ኢትዮጵያዊያን ቆም ብለን የምናስብበት ወቅት ዛሬ ነው – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

   መነፅር

Man was born free and everywhere he is in chains .”

Jean_Jacques  Rousseau

“ ሰው የተወለደው ነፃ ሆኖ ነው።የሁን እንጂ  ( በማስተዋል ብትመለከቱ ) በየትም ሥፍራ በሰንሰለት ውሥጥ ነው ። “

( እንዴት ነው የታሠርንበትን ሰንሰለት በጣጥሰን ሰው መሆናችንን የምናውጀው ?

” The state of nature   has  a low  of  nature  to govern it which obliges everyone ; and reason , which is that law , teaches all man kind , who will but consult it ,  that  being all equal and independent , no one ought to harm another in his life , health , liberty or possession . ”

John  Locke

( ጆን ሎክ, የለዘብተኝነት አባት በመባል ይታወቃል ፡፡ ሎክ የእንግሊዝ ፈላስፋና ሐኪም ነበር። የሎክ ጽሑፎች በፈረንሳዊዎቹ አብዮተኞች ቮልቴር እና ሩሶ ዘንድ የሰረጸ ነው ፡፡ በስኮትላንድ አሳቢዎች እና እንዲሁም በአሜሪካ አብዮተኞች ዘንድ ተሰሚነት ፅሑፈቹ ነበራቸው። በአሜሪካ የነጻነት ድንጋጌ ላይ የጆን ሎክ ስም ሰፍሮ ይገኛል ። የሎክ ኅልዮቶች ብዙ ጊዜ የሚያጠነጥኑት በማንነት ጥያቄወችና በራስ ግምት ላይ ነበር። እንደ ሎክ አስተሳሰብ ሁሉም ያለምንም ዕውቀት እንደተወለደ ይታመናል ። )   Wikipedia

  የመንግስት ተፈጥሮን ለማወቅ ጆን ሎክን አንጠራም ፡፡

ጆን ሎክ ፤ ስለመንግስት ተፈጥሮ እንዲህ በማለት ብያኔ ይሰጣል ፡፡ ” የመንግስት ተፈጥሮ ፣ማንንም በቁጥጥር ሥር አድርጎ በበላይነት ማስተዳደር  ፡፡ ለዚህ አስተዳደራዊ ሥልጣኑም ህግን እንደመሳሪያ መጠቀም ፡፡ በዚህ ተፈጥሮውም ህግን የማስተማር ፡፡ አድርግ አታድርግ የማለት ብቻ ሳይሆን ፤ እያንዳንዱ ሰው ነፃ እና እኩል መሆኑን እንዲሁም ንብረት የማፍራት መብቱ የተጠበቀ መሆኑን ያረጋግጣል ፡፡ ”

በዛሬው ዓለም ፤ የመንግስት ተፈጥሮን ለማወቅ ጆን ሎክን አንጠራም ፡፡ የመንግስት ተፈጥሮ አስተዳዳሪነትና ተቆጣጣሪነት መሆኑ ይታወቃል ፡፡ መንግስት ፤ በህግ አግባብ አገርን እና ህዝብን የማስተዳደር ፤ ንብረትና ሀብቱን ከዘራፊ የመጠበቅ ፤ የህዝብ ዕለታዊ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እንዲሆን ከተማና ገጠሩን በወጉ የመጠበቅ ፡፡ ተቋማቱ በወጉ ስራቸውን እንዲከውኑ የመቆጣጠሪያ መንገድ የመቀየስ ፡፡ ለህግ የማይገዛ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን ላይ ተመጣጣኝ ኃይል በመጠቀም ሊደርስ የነበረውን አደጋ የመቀልበስ ፡፡ የሀገርን ግዛት የመጠበቅና የማስከበር ፡ ወዘተ ፡፡ የመንግስት ተፈጥራዊ ባህሪዎቹ ናቸው ፡፡ መንግስት ሲፈጠር  ፣ እያንዳንዱ ግለሰብ እንዳሻው በግለሰብ ፣ በቡድና እና በአገር ጉዳይ እንዳይፈተፍት ለማድረግና ሁሉም ሰው በአገር ህግ እንዲገዛ ና በህግ አግባብ እንዲተዳደር ለማድረግ ነው ፡፡ ሰው ልጅ የየዕለት እንቅስቃሴው እንዳይስተጓጎል ፤ ጉልበተኞች የላቡን ፍሬ እንዳይቀሙት በማሰብ ይህንን መንግስት የተባለ ከእግዜር በታች ያለ ተቋም ወዶና ፈቅዶ አቋቁሟል ፡፡ ወይም ከህዝቡ መካከል ጥቂቶች በአጋጣሚ ወይም በጉልበት ወይም በውርስ ሥልጣን በመያዝ ፤ እስርቤቱን ፣ ጦርኃይሉን ፤ ባንኩን በመቆጣጠር ፣ የሚያርበደብድ ወይም አሻንጉሊት መንግስት መስርተዋል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ማነህ ባለ ሳምንት? እኔ ነኝ የምትል የአብይ አህመድ የነገው የፖለቲካ ጭዳ

በባሌም ሆነ በቦሌ ፤ ዋነው መንግስት ሆኖ መገኘት ነው ፡፡ ይሁን እንጂ ፤ ማንኛውም መንግስት ፣ ዴሞክራት ባይሆን እንኳ ፣ የመከላከያና የፀጥታ አካሉ እጅግ የሚፈራ ከሆነ ሰርቶ በሌው ሺዓመት ይግዛ እንደሚል የታወቀ ነው ፡፡  የትኛውም መንግስት በጦር ኃይሉ እና በፖሊስ አደረጃጀቱ የሚፈራ አገራዊ   ቁመና ካለው  ወንጀለኞችን እና ድንበር ገፊዎችን ብቻ ሳይሆን ፣ ማንኛውንም ስርዓተ አልበኝነትን ስለሚያሶግድ አገሬው አምባገነኑን አገዛዝ ቢደግፍ አያስገርምም ፡፡

ማንም በጉልበት የደነደነ ወይም ዘርፎ በል የሆነ ፤ የአምሣየው ሰው ንብረት እየዘረፈ ከሚበላበት የቀማኛ መንግስት ሥርኣት የአምባገነን ሥርዓት በስንት ጣዕሙ ፡፡ ።  ማንም ሰው  ህይወቱን በገዛ ፈቃዱ ለማኖር ከማይችልበት የስም ዴሞክራሲያዊ መንግስትም ፣ በየመንደሩ በግለሰብ መብት ላይ የሚወስኑትን አስወግዶ አገርን አንድ አድርጎ በህግ አግባብ የሚያስተዳድር እንደ ቻይና ያለ መንግስት በስንት ጠአሙ ፡፡  የሰሜን ኮርያውም ሳይሻል አይቀርም ፡፡ ከሰላም አንፃር ፤ ራሱን ፈጣሪ ያደረገ መንግስት ሳይሻል ይቀራል ? ( ዘመናዊው የመሳፍንት አገዛዝ ፡፡ ) በዚኽ መንግስት ፣ ለመሪው ቤተሰብ ከመስገድ እና ከቤተሰቡ አንዱ ሲሞት ፣ በአደባባይ ወጥተህ እዬዬ ከማለት ውጪ ፤ ሌላ ሰው ዝንብህን እንኳ እሽ ለማለት ስለማይፈቀድለት ፤  ተፈጥሯዊ የሆነውን  የመኖር ነፃነቱ ስለሚከበርለት የሰሜን ኮርያው ዓይንት መንግስትን ተርተው ህዝብ ቢመርጥ አይገርምም  ፡፡

እኛ አገር እኮ ጆኑ ሎክ (29 August 1632 – 28 October 1704) was an English philosopher and physician, widely regarded as one of the most influential of Enlightenment thinkers and commonly known as the “Father of Liberalism“.  ሰው ፣ በገዛ ፍላጎቱ እንኳን የራሱን ህይወት ለማጥፋት የተፈጥሮ ህግ አይፈቅድለትም በማለት በፖለቲካዊ ፍልሥፍናው ጥንት ቢያሰፍርም እኛንም ከእርሱ በፊት የብሉይ ሥርዓትን ስንቀበል አሥርቱ ትዕዛዘት ላይ እውነቱ ተፅፎ ብናስተውልም ዛሬ ታጥቦ ጭቃ ሆነን የፈጣሪን ህግ በመተላለፍ አምሳያችንን ንፁሁን ሰው እንገድላለን ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ተስፋ ሳይኖር ተስፋ መቁረጥ: የተስፋ ቢሶች ተስፋ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ዛሬ  በእኛ ምድር ፣ ይህ አሳዛኝ እውነት ነው በገሃዱ ዓለም የሚታየው ፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ ፣  እንኳን የገዛ ህይወትህን በገዛ ራስህ እንዳታጠፋ የሚከለክል የተፈጥሮ ህግ  ሊበረታታ ይቅርና አንድ የሰው ቡድን ወይም ግለሰብ ከመሬት ተነስቶ ፣ አንዳችም በደል ያላደረሰበትን ሰው ፣ በቆንቋው ልዩነት ብቻ በተኛበት ሲያርደው ፤ ሲያቃጥለውና በአደባባይ ንብረቱን ዘርፎ በአንድ ቀን ጀንበር ደሃ ሲያደርገው እናስተውላለን ፡፡  ለውይይት እንፈልግሃለን በማለትም ፤ አንድ ህሊና ቢስ ቡድን  በመትረየስ  ክብሩን ሰው እንደረፈረፈም አንዘነጋም ።

መልሱ ግልጽ የሆነ ” የለምን ? ” ጥያቄ

ለምን ይሆን  ከመጋቢት 24 /2010 ዓ/ም ጥቂት ወራት  በኋላ እንዲህ ዓይነቱ ፣ የጭካኔ ተግባር እየተስፋፋ እና አድማሱን እያሰፋ የመጣው  ? ብለህ ጠይቅ ፡፡

በለአገሩ ፣ የተፈጥሮ ቸርነትን ዘንግቶ ፣ መሬቱ ፣ አየሩ ፣ዝናቡ ና ፀሐዩ የፈጣሪ ትሩፋት መሆኑን ረሥቶ ነውን ? ወይሥ ለዓለም ተምሳሌት የሆነ አኩሪ ባህሉን ፣ በበአዳን በመነጠቁ ይሆን  ? ወይስ ኃይማኖተኛነቱን ዘረኝነቱ ሥለአሸነፈውና ፈጣሪን በመካድ ፣ህዝብ በራሱ ላይ ያመጣው መቅሰፍት ነውን ? በማለትም አንተ የተማርከውና የተመራመርከው  አሰላስል ፡፡  የችግሩ ፈጣሪ ካልሆንክ ፤ የመፍትሄው አካል መሆን አለብህና ጥያቄውን መመልስ ያለብህ አንተ ነህና !!

ሁለም ጥያቄዎቼ የዋሁን እና ጨዋውን ፤ ሠርቶና አርሶ ከመብላት ውጪ ተንኮል የማያውቀውን  የኢትዮጵያን ህዝብ ለመልስ የሚጋብዙ አይደለም ፡፡ እነሱ እኮ በማያውቁት ነገርና ጉዳይ ነው ፤ በላ ፣ ግፍና ሥቃይ እንደ ናዳ ፣ እየወረደባቸው ያለው  ።

ዛሬም ፣ ጨዋው ባለአገር ፣ ተፈጥሯዊ መብቱን የሚጠብቅ ፣ ለአምሳያው ነፍሥ የሚሳሳ ፣ ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው እጅግ የበዛ ነው ። የዲያቢሎስን ተግባር በየገጠር ከተሞቻችን እየፈፀሙ ያሉት በፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የሚደገፉ ፤ ሰው መሆናቸውን ነዋይ እና ሃሽሽ  ያሥረሳቸው ና ህሊናቸውን ያጡ ጥቂት ባንዳዎች ናቸው ። በተማሩ ዳቢሎሶች እየተመሩ …

እነዚህ ዳቢሎሶች ፣ከወያኔ አብዮታዊ ዴሞክራሲ   የጥርነፋ እና በሪሞት ኮንትሮል የመግዛት   ሥርዓት መገርሰስ በኋላ እንደ አሸን መፍላታቸው ሰበቡ ደግሞ ” የኢትዮጵያ ብልፅግና በአዲሱ የአብይ መንግስት እውን ይሆናል ፡፡ ” በማለት የደመደሙ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ፤ ” ይህንን የኢትዮጵያን ” ጥገናዊ  ለውጥ ” መቀልበስ ፣ ዘላቂ ጥቅማችንን ከሚያሳጣ አደጋ ያድነናል ፡፡ ” በማለት በማሰባቸው ይመስላል ፡፡

በዚህ ፀሐፊ አስተውሎት ፤ እነዚህ የውጪና የውስጥ ጥቅመኛ ኃይላት ፣ መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ/ም  ፣ ወደሥልጣን የመጣውን ፣የኢህአዴግን አብዮታዊ ዴሞክራሲን የሚቃወመውን  “የለውጥ ኃይል ”  (ሲጀመር እነ ” ቲም ለማ ” (የለማ ቡድን ) ይባል ነበር ። በሥተኋላ በለውጡ መንገድ አቀበትነት ተዳክመው ይሁን በቁልቁለቱ ተዳፋትነት ተንከባለው ፣ አልያም በናዳ ተመተው አይታወቅም ፣ ዶ/ ር ለማ መገርሣ ከጫወታው ውጪ መሆናቸው ይታወቃል።)  ከጅምሩ ለውጡን አለወደዱትም ነበር፡፡

ይህ ለውጥ ግን  በጠ/ሚ  ዶ/ር አብይ አህመድ ” መደመር ” በሚባለው ፍልሥፍና ወይም ደግሞ ” መደመራዊ ዴሞክራሲ ” ጉዞውን የህዝብን የልብ ትርታ እያስተዋለ መጎዝ ጀመረ ፡፡ ይሁን እንጂ ከዓመት በኋላ ፣ ለውጡን በዋይታ ና በሰቆቃ ውሥጥ  ተዘፍቆ እንዳይላወስ የሚያደርጉ እሳቶች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተጠና እና በከፋ መልኩ ተለኩሰው መቀጣጠል ጀመሩ ፡፡

 

የለውጥ ኃይሉም ያለእረፍት ፣ አገርን ለማፍረስ ከሚጥሩ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋር ውጊያ ጀመረ ፡፡  የለውጥ ኃይሉ ከአገር ገንጣይና አፍረሽ ባንዳዎች ጋር   ፣ ሌት ተቀን  እየተናነቀ ወይም  ኢትዮጵያን እሥከ ክብሮ ለትውልድ ለማሥረከብ ቆራጥ አመራራ እየሰጠ   ፤ ” አይዞችሁ ፣ ወደፍትህ ፣ ወደ ዴሞክራሲ ፣ ወደ ጋራ ተጠቃሚነት ፣ ወደ ሠላም ና ፀጥታ ወዘተ ። አሻግራችኋለሁ ፡፡ ብቻ ታገሱኝ ። ጊዜ ስጡኝ ፡፡ ”  እያሉ የለውጥ ጉዞው ቀጥሎ እንሆ    አራተኛ ዓመቱን ጨርሶ ፣ አምስተኛውን ተያይዞታል ። ( መቼም ፣ ከእንዳልካቸው ካቢኔ ጋር አይነፃፀርም ፡፡ ጊዜ ና ፋታ በመጠየቁ፡፡

በበኩሌ ፤ጠቅላይ ሚኒስትራችን  ” ታገሱኝ ። ጊዜ ስጡኝ ” በማለት  የህዝብን ትዕግስት መጠየቃቸው ተገቢ ነው ። የአገራችን ችግር እንደ በጋ ጉም በተአምር ብን ብሎ የሚጠፋ ባለመሆኑ ዜጎችን ትዕግሥትና  ትብብር መጠየቃቸው አግባብ ነው ። ከ 60  ዓመት በላይ የዘለቀን  የጎሣ ፖለቲካን ወይም የቅኝ ገዢዎችን  የተቀነባበረ የቆዳ ማዋደድ የከፋፍለህ ግዛ የተቀበረ   ቦንብን እና የአሜሪካ ና የአውሮፓ ቱጃሮችን ብዝበዛ ና የመክበር መሻትን ፣ በጣት በሚቆጠሩ ዓመታት ለመቀልበሥ አይቻልም ። በዚህ ላይ እውነቱ ሲነገራቸው የማይሰሙ ፣ የጎረቤቶቻቸው መራብ የሚያሥደሥታቸው ፤ በሤጣናዊ አሥተሳሱብ ህሊናቸውን ያጨቁ መሪዎች ፣ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ወይም የእግዜር ውሃ ተጠቅማ በፍትሐዊነት ለመበልፀግ  ሥላሰበች ፣ አንዳችም ጥቅም ሳይጎድልባቸው ፣ ገና ለገና” ኢትዮጵያ ከበለፀገች በትክክለኛው ፍትህና ርዕትህ በሰፈነበት  የዴሞክራሲ መንገድ ላይ መራመድ ከጀመረች ፣ የምናሥተዳድረውን ህዝብ በአባይ ፖለቲካ እያሥፈራራን ፀጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛ ማድረግ አንችልም ። ” በሚል ግላዊ የገዢነት ሥጋት  ፣   የግብፅንና የሱዳንን ህዝብ በማወናበድ በኢትዮጵያ ላይ  በጠላትነት  ለማነሳሳት እየቀሰቀሱ ፣ በህቡ ሰላዮቻቸውን አሰማርተው በኃይማኖት ሥምም  በገንዘብ እየደገፉ ፣የለውጡ  መንግሥት በሙሉ አቅሙ የተቋም ግንባታ ላይ እንዳያተኩር እያደረጉት መሆኑንን ሥናሥተውል ፤በአፍሪካ ውሰጥ መንግሥት የመሆንን አበሳ በእዝን ልቦናችን ለመመልከት አያቅተንም ። እናም ትዕግሥት ና ትብብር እንደሚያሥፈልግ የምንረዳው ሊውጡን ለመቀልበስ ፣ ያሰፈሰፉትን የውጪ ጠላቶቻችንን እና የውስጥ ቅጥረኛ ባንዳዎቻቸውን ሤራ ሥናስተውል ነው  ።

በእርግጥ የዛሬ የዳቦ ችግሩ  የበረታ ህዝብን ፣ ያለ ዳቦ ” ታገሥ..” በትለው  “ረሃብ ሥንት ቀን ይሰጣል ? “ብሎ በጥያቄ ሊያፋጥጥህ ይችላል ። አንተም ፣ ” ተደምራችሁ ፣ ተበዳድራችሁ ፣ ” አንተ ትብሥ ፤ አንቺ  ትብሺ ፡፡ ”  በመባባል ይህን ቀን አሣልፉ እንጂ ነገ ዳቦ በእርጎ ትመገባላችሁ ። ” ብትለው ፣ ( አትለውም እንጂ ) ” ምን ታሾፍብኛለህ ?! ”  ብሎ ይቀየምሃል ። ( እረኛ ቢያኮርፍ ምሰው እራቱ ይሆናል ፡፡ ብለህ እንደማተርትም እገነዘባለሁ ፡፡ )

ዛሬ በኑሮ ውድነቱ የተነሳ በአገራችን ላይ ያንጃበበውን የህልውና ሥጋት እያየን ፤ በህዝብ የዳቦ ጥያቄ ላይ ማሾፍ ከቶም አንችልም ።”  የመደመር መንገድም ወደ ዳቦው ጋር ያደርሥኸል ፡፡ ” በማለት በድሮ  አራዳ ትወራም ፣ በዜጎች ወቅታዊ ጥያቄ ላይ አናፊዝም ።

በትወራ ደረጃ ብቻ ነገሮችን በማየት  በአገራችን በመደመር ፍልሥፍና አደበሥብሰን የማናልፋቸው የህግ ፣የሰብዓዊ መብትና መሰረታዊ የተፈጥሮ መብት ጥያቄዎች እንዳሉ ፤ ይኽ ፀሐፊ ይገነዘባል ።

ሰዎች ያለመንግሥት እንኳን አሥከብረው የኖሯቸውን የየግል መብቶቻቸውን ፤ በቡድን ተደራጅተው በጎሣና በኃይማኖት ሥም  የሚጥሱ ” በላዔ ሰቦች ” በኢትዮጵያ ተፈጥረዋል ። እነዚህን ሰው በላ ግለሰቦች በዋነኝነት ለዚህ እኩይ ሥራ እንዲሰማሩ ያስገደዳቸው የሆድ ችግር መሆኑ መታወቅ አለበት ። ሆዳቸውን ተገን አድረገው ፣ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን የሚያገኙትን ዶላር በመበተን በመላው አገራችን  ያሰማሯቸውም ቋንቋን የመጨቆኛ መሳርያ አድርገው የሚሰብኩ በቀድመው ኢህአዴግ አገዘዝ ወቅት ፣ ያልተገባ ንብረት ያፈሩ ፣ ዛሬም በቃኝን የማያውቁ  የውሥጥ ሥግብግብ  ባንዶች ናቸው ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዕምነት ተቋማት ገለልተኛነት አስከ የት?   

እነዚህ ከአንድ ቋንቋ በቀር የማያውቁ ፤ የዳቦ ተገዢዎች ፣ እንደነዚህ ባንዶች እና  በሰው ደም ለማትረፍ እንደሚሯሯጡት ህሊና ቢስ የተማሩ ነገዴዎች ቢጠግቡ ኖሮ ፣ በሥለት ወገናቸውን ፣ አምሳያቸውን ምሥኪን ሰውን ሁሉ ዐይናቸውን ጨፍነው ቃላት በማይገልፀው ጭካኔ አያርዱም ነበር ። እነዚህ በሆድ ችግራቸው ሰበብ የዳቢሎስን ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች ፣  ንፁሐንን በሚዘገንን ጭካኔ ሲጨፈጭፉ ፣ አሥሮ ለማሥገረፍ፣ለማሳሰር ፣ ለማስገደልና ብቻቸውን እንደ ጅብ ለመብለት የተከለሉ ክልሎች የአደረጃጀት በህሪ የጎላ ትብብር እንዳደረገላቸው ግን መታወቅ አለበት ።  ይህንን ማንም ማሥተባበል አይችልም ። በተወካዮች ምክርቤት ሳይቀር የተንፀባረቀ ኃቅ ነው !!

 

የእኛ ሥርዓት ፣ ጎሣዊ ፣ቋንቋዊ ፣ ብሔር ብሔረሰባዊ ወዘተ ። በመሆኑ  ምክንያት ፣ እውነተኛ ዴሞክራሲን ለማስፈን እንደማይቻልም የቅርብ ጊዜው የፓርላማው ክስተት ይመሰክርልናል ፡፡

አውሮፖም ሆነ አሜሪካ ፣ ኢሲያም ሆነ አውስትራሊያ  ፤ የዴሞክራሲ ምንነት ገብቷቸው ባቋቋሙት  ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሥርዓተ መንግሥት  ውሥጥ ፤ የብዙሃን ሃሳብ የሚተገበርበት  ፣ የአናሳው ሃሳብ የሚደመጥበት ግልፅ አሰራር በአንድ አገር መንግሥት ማዋቅር ውሥጥ አለ ። አናሳዎቹ  የትም ይኑሩ የት ከቀበሌ ጀምሮ እሥከ ክልል ሊወከሉ ፣ ከቀበሌ ምክር ቤት ጀምሮ እሥከ ክልል ምክር ቤት ውክልና ሊያገኙ  ይችላሉ። ዴሞክራሲ ባልሰፈነበት ወይም የተብራራ   ትርጉሙ እንኳን በአብዛኸኛው   ህዝቡ ዘንድ ባልታወቀበት በእንደ እኛ ዐይነቱ ቋንቋ አምላኪ እና በቋንቋ ብቻ ለመበዝበዝ ግለሰቦች እንዲያመቻቸው የእግዜሩ መሬት ለእግዜሩ ሰው ሳይሆን ፤ መሬት በፖለቲካ ውሳኔ ተሸንሽኖ ፣ ለቋንቋ በተሰጠበት አገር የዴሞክራሲን ፅንሥ አሳብ በቀላሉ ማሥፈን ይከብዳል  ። መደመርንም ወደ ርዕዮት ለመቀየር አይቻልም ።

የመደመር ትወራ   ከአሳታፊነት ፣ ከህብረት ፣ ከአንድነት ፣ ሀብትን አቀናጅቶ ከመስራት  አንፃር ለዕድገት ና ለብልፅግና ጠቃሚ ሃሰብ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም ፣ መደመር  ፣ “መደመራዊ ርዕዮት ” እንዲሆን ከመደመር በተፃራሪነት የቆሙት ፣ የብልፅግና አደናቃፊዎች በወጉ ተተንትነው የርዕዮተ ዓለሙ ፀር መሆናቸው መቀመጥ ና መደመር ፣ አሰሱንም ገሰሱንም ይዞ ብልፅግና ለማምጣት እንደማይቻል  በጉልህ በመፀሐፉ መቀመጥ ነበረበት ። ነብርና ፍየል ፤ ደመት ና አይጥ ፤ ጅብና አህያ በግና ቀበሮ ፤ ወዘተ ። በአንድ ላይ በሠላም ደምሬ አኗራለሁ ማለትም አይቻልም ና ፍልሥፍናው የሚያካብታቸውን ወረቶች በግልፅ በመተንተን በቅንነት ፣ በመልካመነት ፣ በሁሉን አሳታፊነት ፣ ከሁሉም በላይ በእውነት ላይ የተመሰረተ መደመርን በተግባር ለመተርጎም የሚያሥችሉ አጠቃላይ ተንተናዎች ሊካተቱበት ይገባ ነበር ።

መደመር የፖለቲካ መሥመር ሊሆን የሚችለው አሰሱን ገሰሱን ሁሉ በመደባለቅ ፤ወይም ቀጣፊውን ከሃቀኛው እኩል መብት እንዲኖረው በማድረግ ከሆነ ፣ እንዴት ቅቡልነት ያገኛል  ? መደመር መቀነሥን ፣ ማባዛትን ፣ ማካፈልን ባላካተተበት አሠራር አሰስ  ና  ገሰሱን ሁሉ ሰብሥበን በመደመር መንገድ እንዴት ለመዝለቅ እንደምንችል በበኩሌ አይገባኝም ።

ጠ/ሚ አብይ አህመድ በመደመር መንገድ መፅሐፋቸው የገለፁትም የመንገዱን ፈታኝነት ነው እንጂ መንገዱ እንደርዕዮት የሚያገለግልበትን ንድፈ ሃሳብ አይደለም ። በበኩሌ መደመር ” ርዕዮተ ዓለማዊነቱ ” ሳይሆን ፍልሥፍናዊነቱ የጎላብኛል ።

ኢትዮጵያ በዓለም ተጨባጭ ሁኔታ ከኃያላኑ አገራት ጋር ሁሉ በጋራ ጥቅም ፣ በሰጥቶ መቀበል መርህ ተግባብታና ተሥማምታ ፣ ጥቅሞን እና ሉአላዊነቷን አሥከብራ አገርን በሚያበለፅግ አካሄድ ተግባብታ ፣ ተባብራ በመሥራት መኖር አለባት ።  ከቻይና ፣ ከሩሲያ ፣ ከጀርመን ፣ ፣ከአሜሪካ ፣ከእንግሊዝ  ፣ከፈረንሳይ ወዘተ ፤ ጋር … ፡፡ ደግሞም ፣  መደመር በውሥጡ ሁሉንም የሂሳብ ሥሌቶች አካቶ ለአገር ጠቃሚ የሆነውን በማባዛት ና በትበብር  ና በወዳጅነት ኢትዮጵያን ለማሥቀደም መጣር ነው ያለበት  እንጂ መደመርን ብቻ ይዞ ሙጭጭ ማለት አለበት ብዬ አላምንም ።

እኛ ኢትዮጵያኖች  የፈለግነውን ያህል ብንመራመር  የምንከተለው  ርዕዮት እና መንገዱ በዓለም ቅቡልነት ያለው መሆን እንደሚገባው የምንገነዘብ ነንና ከዓለም ህዝብ ያፈነገጠ  ርእዮት  ሊኖረን ከቶም አይችልም ።

የዓለም አካል የሆኑት ፣ ቻይና ና ሩሲያ የሶሻሊዝምን እና የካፒታሊዝምን ርዕዮት ቀይጠው ነው ፣ ከካፒታሊዝም አገሮች ጋር ተፎካካሪ ሆነው መዝለቅ የቻሉት ። የእኛ ጠ/ሚ የነበረው አቶ  መለሥ ዜናዊ ግን ፣” ኢትዮጵያን አፍርሼ ፣ እንደ ካርታ በውዤ  ፣ በጎሣ ና በቋንቋ ሸንሺኜ ፣ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ዘላለሜን አውራ ፖርቲ ሆኜ  እገዛለሁ ፡፡ ” ብሎ  ፣ በቅዠት የተሞላ ህልም በማለሙ ነው ፣ ለሥልጣን ያበቃውን ወያኔንን በአፍጢሙ እንዲደፋ ያደረገው ።

በዚህ በ21 ኛው ክ/ዘ አውሮፖ ሳልሄድ ፣አሜሪካ ሳልሄድ ፣ ቻይና ሳልሄድ ፣ ወዘተ ሳልሄድ እቤቴ ቁጭ ብዬ በኢንተርኔት ሁሉንም አገሮች መጎብኘት ብቻ ሳይሆን ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ ፣እና ኢኮኖሚያዊ እድገታቸውን በቅጡ ለመገንዘብ እችላለሁ ።  የዓለምን እውነት እያየው ፣ ለብልፅግና የበቁበትን መንገድ እየተረዳሁም በቅይጥ ፖለቲካዊ ርዕዮት አገር እንድትመራ በማድረግ ና ፣ በመላው አገሬ  ሰላምን ለማሥፈን ፣ በዘር ፣ በቋንቋና በጎሣ ላይ ያልተመሠረተ  ጠንካራ የመከላከያ ና የፖሊሥ ኃይል  አዋቅሬ ፣ አገሬን ከመከፋፈልና ከመገነጣጠል አድናታለሁ እንጂ ፤መለሥ ዜናዊ የነበረውን ገነጣጣይ ሥርዓት እንዴት ይደመር እላለሁ  ?

 

የእኛ ሥርዓት ፣ ጎሣዊ ፣ቋንቋዊ ፣ ብሔር ብሔረሰባዊ ወዘተ ። በመሆኑ  ምክንያት ፣ እውነተኛ ዴሞክራሲን ለማስፈን አይቻልም ።

አውሮፖም ሆነ አሜሪካ ፣ ኢሲያም ሆነ አውስትራሊያ  ፤ የዴሞክራሲ ምንነት ገብቷቸው ባቋቋሙት  ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሥርዓተ መንግሥት  ውሥጥ ፤ የብዙሃን ሃሳብ የሚተገበርበት  ፣ የአናሳው ሃሳብ የሚደመጥበት ግልፅ አሰራር በአንድ መንግሥት አሥተዳደር ውሥጥ አለ ። አናሳዎቹ  የትም ይኑሩ የት ከቀበሌ ጀምሮ እሥከ ክልል ሊወከሉ ፣ ከቀበሌ ምክር ቤት ጀምሮ እሥከ ክልል ምክር ቤት ውክልና ሊያገኙ  ይችላሉ። ዴሞክራሲ ባልሰፈነበት ወይም የተብራራ   ትርጉሙ እንኳን በአብዛኸኛው   ህዝቡ ዘንድ ባልታወቀበት በእንደእኛ ዐይነቱ ቋንቋ አምላኪ እና በቋንቋ ብቻ ለመበዝበዝ ግለሰቦች እንዲያመቻቸው ” የእግዜሩ መሬት ” ተሸንሽኖ በተሰጠበት አገር የዴሞክራሲን ፅንሥ አሳብ በቀላሉ ማሥፈን ይከብዳል  ። መደመርንም ወደ ርዕዮት ለመቀየር አይቻልም ።

በበኩሌ  መደመር የሚገባኝ እዚህ ላይ ነው ።  ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር የሚሉት ተረትም እውን የሚሆነው የኢትዮጵያ ጎሣዎች ሣይከፋፋሉ በኢትዮጵያዊነታቸው ኮርተው በጋራ ሲቆሙ ብቻ እንደሆነ በፅኑ አምናለሁ።   የለውጥ ኃይሉ የመደመር መንገድም በዓለም ህዝብ ቅቡልነት ካለው  ከፍትህ ፣ ከዴሞክራሲ ከነፃነት ና ከእኩልነት አንፃር ቢቃኝ የተሻለ ይመሥለኛል ።

የፅሑፌ መቋጫ

ከላይ በመግቢያዬ እንደጠቀስኩት የአንድ አገር መንግስት በህግ ቅቡልነት ያለው ፣ ከፈጣሪ በታች ፣በህግ አግባብ የተሰጠ ” የሥልጣን ተፈጥሮ ” እንዳለው ሁሉ ፤ እያንዳንዱ ዜጋም ከፈጣሪ የተሰጠው ተፈጥሯዊ መብት እንዳለው መዘንጋት የለበትም ፡፡ ይኽንን መብቱንም ራሱ ሰው ፤ያቋቋመው መንግስት ፤ ሊያከብርለትና ሊያስከብርለት ይገባዋል ፡፡ የዜጎችን መብት ያለማስጠበቅ መንግስትን  ከባድ ዋጋ  እንደሚያሥከፍለው ከእኛ አገር ዜጋ በላይ የሚያቅ  ያለ አይመስለኝም ፡፡ የሀገሬ መንግሥት ይህንን በቅጡ  ይረዳል ብዬ አስባለሁ ፡፡

በዜጎች መብት ሥም ፤ ሁሉን ቻይ በሆነው ፈጣሪ ሥም ፤ ዛሬ በአገራችን ፣ በውስጥ እና በውጪ ፣ በመሸጉ የአገራችን  ልማት ፀሮችና ፣ ችጋርና ችግር ፈልፋዮች ፤ የተሰጠን አዲስ አጀንዳ ፤ በበኩሌ በፈጣሪ በሚያሾፉ ሰዎች እንጂ እምነት ባላቸው ዜጎቻችን የሚተገበር እንዳልሆነ አምናለሁ ፡፡ እናም ፤ ይህ በፈጣሪ ላይ ሹፈት ( ቤተ እምነትን ማቃጠል ) ነገ ከፈጣሪ ፣ የማንቋቋመውን ቁጣ ማስከተሉ አይቀርምና  ፤ሁላችንም ወደ ቀልባችን ተመልሰን  ፈጣሪያችን ቁጣውን እንዲመልሰው ፤  በየእምነታችን ብንፀልይ መልካም ይመስለኛል ፡፡   ደግሞም  ማንኛውም ሰው ሲወለድ አንድ ቀን እንደሚሞት እንጂ አድጎ ና ጎልምሶ ንጉሥ ወይም ለማኝ እንደሚሆን በእርግጠኝነት ለማወቅ አይችልም እና ዛሬ የደላንም ፣ ያለንበትን የአሁን ድሎት ና ምቾታችንን ብቻ ሳይሆን ፣ ንጉሥ እንኳ ሆነን ተንቀባረን  ብንኖር ፤ በሞት ይህቺን ዓለም ተሰናብተን እረቃናችንን ወደዚህ ዓለም እንደመጣን እርቃናችንን ወደአፈራችን እንደመንመለስ ፤ ለአፍታ እንኳ በማስታወስ ፤ የደነደነውን ልባችንን ማለስለስ ፤ ለሻከረው ልባችን ይጠቅመናል ብዬ አምናለሁ ። ዛሬ በመንግስት  አመራር ላይ ያሉም ፣ የመንግስት ሹመኞች በሙሉ ፤ከሞት በኋላ ላለው  ለገዛ ታሪካቸውና እና ለመጪው አገር ተረካቢ ተውልድ የመጨነቅ ግዴታ እንደለባቸውም በመገንዘብ ከህግ እና ከእውነት ጎን በመቆም ይህንን አጥፊ የሞት አጀንዳ ለመቀልበስ ያለረፍት መታገል ይጠበቅባቸዋል ፡፡ ከዚህ አንፃር የመንግስት ሹመኞች ሁሉ ፤ ሰው ሁሉ በተፈጥሮ እኩል መሆኑን እና ተፈጥሮ ደግሞ  ለማንም እንደማታዳላ ከወዲሁ ቢረዱ ፣ ለነገ እውነተኛ ለውጥ ይረዳቸዋል ና ሳይረፍድባቸው ከራሳቸው ጋር ቢታረቁ ና ለአገር ተረካቢው ተውልድ በወጉ ቢያስቡ መልካም ነው ፡፡

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share