ፋኖ ተሰማራ! ፍኖ ተሰማራ! እንደ አሳምነው ጽጌ፤ ገድል ሰርተህ ኩራ! ፋኖ ተሰማራ! ለክብርህ ተታገል፣ ለአንድነትህ ሥራ – ከደረጀ አያኖ

የአቢይ አህመድ አራተኛው የአማራ ክልል ተሿሚ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ፤ “ሁለተኛ ግፌ፣ ጫንቃዬን ተገርፌ፣ ልብሴን መገፈፌ”

በመጀመሪያ ለምን የክልል መሪዎች በክልልሉ ሕገ መንግሥት መሰረት በክልልላቸው ተወካዮች እንደማይመረጡ አይጋባኝም። እንዴት ኦህዴድ የሚመራው ብልጽግና የሁሉንም የክልል መንግሥታት ይሾማል? ወደ ጽሁፌ ስመለስ፣ ለመሆኑ ይህ አራተኛው የኦህዴድ ብልጽግና የአማራ ክልል እንደራሴ፣ ይልቃል ከፋለ፣አሸባሪውና ነብሰበላው ኦንግ ሸኔ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማራዎችን ሲጨፈጭፍ፣ ሲያፈናቅልና ንብረታቸውን ሲያወድም፣ የትኛውን የሕግ ማስከበር እርምጃ ወስዶ ያውቃል?

የዛሬው ፋኖ የስንቱን አማራ ህይወት ቀጥፎ ነው፣ የስንቱን ቤት አፍርሶ ነው የሕግ እርምጃ የምትወስድበት?

የወያኔ አሸባሪ ቡድን አማራን ዙሪያውን ወርሮና ከቦ ሕዝቡን ለወራቶች ከአላማጣ እስከ ደብረሲና ድረስ ሲገድል፣ ሲደፍር፣ ሲዘርፍና ሲያወድም እስከመጨረሻው ከማየትና መውጫህን እያስተካከልክ ከመሸሽ በስተቀር፣ ሕዝቡን ከመወረሩ አስቀድመህ አድነህዋል? የአማራን ሕዝብ ለመታደግ የትኛውን የሕግ ማስከበር እርምጃ ወስደህ ነበር? በዚያ አስክፊና ዘግኛኝ ሰዓት፣ ከብቱን ሸጦ፣ እራሱን አስታጥቆ፣ ለተደፈረችው እህቱና ለተጨፈጨፉት ወገኖቹ ደሙን ያፈሰሰውና ህይወቱን የገበረውን ፋኖን አሁን የሕግ እርምጃ ልውሰድብህ እያልከው ነው? ምን አጥፍቶ? አንተንው በወንበርህ ባቆየ?

 

ፍኖ ከአማራ ጠላቶች ጋር ለመፋለምና ማንነቱን ለማስከበር መጠናከሩና መታጠቁ ሥጋት ሆኖብህ ነው በፋኖ ላይ የሕግ ማስከበር ዘመቻ ያወጅከው? የፋኖ ጥይት ስንት ገደለ?

በወለጋና በመተከል የአማራ ሕዝብ በሺዎች በገጀራ ሲጭፈጨፉ፣ ሆድ እየተቀደደ አማራ እንዳይወለድ በእናት ማህጸን ያለ ሺል ሲቆራረጥ፣ የትኛወን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወስደህ ታውቃለህ? የትኛውን በገፍ የተፈናቀለ የአማራ ሕዝብ መልሰህ አሰፈርክ ታውቃለህ? የማንን ጥቅም እያስከበርክ ነው? ያንተንና የሿሚዎችህን? በየክልሉ ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩት አማራዎች በማንነታቸው ሲጠለፉ፣ ሲሰወሩ፣ ከፎቅ ሲወረወሩ፣ ሲገደሉና ቋንቋቸውን እንኳን እንዳይናገሩ ሲደረጉ፣ እንደ አማራ መንግሥትና አማራ ትንሽ እንኳን ቆርቁሮህ የትኛውን የሕግ ማስከበር ዘምቻ እንዲካሄድ አድርገሃል?

