July 8, 2022
23 mins read

ወዴት ? እንዴት ? ነው፤ የጠ/ሚሩ አካሄድ ? አልገባኝም – ሲና ዘ ሙሴ

12334445rrr 1ኢትዮጵያ በብልፅግና ፓርቲ ደረጃ ፣ ዜግነት በተካደባት በሥም ብቻ የምትወደስ ፤  በመከላከያ ደረጃ ደግሞ በአካል ፣ በተጨባጭ ግዝፍ ነስታ፣ የምትገኝ አገር ናት ። ይኽ እውነት ነው ። ከአራት አመት በፊት ኢትዮጵያ ! ኢትዮጵያ ! እያለ የሚጮኸው ሁሉ ፣ ዛሬ በየቋንቋው እየጮኸ ነው ። ዘውጌነት እጅግ በጠበበ መልኩ  የዛሬ 30 ዓመት በፊት ሚኒልክ ቤተመንግሥት ሲገባ እንደነበረው ምሥቅልቅል አገሪቱን እና ህዝቦን እርስ በእርሱ እንዲጠራጠር እያደረገው ነው ። እንሆ 31 ዓመቱን የደፈነው ዛሬ አንድ ብሎ የጀመረ ይመሥላል ።

ከ30 ዓመት በፊት ባለው በመጀመሪያው ዓመት ፖለቲካል ኢክኖሚ ውሥጥ  መገኘታችን እርግጥ  ይሁን እንጂ ፤  የዛሬዋ ኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ይኽንን እውነት የተገነዘበ አይመሥልም ።  የዛሬዋ  ገዢ ፓርቲ  ሊቀመንበር ከ 3 ዓመት በፊት በአሜሪካ የተናገሩትን ረሥተውታል ። ( የሜኔሶታን የጠቅላይ ሚኒሰትር አብይ አህመድ ንግግርን ለዋቢነት ከዩቲዩብ ላይ አድምጡ ። ከ3 ዓመት በፊት ምን እንደተናገሩ ትገነዘባላችሁ ። ) ዛሬ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የራሳቸውን ንግግር እንደገና ቢሰሙ በዛሬ ንግግራቸው መደንገጣቸው አይቀርም ¡¡ ጠቅላዩ ዛሬ ላይ ሆነው በጥልቅ ካሰቡ የሚረዱት   ኢትዮጵያ  ያልፈራረሰችው የአንድነት ኃይል ያለው ፣ በወጉ የተደራጀ ኢትዮጵያዊ መከላከያ ሠራዊት ሥላላት ብቻ ነው ! !  ለዚህ ጥንካሬው ያበቁት ጠቅላያችን ጭምር ናቸውና በግል አመሠግናቸዋለሁ ። ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ትልቅ ክብር አለኝና… ።

ኢትዮጵያ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት እንዲኖራት የተደረገው ጥረት እጅግ የሚያሥመሠግን ነው ። በዚህ አራት አመት መከላከያ ሠራዊቱን ለመገንባት የተደረገው ጥረት በእውነቱ በቀላሉ የሚታይ አይደለም ። አሁንም ሠራዊቱን በተሞላ ትጥቅ ና ሥንቅ በተደራጀና በመይቆረጥ መልኩ ማጠናከር ተገቢ ነው ። ህይወትን ያህል ለሚሠጥ ሠራዊት የተለየ እንክብካቤ ማድረግ ተገቢ ነው።  ብዬም አምናለሁ ።  ኢትዮጵያ  አገር ወዳድ ጦር ሠራዊት ባይኖራት ኖሮ ሲቪሉ ውሥጥ የተዘራው የከፋፍለህ ግዛ የቋንቋ ጦርነት ዜጎችን ሰው መሆናቸውን አሥክዶ እርስ በእርስ የሚያጫርስ  ይሆን እንደነበር በማሰብም የመከላከያችንን የአገር አሌንታነት መገንዘብና የሚገባውን ክብር መሥጠት የሲቪል ዜጎች ግዴታ ነው ።

