የማኦ ዜዶንግ ትምህርት ለፋኖ – መስፍን አረጋ

“በጥበበኛ የጦር አዛዥ የሚመራ ሠራዊት ሳይታሰብ ግድቡን ጥሶ በሚጎርፍ ደራሽ ውሃ ይመሰላል፡፡  ደራሽ ውሃ ከፍተኛ ቦታን እየለቀቀ፣ ወደ ዝቅተኛ ቦታ እያዘቀዘቀ፣ ዝቅዝቅ በመጉረፉ በሚያገኘው ጨማሪ (እየጨመረ የሚሄድ፣ increasing) ኃይል እንቅፋቶቹን እየጠራረገ ረባዳን ያጥለቀልቃል፡፡  በጥበበኛ የጦር አዛዥ የሚመራ የጦር ሠራዊትም የጠላትን ጠንካራ ጎን እየራቀ፣ ደካማ ጎኑን እየሰነጠቀ፣ እየጎለበተ በመትመም፣ የጠላት ጦር ያልሰፈረበትን የጠላት ግዛት እንበለ ውጊያ በመቆጣጠር ይንቦራቀቅበታል፡፡  ደራሽ ውሃ ወደ መዳረሻው የሚወንዘው አወናነዙን ከመልክዓምድሩ ጋር እያዛመደ ፍጥነቱን፣ ስፋቱንና ጥልቀቱን በመለዋወጥ እንደሆነ ሁሉ፣ በጥበበኛ የጦር አበጋዝ የሚመራ ሠራዊትም ወደ ድል የሚያመራው የጠላቱን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ስልቱን እንዳስፈላጊነቱ በመለዋወጥ ነው፡፡”   ሰንሹ (Sun Tzu)

“የውጊያ እቅድ ከውጊያ በፊት አስቀድሞ ቢዘጋጅም፣ ውጊያው በሚካሄድበት ወቅት ከሁኔታወች ጋር እየተገናዘበ ሊሻሻል የሚችል፣ ካስፈለገ ደግሞ ሙሉ በሙሉ ሊለወጥ የሚችል ኋሽ (dynamic) (ማለትም ተቀያያሪ) እቅድ መሆን አለበት፡፡  የውጊያ እቅድን ድንጋይ ላይ እንደተጻፈ ኗሚ (static) (ማለትም ቋሚ) መመርያ ሙጥኝ ማለት ትርፉ የሽንፈት ጽዋን መጎንጨት ብቻ ነው፡፡  የውጊያ ሂደት የውሃ ላይ ኩበት ስለሆነ፣ ሁኔታወች እየተገናዘቡ ማጥቃት ወደ መከላከለ፣ መከላከል ወደ ማጥቃት፣ መግፋት ወደ ማፈግፈግ፣ ማፈግፈግ ወደ መግፋት ባስፈላጊው ፍጥነት መለወጥ መቻል አለበት፡፡  ይከላከል የነበረ ጦር ሊያጠቃ የሚችልበት ቀዳዳ ላጭር ጊዜ ሊከፈትለት ይችላል፡፡  ያጠቃ የነበረ ጦር ደግሞ ወደ መከላከል እንዲዞር ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊገደድ ይችላል፡፡”   ማኦ ዜዶንግ (Mao Zedong)

ተጨማሪ ያንብቡ:  የሀገርና ወገን አድን ክተት ጥሪ ክፍል ፭ - ቅድመ ምርጫ የኢትዮጵያ መንግስት አዋላጅ ካውንስል ስለመመስረት- ከአባዊርቱ

 

የቻይናው ቻንግ ካይሸክ (Chiang Kai-shek) የቻይናን ሕዝባዊ ሠራዊት በማጥፋት የቻይና ብሔርተኞችን  ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ የኮሚንታንግ (Kuomintang) ጠቅሊሞ (generalissimo) እንደነበረ ሁሉ፣ ዐብይ አሕመድም የአማራን ሕዝባዊ ሠራዊት በማጥፋት የአማራን ሕዝብ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ የኦነግ ጠቅሊሞ (generalissimo) ሁኗል፡፡  ቻንግ ካይሸክ የቻይና ብሔርተኞችን ጨፍጭፎ ቻይናን ለምዕራባውያን ቅኛፍቃሪወች (neocolonialists) እንዲያመቻች  ስንቅና ትጥቁን ያቀርቡለት የነበሩት ምዕራባውያን (በተለይም ደግሞ እንግሊዞችና አሜሪቃኖች) እንደነበሩ ሁሉ፣ ዐብይ አሕመድም የኢትዮጵያ ብሔርተኞ የሆኑትን አማሮችን ጨፍጭፎ ጦቢያን ለምዕራባውያን ቅኛፍቃሪወች እንዲያመቻች ስንቅና ትጥቁን የሚያቀርቡለት ምዕራባውያን (በተለይም ደግሞ እንግሊዞችና አሜሪቃኖች) ናቸው፡፡

የቻይና ሕዝባዊ ሠራዊት በቻንግ ካይሸክ የኮሚንታነግ ሠራዊት ዙርያውን ተከቦ ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ ላይ እንደነበረ ሁሉ፣ የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊትም በዐብይ አሕመድ ኦነጋዊ ሠራዊት ዙርያውን ተከቦ ውጭ ነፍስ ግቢ ነፍስ ላይ ነው፡፡  የቻንግ ካይሸክን ከበባ በርግዶ፣ ወደ ሰሜን ረዥም ጉዞ (Long March) ተጉዞ፣ ወገን ቀጠና ደርሶ፣ ከቻንግ ካይሸክ ምት አገግሞ፣ ቻንግ ካይሸክን መልሶ አጥቅቶ፣ የኮሚንታንግን ሠራዊት እየገረፈ አባሮ ታይዋን ላይ በመሸከፉ እልህ አስጨራሽ ሂደት፣ የቻይና ሕዝባዊ ሠራዊት መሪ (ማኦ ዜዶንግ) እንደተወለደ ፣ የዐብይ አሕመድን ከበባ በርግዶ፣ ወደ ሰሜን ረዥም ጉዞ (Long March) ተጉዞ፣ ወገን ቀጠና (ኤርትራ ደንበር) ደርሶ፣ ከዐብይ አሕመድ ምት አገግሞ፣ ዐብይ አሕመድን መልሶ አጥቅቶ፣ የኦነግን ሠራዊት እየገረፈ አባሮ ነገሌ ቦረና ላይ በመሸከፉ ሂደት የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት መሪ ይወለዳል፡፡

የዐብይ አሕመድን ኦነጋዊ ከበባ እየበጣጠሱ ወደ ሰሜን ተጉዞ ወገን ቀጠና ለመድረስ የሚደረገውን ረዥም ጉዞ ለማሳለጥ ደግሞ የማኦ ዜደንግ በተግባር የተፈተኑ ምክሮች ፍቱን ናቸው፡፡  ከነዚህ ፍቱን ምክሮች ውስጥ ደግሞ ዋናወቹ ሦስቱ ስልታዊ ትእዛዞች (The Three Tactical Commandments) እና አሥሩ ስነስርታዊ ትዕዛዞች (The Ten Disciplinary Commandments) ናቸው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  አበሻ አያድናችሁ ..ፈረንጅ አያድናችሁ”.. ትርክት ወደ ሱዳን/ግብጽ…አያድናችሁ እዉነታ ሲቀየር ፦ ሀዱሽ መለሰ