 

ለምን የአማራ የበኩር ልጅ የሆነው ፋኖ፣ የአያቶቹን ፈለግ ተከትሎ፣ አንዲት ነፍስ ሳያጠፋ፣ አንዲት ስሙኒ ሳይሰርቅ፣ የሕግ እርምጃ እንዲደረግበት ሆነ? ታዲያ ይህን የሚያደርግ የአማራ ወዳጅ ወይንስ የአማራ ጠላት? አማራ ወይንስ የአማራን ለምድ የለብሰ የወያኔና የሸኔ ድብቅ ተኩላ?

ዛሬ፣ ወያኔ ከመቼውም በላይ ተደራጅቶ በአደባባይ የጦርነት ነጋሪት እየመታ ባለበት ሁኔታ፣ በግልጽ ወደ አዋሳኝ የአማራ ከተሞች በብዛት ጦሩን እያስጠጋ እያለ፣ አንዳንዶቹንም ወረዳዎች እየወረረ ባለበት ሁኔታ፣ እንዴት የህዝቡን ዘብ ጠባቂ ፍኖን፣ የይልቃል ከፋለና የተላላኪው ቡድን ትጥቁን ለማስፈታት በችኮላ የሚሯሯጡት? የአማራን ዙሪያ የከበበው የወያኔ ወራሪ ጠላት እንዲመቸው? እንደበፊቱ ያለተካላካይ ገብቶ የአማራን ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ እንዲጨርሰው? ለአርባ ዓመት የተቀማውን ሐገር መልሶ ለመስጠትና ሕዝቡን ወለጋና መተከል እንደተደረገው ለመጨረሻ ጊዜ ለማፈናቀልና ለመጨረስ? ሐገር አልባ ለማድረግ?

 

በዕውነቱ በምን ምክያት ነው በፋኖ ላይ የሕግ ማስከበር እርምጃ የታወጀው? ለወያኔ ወረራ እንዲመች? ኦነግ ሸኔ በሰሜን ሸዋ ተጠናክሮ ወረራውን እንዲቀጥል? ኦፌኮ ትጥቅ አስፈቱልኝ ስላለ? ኦህዴድ የፋኖንና የአማራን መጠናከር ስለሚፈራ?

እውነታው ግልጽ ነው። በብሄር ርዕዮተ አለም የተዋቀረው ብልጽና፣ ወያኔን ተክቶ ባለተራ ሆኗል። ሽመልስ አብዲሳ የዛሬ ሁለት ዓመት እንዳለው አማራና የተቀሩት ክልልሎች ቁማር ተበልተዋል። የየክልሉን መሪዎች የሚሾመው ቁማሩን የበላው የብልጽግና ኦህዴድ ነው። ከሁሉም ክልልሎች ይልቅ፣ የኦህዴድን ብልጽግና የሚያሰጋው ደግሞ የአማራ ክልል ነው። ለምን ቢባል ብእዴን ወያኔን ከጫወታ ውጭ ለምድረግ ታላቅ አስተዋጾ ቢያደርግም ባልገመተው መንገድ የኦህዴድ “የኔ ብቻ” ሰለባ ሆኗል። ስለዚህ የአማራ ክልል እንዲንሰራራ አይፈልግም። ለዚህም ይመስላል መከላከያ ወደኋላ እያፈገፈገ የአማራ ክልል፣ እስከ ኦሮሞ ክልል ድረስ እንዲዘረፍና እንዲወድም ለወያኔ የፈቀደለት። አማራ ወደኋላ ለ100 አመት እንዲመለስ።

ዶክተር ይልቃል ከፋለ አራተኛው የአማራ ክልል ፕሬዜዳንትና የኦህዴድ ተሿሚ ነው። የበፊቶቹ አራት የኦህዴድ ተሿሚዎች ሁሉ በክልልላቸው ሆነው ከአዲሶቹ ተሿሚዎች ጋር ሊዶልቱ ስለሚችሉ፣ ሌላ የፌዴራል ሹመትና ጥቅማ ጥቅም እየተሰጣቸው ወደመናገሻዋ ከተማ መጥተዋል።

ታድያ፣ ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ አራተኛው የአማራ ክልል ፕሬዜዳንትና የኦህዴድ ተሿሚ፣ የአማራ ሕዝብ አገልጋይ ነው ለማለት ይቻላል? ዶክትሩ የሚያወጣቸውን አማራ ጠል መግለጫዎች ብቻ መስማት ይበቃል። አንዳንዴ ከመነጽሩ ጋር አብሬ ሳየው፣ ከሚናገራቸው አንዳንድ የአማርኛ ቃላቶች ጋር፣ መለስ ዜናዊን ይመስለኛል። ወያኔ ቀደም ብሎ ከተከላቸው አማራ ጠልና አማራነታቸውን ከደበቁ ወይም አማራ ሳይሆኑ ከሆኑ፣ የሕዝብ ከሃዲ ካድሬዎች መካከል የኦህዴድ ብልጽና በየተራ እየለቀመ ከሚሾማቸው ተላላኪዎች አንዱ ይሆኑ? የአማራ ሕዝብ በታሪክ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አስፈሪ ውቅት ላይ ይገኛል። ትናንትና እነ ዶክተር አምባቸውና ጄኒራል አሳምነው ጽጌ በተቀነባበረ ሴራ ተገለዋል። ዛሬ ስምንት ጥይት በሰውነቱ ላይ ተተክሎ የአማራን ልዩ ሃይል እየመራ ወያኔን የደመሰሰው ጀግናው ጄኒራል ተፈራ ማሞ፣ እንደ አንድ ወሮበላ ከአዲስ አበባ መንገድ ላይ በፌዴራል ፖሊስ ተጠልፎና ታፍኖ ለተላላኪው ይልቃል ከፋለ ተልኳል። የኦህዴድ አገልጋይና ተላላኪው ይልቃል ከፋለም የጌቶቹን ትእዛዝ ተቀብሎ ባህርዳር ከተማ ከርቸሌ አስገብቶታል። ጄነራል ተፈራ ማሞ ሌላው የአሳምነው ጽጌ ወንድምና የኢትዮጵያ የቁርጥ ልጅ ነው። በፋኖና በአማራ ሕዝብ ሥሙ ሲዘከር ይኖራል። አማራ ብዙ አርበኞች አሏት። በየመንደሩ የበቀሉት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የአማራ ወጣት አርበኞችና ሉሆዳቸው ያልተሰለፉ ኩሩ አማራዎች (ፍኖዎች)፣ ስለናንተ ባንዳና ተላላኪዎች ምን እንደሚያወሩ ጆሮዋችሁ ከሰፊው ሕዝብ እጅግ ስለራቀ አታውቁትም። የናንተ ጆሮ የሚያዳምጠው የካድሬዎቻችሁን ሪፖርትና የኦህዴድ አለቆቻችሁን ትዕዛዝ ብቻ ነው።

ትላንትና ከአሥር ወራቶች በፊት ለተደደረገው ጦርነት እውቅና ሰጠሁዋቸው የሚላቸውን የፋኖ አባሎች እየመረጠና እያበላለጠ ሹመት ሰጥቷል። ሹመቱ ሁለት ጥቅም አለው። አንደኛው ፋኖን የመከፋፈል ዘዴ ነው (ሌሎቹን ከነ ዘመነ ካሴ፣ ማስረሻ ሰጤ፣ አርበኝ መኳንንት፣ ወዘተ)። ዋነኛውና ሁለተኛው ግን በሸለመ ማግሥት “ሀሰትና ስንቅ እያደረ ያልቅ” እንድሚባለው ፋኖን በማለዘብ “ሕግን ለማስከበር” በሚል የሃሰት ፕሮፓጋንዳና ዘመቻ የፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት መሯሯጡ ነው። ይህ አሁን እየሆነ ያል መሬት ላይ የደረቀ ሀቅ ነው።

“ሎሌና አሞሌ ካዘዙት ይውላል” እንዲሉ፣ ፋኖን ትጥቅ የምታስፈቱት ወያኔ ተመልሶ ወልቃይትንና ራያን ለመቆጣጠር እንዲመቸው የተሰጣችሁን ትዕዛዝ ለማስፈጸም ብላችሁ ክሆነ፣ ይህ የሚሆነው በአማራ መቃብር ላይ ብቻ ነው።

 

አዲሱ ትውልድ፤ እንደ ስልሳዎቹ የማይጨናገፍ፣ የባንዳዎችንና የተላላኪዎችን አከርካሪ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚሰብር፣ የአማራንና የኢትዮጵያን ሕዝብ ከነዚህ ከቀን ጅቦች ነጻ የሚያወጣ ትግል ጀምሯል። በፋኖ መሪነትና በ ደጋፊነት የሕዝብ አመጽ ተቀስቅሷል። ሊቀለበስም አይችልም። አዎን ሰላምና ነጻነትን የሚያስከብረው ባለቤቱ ብቻ ነው። ትግልና ነጻነትም የአንድ ሳንቲም ገጽታ ናቸው። ነጻነት ያለትግልና መስዋትነት አይመጣም።

ፋኖ ተሰማራ! ፍኖ ተሰማራ!

እንደ አሳምነው ጽጌ፤ ገድል ሰርተህ ኩራ!

ፋኖ ተሰማራ! ለክብርህ ተታገል፣ ለአንድነትህ ሥራ።

 

ደረጀ አያኖ

4 Comments

  1. አንተም የስምሪቱ አካል ሁን ትእዛዛችን ሂድና ሙትልኝ እንዳይሆን።

  2. አሳምነው ጽጌ መንፈቅለ መንግሥት ሞክሮ ሲሸሽ የተገደለውም አደል? ታዲያ ከመቸ ወዲህ ነው ጀግና የወጣው?

  3. አማራና ፋኖ እንዲያ ስደነፉ ለኢትዮጵያ የሚያልፍላት መስሎኝ ነበር፥ እንዲህ በቀላሉ እንደምቀልጡና ፈስ በፈስ እንደምሆኑ ፍጹም አልገመትኩም ነበር። የጀርባ ኣጥንታቸዉን ስመረምር ለካስ በዘራቸው ቡካታም ጳርጳሮች ናቸዉ። የነርሱን ዘር አይድርገኝ።

  4. ጽንፈኛ አትሁን
    እንደ እባብ በዱላ ቀጥቅጦ ሊገልህ ቢነሳ ተረኛ
    እጅህን አንስተህ ራስህን አትመክት አትሁን ጽንፈኛ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

tedros
Previous Story

ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የሕወሓትን አላማ ማስፈጸማቸውን እንዲያቆሙ ተጠየቀ

Fano 4
Next Story

ይድረስ ለአማራ ፋኖ! – ከብሥራት ደረሰ

Latest from Blog

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ | አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ | አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል | ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

አዲስአበባ ተኩስ ተከፈተ “ለመደራደር ዝግጁ ነን” አረጋ ከበደ\  አዲሱ አዋጅና የቀረበበት ተቃውሞ “የሞተም ሰው ንብረት ይጣራል አብይ አደገኛውን ካርድ መዘዙ ጌታቸው ያጋለጠው ጸብ

ከመጠምጠም መማርን እናስቀድም!

;በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) አብዛኛው አንባቢ ተገንዝቧል ብዬ እንደምገምተው ሕዝብ ለቡና ቲራቲም፣ ለግብዣ፣ ለበዓል፣ ለሰረግ፣ ለሐዘን፣ ለእድር፣ ለእቁብ ለውይይትና ለሌሎችም ማህበረሰባዊ ጉዳዮች ሲገናኝ የሚበዛው አድማጭ ሳይሆን ተናጋሪ  ወይም ደግሞ ለመናገር  መቀመጫውን ከወንበር ወይም
Go toTop