የህብር ሬዲዮ ዕሁድ መጋቢት 29 ቀን 2005 ፕሮግራም
ኢትዮጵያውያን በሳኡዲ አረቢያ የሚደርስባቸው የዘመቻ ግፍ ማቆሚያው የት ላይ ነው? ዓለም አቀፍ መረጃዎች ስለ ሳዑዲ መንግስት የግፍ እርምጃ ምን ይላሉ? በግብጽ ሲናይ በረሀ እንደዋዛ ወድቀው የሚቀሩት ወገኖቻችንስ ጉዳይ?…ትንታኔ ይዘናል
<<...በቬጋስ የሚኖሩና የስራ ማቆም አድማ ያደረጉ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን የኩባንያው የስራ ሀላፊ በአሸባሪነት መወነጀሉ አሳፋሪ ነው። ሁሉም ወገናችን ይህን ተራ ውንጀላ ሊያወግዘው ይገባል ። ...96 ሺህ ሰው የሚመጣበትን የብሮድካስቲንግ ኮንቬንሽን ቦይኮት እንዲደረግ ጥሪ አድርገናል ሁሉም ታክሲ ሾፌር አይጭንም ብለን እንጠብቃለን።ከእኛ ተቃራኒ የቆሙ ወገኖቻችንን ማንነታቸውን እናጋልጣለን። ...>> አቶ ቢኒያም ሰመረአብ ከቬጋስ የታክሲ አሽከርካሪዎች የስራ ማቆም አድማ አስተባባሪዎች አንዱ ጋር ያደረግነው ቃለ ምልልስ
ሌሎችም ቃለ መጠይቆች
ዜናዎቻችን
የግብጽና የሱዳን መንግስታት ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን እንዲታደጉ ዓለም አቀፍ ጥሪ ቀረበላቸው
ሂዩማን ራይት ዎች በእስር ላይ ያሉት የሙስሊም መሪዎች ጉዳይ እንደሚያሳስበው ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ ገለጸ
የሙስሊሙ ህ/ሰብ ለሳምንታት በአደባባይ አቋርጦት የነበረውን ትግል አጠናክሮ ቀጥሏል
ኳታር ኤርትራና ጅቢቲን ለመሸምገል እየጣረች ነው
የቬጋሱ ኢትዮ ስታር የሎስ አንጀለሱን ዳሎል ቡድን 2 ለ 0 አሸነፈ
ቴዲ አፍሮ የወንድ ልጅ አባት ሆነ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አገሪቱ በአደገኛ ሰዎች እጅ መውደቋንና ሕግ እየጣሱ የፈለጋቸውን እንደሚያደርጉ ገለጸ
ኢትዮጵያ ከሱዳን የምታስገባውን ነዳጅ አቋረጠች