የማኤ ዜደንግ ሦስቱ ስልታዊ ትዕዛዞች (The Three Tactical Commandments)  የሚከተሉት ናቸው፡፡

  1. ጠላትሲበረታ አፈግፍግ
  2. ጠላትሲዳከም አጥቃ
  3. ጠላትሲያርፍ አውክ

የማኦ ዜዶንግ አሥሩ ስነስርዓታዊ ትዕዛዞች (The Ten Disciplinary Commandments) ደግሞ የሚከተሉ ናቸው፡፡

  1. ያለቃህንትእዛዝ ቅንጣት ሳትጠራጠርና ላፍታ ሳታንገራግር ፈጽም፡፡
  2. የሕዝብን ንብረት አትንካ፣መርፌም ብትሆን፡፡
  3. ከሕዝብስጦታ አትቀበል፣ ክርም ብትሆን፡፡
  4. ከሕዝብምንም ነገር አተዋስ፣ የግድ መዋስ ካለብህ ደግሞ የተዋስከውን ወዲያውኑ ተጠቅመህ በተዋስክበት ሁኔታ መልስ፣ ካበላሸህም ትክክለኛ ዋጋውን ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
  5. ከገበያምሆነ ከየትም ቦታ ለምትገዛቸው ወይም ለምትሸምታቸው ነገሮች ሁሉ ተገቢ ዋጋቸውን ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
  6. በውጊያወቅት ላወደምከው ወይም ላጠፋኻው ወይም ለጎዳኻው የሕዝብ ሐብት፣ ንብረትና ሂወት ተገቢውን ካሳ ሙሉ በሙሉ ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
  7. የውጊያግርግር ለዘራፊ ያመቻልና፣ በግርገሩ የተዘረፈን፣ የተበዘበዘን ወይም የተመዘበረን የሕዝብ ሐብትና ንብረት አስመልስ፣ ማስመለስ ካልቻልክ ደግሞ ተገቢውን ካሳ እራስህ ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
  8. ሴት፣ወንድ፣ ሕጻን፣ አረጋዊ ሳትል ማናቸውንም ሰው ስታናግር ሁልጊዜም በትሕትና አናግር፣ በተቻለህ መጠን ደግሞ እርዳ፡፡
  9. ልጃገረድ፣ኮረዳ፣ ባለትዳር፣ ፈት፣ ጋለሞታ፣ ሴታአዳሪ ሳትል ሴትን አክብር እንጅ በጭራሽ እንዳትደፍር፡፡  ግዳጅ ላይ እስካለህ ድረስ ከሩካቤ ሥጋ ፈጽሞ ታቀብ፡፡
  10. ምርኮኛምሆነ እስረኛ አታጎሳቁል፣ በተቻለህ መጠን ተንከባከብ፡፡

ሦስቱ ስልታዊ ትእዛዞች እና ካሥሩ ስነስርታዊ ትዕዛዞች በተጨማሪ ደግሞ ማኦ ዜዶንግ ያረቀቃቸው የተለያዩ መመሪያወች ነበሩ፡፡  ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

  1. የአካልብልቶች ብዙ ቢሆኑም፣ የአንድ በአንድ ለአንድ ናቸው፡፡  ዓይን ጆሮን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የደንቆሮ ዓይን ይሆናል፡፡  ጆሮ ዓይንን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የእውር ጆሮ ይሆናል፡፡  እጅ እግርን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የቆማጣ እጅ ይሆናል፡፡  እግር እጅን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የጉልድፍ እግር ይሆናል፡፡  የጦር መሪ የመጀመርያው ተግባር ሁሉም የሠራዊቱ ክፍሎችና አባሎች ላንድ ዓላማ ባንድነት የቆሙ አንድ መሆናቸውን በማሳመን በመካከላቸው ሠራዊታዊ ፍቅርና መከባበር እንዲያደር በማድረግ አንተ ትብስ አንቺ ትብስን ማስፈን ነው፡፡  መናናቅ አብሮ ለመወደቅ፣ መከባበር አብሮ ለመናር፡፡
  2. ጠቢብየጦር አዛዥ ንግግር የማያበዛ ጭምት ነው፣ በቀላሉ የማይበሳጭ ሆደ ሰፊ ነው፣ የሚተማመነው በልቡ ሳይሆን ባይምሮው ነው፣  በእቅድ እንጅ በደመነፍስ አይመራም፣ ደንብና ስርዓትን አክብሮ ያስከብራል፣  ለሂወቱ አይሳሳም፣ ለንብረት አይጓጓም፡፡  ሞት ጅብ ነው፣ የደፈረውን ይፈራል፣ የፈራውን ይደፍራል፡፡  ዘጠኝ ሞት መጣ ሲለሁ አንዱን ግባ ካልከው ዘጠኙም ይመለሳል፡፡
  3. አንዳንድሰወች የራሳቸውን ማንነትና ምንነት አብጠርጥረው ሲያውቁ፣ ስለባላንጣቸው ማንነትና ምንነት ግን ፍንጭ እንኳን የላቸውም፡፡  አንዳንዶቹ ደግሞ የነዚህ ዓይነት ሰወች ተቃራኒወች ናቸው፡፡  ሁለቱም ዓይነት ሰወች ለጦር አመራር ብቁ አይደሉም፡፡  ጠላትህን መርታት የምትችለው ያንተን ብቻ ሳይሆን የጠላትህን ማንነትና ምንነት አብጠርጥረህ ስታውቅ ብቻ ነው፡፡

ስለዚህም ፋኖ የጠላቱን የዐብይ አሕመድን ምንነትና ማንነት አብጠርጥሮ ማወቅ አለበት፡፡  ዐብይ አሕመድ ወተት ነጭ ነው ቢል መታመን የሌለበት ውሸታም ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ የሆኑ አጭበርባሪ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ የሚፈልገውን ለማግኘት እስካስፈላጊው ለመዝቀጥ ቅንጣት የማያቅማማ ዝቃጭ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ በእኩይ ባሕሪ የተጨማለቀ ነውረኛ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ ጥላው የሚያስበረግገው ፈሪ ነው፡፡  ፊሪ ስለሆነ ደግሞ የፈሪነቱን ያህል ጨካኝ አረመኔ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ ለዚሁ ሁሉ የተዳረገው ደግሞ በከረረ የማንነት ቀወስ ክፉኛ የሚሰቃይ የስነልቦና በሽተኛ ስለሆነ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የህልውና ዋሥትናችን የአማራ አንድነታችን!  ወደቀ ሲሉት የሚነሳው፣ደከመ ሲሉት የሚበረታው፣ሞተ ሲሉት ህይወት የሚዘራው ጀግናው አማራ አንድ ሁነህ ተነሥ!

ዐብይ አህመድ ግማሽ አማራ (በዚያ ላይ ደግሞ ከአማራ ጋር የተጋባ) ነው ተብሎ በኦነጋውያን ስለሚጠረጠር፣ ባይነ ቁራኛ እንደሚጠበቅና እያንዳንዷ ድርጊቱ ባጉሊመነጽር (microscope) እንደምትመረመር አሳምሮ ያውቃል፡፡  ትንሽ ቢሳሳት ግዙፍ ውለታው መና ቀርቶ ከሃዲ እንደሚባል ነጋሪ አያስፈልገውም፡፡  እስከጣፈጠ ድረስ ተላምጦ የሚተፋ አገዳ መሆኑን ስለሚያውቅ፣ የሂወቱ አልፋና ኦሜጋ የሆነው ብቸኛው ጥረቱ ጥፍጥናው አልቆ እንዳይተፋ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ኦነጋውያን ትናንት ከሚያምኑት የበለጠ ዛሬ እንዲያምኑት፣ ትናንት ካደረገው የከፋ ዛሬ ማድረግ አለበት፡፡  ስለዚህም በአማራ ሕዝብ ላይ የበለጠ እና የበለጠ ጭራቅ እየሆነ መሄድ አለበት፣ እየሄደም ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ዐብይ አህመድ በማንነቱ ምክኒያት መቸም ከማይወጣበት እኩይ አዟሪት (vicious circle) ውስጥ የገባ ኦነጋዊ አውሬ ነው፡፡

ስለዚህም፣ ፋኖ የራሱን ሕልውና በመታደግ የአማራን ሕዝብ ሕልውና መታደግ የሚችለው ጫንቃው ላይ የተከመረበትን ይህን ኦነጋዊ አውሬ በተቻለው ፍጥነት አሽቀንጥሮ በመጣል ብቻ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድን አሽቀንጥሮ መጣል የሚቻለው ደግሞ ሙሉ በሙሉ ተደግፎ የቆመባቸውን የግራና የቀኝ ምርኩዞቹን በመቀማት ብቻ ነው፡፡  እነዚህ ሁለት ምርኩዞቹ ደግሞ ሌላ ማንም ሳይሆኑ ልክ እንደራሱ እንደ ዐብይ አሕመድ በከፍተኛ የማንነት ቀውስ የሚሰቃዩት ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጡሩነህ ናቸው፡፡

የአማራ ሕዝብ ለዚህ ሁሉ ውርደት የተዳረገው ደመቀ መኮንንን፣ ተመስገን ጡሩነህን፣ ሰማ ጥሩነህን፣ አበባው ታደሰንና መሰለ በለጠን የመሳሰሉት፣ አማራዊ ስም እንጅ አማራዊነት የሌላቸው የአማራ ለምድ የለበሱ የብአዴን ፀራማራ ተኩላወች፣ የአማራን ሕዝብ በገፍና በግፍ እያስጨፈጨፉ በራሱ በአማራ ሕዝብ መኻል ዝንባቸው እሽ ሳይባል እንዲኖሩ ስለተፈቀደላቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

 

4 Comments

  1. አሜሪካ ላይ ቁጭ ብለህ ሃምበርገር እየበላህ ሌላው ለቅዠትህ እንዲሞትልህ ታባብላለህ?

  2. ሰመረ ጥልቅ የሚለው እንደ እርጎ ዝምብ ይባል እንጅ እነርሱ ጋር ያለው እርጎ ሳትሆን ግፋ ቢል አንበታ አለበለዚያ ቁልቋል ነው፡፡ስለዚህ ሲያቃዘው ቢውል እርጎ በህልሙ ይጎብኘው እንጅ እዚያ የለም፡፡

  3. ጭራቁ አብይ አህመድ ወልቃይትን ኢላማ ያደረገና ፋኖን ለማጥፋት ያቀደ በቀርቡ የተዋቀረው የወያኔና የኦነግ ጸረ አማራ ጥምረት ዋና ጸሀፊ ሆኖ በማገልገል ላይ ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይሳካል??? በአማራ በኩል አይሳካም ነው መልሱ፡፤ዉጤቱ ይታያል!!!
    ከዚህ ውጭ አንድ እውነታን አንስቼ ላጫውታችሁ፡፡
    ወያኔ ኦነኝ አፈር ከድሜ አብልቶ ከአገር ውስት ሳያወታው በፊት ዱሮ ሁለቱ አገር ለማፍረስ አንድ በነበሩበት ወቅት አንድ ስምምነት ነበራቸው፡፡ ይሄውም የአማራን ህዝብ ቁጥር አሳንሶ ከኦሮሞ ህዝብ ቁጥር በታች ማድረግ ነበር፡፡ ወያኔ ለተንኮል ሲል ኦነግ ደግሞ በጅልነት ወያኔን አምኖ የአማራ ህዝብ በቁጥር ከኦሮሞ ቀጥሎ ነው የሚለውን መርዘኛ ቀመር አምኖና ተቀብሎታል፡፡ አሁን ድረስ ተረኛው ኦሮሙማ ይህንኑ ተቀብሎ እየተኮፈሰ ሲነፋፋ እየታዘብን ነው፡፡ ለነገሩ ሆዳም የአማራ ሹመኛ ተብየወችም የተስማሙበት ጉዳይ ነበር፡፤
    እውነኡ ግን ሌላ ነው፡፡ ሀቁ በህዝብ ቆጠራ ይረጋገጥ ቢባል ኦነግም ወያኔም አይሆንም ብለው ክችች ነው የሚሉት፡፤ እውነት ግን ጊዜዋን ጠብቃ ሀቁን ታወጣዋለች፡፡ በአማራ በኩል ያለው አቋም አንድና የማይናወጥ ነው፡፤ ህዝብ ቆጠራ ተደረገም አልተደረገም አማራው ለጠላቶቹ የሚያረጋግጥላቸው አንድ ነገር ቢኖር 50 ሚሊዮኑ አማራ በሙሉ ፋኖ መሆኑን ነው፡፡ አለቀ፡፡ ፋኖ የአማራ ደምና አጥንት ነው፡፡ እናንተም እኛም ይህንኑ እውነት በሚገባ እናውቀዋልን፡፡ ታሪክም መዝግቦ ይዞታል፡፡ ስለዚህ የአሁኑ የአብይ አህመድ የኦርሞ ጦርን የአማራ ልዩ ሀይል መለዮ አልብሶ ፋኖን ለማስጨፍጨፍ መወራጨቱ የራሡን ውድቀት ከማፋጠን ውጭ የሚያመጣለት አንዳች ነገር የለም፡፡ ፋኖ ማለት 50 ሚሊዮን ህዝብ ስለሆነ ገድለህ አትጨርሰውም፡፡
    አንተ የአገሪቱ ጠ/ሚ/ር ሆነህ በኦሮሚያ የተጨፈጨፉትን ንጹሀን በቴሌቪዥን ቀርበህ በዘር እየለየህ የቆጠርክልን እለት ነበር እርም አብይ አህመድ ማለት የሚገባን፡፡ በኢትዮጵያዊነት መቃብር ላይ ኦሮማዊነትን ለመትከል አበክረህ እየሰራህ እያየን ደጋግመህ “ኢትዮጵያ አትፈርስም” ስትለን አለማፈርህ የሚያስረዳው የአንተን ምንኛ ፈጣጣ መሆንህን ብቻ ሳይሆን እኛ ቁልቁል የቱን ያህል ወርደን እንደተታለልን ጭምር ነው፡፡
    ወያኔ በበኩሉአንድ ሀቅ አለ፡፡ በውጭም በውስጥም አማራን አጣብቂኝ ውስጥ ከትቼ የወልቃይትና ራያ ለም የአማራ መሬቶችን ወስጄ ታላቋ ትግራይን በአገርነት እመሰርታለሁ የሚለው ህልም ቅዠት ሆኖ ይቀራል ፡፡ ምእራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ ብሎ ነገር የፈጠረው የባንዳው ውላጅ መለስ ዜናዊ ነበር፡፡ ምንጊዜም አይሳካም፡፡ የሚሳካ የሚመስል ግን አንድ ነገር አለ፡፡ ይሄውም ትግራይ ለም የአማራ መሬትችን ወልቃይትንና ራያን መከጀሏን ትታ በራሷ ማለትም ዱሮም አሁንም ባለችበት ቅርጿ፣ ወርዷና ቁመቷ አገር መሆንን ልትሞክረው ከወሰነች ትችል ይሆናል፡፡ በአማራው በኩል ወልቃይትና ራያ ላይ ሙጭጭ ማለቷን እርም ብላ ትታ አገር መሆን ከፈለገች መንገዱን ጨርቅ ያድግርግላት እንላለን፡፡
    ሲጀመር በታሪክ ምእራብ ትግራይና ደቡብ ትግራይ ብሎ ነገር የለም፡፤ በጎንደር በኩል ያለው መሬት ወልቃይት ሲሆን ኗሪውም ወልቃይቴ ነው የሚባለው፡፡ በወሎ በኩልም ያለው መሬት ራያ ሲባል ኗሪውም ራያ ራዩማ ነው የሚባለው፡፡ ይህንን እውነትም ታሪክም ያውቁታል፡፡
    ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይጠብቅ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share