢትዮጵያዊነትን ካባ ልበስ፡፡ ሆን ብለህ አስበህና አቅደህ እያስደርግህ ያለውን የተረኞቹን ኦርሮሙማወች ድንፋታ፣ ዘረፋና ጭፍጨፋ በቶሎ አስቁም፡፤ በቶሎ ተአማኒ የህዝብ ቆጠራ እቅድ  አውትተህ ወደ ተግባር ግባ፡፡ በዚሁ መሰረትም ትክክለኛ ህዝቡ በነጻነት የተሳተፈበት ፌደራላዊ ስርአትን የሚያዋልድ ሀሳብ ደፍረህ ይዘሀ ቀርበህ አሁንም ወደ ተግባር ግባ፡፤ ለዚህ ቅድሚያ የሚያስፈልገው በነጻነትና በሙያ ከህዝብ የተመረጠ ኮሚሽን መቋቋም ስለሆን ይህ ኮሚሽን ተቋቁሞ ይምራው፡፡ አንተ ለሰራሀቸው ወንጀሎችህ በይፋ ወጥተህ የኢትዮጵያን  ህዝብን ይቅርታ ጠይቀህ  ከስልጣንህ ልቀቅ፡፡! አለበላዚያ አንተም ተዋራደህ፣ ህዝቡንም፣ አሪቱን ጎድተህ ፣ታሪክህንም አበላስተህ  የወንጀለኛነት ፍርድህን ታገኛለህ፡፤

ከብጥብጡ በኋላ ያለቀው አልቆ አገሪቱ በራሷ ጊዜ ተመልሳ አገር ልትሆን ትችል ይሆናል፡፡ ካልሆነም የሚብስበት ይታያል፡፡ መቼስ ምን ይደረግ ባለጌ ያቦካው ሊጥ ሆነና ነገሩ!!!

 

 

2 Comments

 1. አሜሪካ ነጻ አገር ሆና የተመሰረተችው እኤአ በ1776 ሲሆን ይህ በሆነ በ14ኛው አመት ማለትም ከ1790 ጀምሮ በየአስር አመቱ የህዝብ ቆጠራ ይደረጋል፡፡ ይህ አይነት አሰራር በዙ ጠቀሜታ ስላለው በብዙ አገሮች ውስጥ ይፈጸማል፡፡
  ወያኔ አማራን ጠላት አድርጎ ስለሚያስብ አማራን የጎዳሁ መስሎት ከአማራ ርስቶች ውስጥ ወልቃይት ጠገዴንና፣ ራያን ወደ ትግራይ፣ መተክልን ወደ ቤንሳንጉል ክልልና ሸዋ ውስጥም የተለያዩ ቦታወችን ወደ ኦሮሚያ አካልሏል፡፤
  ይህ ሲሆን አንድም የአማራ ህዝብ ጥቅምን የሚያስከብር ወይንም ለምን አላግባብ እንደዚህ ይሆናል ብሎ የጠየቀ ትክክለኛ የአማራ ህዝብ ወኪል አልነበረም፡፡ አሁንም የለም፡፡ አሁንም ቢሆን በተለያዩ ኦሮሚያ በተባለው ክልል ውስጥ በሚገኙ ከተሞችም ውስጥ የአማራው ቁጥር ከ60% በላይ አማራ ነው፡፤ ምሳሌ ናዝሬት ፡፡
  ኦሮሙማወች ሊውጧት ዳር ዳር እያሉ ባለችውና ስድስት ሚሊዮን ህዝብ በሚኖርባት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የአማራው ቁጥር ከ60% በላይ እንደሆነም ተረጋግጧል፡፤ አሁን ዲሞግራፊውን ለመቀየር በአብይ አህምመድ መሪነት ኦሮሙማወች የሚያደርጉትን ትንቅንቅ ተኝክረን ካልመከትነው ዉጤቱ አስጊ ይሆናልና ህዝቡ ሆ ብሎ ወጥቶ ያለቀው አልቆ የተረፈው ነጻ ሆኖ መኖር የሚችልበት ሁኔታን አናፋጥን፡፤ ዝም አንበል!!!እንነሳ!! ሀቁን እንጋፈጠው!!!

 2. አብይ አህመድ ያለቀው ህዝብ ያልቃል እንጅ ፈቃደኛ ሆኖ ስልጣኑን አይለቅም፡፤ በተፈጥሮው ውሸታም፣ ምላሳም፣ ነፍሰ በላና ጨካኝ ሰው ነው፡፡
  ዞሮ ዞሮ አገሪቱ በተረኞቹ ኦሮሙማወቹ ታምሳ ታምሳ ሲበቃት ተመልሳ ትነሳ ይሆናል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሁሉም ስያለቅስባት ይኖራል እንጅ ኦሮሞ ብቻውን ወይንም ትግሬ ብቻውን ወይንም አማራ ብቻውን ነጻ ህዝብ ህኖ በሰላም ሊኖር የሚችልበት ሁኔታ ፈጽሞ አይኖርም፡፡ በጭራሽ፡፤ የኢትዮጵያ አገርነት አመሰራረት የተለየ ባህሪ ያለው ስለሆነ ወይ በአንዲነት ያልፍልናል ወይንም በተናጠል ስናለቅስ እንኖራለን፡፡ እስከዚያው ተረኞቹ ይዝረፉ፡፡ ይፈንጩ፡፡
  ፋኖን በሚለከት፦ አብይ እየፈራም ቢሆን ሊያጠፋው የዘመተበት ፋኖ አፈር ልሶ ይነሳል፡፤ ህዝቡ ተማምሎ የቆመው ከፋኖ ጎን ስለሆነ መጀመሪያ የአማራ ሆዳሞችን ከያሉበት ለቃቅሞ ያጸዳቸውል፡፤ አካባቢውን ከእነ ግርማ የሽጥላ አይነቶቹ የአብይ አህመድ አስከሮችና ጸረ አማራ ሆዳም አማራዎች አካባቢውን ነጻ ያደርጋል፡፤
  ቀጥሎም ሆ ብሎ ነፍጡን በማንገብ በኢትዮጵያ አንዲነት ከሚያምኑ ወንድሞቹ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ከግፈኞች አገዛዝ ነጻ ያወጣል፡፡
  ነውር ስለማያውቁ ትናንትና በእስልምና ሀይማኖት ላይ ያደረጉት መፈንቅለ ሀይማኖት አመራር አሳፋሪ ነው፤፡
  መጨረሻ ላይ ግን የትም አይደርሱም፡፤

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share