በላይነህ አባተ ([email protected])
አማራ ሆይ! አባቶችህ ከመለኮት ቀጥሎ ሲጨነቁ የኖሩት ለክብርና ለነፃነት እንደነበር ታውቃለህ፡፡ ለክብርና ለነፃነት ከነበራችው ወደር የሌለው ፍቅር የተነሳም እንኳን ለራሳቸው አገር ነፃነት ለመላው አፍሪካም በተለያዬ መንገድ አስተዋጽዖ እንዳደረጉ ታውቃለህ፡፡ ለአረብ፣ ለኤስያና ለላቲን አሜሪካ አገሮችም ነፃነታቸውን እንዲያገኙና በቅኝ ገዥዎች የተገፈፉትን ክብር መልሰው እንዲጎናፀፉ አርአያ እንደነበሩ ታስታውሳለህ፡፡
የእነዚያ ለዓለም የተረፉት የጀግኖች ልጆች አንተ አማራው ዛሬ ዘርህ በላንባ ዲና እየተፈለገ ሲጨፈጨፍ ድምጥህን እንዳታሰማም ቆሻሻ ሌባ ጣት ሲቀሰርብህ ምን ተሰማህ? ጅላንፎና ሆዳም ይህቺ ሌባ ጣት የተቀሰረው የሕዝባቸው በጭራቆች መታረድ ወኔአቸውን ተፈታትኗቸው ጥያቄ ባነሱት የሕዝብ ተወካዮች ብቻ ሊመስለው ይችላል፡፡ አማራን እንደ ቡግንጅ ሰቅዞ ይዞና እንደ እግር ብረት አስሮ የሚያሳርደው ብአዴንም ይህቺ ቀን ያሾላት ቆሻሻ ሌባ ጣት ከተደቀነበት የአማራ ሕዝብ ጎን ሳይሆን የአማራ የዘር ፍጅት እዳይሰማ ተከለከለው አፈ-ጉማሬና ተጌቶቹ ጀርባ ተሰልፏል፡፡
ክብሩንና ሕዝቡን በሆዱ የሸጠው ብአዴን ዓይኑም አይምሮውም ስለታወረ ይህቺ ቆሻሻዋ ሌባ ጣት በእርሱም የተደቀነች መሆኗንና አንድ ቀን ዓይኑን እንደምታፈሰው ሆዱ ጋርዶት አልታየው ብሏል፡፡
አማራ ሆይ! ይህች ሌባ ጣት አማራ በመላ አገሪቱ ወደፊትም የዘር ፍጅት ሲደርስበት ድምጡን ሳያሰማ ዝም ብሎ እንዲገዛ የተቀሰረች ቆሻሻ ሌባ ጣት መሆኗን ተገንዝበሃል? ይህች ቀን ያሾላት ሌባ ጣት ህጻናት ከእናቶቻቸው የእሬሳ ክብር እንደ ድንች እየተፈነቀሉ ሲወጡ አንተ አማራው የሚኪያሄድብህን የዘር ፍጅት ለወገንህና ለዓለም ሕዝብ እንዳታሳውቅ፣ ለሞቱት እንዳትጸልይና ሐዘንህን እንኳ አንዳትገልፅ “ዝምበል” ያለች መረኗን የለቀቀች አውራ ጣት መሆኗን ልብ ብለሃል?
ይህቺ የተቅነዘነዘች ሌባ ጣት አማሮች በዘራቸውና በቋንቋቸው እየተመረጡ ሲታረዱ የከፋቸው አማራዎች ድምፅ ለማሰማት ሲፈልጉ ልሳናቸውን ልትዘጋና ዓይናቸውን ልትዝቅ የተቀሰረች ወቢ የተፋት ቆሻሻ ሌባ ጣት መሆኗን ተገንዝበሃል?
ይህቺ ሌባ ጣት ለሰላሳ ዓመታት በአማራ ላይ በተደረገው የዘር ፍጅት በመላ አገሪቱ እንደ ቅጠል በረገፉት ሕጻናት፣ እርጉዞች፣ ወጣቶች፣ ባልቴቶችና አዛውንቶች አስከሬን ያልተጣፈረ ጥፍሯን የሰካች አረመኔ ጣት መሆኗን አስተውልሃል?
አማራ ሆይ! ይህቺ ሌባ ጣት አሁን በመላው ዓለም በሚኖረው አማራ ብቻ ሳይሆን በመጪው ትውልድም የተቀሰረች ጥጋብ ታለአቅሟ አፈር ቅሞ እንደ አበጠ ቅንቡርስ የነፋት ጣት መሆኗን አጢነሃል?
አማራ ሆይ! ጽንሶችህ ተማህጸንህ፣ ልጆችህ ተጉያህ፣ ወላጆችህ ተቤተክርስትያንና ተመስጊድህ በየቀኑ በጅምላ በጭራቅ ሲታረዱ በአንድ መስመር ተሰልፈህ እንደ አያቶችህ ለመመከት ምነው ዘገየህ?
አማራ ሆይ! አባቶችህ እንኳን ሌባ ጣት ተቀስሮባቸው ክብርን በሚነካ መንገድ ቀና ብለው ሲያዩአቸው እንኳ ምን ያደረጉ እንደነበር ታውቃለህ፡፡ ምነው አንተ ያለ አባቶችህ ታሪክና ባህል ጥቃትን ተለማምደህ ለተጨፈጨፈ ወገንህ እንዳትጸልይም የቆሻሻ ሌባ ጣት መቀሰሪያ እስከ መሆን ደረስክ?
አማራ ሆይ! ወገንህ በሺህና በሚሊዮን ሲጨረገድ ሌላው ቀርቶ እንዳታዝንና እንዳትጸልይ ባለጌ ቆሻሻ ሌባ ጣቱን እየቀሰረ “ዝም በል!” እያለህ እስከ መቼ ትኖራለህ?
ሰኔ ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ. ም.