አቢይ አህመድ በዛሬው የፓርላማ ውሎው የፖለቲካ አላዋቂነቱና ድንቁርናው ለይቶለት ፍጥጥ ብሎ በመውጣቱ ብዙዎች “የአእምሮ በሽተኛ” እያሉት ነው

ሀ. “አሜሪካ ውስጥ በስድስት ወራት ብቻ 20 ሺህ ሰዎች ሞተዋል ስለዚህ በኢትዮጵያ የሞተው ሰው ቁጥሩ ከዚህ ግባ አይባልም…” በማለት አድበስብሶ ለማለፍ የሞከረበት መንገድ ሰውየው ፒ.ኤች.ዲውን ያገኘው በጓሮ በር ነው የሚባለው እውነትነት አለው! በእርግጥ ያልተማረ ሰውም ይህን ከድንቁርና በታች የሆነ ሀሳብ ይናገረዋል ተብሎ ፈፅሞ የሚጠበቅ አይደለም፡፡ አሜሪካ ውስጥ ሰዎች የሚገደሉበትንና ኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ ነገድ ብቻ ተለይቶ የሚጨፈጨፍበትን አውድ እንተወውና ደንቆሮው አቢይ አህመድ በተነተነበት መንገድ ሞትን በቁጥር እናነፃፅር ብንል አሳዳጊዎቹ ወያኔዎችና እሱ ራሱ በቀሰቀሱት ጦርነት ብቻ ሚሊዮኖች ረግፈዋል፤ በወለጋ ምድር በየቀኑ የሚጨፈጨፈው ሰው እውነቱ ስለማይነገር እንጂ ቁጥሩ የትየለሌ ነው፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ የሰዎች መታረጃ ቄራ ሆናለች፤ አገዳደሉን ራሱ ብናይ አሜሪካ ግፋ ቢል በጦር መሳሪያ እሩምታ ተኩስ ነው ሰዎች የሚገደሉት እዚህ ግን በተለይም ወለጋና ቤኒሻንጉል ሰዎች በዘግናኝ መልኩ በስለት ይታረዳሉ፤ በቀስት ይወጋሉ፤ ህጻናት በማጅራታቸው በሳንጃ ታርደው ስጋቸው እንደ ዶሮ ተበልቶ ለቀባሪ አስቸግሮ ይገኛል፤ እርጉዝ ሴቶች ሆዳቸው በሳንጃ እየተቀደደ ሽላቸውን በእጆቻቸው እንዲታቀፉ እየተደረገ ነው፤ የአራት ቀን፣ የአምስት ቀን አራሶች ጨቅላ ህፃናት ከእናቶቻቸው ጋር በግፍ እየተጨፈጨፉ ነው፤ የሰው ስጋ ተበልቷ፤ ሰው ከእነ ነብሱ ተቃጥሏል… ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው እንግዲህ ዘር ጎሳና ነገድ እየተመረጠ ነው፡፡

ለ. “መንግስት በቅድሚያ የህዝቡን ሰላም ይጠብቅ” ተብሎ ሲጠየቅ ደግሞ “ህዝቡም የመረጠውን መንግስት እየሰማ አይደለም… ለሰላም አልቆመም…” በማለት ጥፋቱን ወደ ህዝብ ለማላከክ ሞክሯል፤ በእርግጥም ይህ አባባል በዓለም የሌለ ንግግር በመሆኑ አብዛኞቹ የአእምሮ ህመም አለበት ቢሉ የሚፈረድ አይደለም፤ “ህዝብ እየተጎዳ ስለሆነ መንግስት ለህዝቡ ይድረስለት” ተብሎ የተጠየቀ የአገር መሪ “ህዝቡ ራሱ ነው ጥፋተኛ” ብሎ ለማምለጥ ሲሞክር ስታይ ሰውየው አእምሮው ገና አልበሰለም በእንጭጭ ደረጃ ነው የሚገኝ፣ ግልብና ጥሬ ነው ብለህ የምታልፈው ብቻ አይደለም፤ ሆነ ብሎ አገር ለማፍረስ እየሰራ ነው ብለህም እንድታረጋግጥ ያስችልሃል፡፡ ብቻ ለዚህ ምገልፅባቸው ቃላት ስለሚያጥሩኝ ይህን ብቻ ብየ ልለፈው…

ተጨማሪ ያንብቡ:  አሥሩ ዋንጫዎች:- አሥሮቹ ጀግኖችና አሥሩ ዓመታት በኦልድትራፎርድ – ክፍል 2

ሐ. የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የጠየቁትን ሲመልስ “እዚህ በመንደር ተደራጅታችሁ መጥታችሁ እኛን ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ድርጅት ይዘን የተቀመጥነውን፣ ለኢትዮጵያ አንድነት የምንለፋውን… አትውቀሱን…” ብሎ በድፍረት ተናገረ፡፡ ጠያቂው ሰው አባቱ ይሆናሉ፤ ምንም አይነት ክብር ሳይሰጣቸው ሊያበሻቅጣቸው ሞከረ፤ ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ለአማራ ህዝብ ያደረበትን ንቀት ያሳያል፤ ምክንያቱም ሰውየው የአማራ ተወካይ ናቸውና፤ በሌላ በኩል ደግሞ እሱስ ገና ከአስራ አራት ዓመቱ ጀምሮ በመንደር የተደራጀው ህወሓትን ተቀላቅሎ እድሜውን የጨረሰው በኦህዴድ የጎሳ ፖለቲካ አይደለምን? አሁንስ ቢሆን የኦሮሞ ብልፅግና፣ የአማራ ብልፅግና፣ የደቡብ ብልፅግና፣ የሶማሌ ብልፅግና፣ የአፋር ብልፅግና፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብልጽግና… ወዘተ በሚል የመንደር ፓርቲ እንጅ መቼ በተግባር አገራዊ ፓርቲ መስርተው ነው ጉራውን የሚነፋብን? መጀመሪያ ያወጡትን ማለትም ገና ይፋ ሳያወጡ በውስጥ የሰየሙትን “የኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ” የሚል ስም ጥለው “ብልፅግና ፓርቲ” የሚል ስያሜ ይዘው ብቅ ያሉት እኮ የኦሮሞ ብልፅግና፣ የአማራ ብልፅግና፣ የደቡብ ብልጽግና… እያሉ በየመንደሩ ሸንሽኖ ለመጥራት እንዲመቻቸው ነው፤ በኢህአዴግና በብልፅግና መካከል የስም እንጂ የተግባር ለውጥ የለም፡፡ ብዙ በጣም ብዙ ማለት ይቻል ነበር ከዛሬው ንግግሩ ሃሳብ እየመዘዙ ግን ከንቱ ድካም ነው ሚሆነው፤ እንደዚህ አይነት ሃፍረትየለሽ ወራዳና ውሸታም ሰው በዓለም ላይ ታይቶ አይታወቅም…

 

2 Comments

  1. የጽሁፉ ባለቤት ቴዎድሮስ ጸጋዬ ነው ማለት ነው? የአሰዳደብ ስልቱ ቴዎድሮስ ጸጋዬ በባለቤትነት ያስመዘገበውን የስድብን ስልት የተከተለ ነው።

  2. አትልፉ ዓለሙ ሁሉ ጠምብቷል። አሁን እንሆ የድሮውን የጃፓን ጠ/ሚ በጥይት መገደሉ ተሰምቷል። ለዚህ ነው ሁሉ ነገር ወደ እብደት እየተለወጠ ነው የምለው። የኢት/ጠ/ሚር የፓርላማ ውሎ የሚያስገርም ነበር። ከካሊፎርኒያ እስከ ቺካጎ የሙታንን ቁጥር ሲነግረን አዲስ አበባ ውስጥ ስለሆነውና ስለሚሆነው የነገረን አንድም ነገር የለም። በከተማዋ ወንጀል ሊፈጸም ነበር ብሉናል። ችግሩ ጠ/ሚሩ ራሱን ማዳመጥ የሚወድ ይመስለኛል። ለኦነግ ሸኔ ታደላለህ ሲባል ሃሜት ነው ምናምን እያለ ደነፋ እንጂ እኔና መንግስቴ ከዚህ አጥፊ ቡድን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለንም፤ ያላቸው ካሉም በመረጃ የሚገባቸውን ቅጣት ያገኛሉ አላለም። ጠ/ሚሩ መሰረቱ ተናግቷል። “በአዲስ አበባ ከፍተኛ የኦሮሞ ጥላቻ አለ” እያለ እየለፈፈ ስለ መደመር ማውራቱ ምንም ፍሬ ቢስ ነው። ለመላ ህብረተሰብ የሚሰራ የሃገር መሪ አንድን ብሄር ተገን አርጎ እንዲህ ያለ ነገር መናገሩ ችግሩን እንደሚያባብስ እንዴት አይረዳም?
    በወለጋ ስለሚሆነው የዘር ጭፍጨፋ ሲያወራ የሞተው ኦሮሞም ነው፤ የማረክናቸው ከትግራይና ከደቡብም የሆኑ የኦነግ ተሰላፊዎች አሉ እያለ ማውራቱ ለኦነግ ሸኔ ጠበቃ የቆመ አስመስሎታል። ወለጋ ውስጥ ኦሮሞ አይሞትም ብሎ የሞገተ ማንም የለም። ግን በዘራቸውና በቋንቋቸው ተመንዝረው ቤት እየተዘጋባቸው የሚጋዪት አማሮች ናቸው። ልጆቹን ውትድርና የላከውን፤ አባቱ ለጸጥታ ሃይሎች ልጅ የቀበረውን የጦር መሳሪያ በማመላከቱ የተገደሉት የሚያሳየው የኦሮሞ ነጻ አውጭ ማለት የኦሮሞ ባርነት አምጭ መሆኑን ነው። አማራውን ገድለውና ዘርፈው ሁሉም ነገር እንደፈለጉት ሲሆን ኦሮሞው ኦሮሞውን አይበላውም ያለው ማን ነው? ከጠ/ሚሩ አፍንጫ ስር ተቀምጠው አይደል እንዴ ስለ ኦነግ ሸኔ የሚሞግቱት? በዚህ አሸባሪ ሃይል በየጊዜው የሚጨፈጨፉት ሰዎች ደም ወለጋን የደም መሬት አርጓታል።
    ጠ/ሚሩ ሁሉን አውቃለሁ ማለቱን ትቶ የሃገር ሰላምን የሚያደፈርሱትን አይቀጡ ቅጣት እስካልሰጠ ድረስ ያው ደጋግሜ እንዳልኩት ይህ ችግር ተራብቶ የራሱንም ህይወት እንደሚበላው የታወቀ ነው። ቆራጥነት በመረጃ ተደግፎ ሆን ብለው ህዝባችን የሚያተራምሱትን ማሰር፤ መግደል እስካልተቻለ ድረስ የሃገሪቱ የወደፊት ተስፋ ጠ/ሚሩ ደጋግሞ እንደሚነግረን እንደ ሶሪያ፤ሊቢያና የመን እንደሚሆን አያጠራጥርም። ዪክሬንን አሁን ከራሽያ ጋር ላለችበት መከራ የዘፈቋት አሜሪካና አጋሮቿ ዪክሬን በራሺያ ሃይሎች ሥረ መሰረቷ ሲፈራርስ እሳት ከማቀበል የተለዬ ምንም ነገር አላረጉም። የኔቶ ግርግርም ዝም ብሎ ነው። ኔቶ ሊቢያን ሲያፈርስ፤ ዪጎዝላቪያን ሲሸነሽን ነው ጉልበቱ። ከራሺያ ጋር የመግጠም ህልም የለውም። አሁን ራሺያና ቻይና አብረው ሰሜን ኮሪያንና ኢራንን አስከትለው አይቀሬው የዓለም እንደገና ለሁለት መሰንጠቅ እየመጣ ነው። እኛንም በዚህ በዚያም እሳት እያቀበሉ ስንገዳደል ከሩቅ በማየት ተርበዋል ስንዴ እናቀብል እያሉ የዓለም መሳለቂያ ያረጉናል እንጂ በሰላም ችግሮቻችን ፈተን እንድንኖር አይደግፉንም።
    በመጨረሻም ጠ/ሚሩ ቃሉ አጭር፤ ተግባሩ ረጅም፤ ይህ ዘር ይህ ቋንቋ ተጠላ እያለ ባይለፈልፍ መልካም ነው። በመደመር ሂሳብ ወደ ስልጣን ከወጣ ወዲህ ሃገሪቱ ከመሰረቷ እንድትናጋ ያደረጋ የዚህ የኦሮሞ የእኛ ወረፋ ነው ማለት ነው። ይህ ለኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለቀሪው ወገናችን ጠቃሚነት የለውም። እናንተ ጊዜአዊ መንግስት ይቋቋም የምትሉ ሙታኖች ደግሞ እረፉ። በኢትዪጵያ የጊዜአዊ መንግስት እድሜ የትንኝ ነው። ፍሬ የለውም። ተውት፤ እርሱት፤ በፊት የታየ ያልሰራ ጉዳይ ነው። በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share