እንደ ኢትዮጵያ ዓይነት አሥቀያሚ የሆነ ሰውን በቋንቋ የሚያገል  ሥርዓት በዓለም ላይ ከቶ በሌለበት አገር ፣ ይኽን የመሠለ አገር ወዳድ ሠራዊት ባይኖረን ምን ይውጠን ነበር ?  ጦሩ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች ሥብሥብ ቢሆንም በአገር መከላከያ ሠራዊትነቱ  በአንድ ገመድ የተገመደ አንደ አንድ ሰው ለኢትዮጵያ የሚያሥብ ባይሆን ኖሮ ፣ እቺ አገር ምን ይውጣት ነበር ? … የተለያየ ቋንቋ የሚናገሩ ዜጎች  በሚኖሩባት አገር ውሥጥ ፣ ያውም ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው ከተሞች ፣ ዜጎች ለአንድ ቋንቋ በባርነት የተሰጡበት  አገር ብትኖር ኢትዮጵያ ሆና እንኳ በመከላከየ በለው የሰው  እኩልነት ፣ ፍቅር እና አንድነት ኢትዮጵያ በኢትዮጵያነቷ ፀንታ እየኖረች ነው ። እንደሲቪሉ ፖለቲካማ ኢትዮጵያ ገና ድሮ ጠፍታለች ። የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒሥትር  አብይ አህመድ ከየአቅጣጫው እንደ ሐምሌ ዝናብ የሚወርድባቸውን የነገር ዶፍ ተቋቁመው ፣ በተግባር ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚያያረጋግጥ ፖለቲካዊ ተግባር ከመከላከያ ጋር ሆነው እሥካላደረጉ ድረሥ ከሆድ ያልዘለለ ሃሳብ የሚያመነዠግ ያልተለወጠ  የቀድሞውን የኢህአዴግ ካድሬ ይዘው  አገሪቱን ምናልባትም እኛ ወደ አልታየን ታላቅ አገር የሚያሻግሩበት አንዳችም መንገድ የለም ።

ለምሣሌ ፣ አማርኛ ቋንቋ ከነ ፊደሉ ጥንታዊ መሆኑንን እያወቁ ፣ የአገሪቱ ብሔራዊ ቋንቋ እንዲሆን በማድረግ በመላ ኢትዮጵያ ከተሞች የሚኖሩ ዜጎች የመምረጥና የመመረጥ መብታቸው እንዲከበር ከማድረግ ይልቅ ፣  ጭራሽ አገርን ሰማንያ ቦታ የሚከፋፍለውን የቋንቋ ክልልን ለማሥፋፋት ያስገደዳቸው የሚከተሉት የኢህአዴግ ህገመንግሥት መሆኑ ቢታወቅም ይኽንን ሥርዓት ለመለወጥ አንዳችም አብዮታዊ  እንቅሥቃሤ ለማድረግ ፍቃደኛ አልነበሩም ። ( ፕሮፊሰር መሥፍን እና አንአንድ ምሁራን ግን በየፅሑፉ ጎትጉተው ነበር።)  ፍቃደኛ ባለመሆናቸውም ፣  ነገ በታላቅ ጥረት  የገነቡት ሁሉ  በቀላሉ እንዲፈርስ በየዋህነት የቋንቋን ፣ የዘውግን ፣ የመንደርተኝነትን ሥርዓተ መንግሥት አጥብቀው ይዘዋል ። …

“ በኢትዮጵያ ውሥጥ ያለው ሰው ሁሉ እኩል ነው ። በዜግነቱ ። አማራ ትልቅ ና ወላይታ ትንሽ ነው ። ብሎ ሥልጣኔ የለም ። ድንቁርና እንጂ ። ኦሮሞ ከማንም አይበልጥም ከማንም አያንሥም ። እኩል ነው ። ሰውን ከሰው የሚያበላልጠው ሥርዓት የፊውዳሉና የባሪያ አሣዳሪው ሥርዓት እንደነበር እናውቃለን ። እኛ 200 ና 400 ዓመት ወደኋላ እየኖርን ይመሥለኛል   ። … “ በማለት የማይከፋፍልና ሰዎችን የሚያዋህድና የሚያፋቅር ሥርዓት እንደመገንባት ቷ ጋብቻ ከልክል ዘራወዊ የቆዳ ማዋደድ ሥርዓትን አልፋታም ፤ የሙጥኝ ብለዋል ።  ከሃምሳ ቋንቋ  በላይ ባለበት ክልል ለሲዳምኛ ቋንቋ ተናገሪዎች ብቻ የሚበሉበትን የወርቅ ሠሐን በማቅረብ ፣ ሌላውን ዜጋ የበይ ተመልካች ማድረግ እንዴት እንደሚያዛልቅ በበኩሌ አይገባኝም ። ከ 200  ዓመት በፊትም የሞተ ሥርዓት  ይመሥለኛል ።

በበኩሌ ” ጠ/ሚሩ ከሰኔ 24/ 2010 ንግግራቸው ባያፈገፍጉ ኖሮ ከዚህ የሞተ ጥንታዊ ሥርዓተ  መንግሥት መውጣት ይችሉ ነበር ። ብዬ አምናለሁ ።ብረትነ በግለቱ እንዲሉ በወቅቱ   ታላቅ ለውጥ ለማምጣት ሁኔታው የተመቸ ነበር ።   ” የሚባለውን ትችት  አላምንበትም ። ይልቁንስ በወቅቱ እርሳቸው አብጠርጥረው የሚያውቁት  የተጠናከረ የመከላከያ እና የፖሊስ ሠራዊት አልነበራቸውም ።  ” ዛሬ  አንድ ለእናቱ የሆነ  ኢትዮጵያዊ ኃይል ከጎናቸው በመሆኑ   እርሱን ይዘው በሆዳም ካድሬ የተሞላውን   የጅብ ክልላዊ ሥርዓትን ማፍረስ ይችላሉ ። ” ብዬ አምናለሁ ። በበኩሌ የሃቀኛውን ጋዜጠኛ የታምራት ነገራ  ሃሳብ እጋራለሁ ። የጅብ አሥተዳደር የሌለበት ፣ ትክክለኛ የሆነ በክፍለ አገራት የተደራጀ ፣ የከተማና የገጠሩ ነዋሪ በቋንቋ ሳይወሰን በምርጫ ላይ ተሳትፎ የሚያደርግበት ከቀበሌ ካድሬ የፀዳ በግልፅኝነት ና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ የመዘጋጃቤት አገልግሎት ያለው ፣ የፍትህ ተቋማቱ ከቋንቋ ተፅእኖ የወጡ ፣ ከኔት ወርክ ቋንቋዊ እና ንዋያዊ አሠራር ነፃ የሆኑ ተቋማት መገንባት ይችላሉ ።

የሚቋቋሙት የፀጥታ   ተቋማትም በህግ የበላይነት የሚያምኑ እና  ዜጎችን ለማሥፈራራት እንዳሻቸው የማያሥሩ ህገወጦች ወይም በመንግሥት ላይ ሌላ መንግሥት ያልሆኑ አካላት እንዲሆኑ ያደርጋሉ ።  እናም ቋንቋ ላይ መሠረት ያደረገ ኢ ዴሞክራሲና እና የሰብአዊነት ፀር የሆነው ሥርዓተ መንግሥቱ በቀላሉ ለመቀየር አሁን የሚቻልባቸው አማራጮች የሰፉ ናቸው ።  ። “ የንፁሐን ዜጎች የሞት ምንጪ ብልፅግና የሚያራምደው ኢህአደግአዊ የፖለቲካ መንገድ ነው ። ብልፅግና እያራመደ ያለው መለሥ ከመሞቱ በፊት ሊቀይረው ያሠበውን የቋንቋ ፖለቲካ ሥርዓትን ነው ። “ የሚባለውን እውነት አምኖ ወደ መፍትሄው መምጣት ይቻላል ። መከላከያውን ይዞ ።

እውነተኛ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ከተፈለገ ይኽ የቋንቋ  ሥርዓት በሥብሦልና   ከቀበሌ ጀምሮ በሰለጠነ መንግሥታዊ መዋቅር መቀየር አለበት ። በገሃድ የሚታየው የአጨብጫቢነት እና የእበላ ባይነት ካድሬው ሥርዓትም ላይመለሥ መቀበር አለበት ። መቀበር ሥል ሰዎቹ ሣይሆኑ ተጠራርቶ በቡድን የመዝረፍ ና የመበልፀግ አሥተሣሠቡ ። የጨካኝነት ፣ የገዳይነት ፣ የዘራፊነት ፣ የውሸት ፣ የቀጣፊ ና ቀሳፊነት መንፈሱ መቀበር ይኖርበታል ። ማለቴ እንደሆነ ይሰመርበት ።

ይኽ የዘራፊነት የነጥቆ በልነት ፣ እንዲሁም በኃይማኖት ና በዘውግ  ሥም ፣ ግብፅ በእጅ አዙር  በምትበትነው ፔትሮ ዶላር እገዛ ፣ አገርን የማፍረስ ስውር ሤራ ነው ። ይኽ ሥውር ሴራም እሥካልተበጣጠሰ  እና ተንኮታክቶ ወደ ግብአተ መሬቱ እሥካልገባ ጊዜ ድረስ ፣ ይኽቺ አገር  አደጋ ውሥጥ ናት ። አገራችንን ለማዳን ግን ቀድመን ልንሰዋላት ዝግጁ መሆን አለብን  ሁላችንም  እንሞታለን ።  የሁላችንም ሞት እርግጥ ነው ። ይኽንን አውቀን ለነገ አገር ተረካቢው ትውልድ የምናስብ ከሆነ ፣ በቁርጠኝነት ጅቦችን ከህዝብ አሥተዳዳሪነት ወንበር ላይ ለማንሣት የሚያሥችል ሥር ነቀል ለውጥ ማድረግ አያዳግተንም ።

ዛሬም አገሪቱን እየመዘበሩ በቢሊዮን ዶላር የሚያሸሹ ጅቦችን በጉያችን ይዘን ” አገርን እያበለፀግን ነው ” እያልን ብንደሰኩር ዋጋ የለውም ። ለመፍትሔው ከዘገየን ነገ የሠራነውን ሁሉ በማፈራረስ በየፖርኩ አጠር ላይ ልብሳቸውን አጥበው የሚያሰጡ ለሆድ ያደሩ ቅጥረኛ ባለጠብመንጃዎችን የምናይበት መንገድ ብዙ ነው  ። ዛሬም ወደ እዛ የሚወስደው መንገዱ ክፍት ነው ። ወያኔ ከጠርሙሱ እንዲወጣ ያደረገው ጂኒ ወደ ጠርሙሱ አልገባም ። የሚያሥገባው አልተገኘማ ! የኢትዮጵያ ህዝብ ጠ ሚ አብይ አህመድ ይኽንን ጂኒ ወደ ጠርሙሱ ውስጥ ከተው ፣ በቀላሉ በማይከፈት ክዳን ከድነው ለዘላለሙ ያሽጉታል ብሎ ህዝብ ተሥፋ አድርጎ ነበር ።  ይኸው አራት ዓመታቸው ለበለአገሩ  ጠብ ያለ ነገር የለም ። ጭራሽ በንግግራቸው ባሌ ጎባ ና ቆቦ እየረገጡ አደናግረውነል ። ( አራንባ ና ቆቦ ከምንል ባሌጎባ ና ቆቦ ብንል እውነታውን  ይገልፃል ፣ ብዬ ነው ። )

ጠቅላዩ በአንድ ወገን የታሪክ አሥተማሪ ፣ በሌላ በኩል የፍልሥፍና ምሁር ሆነው ለመታየት ሲጥሩም ብዙን ጊዜ  ይሥተዋላሉ ።  የሰኔ 30/2014 ዓ ም የፖርላማ  ንግግራቸውን ብቻ አዳምጠን እዚህ ድምዳሜ ላይ መድረሥ አይሳነንም ። … ለኢትዮጵያ ታሪክ ና ባህል እንዴት እንደሚቆረቆሩና በአገሪቷ ና በህዝቧ ላይ ታሪካዊ ጠላቶቿና የማይጠረቁ የኢምፔሪያሊዝም ኃይሎች በኃይማኖት ና በጎሣ የሚያቀነባብሩት ሤራ  ምክርቤቱና ፓርላማው  ልብ እንዲለው በአፅኖት መናገራቸውን ሥናሥተውል ፣ ሰውየው የያዘ ይዞቸው ነው እንጂ በአንድ ቀን ታሪክ ሊሰሩ እንደሚችሉ እናስብና ። ወዲያው ደግሞ ወደ ጎሣ እና ዘውግ ጉያ ገብተው የሚከተሉት ሥርዓት የከሰተውን  ምሥቅልቅል በመካድ ” ወደ ዳገት እየወጣን ነው ። ዳገቱ ላይ ጉልበታችሁ አይዛል ። ” ይሉናል ። እኛም “ የዘውግ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዳገት የፍቅር ተራራ አናት ላይ እንዴት ሊያወጣን ይችላል ? “ብለን እንጠይቃለን ።

በዚች አገር ላይ ብቻ ያለ እጅግ የሚያሥጠላ ፣ ሰውነትን የካደ ፣ በቋንቋ ብቻ አንዱ ቋንቋ ተናገሪ ቋንቋ የማይናገረውን የበይ ተመልካች የሚያደርግበት ፤  ከባርያ አሳዳሪ የከፋ አገዛዝ ለማንቆላጰላጠሥም ይዳዳሉ ። እንዲህ ዓይነቱ ንግግራቸውን በማሥተዋል ና አፍንጫቸው ሥር በአዲስአበባ በቋንቋ ኔት ወርክ ምድረ ካድሬ ሲሾሾም እና  ረብጣ ብር እየተቀበለ በቋንቋ ሥም የሠራተኛ ቅጥር ሲፈፅም ሥናሥተውል  በእውነቱ እጅግ እናዝናለን ። ጠቅላዩ እግዜር እንዳይደሉ ግን እናውቃለን ። ሆኖም ያነበቡ የተመራመሩ አማካሪዎች አሏቸው ። ይባላል ። በበኩሌ ያላቸውን ክፍተት እንዲሞላ  ምነው በጣም ብዙ ያነበበው እና ሰለ ሰው ከነቱነት የጠለቀ ዕውቀት ያለው አለማየሁ ገላጋይ አማካሪያቸው በሆነ ብዬ አሥባለሁ።  ቢያንስ ዓለማየሁ ገላጋይ በሰውና በፈጣሪ መካከል ያለው ትስስር በህሊና እንደሆነ እና ሰው ለራሱ እና ለህሊናው ታማኝ ከሆነ ሌላው ሊያስጨንቀው እንደማይገባ በጥልቀት ሥለሚረዳ እና መሞቱን በሚገባ የተረዳ ፤  ዓለምንም  ከ ሀ እሥከ ፐ በጥልቅ የተገነዘበ ፣ ዓለማወቁንም  የሚያውቅ በመሆኑ ፤ ዓለምን እሣቸው ባላዩት መንገድ ያሳያቸውና የመሪነት ሚዛናቸውን እንዳይሥቱ ያግዛቸው ነበር ብዬ  አሰብኩ ። ” ማሰባችን ለእግረ ሙቅ ዳረገን ። ” አለ ተመሥገን ደሣለኝ ። ”

አሌክሶቪች አማካሪያቸው ቢሆን ኖሮ ፣ ሥለ እውነት ሲባል ፣ እንደ ሶቅራጦስ መርዝ ጨልጦ መሞት በሰው ዘንድ ታላቅ ዘላለማዊ ከበሬታ እንደሚያሥገኝ  በመግለፅ ፣ ከዘውግ ፖለቲካ  የሚወጡበትን መንገድ ፣ ከእውነትና ከፍትህ አንፃር በመጠቆም ፤ ተወዳጅነታቸው እንደ ፀና እንዲቀጥል ያግዛቸው ነበር ። …ይኸው ዛሬ ብርቱ  አማካሪ በመጥፋቱ   ፣ የዘውግ ፖለቲካን ሃይ የሚለው ጠፍቶ ኢየሱስ ክርስቶስም ”  በኩሽ እና በሴም ዝርያ ተፈርጆ  ወደዘውግ የማንነት ሽኩቻ ውሥጥ ወርዶ ሥናይ እምነት በአሥተዋይ መካሪ እጦት ኮስሶ ሥናይ እጅግ  አዝነናል ። ሰው ሃቅን ከወሬ አንፃር እንደዋዛ በማውራት ከሃቅ ጋር መላተም የለበትም ።

ጠቅላዩም ” ኢትዮጵያ በታሪክ እና በሥልጣኔ ቀደምት የሆነች ፣ ብቻ ሳትሆን የሰው ዘር መገኛ ጭምር ናት …አብዛኛዎቻችን ታሪክን አናውቅም እንጂ ታሪክን በቅጡ ብንረዳ በኢትዮጵያ እንኮራለን ። ”  ብለው ፣  ሲናገሩ  ሃቁን   መጋፈጥ  ከተሳናቸው ነገራቸው ቀልድ ነው የሚሆነው  ። …

ሞት ላይቀር ዞሮ ፣ ዞሮ ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ተወዶና ተፈቅሮ መሞት በራሱ ታላቅ ፀጋ ነው ።  ጠቅላይ ሚ /መለሥ ፣  ከመሞታቸው በፊት አባይን ለመገደብ መነሳታቸው እና  ቀስ፣ በቀስ ሥርዓቱን ለመቀየር ውጥን በመያዛቸው ( የኢህአዴግም ሆነ የህውሃት ሥያሜ እንዲሁም የሌሎቹ በሂደት አይቀሬ እንደነበር ፣ የቀድሞ የኢህአዴግ ሥራ አሥፈፃሚ ና ማአከላዊ ኮሚቴ ውይይቶች ያሣብቃሉ ። ) ነው ፤  ድንገት ሲሞቱ አገር እንዲያለቅስላቸው መግፍኤ የሆነው ። መቼም ”  ሰው ከልሞተ እና ከአጠገባችን እስከወዲያኛው ገለል ካላለ አይመሰገንም ” እንዲሉ ፣ ዛሬ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒሥቴር እሥከአመጡት ጣጣና በአሥረአንደኛው ሰዓት  ጣጣውን  ለመግፈፍ የሄዱበትን እርቀት በእዝን ልቦናችን እናስተውላለን ። ከዚህ እውነት አንፃርም ፤ የዛሬውን የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር አካሄድ ፤ ወዴት ወዴት ነው ? እንዴት እንዴት  ነው ?  የእርሷ አካሄድ ? አልገባንም ! ብለን  እንጠይቃለን ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop