መንግስት ታሞ ደክሞ ተኝቷል ባልጋ ላይ፤
ወዴት እንሄዳለን ሞት ሽረቱን ሳናይ።
መንግስት ታሟል አሉ ሊያናጋው ስራቱን፤
ማንም አያውቀውም ሞትና ሽረቱን።
ሞትማ ቋሚ ነው ጥንትም የነበረ፤
ሳይሰሩ መሞት ነው ከሞት የመረረ፤
ትውልድ ያሳፈረ።
ከእውነት ጋር ተጣልቶ መናገር ስለእውነት፤
ተንኮልን አርግዞ በቅጥፈት መዋተት፤
ክፉው ሞት እሱ ነው ሰው ሳይሆኑ መሞት።
“In the relations of week government and a rebellious people there comes a time when every act of the authorities exasperates the masses, and every refusal to act excites their contempt”
John Reed.
Does it seem familiar?
የህዝብን ብሶት የማይሰማ፤ ችግሩን የማይረዳ መንግስት ከህዝብ በተቃርኖ የቆመ በመሆኑ እድሜው አጭር ነው። ምንም የህዝብ ጥያቄ ሳይመልስ እለተ ሞቱን ይጠባበቃል።
“I have no religion, and at times I wish all religions at the bottom of the sea. He is a weak ruler who needs religion to uphold his government; it is as if he would catch his people in a trap.”
Mustafa Kemal Ataturk
No pun intended here. እምነት የግል ሃገር የጋራ ይስማማኛል።
የኢትዮጵ ታሪክ አነሰም በዛም የዘመነ መሳፍንት ታሪክ። ነው። ሃገራችን በሰላም ከኖረችበት የሚበልጠው የርስበርስ ጦርነት ያሳለፈችው ታሪኳ ነው። በታሪክ የሚታወቀው ዘመነ መሳፍንት ከእያሱ ሁልተኛ ( 1730.) እስከ ቴውድሮስ ሁለተኛ( 1855) ከመቶ አመት በላይ የወሰደ እልቂትና ግርግር ዘመን ይሁን እንጂ ከዚያ በፊትም ሰላም ነበር ማለት አይደለም።
ዛሬም ከዚያ የተለየ ታሪካዊ አጋጣሚ ላይ አይደለንም። ጉዟችን የሚያሳየው ያን የጥንቱን ጎዳና ነው። በያካባቢው ልዑላን እንዳሽቸው የሚያገላብጧቸውን ክልሎች ተቀራምተው ይዘዋል። ከድሮው የሚለዩት በህግ የተከፋፈሉት መሆኑ ብቻ ነው።
እንድዘመነ መሳፍንቱ ዛሬም አትድረሱብን ይህ የኛ ድርሻ ነው የሚሉን የዘውግ ልዑላን ተፈጥረዋል።
የሌለው የኢትዮጵዊ የሆነ መንግስት ነው።
የኦሮሞ ተስፋፊ መንግስት ተመስርቷል፤
የትግሬ እብሪተኛ መንግስት ተመስርቶ ወራሪ ሆኖ አገር ያራውጣል፤
እንደነገሩ የሆነ የአማራ መንግስትም አለ፤
የሲዳማ፤ የጋምቤል። የሶማሊ፤ የአፋር፤ የደቡብ የቤኔሻንጉል ወዘተ ትናንሽ መንግስታት ተፈልፍለዋል፤ ያውም በህግ።
የሌልው የኢትዮጵያ የሆነ መንግስት ነው።
የሌልው የህዝብ መንግስት ነው።
ያለው በጸና ታሞ ያልጋ ቁራኛ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ነኝ የሚለው መንግስት ልክ እንደዘመን መሳፍንቱ ወቅት እንደነበሩት የስም ንጉሶች ከአልጋው ላይ አለ፤ በጠና እንደታመመ ነው። የብዙወች ጥያቄም ከመዳን ወይም ከመሞቱ ላይ ነው።
ከታሪካችን ከተነሳን መዳኛ እንደሌለው በሃዘንም ቢሆን፤ በድንጋጤም ቢሆን እንገነዘባለን። የዘመነ መሳፍንቱን ያህል እረጂም ጌዜ የሚወስድም አይደልም። ይህም ማለት ከአልጋ ቁራንኛነቱ በሞት ከታከመም በሽረት የሚገላገልበት ጊዜ ብዙ አይሆንም ማለት ነው። የዘመኑ የየአካባቢው ባለጊዜውች በእብሪት ተወጥረው ቅራኔውችን እየወጠሯቸው ስለሆነ ብዙ ጊዜ አይወስድም። አሁንም ያለንበት በአሁኑ ዘመነ ግርግር( ዘመነ ባለጌዜ) የታሪክ ወቅት ነው።
የድሮውን የዘመነ መሳፍንት አመጣጥና አፈጻጸም ለማወቅ ታሪክ ማንበቡ መልካም ቢሆንም አሁን በተግባር እያየነው ነውና ይህን ወደ ኋላ መልሶ ማየት ያን የጥንቱን አስቀያሜ ታሪካዊ እውነታ ያሳየናል። በ13ኛው ክፍለዘመን ብቻ ከሰባት ያላነሱ ነገስታት ከአንድ አመት ያላለፈ ንግስና ነበራቸው፤ የትንቅንቅ ዘመን፤ ታሪካችን ነው።
በዘመነ መሳፍንት ዋዜማ ከአስራስምንቱ ነገስታት አስሩ ካምስት አመት በታች ነው በዙፋናቸው የቆዩት፤ የትግል ዘመን፤ የትንቅንቅ ዘመን፤ ታሪካችን ነው።
ከዚያ የቁልቁለት ጉዞው ተፋጠነ፤ ዘመነ መሳፍንት ተወለደ። ለስሙ እንዳዛሬ ንጉሳን በዙፋናቸው ላይ ይኑሩ እንጂ የሚያሽከረክሯቸው የያካባቢው ልዑላን ነበሩ። ዘሬ የምናየውን ክስተት ይመስላል.።
ዛሬም ልክ እንደዚያኛው የአሁንም ዘመን ባልጌዜወች ሰወች ሲገደሉ የሚቀጣ ወይም የሚያስቆም መንግስት የለም። ይህ አቅም በማጣትም ይሁን በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረት ይሁን ውጤቱ አንድ ነው የሰው ልጆች ሲያልቁ ማየት።
የአሁኑ ዘመነ ባልጊዜውች ከድሮው የሚለዩት እነሱን ያልመሰላቸውንም ማሳደድ የኛ ነው ከሚሉት የትርክት ግዛት ማስወጣትን መጨመሩ ነው፤ የድሮው በሰላም መገዛትን እንጂ የማንንም ደም እንድውሻ የማሽተት ፍላጎት አልነበረውም። ይህ የአሁኑ ባለጊዜወች ያሻሻሉት መስፈርት ነው።
የቀድሞው ዘመነ መሳፍንት የጎንደር ንጉሳን ማዕከሉ ላይ ተከበው ቀስበብቀስ ነው የከሰሙት። የሚናገሩት ሳይሰማ የፈረዱት ሳይጸና አቅመ ቢስ ሆነው ነው ኢትዮጵያን ብዙ ያካባቢ ልዑላን የተቀራመቷት።
የዛሬውም አዲስ አበባን ማዕከል አድርጎ ከመንግስት አልጋ ላይ ይቀመጥ እንጂ አልጋው ለጸና ህመሙ ማስታመሚይ ነው፤የማዕከላዊ/ኢትዮጵያዊ መንግስትነት እንድጥንቱ ሁሉ አሁንም እየከሰመ ነው። ያለውን ሃይል መጠቀም የፈራ ወይም ያልፈቀድ መንግስት ህዝብ ሲፈናቀልና ሲገድል እያየ ደብቁኝ የሚል መንግስት የታመመ መንግስት ነው። ወደ ገደሉ አፋፍ ላይ የደረስ አቅመ ቢስ ታማሚ መንግስት ነው። ሞቱ መቃረቡን ካላየ አስቀድሞ የመሞቱ ምልክት ነው።
እርግጥ ነው በአልጋ ቁራኛ ያለ ይሞታል ወይም ፈጣሪው ምህረት ካደረገለት ሊድን ይችላል፤ ለመሞት ምንም ማድረግ የለበትም በሽታው በቂ ነውና። ለመዳን ግን ትልቅ ህክምና ያስፈልገዋል። ማረኝ ብቻ በቂ አይደለም፤ ምህረት የሚያመጡ መድሃኒቶችን ማፈላለግ የግድ ይላል። እንዲህ በጽኑ የታመመ በሽተኛ በመጀመሪያ የበሽታውን መንሰኤ መረዳት ይኖርበታል።
እውነተኝነትን ማጣት አንዱ በሽታው ነው፤
አድሎአዊነቱ ሌላው የበሽታው አካል ነው፤
ያለውን አቅም በሚገባ ተረድቶ ለሰላም ጦሩን አሸናፊ የማድረግ ወኔ ቢስነት ሌላው በሽታው ነው፤ ያሸነፈን ጦር ተሸናፊ የሚያደርግ በሽታ የተጠናወተው ነው።
ለመዳን በቅድሚያ በሽታውን ማወቅ ያስፈልገዋል፤ መራራውን ክኒን ለመዋጥም ቆራጥ መሆን አማርጭ የሌለው የፈውሱ አንድ አካል ነው።
ታሪክ ያልመከረውን፤ ያላስተማረውን መከራ ይመክረዋል ግን ያኔ ነገሮች ዘግይተዋል ሁሉም ቀና ጎዳናዎች ተዘግተዋል፤ ተበላሽተዋል።