የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዜብሔርን ለእግዚያብሔር ስጡ! ባላገር የሚበላው ቢያጣ፣የሚከፍለው አያጣም!

ሚሊዮን ዘአማኑኤል (ኢት-ኢኮኖሚ)

የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዜብሔርን ለእግዚያብሔር ስጡ!  “Give to Caesar what belongs to Caesar and to God what belongs to God.”

ፕሮፌሰር ለገሠ ነጋሽ ፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ዛፎች በማጥናት፣ ዘራቸውን በማፍላት፣ በማቆየት በእድሜ ልክ ስራቸው ‹‹የዛፎች ባለፀጋ›› ወይም “The Lord of the Trees”  በመባል በዓለም ይታወቃሉ፡፡ የኢትዮጵያና የአፍሪካን ዛፎች በማስረጃ በማጥናት ትልቅ አስተዋፆኦ ያደረጉ ሳይንቲስት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዛፍ በመትከል፣ በማስተከል እንኳን ኢትዮጵያዊያን የኢትዮጵያዊያን ምድር ይመሰክርላቸዋል፡፡ ስለ ፕሮፌሰር ለገሠ ነጋሽ ሥራና ዓለም አቀፍ እውቅና ለማወቅ  በ2012 እኤአ ቪዲዬ በመመልከት regreening the desert with john d. liu vpro documentary 2012  በመመልከት ምሥክርነታችሁን ስጡ፡፡ ‹‹የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዜብሔርን ለእግዚያብሔር ስጡ!›› ተብሎልና፡፡

  • Legesse Negashis Prof Emeritus of Plant Physiology in the Dept of Plant Biology (Addis Ababa University). A pioneer in Ethiopia’s native trees physiology .

https://www.google.com/search?q=regreening+the+desert+with+john+d.+liu+vpro+documentary+2012&source/

 

ዶክተር ፋንታሁን መንግሥቱ፣ ላለፉት ሦስት አስርት አመታት በግብርናው ዘርፍ ‹‹የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ማዕከል›› በመምራትና ብዙ ሳይንቲስቶች ጋር በህብረት በመሥራት በተለይ በኢትዮጵያ የቆላ ስንዴ መስኖ ልማት እድገት  በማስተዋወቅና ለተገቢው ሥነ-ምድር፣ ተገቢውን ምርጥ ዘር በማቅረብ የኢትዮጵያን የስንዴና የበቆሎምርቶች ከፍተኛ እንዲሆን በማድረግ ከሳህራ በታች ካሉ አፍሪካ ሃገራት ኢትዮጵያ  ሁለተኛ ደረጃ እንድትሆን ሳይንቲስት ልጆቾ ታሪክ ሠርተዋል፡፡ የዶክተር ፋንታሁን መንግሥቱና ጎደኞቻቸውን ሥራ  በተለያዩ ቪዲዮች በመመልከት ለሥራቸው እውቅና በመስጠት ብሄራዊ ጀግኖች መሆናቸውን  እንመስክር፡፡ ‹‹የቄሣርን ለቄሣር፣ የእግዜብሔርን ለእግዚያብሔር ስጡ!›› ተብሎልና፡፡

 

በዓለማችን የስንዴ ምርት ክምችት ሊያልቅ 70 ቀናት ቀርቶታል!!!!

የተባበሩት መንግሥታት በዓለማችን የስንዴ ምርት ክምችት ሊያልቅ ሰባ ቀናቶች ብቻ እንደቀረውና አስር ሚሊዮን ህዝብ በሞት አደጋ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ በዓለማችን የምግብ ቀውስ እየተባባሰ የመጣው ከራሽያና ዩክሬን ጦርነት ጀምሮ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በዓለማችን የምግብ ቀውስ በቅርቡ እንደሚከሰት አስጠንቅቆል፡፡ በዓለማችን በ2008 እኤአ የስንዴ ምርት ክምችት በቀነሰ ጊዜት በተመሳሳይ የምግብ እጥረት ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ‘’In a shocking revelation, the United Nations on Monday announced that the world has only 70 days of wheat left. The food crisis has deepened as the Russian-Ukraine war continues. The U.N. has warned the world of the impending crisis. Such a crisis last happened in 2008, when the world’s wheat stock went low. However, experts say it will be long before the wheat crisis goes away’’………………..(1)

የዓለማችንን የስንዴ ምርት አቅርቦት ሃያ አምስት በመቶ የሚሽፍኑት ከጦርነቱ በፊት በዩክሬንና ራሽያ ነበር፡፡ በዓለማችን የዓየር ሁኔታ ቀውስ የተነሳ አሜሪካና አውሮፓ የስንዴ ምርት ቀንሶል፡፡ ሃገረ ህንድም የስንዴ ምርት ወደ ውጭ ሃገራት ኤክስፖርት ሆኖ እንዳይሸጥ አግዳለች፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ኃላፊ ዴቪድ ቢስሌይ የራሽያና ዩክሬን ጦርነት በዓለማችን ላይ ከፍተኛ የድርቅና የርሃብ አደጋ አንጃቦል፣ ለአስር ሚሊዩን ህዝብ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ የህንድ መንግሥት የስንዴ ኤክስፖርት ማድረግ አግዳለች፣ በዓየር ፀባይ የተዛባ ለውጥ መነሻ ምክንያት የስንዴ ምርት ምርታማነት በማሽቆልቆሉ የተነሳ ወደ ውጭ የሚላከው የስንዴ ምርት እገዳ ተጥሎበታል፡፡  “India’s Ban on Wheat Export:-On May 16, India banned wheat exports due to the extreme weather conditions that hampered production. As a result, the  prices in the country too hit a record high. India’s sudden move to stop the exports has also affected the global market and saw a steep surge in prices.”…………..(2)

ተጨማሪ ያንብቡ:  እጁ በንጹሀን ደም የተጨማለቀው አብይ አህመድና የአማራው የህልውና ተጋድሎ

ኢትዮጵያ በግብርናው ኢኮኖሚ ዘርፍ የምታመርተው በአንደኛ ደረጃ የበቆሎ ምርት፣ ሁለተኛ የስንዴ ምርትና ሦስተኛ የጤፍ ምርት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የስንዴ ምርት ከአጠቃላይ የብሔራዊ ምርት አስራአምስት በመቶ ይሸፍናል፡፡ ኢትዮጵያ ከሳህራ በታች ካሉ አፍሪካ አገሮች በስንዴ ምርት አምራችነት አንደኛ ስትሆን ከአፍሪካ አገራት በስንዴ ምርት  ደቡብ አፍሪካ   አንደኛ ስትሆን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ የኢትዮጵያ አማካኝ የስንዴ ምርታማነት ሁለት ነጥብ አራት ቶን (24 ኩንታል) በሔክታር፣  ግብፅ ስድስት ነጥብ ሰባት ቶን (ስልሳ ሰባት ኩንታል) በሔክታር፣ ደቡብ አፍሪካ ሶስት ነጥብ አምስት  ቶን (ሠላሳ አምስት ኩንታል) በሔክታር እንዲሁም ኬንያ ሦስት ቶን (ሠላሳ ኩንታል) በሔክታር የስንዴ ምርታማነት እንዳላቸው የሪሰርች ጌት ጥናተ መረጃ ያመለክታል፡፡

“… In Ethiopia, wheat ranks second after maize (Zea mays L.) in total production and third after tef and maize in the cultivated area [1]. Wheat provides about 15% of the national caloric intake [2]. Ethiopia is ranked first in wheat production in sub-Saharan Africa (SSA) followed by South Africa [3]. …

… Ethiopia is ranked first in wheat production in sub-Saharan Africa (SSA) followed by South Africa [3]. However, its average productivity of 2.4 t ha −1 is lower than 6.7, 3.5, and 3.0 t ha −1 reported in Egypt, South Africa, and Kenya, respectively [2]. Ethiopia still imports wheat to meet the growing local demand due to population growth, the emergence of agro-processors, urbanization, and increased household income [4,5]. …” ……………..(3)

 

በ2021/22 እኤአ በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት 5.52 (አምስት ነጥብ ሃምሳ ሁለት) ሚሊዮን ቶን የነበረ ሲሆን፣ የስንዴው እርሻ የሸፈነው ስፍራ 1.95 (አንድ ነጥብ ዘጠና አምስት) ሚሊዮን ሔክታር መሬት ሲሆን የስንዴው ምርታማነት ደግሞ 2.83 (ሁለት ነጥብ ሰማንያ ሦስት) ቶን በሔክታር  ነበር፡፡

በ2022/23 እኤአ በኢትዮጵያ የስንዴ ምርት 5.7 (አምስት ነጥብ ሰባት) ሚሊዮን ቶን ይሆናል ተብሎ ይገመታል፡፡ የበቆሎ ምርትም አስር ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን እንደሚሆን ተተንብዬል፡፡ የስንዴው እርሻ የሸፈነው ስፍራ ሁለት ሚሊዮን ሔክታር መሬት ሲገመት፣ የስንዴው ምርታማነት ደግሞ 2.85 (ሁለት ነጥብ ሰማንያ አምስት) ቶን በሔክታር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ …. በ2022/23 እኤአ ኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ከውጭ ማስገባት ታቆማለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ የስንዴ ምርት ወደ  ውጭ ትልካለች በማለት ለፓርላማ ቃላቸውን ሰጥተወል፡፡   የተባበሩት መንግሥታት በዓለማችን የስንዴ ምርት ክምችት ሊያልቅ ሰባ ቀናቶች ብቻ እንደቀረውና አስር ሚሊዮን ህዝብ በሞት አደጋ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡  የዓለማችንን የስንዴ ምርት አቅርቦት ሃያ አምስት በመቶ የሚሽፍኑት ከጦርነቱ በፊት በዩክሬንና ራሽያ ነበር፡፡ በዓለማችን የዓየር ሁኔታ ቀውስ የተነሳ አሜሪካና አውሮፓ የስንዴ ምርት ቀንሶል፡፡ ህንድም የስንዴ ምርት ወደ ውጭ ሃገራት ኤክስፖርት ሆኖ እንዳይደረግ አግዳለች፡፡ ከዚህ በመማርም የስንዴ ምርት ከሃገረ ኢትዮጵያ እንዳይወጣ ማድረግ ያስፈልጋል እንላለን፡ምክንያቱም የተባበሩት መንግሥታት በዓለማችን የምግብ ቀውስ በጦርነትና በዓየር ሁኔታ መዛባት የተነሳ ድርቅ በቅርቡ እንደሚከሰት አስጠንቅቆል፡፡

  • In marketing year 2021/22, wheat production is estimated to be 5.52 million tons. This is due to satisfactory rainfall distribution in surplus producing areas of the country and minimum level of pest and diseases that resulted in very small quantity and quality losses. In 2021/22, harvested area is estimated at nearly 1.95 million hectares with wheat yield estimated at a record 2.83 tons/hectare.
  • Wheat Production: Ethiopia Wheat production for 2022/23 is projected at 5.7 million tons, up by 3.26 percent over the 2021/22 production estimate and harvested area is forecast at nearly 2 million hectares and the wheat yield is estimated at a record 2.85 tons/hectare.
  • Ethiopia removed tariff tax and other taxes on imported food grains and flour through a directive issued in September 2021. This helped to increase the legal wheat product and flour imports into the country. Ethiopia is planning to stop importing wheat in 2023. However, it is a very unrealistic and unachievable target within such a short period of time and with limited resources to adopt necessary technologies.
ተጨማሪ ያንብቡ:  የመጨረሻው መጀመሪያ እየተቃረበ ነውን? (ጌታቸው ማ. & ሳጅን ዮሮሱን)

 

በኢትዮጵያ የስብዓዊ ረድኤት ሁኔታ

በኢትዮጵያ አጠቃላይ የስብዓዊ ረድኤት ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን እያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ይገኛል በአንድ በኩል የጦርነቱ ሁኔታና ግጭቶች ምክንያት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የዓየር ሁኔታ መዛባት ያስከተለው ድርቅና ርሃብ ሁኔታን አስከትሎል፡፡ በኢትዮጵያ በ2020 እኤአ አሰቸኮይ የስብዓዊ እርዳታና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር 8.4 (ስምንት ነጥብ አራት) ሚሊዮን  ህዝብ የነበረ ሲሆን በ2021 እኤአ 23.5 (ሃያ ሦስት ነጥብ አምስት) ሚሊዮን  ህዝብ ፣ በ2022እኤአ 29 (ሃያ ዘጠኝ) ሚሊዮን ህዝብ የስብዓዊ ረድኤት ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው  ተገልጾል፡፡ “More than 29 million people were estimated in need of humanitarian assistance and protection at the beginning of 2022, compared to 23.5 million people at the beginning of 2021, and 8.4 million people in 2020. Nearly three quarters of the people in need this year are women and children.”

በኢትዮጵያ በ2022 እኤአ 2.9 (ሁለት ነጥብ ዘጠኝ) ሚሊዮን በላይ ህፃናት ከትምህርት ገበታቸው ላይ  የተፈናቀሉ ሲሆን  ዋነኛ ምክንያት ጦርነትና የድርቅ አደጋ  ነበር፡፡ በኢትዮጵያ 8660 (ስምንት ሽህ ስድስት መቶ ስልሳ) ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በጦርነቱ ወድመዋል፡  ከወደሙት ትምህርት ቤቶች ውስጥ  ሰባ በመቶ የሚሆኑት የሚገኙት በአፋር፣ አማራና ትግራይ  ክልሎች ውስጥ ነው፡፡ “As of May 2022, more than 2.9 million children across Ethiopia remain out of school due to conflict and drought. This represents 17 per cent of the school age population Almost 50 per cent of those out of school children are entering their third year without any access to learning, heightening the risk of a lost generation for children in northern Ethiopia Based on school damage assessments in May, more than 8,660 schools across Ethiopia are fully or partially damaged, 70 per cent of which were in Afar, Amhara and Tigray due to the North Ethiopia conflict.”

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትዝብት: የአገርቤት ቆይታዬ - አገሬ አዲስ

 

በትግራይ የነበረው የረሃብ አደጋ ስጋት መቀልበሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለጸ

‹‹ባለፈው ዓመት የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል አንዣቦ የነበረው የርሃብ አደጋ ስጋት መቀልበሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለጸ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይህን ያለው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች የስብዓዊ እርዳታ ማድረስ መቻሉን ተከትሎ ነው፡፡ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኃላፊ ኤድሪያን ቫንዳክናብ ዓርብ ሐምሌ 8 ቀን 2014 ዓ/ም ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ድርጅታቸው የስብዓዊ እርዳታውን ማድረስ በመቻሉ፤ በትግራይ ክልል ተከስቶ የረሃብ አደጋው ስጋት ተቀልብሶል ብለዋል፡፡……..ለ2.1 ሚሊዮን ሰዎች ምግብ ለማድረስ ታቅዶ ለ1.1 ሚሊዮን ሰዎች የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳት  ማድረሱን ኃላፊው ለቢቢሲ ገልፀዋል፡  የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከትግራይ በተጨማሪ በአማራ እና በአፋር ክልሎች ለሚገኙ  በርካታ ሰዎች መሠረታዊ የስብዓዊ እርዳታ ቁሶችን አድርሻለሁ ብሎል፡፡….. በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ አፋርና አማራ ክልሎች የተዛመተው የሰሜን ኢትዮጵያዊው ጦርነት ከፍተኛ ስብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስከትሎል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት በሦስቱ ክልሎች የሚገኙ ከ9 ሚሊዮን የማያንሱ ሰዎች አስቸኳይ የስብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዎል ሲል ነበር፡፡ ይህ የእርስ በእርስ ጦርነት ከፍተኛ የስብዓዊ መብት ጥሰቶችንንም አስከትሎል፡፡››…………..(4)

በጦርነት የርሃብን ዘር ከትግራይ ምድር ላይ የዘራው ወያኔ አቆማዳውን ሸክፎ ከመለመን በቀር የግብርና ምርት ለማምረት  አልታደለም፡፡ ወያኔ በትግራይ ህዝብ ላይ የነበረው የረሃብ አደጋ ስጋት መቀልበሱን ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ሲሰማ ደነገጠ፡፡ ወያኔ እናመሰግናለን ከማለት ይልቅ እልቆ መሳፍርት የእህል ጭነት እንዲላክለት በመፈለጉ የእህሉን እርዳታ ሸጦ የጦር መሳሪያ ለመሸመት አልሞ የነበረው ስለከሸፈበት ሌላ ትያትር በህዝቡ ላይ ለመስራት አቅዶል፡፡ ህዝቡን ይበልት ለማስራብ ወያኔ ግብር መጣልና ከአንድ ቤተሰብ ሁለት ልጆች ለጦርነቱ አዋጡ በማለት የትግራይን ህዝብ በማሰቃየት ላይ ይገኛል፡፡ ወያኔ ከትግራይ ገበሬዎች ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣል ‹‹ባላገር የሚበላው ቢያጣ፣ የሚከፍለው አያጣም!!!›› በማለት ገበሬዎች እንዳያርሱና ርሃብና ጠኔ በትግራይ ህዝብ ላይ እንዲያንዣብብ አቅደው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

 

ምንጭ

(1) https://curlytales.com/UN Says World Has Only 70 Days Of Wheat Left; 10 Millions At Risk (curlytales.com)/ by Sanmita A May 23, 2022 578

(2) Ethiopia – Humanitarian Update Situation Report, 27 Jun 2022Format

Situation Report Source OCHA

(3) Wheat production, consumption and import, Ethiopia (1995/96 – 2012/13)   | Download Scientific Diagram (researchgate.net)

(4) በትግራይ የነበረው የርሃብ አደጋ ስጋት መቀልበሱን የዓለም ምግብ ጵሮግራም ገለፀ/ 16 ሀምሌ 2022

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share