March 25, 2022
2 mins read

መረጃ ትኩረት: የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች!

277156749 548223840202209 4980340313180757304 n

277156749 548223840202209 4980340313180757304 nይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት፣ በአዲስ አበባ ካሉት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች መካከል በአንዱ በህገ ወጥ መንገድ ተሰቅሎ የሚገኘው የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ ነው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ውስጥ ባሉ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች ጠዋት ጠዋት ተማሪዎች ተሰባስበው መዝሙር በሚያሰሙበት ጊዜ፣በአንድ ረድፍ የኦሮሞ ተማሪዎች ከኦሮሚያ ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቆመው የኦሮሚያ ክልል መዝሙርን ፣ በሌላ ረድፍ ሌሎች ተማሪዎች ከኢትዮጵያ ፊት ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቆመው የኢትዮጵያን ብሔራዊ መዝሙርን እየዘመሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ አካሄድ ፍፁም አደገኛ እና ሕገ ወጥ መሆኑን አብዛኛው የከተማዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡

እንደሚታወቀው፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ከአስተሳሰቡና ከፍላጎቱ ውጭ የተጫነበት የከተማዋ አስተዳደር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየሄደበት ያለው መንገድ በእጅጉ እያሳሰበው ይገኛል፡፡ በተለይ የገዥው ፓርቲ ከህወሓት ጋር የመታረቅ ተስፋው እየለመለመ በሄደ ቁጥር፣ በከተማዋ ነዋሪ ላይ የሚያደርገው ዘረኛ ተፅዕኖ እየበረታ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ዋነኛ መገለጫዎች መካከል፣ በአዲስ አበባ የመንግሥት ት/ቤቶች የኦሮሚያ ክልል ባንዲራን መስቀል፣ ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ህገ-ወጥ ነው ብሎ ክልከላ ማድረግ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችን እንደ ጠላት በማየት በአፈሳ ለጅምላ እስር መዳረግ፣ በከተማዋ መስተዳድር ውስጥ ያለው ዘረኝነት መባባስ ይገኙበታል፡፡

#ኢትዮጵያ

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
·

3 Comments

  1. ታዲያ ምን አለበት በአገሩ በኢትዮጵያ ነዉ የተሰቀለው፤ አንተ የራስህን ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ ትሰቅል የለ እንዴ?

  2. ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ are you scared for your own safety or you are pretending being thoughtful to residents of addisababa who belong to amhara tribe and support fano genociders ?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

169968
Previous Story

የወያኔ ህወሓት ጦር የፈጸመው የአስገድዶ መድፈርና ጭፍጨፋ ወንጀል

hr 6600 1
Next Story

የፓትርያርኩ HR 6600 ላይ ያነጣጠረው ሴራና የጋዜጠኛ አርአያ ያልተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች በስለ ሀገር

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop