ሕዝብ ሲቆጣ ማስቀየሻው ፎቶ መቀየር ነው። ምናልባት እንደ ተራ ፌስቡከር ላይክ ለቀማ? (በጭብጨባ ስለመጣ መጽናኛው ይሆናል) ወይ ደግሞ ለራሱም “I’m alright” የሚልበት መንገድ። ወይስ “ምን ታመጣላችሁ? ተዘቅዘቁ” የሚልበት መንገድ?
ብቻ ከዚህ ቀደም ለመጨረሻ ጊዜ ፎቶዎቹን የቀየረው January 11 እነ ስብሀት ነጋ ይፈቱ በተባለ ማግስት “እነ ስብሀት ነጋ ይፈቱ ሲባል፣ እኔም ደንግጫለሁ” ብሎ ያላገጠ እና ሕዝብ የተቆጣ ጊዜ ነበር።
ይኸው ስንትና ስንት ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፎ ሲታዘን፣ ምን ታመጣላችሁ በሚመስል መልኩ ፎቶዎቹን ቀይሯል።
ይኽ ድርጊቱ እስከዛሬ ካደረጋቸው በላይ፣ ስለታየው እና ስላልታየው ማንነቱ በደንብ የሚያሳይ ነው።
ሕዝብ ፕሮፋይሉን በጥቁር ሲለውጥ፣ የሚመገበው ደም ደም ሲለው፣ ምድር ላይ ቀይ የደም አሻራ ታትሞ ሲለቀስ፣ እሱ አረንጓዴ አሻራ ብሎ መለጠፉን ታሪክ ይቅር አይለውም። የጎረቤት ለቅሶ እንኳን ይከበራል። በየትም አገር አስከሬን በክብር ያልፋል። ለእሱ ምናልባት የሰው ልጅ ዋጋ ከእንጨትም በታች ነው።
በዚህ ልክ እንዴት ልበ ደንዳና መሆን ይቻላል?
ለማንኛውም “እንደ እኔ የተሰደበ የለም” ብሎ እልሁን ቢዘረግፍም፣ እንደሱ የተደገፈ የለም።
ሕዝብ ካናቴራ አሰርቶ የድጋፍ ሰልፍ ካደረገ፣ ዛሬ አራት አመቱ።
ቦንብ ያፈነዱበት ሰኔ አስራ ስድስት ዛሬ አራት አመቱ።
ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ “የቀን ጅቦች” ካለ አራት አመቱ።
ይገርማል ብቻ። ያኔ fbi መጥቶ ያጣራ ሲባል እንኳን ለምን ማለት አይቻልም ነበር።
ዛሬ እንጠይቅ እስኪ። ከሌላው ግድያ ምን ለይቶት ነበር ኤፍቢአይ ያጣራ የተባለው? ውጤቱስ ምን ነበር? ማን አፈነዳው? የውጤቱን ማለቴ እንጂ ውስጥ ውስጡን ተብሎ ያለቀውን ማለቴ አይደለም።
በዚያ ድንጋጤ ውስጥ ዘና ብሎ ሆስፒታል ድረስ ወስዶ ያስጠየቀው “አዛኝነቱ” ዛሬ የት ገባ?
ያኔ የቆሰሉት ግን ደህና ናቸው?
ብቻ ይኽም ቶሎ ይረሳል።
ያም ሆነ ይህ ግን የደነደነ አንገት ሁሉ መሰበሩ አይቀርም!
\