July 19, 2022
10 mins read

ጭራቅ አሕመድ የአማራን ሕዝብ በዚህ ደረጃ ለማታለል እንዴት ቻለ?

Abiy killer

 

ወያኔ ሊጥ አቡኪ፣ ኦነግ ዳቤ ጣይ
ተበላህ አማራ አትነሳም ወይ?

ያማራ ሕዝብ ሆይ፣ ያመንከው ፈረስ
ረጋገጠህ ጥሎ በደንደስ፡፡
በወደክበት እንዳትጨረስ
እንዳባቶችህ ፎክረህ ተነስ፡፡

ሰይጣን ነውና የቀመሰ ምስ
ከጥፋት መቸም የማይመለስ፣
አፈሙዝ አዙር አልመህ ተኩስ
ፈረሱን በለው አናቱን በርቅስ
በገደል ጣለው ወድቆ ይከስከስ፡፡

ጭራቅ አሕመድ የትግሬን ሕዝብ እንደ ሕዝበ አላታለለም፡፡ የኦሮሞንም ሕዝብ እንደ ሕዝብ አላታለለም፡፡ የአማራን ሕዝብ ግን እንደ ሕዝብ ማታለል ብቻ ሳይሆን አነሁልሏል፡፡ ስለዚህም መሠረታዊው ጥያቄ ለምን የሚለው ነው፡፡

ክቡር መጽሐፍ ቦ ጊዜ ለኩሉ (ለሁሉም ጊዜ አለው) እንዳለው፣ ጭራቅ አሕመድ በውሸት፣ ለውሸት የተፈጠረ፣ ውሸት በልቶ ውሸት የሚያራ ውሸታም መሆኑ አገር ያወቀው፣ ፀሐይ የሞቀው ሁኗል፡፡ ለወያኔ ወታደሮች ሲላላክ ያደገ በመሆኑ ደግሞ በልጀነቱ የበሻሳ ኪስ አውላቂ ባይሆን እንጅ ቢሆን አያስገርምም፡፡ አኳኋኑና የንግግር ዘይቤውም የሚጠቁመው ይሄንኑ ነው፡፡ ምናልባትም ደግሞ ወያኔና ኦነግ ከጋቱት በላይ የአማራ ጥላቻውን እጅግ ያከረረበትና አማሮች በሥራም ሆነ በሌላ ምክኒያት ወዳለሁበት አይምጡብኝ እስከማለት የደረሰው፣ በተወለደበት ከተማ ላይ ለቡና ለቀማ የመጡትን የላኮመልዛና የጎጃም ሠርቶ አደሮች ኪስ ለማውለቅ በመዳረጉ ሊሆን ይችላል፡፡ የበሻሻ ኪስ አውላቂ ከነበረ ደግሞ ኪስ ወለቃው በከሸፈበት ቁጥር የሚቀምሰው የጎጃሜወችና የላኮመልዜወች ቆመጥ ዱላ የአማራ ጥላቻውን ይበልጥ እንደሚያከፋበት ግልጽ ነው፡፡ አማራ በታረደ ቁጥር ደስታውን ለመግለጽ አበባና ችግኝ የሚተክልበትም አንዱ ምክኒያት ይሄው ይሆናል፡፡
ወያኔ የአማራ ጥላቻ እየጋተ አሳድጎት፣ ሹሞትና ሸልሞት፣ ለወግ ማዕረግ ሲያበቃው፣ አማራ ያገባው ባጋጣሚ ሳይሆን ሥራየ ብሎ ከሆነ ደግሞ፣ የአማራን ሴት ለሚስትነት የመረጠው በአማራ ላይ ያለውን ቂምና በቀል ለመወጣት ሲል ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ በረከት ስምዖንን ጨምሮ የአማራ ጥላቻቸው መሪር የሆነ ወያኔወችና ኦነጎች ሚስቶቻቸው አማሮች መሆናቸውን መታዘብ ያስፈልጋል፡፡ ነጭን አምርረው የሚጠሉ የአሜሪቃ ጥቁሮች አብዛኛውን ጊዜ የሚያገቡት ነጭ ሴቶችን እንደሆነ ሁሉ፡፡
ጭራቅ አሕመድ የወጣለት አታላይ ቢሆንም፣ የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ ከማታለል አልፎ ሊያነሆልል የቻለው ግን፣ ባታላይነት ክሂሎቱ ብቻ ሳይሆን፣ የአማራ ሕዝብ ለመታለል ዝግጁ ሁኖ በጉጉት እየጠበቀው ስለነበር ነው፡፡

ባሏ ከሌላ ሴት ጋር የሚማግጥባት ሴት፣ ትዳሯን ላለማፍረስ ካላት ከፍተኛ ጉጉት የተነሳ፣ እሷ ጋር ብማግጥም የማፈቅረው ግን አንችን ነው እያለ በመዋሸት እንዲያሳምናት አጥብቃ ትመኛለች፡፡ ባልየው እኩይ ከሆነ ደግሞ ውሸቱን ለማመን ሙሉ ዝግጁ ሁና በጉጉት የምትጠባበቀውን ሚስቱን በቀላሉ ያሳምናታል፡፡ እሷ ደግሞ ባሏ እንደማያፈቅራት በልቧ እያወቀች፣ ውሸቱን ውነት አድርጋ በመውሰድ፣ የሚያፈቅረው ውሽማውን ሳይሆን እኔን ነው እያለች አጉል በመኩራራት፣ ራሷን በራሷ እየደለለች ኑሮዋን ለመግፋት ትጣጣራለች፡፡ ሐቁ ፊት ለፊት ሲጋፈጣት ደግሞ ዓይኖቿን ክናብ፣ ጆሮዋን ዳባ አልብሳ ዓይታ እንዳላየች፣ ሰምታ እንዳልሰማች ትሆናለች፡፡ ወይም ደግሞ ሐቁን ራሷ ለራሳ ለማስተባበል የማይመስሉ ምክኒያቶችን ትደረድራለች፡፡ ጎሽ ለልጇ ስትል እንደምትወጋ፣ እሷም ለትዳሯ ስትል ትወጋለች፡፡ የአማራ ሕዝብ በዚች ሴት፣ ትዳሯ ደግሞ በጦቢያ ይመሰላሉ፡፡

የአማራ ሕዝብ ከትግሬና ከኦሮሞ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ የሚያስቀድመው አማራነቱን ሳይሆን ጦቢያዊነቱን ነው፡፡ የአማራ ሕዝብ ጦቢያ ከምትፈርስበት ራሱ ቢፈርስ ይመርጣል፡፡ ስለዚህም ወያኔ ለሃያ ሰባት ዓመት ጦቢያንና ጦቢያዊነትን አለመጥን ሲያዋረድና፣ ከዛሬ ነገ አፈራርሳታለሁ እያለ ሲዘት፣ እንደ ሕዝብ አንጀቱ እየቆሰለ፣ እንደ ሕዝብ ልቡ በስጋት ይንጠለጠል የነበረው የአማራ ሕዝብ ብቻ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ከወያኔ ሹሞች (በተለይም ደግሞ ጭራቅ አሕመድን ከመሳሰሉ የበላይ ሹሞች) የጦቢያ አፍቅሮትን መጠበቅ፣ ከዕባብ እንቁላል ርግብ መጠበቅ መሆኑን ልቦናው ቢያውቅም፣ አንድ ደፋር የወያኔ ሹም አደባባይ ወጥቶ ጦቢያን አፈቅራታለሁ በማለት ዋሽቶ ውሸቱን እንዲያሳምነውና ከጭንቀቱ እንዲገላግለው፣ የአማራ ሕዝብ በልቡ ይማጸን ነበር፡፡ ጭራቅ አሕመድም ያደረገው ሌላ ምንም ሳይሆን ይሄንኑ ነው፤ ለመታለል ዝግጁ ሁኖ በጉጉት ይጠባበቅ የነበረውን የአማራን ሕዝብ ማታለል፡፡

ስለዚህም የእፍኝቱ የወያኔ ልጅ ጭራቅ አሕመድ አማራን በደንብ ቢያታልልም፣ አማራን በደንብ እንዲያታልል ሁኔታወችን በደንብ ያመቻቸለት ግን አባቱ ወያኔ ነበር፡፡ አታላይነቱን የአማራ ሕዝብ ሲነቃበት፣ በድርድር ሰበብ ወደ አባቱ ወደ ወያኔ ፊቱን ያዞረውም፣ አባቱ ጉያ ውስጥ የግድ መሸጎጥ ስላለበት ነው፡፡

ጦቢያ ከኦሮሚያ ትውጣ (Ethiopia out of Oromia) የሚሉትን ኦነጋውያንን ከልባቸው የሚያፈቅሩትን ኦሮሞወችን፣ ጦቢያን አፈቅራታለሁ በማለት ማታለል አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያ የረከሰች አገር ናት፣ ከዛች ከሃዲ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ራስህን አግልል በሚሉት ወያኔወች የሚመሩትን ትግሬወችንም ጦቢያን አፈቅራታለሁ በማለት ማታለል አይቻልም፡፡ አምላኩን የጦቢያ አምላክ የሚለውን የአማራን ሕዝብ ግን ጦቢያን አፈቅራታለሁ በማለት በባዶ ንግግር ብቻ ባርያ ልታደርገው ወይም ልትሸጠው ትችላለህ፡፡ የወያኔ ቂልነት እዚህ ላይ ሲሆን፣ የጭራቅ አሕመድ ብልጥነትም እዚሁ ላይ ነው፡፡

እጅግም ስለት ይቀዳል አፎት እንዲሉ፣ ጭራቅ አሕመድም ብልጥነቱን አለቅጥ አብዝቶ ራሱን በራሱ በመበልጠጥ ገሃድ አወጣ፡፡ ስለዚህም፣ ካሁን በኋላ ጭራቅ አሕመድ አማራን መብላት የሚችለው በማታለል ሳይሆን ይበልጥና ይበልጥ ጭራቅ በመሆን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሆይ፣ ጭራቁ በልቶ ሳይጨርስህ በፊት በልተኸው ተቀደስ፡፡

ጭራቅ አሕመድ ዐሊ የኦነጉ ኦቦ
አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ፡፡
ባንደበቱ መስሎ የኢትዮጵያ ሙሴ
በምግባሩ ሆነ የኦነግ ራምሴ፡፡
በመውረስ ያገኘው ከወያኔ አባቱ
መዋሸት ማጭበርበር ነውና ፍጥረቱ፣
አንዴ ቢያታልለን የሱ ነው ኀፍረቱ
ሁለቴ ቢደግም የኛ ነው ጥፋቱ፡፡

መስፍን አረጋ
[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop