March 21, 2022
32 mins read

የሂትለርና ሙሶሊኒ መጨረሻ ለአቢይና ሸመልስም አይቀርላቸውም!!

ይነጋል በላቸው

“የ‹ብፁዕ አባታችንን‹ አስከሬን ለመሸኘት በሻይ ሰዓት አንድ ክርስቲያን መሳይ፣ ሁለት እስላሞች ሆነን ሄደን ነበር፡፡ ከመሃላችን ኦርቶዶክስ አልነበረም፡፡” በእግዜር እጅ የተያዘው ወፈፌው ጠ/ሚኒስትር ከተናገረውና በዩቲዩብ ሲንሸራሽር ካዳመጥኩት የተወሰደ ንግግር ነው፡፡ አዎ፣ ዘበናይ ከሆኑ አይቀር እንደዚህ ነው፡፡ በሻህ ዘለሌ አቢይ ግራኝ አህመድ በስድብና በዘለፋ የማያጥረገርገው ሰው የለም፡፡ ጥጋብና ዕብሪት አናቱ ላይ ወጥቶ የሚጨፍርበት እንደአቢይ አህመድ ያለ ማንም የለም፡፡ የፓርላማ አባላቱንማ ከውሻና ድመቱም አሳንሶ ሳያያቸው አይቀርም፡፡ እንዴት እንደሚጫወትባቸው ወደጽሑፍ በመለስነውና ራሱን በራሱ ለማስመረጥ ባደረገው አሳፋሪ የምርጫ ሂደት ወረድ ብለን መረዳት እንችላለን፡፡ የኢትዮጵያ መጨረሻ እንዲህ መሆኑ ያሳዝናል፡፡ በነአክሊሉ ሀብተ ወልድ ወንበር ላይ እንዲህ ያለ የሰው ልክ የማያውቅ ስድ አደግ መደዴ ሲቀመጥበት እንደማየት ትልቅ ውርደት የለም፡፡ ታዛቢ ትልቅ ሰው አለመኖሩ በጄ፡፡ ለካንስ ቀደምት አባቶች “ከሰው መርጦ ለሹመት፣ ከእንጨት መርጦ ለታቦት” ይሉ የነበረው እንደአቢይ ያለ ቅሌታም ትንንሽ የሥልጣን ቦታዎችንም ቢሆን ከያዘ አንድ ነገር እንዴት ሊበለሻሽ እንደሚችል ለመጠቆም ኖሯል፡፡

shimeles and abiy killers“ካላባዱ ወይም ካልነገዱ የልብ አይገኝም” ይባላል፡፡ እውነት ነው፡፡ አንድ ሰው ካላበደ ያሻውን አያደርግም ወይም አይናገርም፡፡ በየግላችን የምናስባቸው፣ የምንሆናቸውና የምናደርጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፤ አንዳንዶቹን በአደባባይ ብናደርጋቸው በዕብድነት ያስፈርጁናል፡፡ ለምሣሌ – ምሣህን በሣህን ይዘህም ሆነ አስፋልቱ ላይ ደፍተህ ቸርቺል ጎዳና መሀል አስፋልቱ ላይ ቁጭ ብለህ አትበላም፡፡ መብላትህ በራሱ ግን አስፈላጊ ነገር እንጂ የሚቃወሙት አይደለም፡፡ አውራ ጎዳና ላይም አትጸዳዳም – ካላበድክ በስተቀር፤ መጸዳዳት ግን በቦታውና በጊዜው ሲሆን አስፈላጊና ግዴታም ነው፡፡ ስለሰውም ሆነ ስለተለያዩ ጉዳዮች በውስጣችን የሚቀሩ ብዙ የምናስባቸው ነገሮች አሉ፤ ነገር ግን ወደውጪ የምናወጣቸው ጥቂቶቹንና በሥርዓትና በጨዋ ደምብ የተዋዙትን ነው፡፡ ሁሉን የምናስበውን ነገር እንዘርግፈው ብንል ከማንም ጋር አንኗኗርም፤ ጓደኛም ሆነ የትዳርና የፍቅር አጋርም አይኖረንም፡፡ አንድ ሰው በሌሊት የሚቃዥ ከሆነ ብቻ ነው የውስጡን ድብቅ ምሥጢር የሚያወጣው – እንዲያም የሚሆነው ይሉኝታንና ሀፍረትን የሚያውቀው ሃቅን ደባቂው ኮንሸስ ማይንድ እውነትን እንዳለች አፍረጥርጦ በሚገልጸው በእውነተኛው የሰብኮንሸስ ማይንድ ተበልጦ ሲገኝ ነው – በፍሩዲያን አነጋገር፡፡ ለምሣሌ ከኤርምያስ ጋር የተዳራች ሚስት ከባሏ ከዳንኤል ጋር ተኝታ በቅዠት “ውይ ኤርሚ ቀስ …. ቀስ ….እንጂ … አሳመምከኝ እኮ ….” ልትል ትችላለች፡፡ ባለጌ አትበለኝ፡፡ እውነትን መናገር አያስወቅስምና ባለጌህን እዚያው ፈልግ፡፡ ያኔ ታዲያ ዳኒ ካልተኛና ይህን ጉድ ከሰማ ምን ሊከሰት እንደሚችል ዳንኤሎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎቻችንም እናስበው፡፡ በዚህን ዓይነቱ መጥፎ ጠባይ የሚዋረዱ ብዙዎች ናቸው፤ አያድርስ በል ይልቁንየስ፡፡ ይህን ዓይነት ጠማማ ጠባይ ቤተ መንግሥት ገብቶ በእንቅልፍ ሳይሆን በእውን ሲተገበር ይታይህ እንግዲህ – “አገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል”፤ ሀገር ስትጃጃ አቢይን የመሰለ ወላድ አትይህ ዓይነት ጠባየ ብልሹ ይወለድና በትረ መንግሥትን ይጨብጣል – ከዚያም ሀገር ምስቅልቅሏ ይወጣል፡፡ ተደጋግመው የሚጠቀሱ እንደነጄኔራል አላዲን፣ እንደነ ኢዲያሚን ዳዳ ያሉ የእውነተኛው ዓለምና የምናቡ ዓለም ዕብድ አምባገነኖችን እዚህ ላይ ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ ዓለማችን በርካታ አምባገነኖችን ብታውቅም የአቢይ ግን ከማንም ጋር የሚወዳደር አይመስለኝም፡፡ የአፍ ልጓም(ፍሬን) የሚባል በጭራሽ የለውም እኮ!!

ከፍ ሲል እንደጠቆምኩት አቢይም ልክ እንደዚህች ዳኒ ጋር ተኝታ ኤርሚን እንደጠራችው ባለጌ ሴትዮ ነው፡፡ ጨርቁን አልጣለም እንጂ ለይቶለት ማበዱ ሃቅ ስለሆነ ምን መናገርና ምን አለመናገር እንዳላበት እንኳን አያውቅም፡፡ ሰው አላወቀለትም እንጂ የሥነ ልቦናና የሥነ አእምሮ ህክምና የሚያስፈልገው ሕጻን አይሉት ጎልማሣ ሁለ ነገሩ የተደበላለቀበት “ሰው” ነው፡፡ አጠገቡ ያሉትም ቢሆኑ ብዙዎቹ ይህ ዓይነቱ ህክምና ያስፈልፈጋቸዋል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ አጃቢዎቹ ከማጨብጨብ ውጪ የሚያውቁት ሌላ ነገር የለም፡፡ እንቅልፍ ይዟቸው እንኳን ጭብጨባ ካነቃቸው ተደናግጠው ያጨበጭባሉ፡፡ የጭብጨባው መንስኤ የነሱ መወገዝና መወቀስ ሊሆን ቢችል ለነሱ ደንታቸው አይደለም፡፡ ሀገር በነዚህ ሙታን  ስትመራ ማየት ያሳዝናል፤ ያ. ን. ገ. በ. ግ. ባል፡፡

አቢይ ከፍ ሲል የተናገረውን ብንፈትሸው ብዙ ይናገራል፡፡ ሰዎቹ ማን ሊሆኑ እንደሚችሉ ገምት ብባል ምናልባት ደመቀ መኮንን፣ አደም ፋራህና እርሱ ራሱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አንድ ክርስቲያን መሳይ ያለው አንድም ራሱን ወይም ራሱን ካልሆነ ደመቀን ነው፡፡ ሁለት እስላሞች ያለው አንድም ራሱን ወይንም ራሱን ካልሆነ ደመቀንና አደምን ሊሆን ይችላል፡፡ ሰውዬው ከባሕርይ አባቱ ከመለስ የበለጠ አሽሙረኛና – ለቃል አጠቃቀሜ ይቅርታ ይደረግልኝና – የሴተኛ አዳሪ ዓይነት ጠባይ ያለው በመሆኑ ንግግሩ ሁሉ ሽርደዳ ይበዛዋል፡፡ ዋናው መልእክቱ ግን ኦርቶዶክስን እንዲያጠፋ ለላኩት የሴቴኔዝም እምነት ተከታዮች ኦርቶዶክስን እያጠፋላቸው መሆኑን ለሴቴኒስቶቹ ወይንም ለሉሲፈራውያን ጌቶቹ አስረግጦ መናገሩ ነው፡፡ ክርስቲያን መሳይ ያለው ራሱን ከሆነም ከአንድ እኔ ከማውቀው የቀደመ ትንቢት ጋር ስለሚገጥም መጥፎ አይደለም፡፡ ክርስቲያን ነኝ እያለ በውስጡ ግን የሌላ እምነት ተከታይ መሆኑን እውነተኛ ማንነቱን ማወቅ ለሚፈልጉ ኅቡዓን ድርጅቶች እያሳወቀ ነው፡፡ ወንድሜ – የዚህ ዘመን ሀብትና ሥልጣን ነፍስህን ለሆነ አጋንንታዊ ኃይል ገብረህ እንጂ እንዲሁ በነጻ አታገኝም፡፡  አቢይም ከዚህ ዓይነቱ የወቅቱ ዓለማቀፋዊ ፋሽን ውጪ ሊሆን አይችልምና ከርሱ ጽድቅን መጠበቅ፣ ከርሱ መልካምነትን መሻት ሞኝነት ነው፡፡ ለነፃነትህ በምትችለው ታገል ይልቁንስ፡፡

በመሠረቱ አንድ የሀገር መሪ የፈለገውን ዓይነት ሃይማኖት የመከተል መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ መብት የሌለው ግን የሚመራውን ሕዝብ በጎሣና በሃይማኖት፣ በቀለምና በዘር ሐረግ እየከፋፈለ፣ ነባር የአያት ቅድመ አያት ድምበሮችን እየጣሰ መሬት በመሸንሸንና ያንዱን ወዳንዱ በማጠቃለል ወንድምና ወንድምን ማፋጀትና ንጹሓንን ማፈናቀል ነው፡፡ እንጂ በ120 ሚሊዮን ሕዝብ መካከል አንድ ሃይማኖት፣ አንድ ባህል፣ አንድ ቋንቋ  …. ብቻ ይሰልጥን አይባልም፡፡ ቋንቋን ጨምሮ ሁሉንም ዜጋ የሚያገለግሉ ማኅበረሰብኣዊ ቁሣዊና አእምሯዊ ዕሤቶችን በጋራ ማዳበሩ ግን የነበረና ያለ በመሆኑ ሊበረታታ እንጂ ሊነቀፍ እንደማይገባው በዚህ አጋጣሚ ማስታወስ እወዳለሁ፤ ከዚህ አኳያ በዐዋጅና በጉልበት ሳይሆን በነባራዊ ታሪካዊ ሁኔታዎች ሳቢያ የወልነት ማዕረግ የተሰጣቸውን አማርኛን የመሰሉ የጋራ ንብረቶችን መንከባከብና ማሳደግ ሲገባ ማጥፋት ወይንም ለማጥፋት መሞከር ራስን እንደማጥፋት ነውና ሊታሰብበት ይገባል፡፡

ከዚህ ነጥብ አንጻር የኦሮሙማ አማራንና አማርኛን የማጥፋት ዘመቻ ምን ያህል ሊሳካ እንደሚችል በቅርቡ የምናየው ይሆናል፡፡ የኔ ሥጋት ግን ያላሰቡትን ነገር እንዳያጠፉ ነው፤ በ”ከወፈሩ ሰው አይፈሩ” ዘመን አመጣሽ የዱባ ጥጋብ ተገፋፍተው እየፈጸሙት የሚገኙት ግፍና በደል ሁሉ ወደነሱ እንደሚዞር ቅንጣት አንጠራጠር፡፡ አማራዊነት (አማራነት አላልኩም) የያዘ ይዞት እንጂ እንኳንስ ለኢትዮጵያ ለአፍሪካም የሚበቃ እምቅ ኃይልና መለኮታዊ ፀጋ አለው፤ ያም በቅርብ ይታያል፡፡ ኢትዮጵያን በማጥፋትና በማልማት ረገድ የማን ሚና የጎላ እንደሆነ በተለይ ያለፉት 50 ዓመታት በቂ ምሥክር ናቸው፡፡ አማራነት የቅርብ ጊዜ ክስተት ነው፤ መሬት ያልያዘና በጥቂቶች የሚቀነቀን፡፡ አማራዊነት ግን ከኢትዮጵያዊነት ጋር የተሰፋ ትልቅ ሀገራዊ ራዕይ ነው፡፡ የዚያ ራዕይ እምብርት ደግሞ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ነው፡፡ አማራ ጠላቶቹን ማሸነፍ ያቃተውም ለዚህ ነው – አልጠብም ማለቱ የወለደው ስፋቱ ያመጣበት ችግር ኅልውናውን ሳይቀር ተፈታትኖበታል፡፡ ይህ ሁኔታ ግን ከእንግዲህ ብዙም አይቀጥልም፡፡ ሠርገው የገቡበትን ብአዴንን የመሰሉ እባቦች በቅርቡ ይመነጥራቸዋል፡፡ ከኢትዮጵያዊነትና ከኢትዮጵያ ውጪ የኔ የሚለው ነገር ስለሌለው እርሱን ከሚመስሉ ከኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ውጪ የሚሸጎጡበት የዘርና የጎጥ መደበቂያ ዋሻ ከሌላቸው ሌሎች ወገኖቹ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን ይታደጋታል – አማራ፡፡ ወደድንም ጠላንም፣ ታበይንም አልታበይንም ፣ ወፈርንም ከሳንም … እውነቱ ይሄው ነው፡፡ አሁን ያሳወራቸው ዕብሪተኞች፣ ነገ ብርሃን የሰጣቸው ሰዎች የሚሉትን ባይሰሙ አይደንቅም፡፡ ከትናንት የማይማር ደንቆሮ የሀገርንና የዜጎችን ዛሬ ማበላሸቱ ግና ያበሳጫል፡፡

ሀገርን በፍትህና በርትዕ ማስተዳደር ከሃይማኖትም፣ ከዘርም፣ ከፆታና ከጎሣም በላይ ነው፡፡ ዘርና ሃይማኖት ከሰውነት አይበልጡም፡፡ እኛ ግን እንደአለመታደል ሆኖ የሚገጥሙን አስተዳዳሪዎች አስተሳሰባቸው ከአፍ እስካፍንጫ ብቻ ሆነና አንዱን ሕዝብ እየነጣጠሉ ይጫወቱበት ይዘዋል፡፡ ኢትዮጵያን እየመሩ “ትግሬ ትግሬ፣ ኦሮሞ ኦሮሞ” ማለት የጤንነት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያን እየመሩ የኢትዮጵያ አንዱ ሰበዝ የሆነውን አማራ ከያለበት በተለይም ከወለጋና ከሌላው ”ኦሮምያ” የሚባል ክልል ውስጥ እያሳደዱና መውጫ ኮሪዶር እንኳን እያሳጡ መጨፍጨፍ ከጤንነት መዛነፍም በላይ ነው፡፡ አንድ  መቶ ዓመትም በቅጡ ለማይኖርበት ምድራዊ ሕይወት ሲባል በሥልጣን ሱስና በሀብት አራራ ተለክፎ እንዲህ ባለ ከላይ እስከታች በተዛመተ ዕብደት ታውሮ የገዛ ወገንን ማረድ ለነገው ታሪክ ጥቁር ጠበሳ መጣል ነውና አክራሪ ኦሮሞዎች ቆም ብለው ለማሰብ ጊዜ ቢያገኙ ደስ ይለኛል፡፡ አቢይና ሽመልስ ዛሬ አብደው የሚሠሩትን እንደማያውቁ ግልጽ ነው – ይህን ከተረዳንም ቆይተናል፡፡ ሌላው ተከታይ ግን ወደአእምሮው መመለስ አለበት፤ ተያይዞ ማበድ ለተያይዞ መጥፋት በር ይከፍታልና ሁሉም ይጠንቀቅ፡፡ አክራሪው መንጋ ወደኅሊናው መመለስ ያለበትም ለአማራው ሲል ብቻ ሳይሆን የነገን የፈጣሪና የታሪክ  ፍርድ ከአሁኑ በማሰብ ጭምር ነው፡፡ ልብ ብለን ካስተዋልን ሟች ከገዳይ የሚበልጥ አበሳ የለበትም፡፡

አቢይ ክርስቲያን መሳይ ያለው ደመቀን ከሆነ ያው አምባገነኖች በተከታዮቻቸው እያፌዙ ስለሚዝናኑ በርሱ ላይ መቀለዱ ነው፡፡ ነገር ግን አቢይ አስተዳደግ የበደለው መረን ስለሆነ እንጂ ቢያንስ በታላቅነቱ ደመቀን ሊያከብረው በተገባ ነበር፡፡ የማያድግ ልጅ በአባቱ እንትን ይጫወታል እንዲሉ ነውና ግና ይህ በሰይጣን መንገድ እየነጎደ ያለ በቁሙ የጠፋ ጎልማሣ ቄስ የለ ጳጳስ፣ ትልቅ የለ ትንሽ ሁሉንም እንዳዋረደ አለ፤ የትንንሽ አእምሮ ባለቤቶች ሰውን በተለይም ይበልጡናል ብለው የሚገምቱትን የቅርብ ሰው በማዋረድ እንደሚያገኙት ደስታ የሚያዝናናቸው ሌላ ነገር ፈጽሞ የለም፡፡

የአቢይን ተፈጥሯዊ ዝንፈት ተናግሮ መጨረስ አይቻልም፡፡ ይህን ሰው ስመለከትና ንግግሩን ሳዳምጥ ሁልጊዜ የሚሰማኝ የሀፍረት መሸማቀቅ የተለዬ ነው፡፡ በበኩሌ ፈጣሪን ምን በድዬው በዚህን ዘመን እንደፈጠረኝ አላውቅም – መፈጠሬ የማያልፈኝ ዕጣ ቢሆን እንኳን ግንቦት 19 ቀን 1983ዓ.ም ብሞት ኖሮ ይሄኔ ተገላግዬ ነበር፡፡ ከዓለም ሀገሮች ውስጥ በዚህን ዓይነት ወራዳ ስብዕና ያለው ግለሰብ የሚመሩ ሀገሮች ይኖራሉ ብዬ መገመት ይከብደኛል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሌሎች ሕዝቦች ጋር ሲነጻጸር ይህን ያህል የከፋ ነው ብዬ ስለማልገምት ፈጣሪ ይህንን የመሠለ የሰውነት ወዘና የሌላው ዐውሬ ለምን እንዳዘዘብን ለመረዳት ተቸግሬ እጨነቃለሁ፡፡ ወገኖቼ እባካችሁን ጸልዩልኝ!!

አሁን ሥልጣን ላይ ያሉት ጉዶች የሚሉትንና የሚያደርጉትን ስታዘብ ከምንጊዜውም በላይ በኢትዮጵያዊነቴ አፍራለሁ። “ከፈተና ወደ ልዕልና” የሚለውን ሰሞነኛ የብል*ግና መፈክር ካነበበኩ ወዲህ ደግሞ በምን ዓይነት “ሰዎች” እጅ ውስጥ እንደገባን በማሰብ ጭንቅላቴ ሊፈነዳ ነው። በዜጎች ስቃይ የሚደሰትና ጮቤ የሚረግጥ መንግሥት ማየት ያላሣበደ ሌላ ምን ሊያሣብድ ይችላል? አገር በጦርነትና በኑሮ ውድነት እየታመሰች እነሱ በድሆች ገንዘብ ጠግበው ይጨፍራሉ፡፡ አብዛኛው ሕዝብ በርሀብ እየተንጠራወዘ እነሱ ድልቂያ ላይ ናቸው፡፡ ሙስናው ሰማይ ዘልቆ በእግር ተሄዶ አንድም ነገር አይፈጸምም፡፡ የህክምና ዕጦት፣ የታኅታይ መዋቅር ዕጦት፣ የፍትኅ ዕጦት፣ ጥራት ያለው ትምህርት ዕጦት፣ … ምን አለፋህ የዕጦቶች ሁሉ መናኸሪያ ሆናለች ሀገራችን፡፡ ያለን ዋና አንጡራ ሀብት “የለም” ብቻ ነው፡፡ ምንም ነገር ፈልገህ የትም ቢሮና መሥሪያ ቤት ሂድ – የምታገኘው መልስ “የለም” ነው፡፡

“ሀገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራል” መባሉ ትክክል ነው። ያለንበት ድቅድቅ ጨለማ በአቢይ አጠራር ደግሞ “ልዕልና” እጅግ ያስፈራል። ወለጋና ቤንሻንጉል ወደአዲስ አበባ እየገሠገሡ መሆናቸውን ያልተረዳ ተኝቶ እንቅልፉን ሲደቃና ዓለሙን ሲቀጭ ማየት ደግሞ ከሁሉም ይበልጥ ያናድዳል፤ያስደነግጣልም። መልካም የዕልቂት ዘመን ይሁንልን ለማንኛውም። በእሳትና በሜንጫ ሣይሆን በሰለጠነ መንገድ በጥይት እንዲገድሉን ሊቀ ሣጥናኤል ለልጆቹ ኦሮሙማዎች ልቦና ይስጥልን። መልካም ዕለተ ሰንበት። መጋቢት 4 ቀን 2014ዓ.ም

  •  •  •

ከዚህ በታች ያሉት የተለያዬ ይዘት ያላቸው ነጥቦች ከራሴና ከሌሎች የፌስቡክ ገፆች የወሰድኳቸው ናቸው፤ በጣም ጠቃሚ እንደሆኑ ስላመንኩ አካፈልኳችሁ፡፡

አማራ ኅልውናውን አስጠብቆ ከባርነትና ከታወጀበት ዕልቂት ነጻ መውጣት ከፈለገ ጠላቶች አናቱ ላይና ጉያው ውስጥ ካስቀመጡበት ከብአዴን ጋር ተፋልሞ በቅድሚያ እነሱን ማሸነፍና ማስወገድ አለበት። አለዚያ ውኃ መውቀጥ ነው። ከአቢይ ምስለኔዎች ሞትና ስደት እንጂ ሌላ መልካም ነገር አይገኝም።

አጋጣሚ ወይንስ ምን?

ዛሬ በፌስቡክ የተመለከትኩት አንድ መረጃ አስገርሞኛል፤ አስደንግጦኛልም። በቁጥሮች አምናለሁና።

አንደኛውና ሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች የጀመሩባቸው ቀናት ወራትና ዓመታት ሲደመሩ የሁለቱም 68፣68 ናቸው። የዩክሬይንና ራሽያ ጦርነት የጀመረበትም (እ.አ.አ 24.2.2022) ቀኑ፣ ወሩና ዓመቱ ሲደመር 68 ነው። እንዴት ነው ነገሩ?? (ዝርዝሩ ይህን ይመስላል፡- WWI – July 28, 1914 – 28+7+19+14=68); (WWII- Sept. 1, 1939 – 1+9+19+39=68); (WW? – Feb. 24, 2022 –  24+2+20+22=68) ፥ “ጠርጥር ገንፎም አለው ስንጥር” ነው።

ይች ግጥም ደግሞ በጣም ገላጭ ናት!

ቁሳቁስ ተወዶ የሰው ልጅ ረክሷል፤

ሟቹ ተፈርጆ ገዳይ ተሞግሷል፤

ከቅድስቷ ሀገር ካፈሩ ተፈጥረን፤

ከሄሮድስ ጭካኔ ተገኝተናል በልጠን፡፡

ፍቅር ከነነፍሱ ተቃጥሎ እየሞቅን፤

እሳቱ ሲጠፋ እየቆሰቆስን፤

አፍርተናል ጀግኖች አግኝናል ትውልድ፤

ሰው እንደደመራ አጨብጭቦ እሚያነድ፡፡

 

በዓለም ታይቶና ተሰምቶ የማያውቅ ጠቋሚም፣ አስመራጭም፣ ተመራጭም አንድ ግለሰብ የሆነበት የብልጥግና ፓርቲ ፕሬዝደንት የምርጫ ሂደት!

… በፊቱ ላይ ማዲያቶች በዛ ብለው ይታያሉ፡፡ የንግግሩ ለዛና ላህይ እንደወትሮው አይደለም፡፡ ብዙ በመሮጡ ብዙ የደከመው ይመስላል፡፡ ለዚያም ሳይሆን አይቀርም ማዲያቱን በአርቲፊሻል ቀለማት ለማጥፋት እንኳን ፍላጎት ወይንም በቂ ጊዜ ሳይኖረው ወደስብሰባ አዳራሽ የገባው፡፡ ቅስሙ ስብር ብሏል፡፡ አነጋገሩ ሁሉ ከድካምና ከተስፋ መቁረጥ የሚመነጭ ይመስላል፡፡ የሚያምነው ሰው በማጣት ሊሆን ይችላል ሌላ ሰው ማከናወን ያለበትን የምርጫ ሂደት በፈጣጣ ራሱ ሊያደርግ የአስመራጭ ኮሚቴን የሥራ ቦታ በድፍረት ተረክቧል፤ ይህ ዓይነት አሠራር በጭራሽ የተለመደ አይደለም፤ ሽመልስንና አዳነች አቤቤንም ላስመራጭነት ሊያምን አልቻለም ማለት ነው፡፡ አንዳንድ የፓርላማ አባላትም በዚህ ድፍረቱ ሳያፍሩበት አልቀሩም፡፡ በዚያ መድረክ ራሱን ብቸኛ የብልጽግና ዕጩ ፕሬዝደንት አድርጎ ጠቁሟል፡፡ የሚገርም የምርጫ ሂደት ነው፡፡ አቢይ በመጨረሻው እንዲህ ለይቶለት ዐበደ፡፡ ጥቂት የማይባሉ የፓርላማ አባላት ተገርመው “ይህ ሰው ምን እያደረገ ነው?” በሚል ውስጣዊ መግባባት እርስ በርስ እየተያዩ ሁኔታውን በድንጋጤ ይከታተላሉ፡፡ አሽቃባጮችም እጃቸው እስኪዝልና እስኪላላጥ  ማጨብጨባቸውን ቀጥለዋል፡፡ አንዳንዱ የፓርላማ አባል እጁን አፉ ላይ ጭኖ የምርጫውን ሂደት በአግራሞት መከታተልን መርጧል፡፡ በዚህን መሰሉ የጨረባ ተዝካር ሙስጠፌን የመሰለ ግሩም ሰው መኖሩ ለራሱ ለሙስጠፌና ለማንኛውም ጤናማ ተራ ዜጋም የሚያስከትለው ብስጭት ቀላል አይደለም፡፡ አእምሮውን በአግባቡ የሚጠቀም ዜጋ በዚያ ድራማ ውስጥ በመገኘቱ ራሱን ሳይወቅስና ለሆዱ ሲል የገባም ሆዱን ሳይረግም አይቀርም፡፡

ለማንኛውም እንዳለ ወደጽሑፍ የገለበጥኩትን አቢይ ራሱን ያስመረጠበትን “ዴሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት” ቀጥለን እንይ፤ ያስቀመጥኩትን ማስፈንጠሪያም ተከተሉና ጉዱን እዩ፡-

“ … አቢይ ፕሬዝደንት እንዲሆን ዕጩ የቀረበውን ሴከንድ የሚያደርግ ሰው … የሳቸውን ሃሳብ የሚደግፍ ማለት ነው፡፡ … በንደዚህ አይደለም፡፡ በመናገር ነው፡፡ እሺ ጥሩ ሴከንድ እሚያደርግ በርካታ ሰው ስለወጣ ‹(እሱ) ይቅርና አቢይ ባለፉት አራት ዓመታት ብልጽግናን ስለመራ አሁን ይበቃዋል፤ ከአቢይ የተሻለ ሰው ብንመርጥ ለኢትዮጵያም ለብልጽግናም ይበጃልና ዕጩ ሆኖ መቅረብ የለበትም› የሚል ሰው ዕድል ልስጠው፡፡ ፀጥታ! ፀጥታ! ይህ ብዙ ሰዎች የሚታዘቡት ምርጫ ነው፤ ዴሞክራሲያዊ መሆን አለበት፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሃሳብ ያላቸው ካሉ ለማድመጥ ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ‹አቢይ ዕጩ መሆን የለበትም› ብሎ ሃሳብ የሚያቀርብ ካለ ዕድል እንስጠው፡፡ በንግግር ባይሆንም ‹በእጄ እቃወማለሁ‹ እሚል ካለም ችግር የለውም፡፡ የመጨረሻ ጥሪ ነው – እሚቃወም ሰው ….” (ይህ ሰው የሚመራት ሀገር ውስጥ መገኘት ራሱ ክፉኛ መረገም አይደለም ትላላችሁ?)

እናንተው ፍረዱኝ፡፡ ይህ ዓይነቱ ወራዳ ሰው በሚመራት ጦርነትና ርሀብ፣ ድንቁርናና ማይምነት፣ መንግሥታዊ ሽብርተኝነትና ዘረኝነት፣ ስደትና መፈናቀል፣ ሙስናና በቃላት ሊገለጽ የማይችል የኑሮ ውድነት ዋና መገለጫዎቿ በሆኑ እጅጉን የምታሳዝን ሀገር ከመኖር አለመወለድ በስንት ጣሙ!! (https://www.youtube.com/watch?v=AjWeGyVzfls)

 

ኢትዮጵያ ሆይ! እግዚአብሔር ይሁንሽ፡፡  

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop