June 25, 2022
6 mins read

በሀገራችን ኢትዮጵያ በኦሮምያ ክልል በጊምቢና በአካባቢው በንጹሐን ዜጐች ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተሰጠ መግለጫ !

288857234 536707461468408 2978740509679881975 nሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. በሀገራችን ኢትዮጵያ በኦሮምያ ክልል በጊምቢና በአካባቢዋ ይኖሩ የነበሩ ንጹሐን ዜጎች ወገኖቻችን አገራችንና ምድራችን ብለው በሰላም ይኖሩ በነበሩበት ቤታቸው በድንገት በደረሰባቸው አሰቃቂ ግድያና የነፍስ መጥፋት በመፈጸሙ ቤተ ክርስቲያናችን በእጅጉ ሐዘን ተሰምቷታል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አገረ እግዚአብሔር እየተባለች ሕዝቧም ሕዝበ እግዚአብሔር እየተባለ ቢጠራም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን እየታየ ያለው የርስ በርስ ግጭት በተለይም ሀገር ሰላም ብለው ከምንም ጉዳይ ጋር ንክኪ የሌላቸው ንጹሐን ዜጐች ላይ እየተፈጸመ ያለው ስደት፣ ግድያና ሞት ኢትዮጵያዊ መልካችንን የቀየረ እግዚአብሔርንም የሚያሳዝን ዕኩይ ተግባር በመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን ታወግዛለች፡በተለይም በዕለቱ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያና ሞት በሕጻናት፣ በሴቶችና በሽማግሌዎች ላይ የተፈጸመ መሆኑን ሐዘኑን ከፍተኛ ያደርገዋል፡፡
ቀን ያልፍልናል ሕጻናት ልጆቻችንን አሳድገንና አስተምረን ለአገርና ለወገን መከታ ይሆናሉ በሚል ራእይ ማልደው እየተነሱ አምሽተው እየገቡ ነሯቸውን በረሀብ፣ በጥም፣
በራቁትነትና በሕመም እያሳለፉ የነበሩ ወገኖቻችን ይህም በዛባችሁ ተብለው በአሰቃቂ ግፍና ጭካኔ በተሞላበት ግድያ ሕይወታቸው እንዲያልፍ መደረጉ መላውን ዓለም አሳዝኗል።
በመሆኑም እንዲህ ዓይነት አስከፊ ድርጊት ልማትን፣ እድገትና ብልጽግናን ለምትመኝ በዚህም ጎዳና ዳዴ እያለች ላለች ሀገር ቀርቶ ለሰለጠኑትና ላደጉትም አገራት የማይበጅ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን ድንበር ተሻግሮ የመጣ ወራሪ ጠላት በሌለበት የግል ፍላጎትን ለማሟላት ሲባል በተደረገ የእርስ በርስ ግጭት መሆኑ እንደ አገር ሁላችንንም ሊያሳፍረን ሊደገምም የማይገባ ድርጊት ነው፡፡
ሰላም በዓለም ላይ ለሚኖሩ የሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንስሳቱና ለአራዊቱ ለምድሩም ሆነ ለሰማዩ አስፈላጊ በመሆኑ ከእንዲህ ዓይነት የጥፋት ተልዕኮ መጠበቅ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡
በመሆኑም ሰው ሁሉ በዚህ ዓለም ሲኖር ሠራተኛው ሠርቶ ለመበልፀግ ነጋዴው ነግዶ ለማትረፍ በሽተኛው ድኖ በጤና ለመኖር ተማሪው ተምሮ ለማወቅ በአጠቃላይ ዜጐች ማልደው ለመውጣትም ሆነ አምሽተው ለመግባት በምድራችን ሰላም ሲገኝ እርስ በርስ መተማመን ሲኖር በመሆኑ መላው ኢትዮጵያውያን ዜጐቻችን ለሰላምና ለአንድነት ተባብሮና ተከባብሮ ለመኖር እጅ ለእጅ ተያይዘን የምንነሳበት ጊዜ አሁን መሆኑን ቤተ ክርስቲያናችን ታስገነዝባለች፡፡
ሀገራዊ ሰላም የሚገኘው በሰዎችና በሰዎች መካከል ኀብረት ሲኖር በመሆኑ መንግሥት በዜጐች መካከል ለጥላቻ ለአለመግባባትና ለመለያየት ምክንያት የሚሆነ በሰላምና በትዕግሥት በመቻቻልም ጭምር ለመኖር የማያስችሉ ድርጊቶችን ጊዜ ሳይሰጥ ከኅብረተሰቡ መካከል ነቅሶ ማስወገድ ይኖርበታል፡፡ ከዚሁ ጋር የዜጎች ሰላምና አንድነት የሚጠበቅበትን ሥራ ባለማቋረጥ ማከናወን የሚገባው መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡ በቀጣይም በየትኛውም የአገራችን ክፍሎች እንዲህ ዓይነት የጥፋት ድርጊት እንዳይደገም አስፈላጊው የዜጐች ጥበቃ እንዲደረግ አጥብቀን እናስገነዝባለን፡፡
እንዲሁም በግፍ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉትና በስደት ላይ አሁንም በሞትና በሕይወት መካከል እየተጨነቁ ለሚገኙ ወገኖቻችን አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው እናሳስባለን፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን ትመኛለች፡፡ በዚህ ዕኩይ ተግባር ሕይወታቸው ላለፉ ወገኖቻችንም እግዚአብሐር ነፍሶቻቸውን እንዲምርልን ትፀልያለች፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለአገራችንና ለሕዝባችን ሰላሙን ይስጥልን፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop