May 12, 2022
3 mins read

የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ በክንዱ ቀልብሶ ህልውናውን ያረጋግጣል – ፋኖ

Fanoየአማራን ፋኖ በመለያየት እና ለስርዓቱ ይመቹኛል ያሉትን በመሸለም የፋኖን አንድነት ለመበታተን የሚደረገውን ሴ*ራ ፍጹም አጥብቀን እንቃወማለን!!!
ሸዋ ፋኖ ግንቦት 3/2014 ዓ.ም
እንደሚታወቀው የአማራ ህዝብ ካልተበታተነ እና አቅመ ቢስ ካልሆነ የአማራን ህዝብ ካላ*ጠፋሁ በማለት ህወሃት የአማራ ክልልን በወረረበት እና ጦርነት ባወጀበት ሰዓት መንግስት ይህን የህለውና አደጋ ለመመከት ክተት ባወጀበት ሰዓት ፋኖ ቅሌን ጨርቄን ሳይል በመሰለፍ በተለያዩ ግንባሮች ብዙ ገድ*ሎች*ን ፈጽሟል።
ማርከህ ታጠቅ በሚለው መመርያ
መሰረትም ማርኳል ታጥቋል
በዚህ የህልውና ዘመቻ ሂደት ውስጥም ጓዶቹ ተሰውተዋል።
ይሁን እና ሃገሩቷን እያስተዳደርኩ ነው የሚለው ስርዓት ይህንን ትጥቅ ለማስፈታት ረጅም ርቀት እየተጓዘ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ የተወሰኑ የፋኖ አመራሮችን በመምረጥ እውቅና እና ሽልማት የመስጠት ሂደት አድርጓል።
የሸዋ ፋኖ ይህን ፋኖን የመበታተን እና እውቅና የመስጠት ሂደትን የማያምንበት እና የሚቃወመው መሆኑን አስረግጠን እናሳውቃለን።
በመሆኑም የሸዋ ፋኖ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫዎች አውጥቷል።
1) የህልውና ዘመቻው ባልተጠናቀቀበበትና ትህ*ነግ መራሹ ጽን*ፈኛ ሃይል በተለያዩ የአማራ ግዛቶች ላይ ጦርነት ባወጀበት ሰዓት ጦር*ነቱ እንደተጠናቀቀ አድርጎ የሚደረገውን አካሂድ በፍጹም የማንቀበለው ነው።
2) ፋኖ የህዝብ ጠበቃ እና አገልጋይ ሆኖ ሳለ ህይወ*ቱን ሰው*ቶ የታጠቀውን ትጥቅ ለማስፈታት የሚሄደውን ሂደት እንዲቆም እናሳስባለን።
3) የአማራ ህዝብ ከምን ጊዜውም በላይ ባራት አቅጣጫ ተከቦ የህልውና አ*ደጋ ተጋር*ጦበታል ስለሆነም ለሁለንተናዊ ትግ*ል ራሱን እንዲያዘጋጅ እና ከፋኖ ጎን እንዲቆም ጥሪ እናስተላልፋለን!!!
4) የአማራ ህዝብ ህልውና ባልተረጋገጠበር ሁኔታ ሸዋ ፋኖ ምንም፡አይት እውቅና እና ሽልማት የማይፈልግ መሆኑን እናሳውቃለንየፋኖ ሽልማቱ የአማራ ህዝብ ነፃነት መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን!!!
የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ በክንዱ ቀልብሶ ህልውናውን ያረጋግጣል።
ድል ለሰፊው አማራ ህዝብ ይሁን!!!
ሸዋ ፋኖ ግንቦት 3/2014
ደብረብርሃን!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop