March 20, 2022
21 mins read

የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የምክርቤት ስብሰባ የአቋም መግለጫ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት እሑድ፣
መጋቢት ፲፩፣ ፪ሺ ፲፬ ዓ.ም. (Mar. 20, 2022)
ቅጽ  ቁጥር ፭

Moresh  Aእኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት (ሞወዐድ) ምክር ቤት አባላት በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ አርብ መጋቢት ፱ ቀን ፪ሺህ ፲፬ ዓ.ም. (Friday, March 17 2022) አድርገናል። ስብሰባው የተከፈተው ከ30 ዓመት በላይ በተለይም ባለፉት 4 ዓመታት በግፍ የተጨፈጨፉትን ዐማራ ወገኖቻችንንና ከዚህ አለም የተለዩትን የሞረሽ ወገኔ አመራር አባላትን አቶ ተኮላ ወርቁንና አቶ ከበደ ይመር እንዲሁም በሞረሽ የተዘጋጀውን ስለዐማራ ህዝብ የዘር ጭፍጨፋ ጥናታዊ ፅሁፍ ወደ እንግሊዝኛ የተረጎሙት እውቁን ኢትዮጵያዊ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን በማስታወስ የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት በማድረግ ነበር።

በመርሐ-ግብሩ መሠረት፤ የሞወዐድ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ያቀረበውን የሥራ እንቅስቃሴ ሪፖርት እንዲሁም በሞረሽ ወገኔ የሚተዳደረው የዐማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የስራ ክንውን ላይ በሰፊው ተወያይተን፣ ሪፖርቱ የድርጅቱ ቋሚ ሰነድ ሆኖ እንዲያዝ አጽድቀናል። ከዚህም በላይ፣ የሞረሽ ወገኔ የወደፊት የሥራ እቅድ ላይ በጥልቀት ተወያይተን የሥራ እቅዱን እንዳለ ተቀብለነዋል። በመጨረሻም፣ በወቅታዊ የአገራችን አሳሳቢ ፖለቲካ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዩች ላይ ስፊ ጊዜ ወስደን በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ባለ 12 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል።

 

  1. ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ እ.ኢ.አ ከ 2009 ዓ.ም. ወይም እ.ኤ.አ 2017 ጀምሮ ለውጥ ተብየው ዳግማዊ ኢህአዴግ እስኪመጣ ድረስ ዐማራ ድምጽ ራዲዮ(ዐድራ) የተሰኘ የራዲዮ አቋቋመ። ዐድራ የዐማራ ድምጽ ሆኖ ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግና ድምፅ አልባ ለሆነው ዐማራ ድምፅ ለመሆን ለቆመለት ዓላማ ስኬት ዕውን መሆን፣ የዐማራው ድምፅ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ እንዲያስተጋባ፣ የዓለም ማሕበረሰብ በዝምታ፣ የነገዱ ምሁራን በቸልታ የሚመለከቱትን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲቆም፣ ወንጀለኞች ለፍትሕ እንዲቀርቡ እገዛና ድምፅ በመሆን ሳይቋረጥ አገልግሎት ሰጥቷል።

ለውጥ ተብየው ዳግማዊ ኢህአዴግ እንደመጣ ሞረሽ ዐድራን አሳድጎና አጠናክሮ ዐማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) – Amara Media Center (AMC) በሚል ስያሜ ድምፁ ለታፈነው የዐማራው ነገድ ልሣንና አንደበት እንዲሆን በማሰብ ሕዝብን ለማንቂያ፣ ለማስተማሪያ፣ ለማሳወቂያና ለማደራጃነት የኢንተርኔትና የሳተላይት ቲቪ (መረጃ ትቪ) በመላው ዓለም እንዲተላለፍ በማድረግ ኣመርቂ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ይህ ከፍተኛ ቁጥር አድማጭ ያለው የአሚማ (AMC) አሁንም ተጠናክሮ የሚያድግበትን መንገድ ዳር ለማድረስ ቆራጥ እርምጃ ለመውሰድ ቃል እንገባለን።

 

  1. ምክር ቤቱ ዐማራው በመላው ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ አስከፊና በእልህ አስጨራሽ መከራ ውስጥ እንደወደቀ ተገንዝቧል። ዐማራው የገጠመውን ዘርፈ ብዙ ችግሮችም በአንክሮ መርምሯል። በመሆኑም ዐማራው በዚህ በመኖርና በመጥፋት መስቀለኛ መንገድ ላይ ሆኖ ፊት ለፊቱ አፍጦ የሚያዬውንና ብዙ ንፁሀንን የቀጠፈውን ፍጅትና እልቂት መላ ለማለት በዐማራው ህልውና ላይ በፅናት ከሚሰሩት አለን! ዓለም አቀፍ የአማራ ማህበራት ህብረትን ከመሳሰሉ በጋራ ከሚሰራባቸው ድርጅቶች ጋር ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል።

 

  1. ዘረኛው የኦሮሙማው አገዛዝና በሎሌነት ዐማራን በማስፈጀት የሚታወቀው ብአዴን/አዴፓ/ የዐማራ ህዝብ ብቸኛ አለኝታ የሆነውን ፋኖን በማሳደድ ላይ ነው። ፋኖ ትጥቅና ስንቅ ሳይጠይቅ ውድ ህይወቱን ሰውቶ አገሩንና ህዝቡን ከጠላት በመከላከሉ ክብር፣ ሽልማትና ሙገሳ ይገባው ነበር። እንዳለመታደል ሆኖ ብልፅግና ተብየው የቀድሞው ብአዴን ለተረኛው አገዛዝ አጎብድዶ ፋኖን በመምታትና በማስመታት ሕዝባዊ ትግሉን ለማዳፈን በየአቅጣጫው በመሯሯጥ ላይ ስለሆነ፤ ለፋኖ፣ ለዐማራ ልዩ ኃይልና ለመከላከያ እንዲሁም ለዐማራ ልጆችና ለአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት እንደሚከተለው ጥሪውን ያቀርባል።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት እሑድ፣ መጋቢት ፲፩፣ ፪ሺ ፲፬ ዓ.ም. (Mar. 20, 2022) ቅጽ  ቁጥር ፭

3.1 ዘራፊውና ሎሌው አዴፓ በሸፍጥና ክደት ፋኖን የሚያስመታው ፋኖን በመከፋፈል፣ ለጊዜው መምታት የሚፈልገውን የተለየ አደረጃጀት ያላቸው በማስመሰል “ጥፋተኞችና ስጋት የሚሆኑ” የሚል ስም በመስጠት ቢሆንም እውነቱ ግን በሁሉም የዐማራ የቁርጥ ቀን ልጅ የዐማራ ፋኖ ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ በመገንዘብ ፋኖ ከመቸውም በበለጠ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል፤

3.2 የዐማራ ልዩ ኃይልም ሆነ በመከላከያ ውስጥ ያለው የዐማራ ልጅ ፓለቲካው በሸፍጥና በክህደት የተሞላው መሆኑን መረዳት አለበት። ስለዚህ ፓለቲካው ዐማራን በዐማራ የማስመታት እሳቤ ያለው ስለሆነ የዐማራ ልዩ ኃይልም ሆነ በመከላከያ ውስጥ ያለ ዐማራ ሁሉ ፋኖን ማጥቃት ዐማራን ማጥቃት መሆኑን ተገንዝቦ ጥንቃቄ እንዲያደርግ። በመንግስት ጫና የአማራ ልዩ ኃይል እንዲበተን ከተደረገ ወይም የመከላከያ አባል የሆናችሁ በማንነታችሁ ከሰራዊቱ እንድትወጡ ከተደረገ፣ ፋኖን ተቀላቅላችሁ የወገናችሁ የአማራ ህዝባዊ ኃይል አካል እንድትሆኑ በማሳሰብ፤

 

3.3 በመላው ኢትዮጵያና በውጭ አገር የሚኖር ዐማራ እንዲሁም ኢትዮጵያ በአገዛዙ እየፈረሰች እንደሆነ የተገነዘበ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ከፋኖ ጋር በመቆም አጋርነቱን እንዲያሳይና ህዝብን ከእልቂት፣ አገሩን ከመፈራረስ እንዲታደግ አፅንዖት ሰጥቶ ጥሪውን ያቀርባል።

  1. ቀደም ሲል በትግሬ-ወያኔዎች፣ አሁን ደግሞ በተረኞቹ የኦሮሙማ አራማጆችና የእነርሱ ተባባሪ ወንጀለኞች እገዛ ለአለፉት 30 ዓመታት የዐማራን ሕዝብ ማሕበራዊ ረፍት በማሳጣት የምድር ላይ ሲኦል ሕይወትን እንዲገፋ ተደርጓል። በዐማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጽዳት (Ethnic Cleansing) እና የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ(Genocide) በመፈጸምና በማስፈፀም እጃቸው ያለባቸው ሁሉ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የዐማራው ሕዝብ ለደረሰበት የዘር ማጽዳት እና የዘር ጭፍጨፋ መንግሥት ካሳ እንዲከፍልና እንዲሁም በዐማራው ሕዝብ ላይ የዘር ማጽዳትና የዘር ጭፍጭፋ እንደተካሄደበት ይፋዊ እውቅና እንዲሰጥ አጥብቀን እንጠይቃለን።

 

  1. ይሉኝታ ቢሱና ዘረኛው የኦሮሙማ አገዛዝና ተባባሪዎቹ የወንጀል ሥራ አስፈፃሚ አካላት ዐማራውን ለማዳከምና ለማጥፋት ወጣት ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታቸው ማሰናከል አንዱና ዋናው ሆኖ አግኝተውታል። ከደምቢ ዶሎ ታፍነው ተወስደው የተሰወሩት 17 ተማሪዎች፣ በርካታ ልጃገረዶች፣ ደብዛቸው እንደጠፋ ብናውቅም ዘመዶቻቸው ግን እርማቸውን ሳያወጡ ለአመታት በስቃይ ላይ ናቸው። ደባው ቀጣይነት ስላለው ዛሬም በትምህርት ሚኒስቴር፣ የሁለተኛ ደረጃ የመልቀቂያ ውጤት ዝርፊያ አካሂዷል። በዚህም ለከፍተኛ ትምህርት ካለፉት ከ 150,000 ተማሪዎች ውስጥ 130,000 የኦሮሞ ተማሪዎች እንደሆኑ ታውቋል። ይህ በፐርሰንት ሲሰላ 87% የዩኒቨርስቲ ተማሪውን ኦሮሞ ለማድረግ በተያዘ ዕቅድ መሆኑ ነው። በኦሮሙማ ሌላው ኢትዮጵያዊ ተማሪ ሁሉ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዲገባ አልተፈቀደለትም። የሌላውን ነገድ ትውልድን የማምከን የውጤት ዘረፋና አድልኦ የተፈፀመው የግንቦት 7ቱ/ኢዜማ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ መሆኑ ደግሞ “የፈራነው ደረሰ” ያሰኛል። አይን ያወጣው የውጤት ዘረፋ የነገ ብሩህ ተስፋ የነበራቸውን ኦሮሞ ያልሆኑት የኢትዮጵያ ወጣት ተማሪዎች ላይ ሁሉ ያጠላ ስለሆነ እንቃወማለን። በዩኒቨርስቲው የአድዋ በአልን አከበራችሁ፣ የሚኒሊክን ቲሸርት አደረጋችሁ፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ያለበት ነጠላ ለበሳችሁ እየተባሉ በዐማራ ልጆች ላይ የሚፈፀመው ተደጋጋሚና ዘርፈ ብዙ ጥቃት አጥብቀን እንቃወማለን።

 

  1. ዐማራው ሕዝባችን ተወካይ እንዳይኖረው ተደርጎ በከፍተኛ ሴራ በተገገለለበት ሁኔታ አጽመ እርስት መሬቶቹን ተቀምቶ የተከለለበት አከላለልና ከኢትዮጵያውያን እሳቤ ውጪ በኢትዮጵያ በሰንደቅ አላማ ላይ የተለጠፈው የወያኔ አርማ፤ ፀረ-ክርስቲያንና ፀረ-እስላም አርማ በመሆኑ አርማውን የዐማራ ሕዝብ የማይቀበለውና የሚያወግዘው መሆኑን እናሳውቃለን።

 

  1. ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ የሆነው፤ የትግሬ-ወያኔና / ኦነግ በጋራ ያረቀቁትና ያፀደቁት፤ አሁንም በስራ ላይ ያለው ሕገ-መንግሥት የኢህአዴግ ወራሽ ተረኛው የአብይ አህመድ የኦሮሙማ አገዛዝ ዛሬም ጥላ ከለላ ሆኖት ዐማራን አሰቃቂና አረመኒያዊ ጭፍጨፋ እያደረገበት ነው። እነዚህ ዐማራ ጠል አገር አጥፊዎች ይህ በህገ መንግሥት ስም የተፃፈ ህገ አራዊት ተወግዶ ሌላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ደህንነት የሚያስከብር ህገ መንግሥት እስካልተለወጠ ድረስ የዐማራ ህዝብ ከጥቃት እንደማይድን፤ አብይ አህመድ አፍ ላይ ብቻ ያለችው የበለፀገች የኢትዮጵያን ለማየት የማይቻል መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።

 

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት እሑድ፣ መጋቢት ፲፩፣ ፪ሺ ፲፬ ዓ.ም. (Mar. 20, 2022) ቅጽ  ቁጥር ፭

  1. አገርን በክብር የመምራት ሞራልና ብቃት የሌለው የኦሮሙማ አገዛዝ በጠራራ ፀሀይ ታቦት ለማንገስ፣ ፈጣሪያቸውን ለማመስገን በሚታደሙ ምዕመናን ላይ ሳይቀር፣ ዐማራና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን በአይናችን አንይ በሚሉና የጥላቻ ፓለቲካ የተመረዙ፣ መሉ ትጥቅና የመንግሥት ሽፋን ያላቸው የኦሮሞ ገዳይ ልጆችን እያሰማራ በተደጋጋሚ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ላይ የሚፈፀምን ግድያ እንቃወማለን።

 

  1. በኦሮሙማ አገዛዝ፣ አገርን አንድ ያደረጉ፣ በአለም ላይ ለጥቁር ህዝብ ክብርን ያጎናፀፉትና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸውን

ዳግማዊ አፄ ምኒሊክን በሀሰት ትርክት ስማቸውን ለማጠልሸት ቢሰራም ለኦሮሞ ልጆች የጋተውን ጥላቻ ለሌላው ማህበረሰብ ለመጋት አልተሳካለትም። ስለዚህ አገራዊ ክብረ በዓል በመጣ ቁጥር በነገድ መደራጀት የማይፈልገውና ራሱን የአዲስ አበባ ልጅ ብሎ የሚጠራው ህዝብ በየጊዜው አበሳውን ያያል። የአድዋንና የካራማራን ክብረ በዓል በደማቅ ድምቀት ያከበሩትን የአዲስ አበባ ወጣቶች አሳዶ ማሰሩን እንዲያቆምና የታሰሩትም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ህዝባዊ ግፊት እንዲደረግ እናሳስባለን።

 

  1. አዲስ አበባን በተመለከተ የኦሮሙማ አራማጁ አብይ አህመድ ከንቲባ አድርጎ በአዲስ አበባ ህዝብ ላይ በጫነበት ከንቲባ አማካይነት ለኦሮሙማ ቤተመንግሥት ማስፋፊያም ሆነ ለሌላ ተግባር ነዋሪውን የአዲስ አበባን ህዝብ መፈናቀል አጥብቀን እንቃወማለን። አገዛዙ አዲስ አበባን ደፍጥጦ የኦሮሞ ለማድረግ ሲል ያለ ይሉኝታ የአዲስ አበባ ፓሊስ አባላትን ማባረሩ እንዲቆም እንጠይቃለን። በአዲስ አበባ ከተማ ታሪካዊ አሻራዎችን ለማጥፋት በአገር እድገት፣ እድሳትና ብልፅግና ስም የሚደረገውን ደባም እንዲቆም እንጠይቃለን።

 

  1. ወያኔ “ከዐማራ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ” ብሎ በእብሪት የተነሳበት፣ አብይና አጋሮቹም ሀይ ሀይ ብለው በደባ ያስጀመሩት ጦርነት ዐማራን ብዙ የህይወት መስዋዕትነት፣ የስነልቦና ጫናና የንብረት መውደምን አድርሶበታል። በአገዛዙ ጦርነቱ እንዲጠናቀቅ ባለመፈለጉ አፋር የጦርነት ቀጠና ሆኖ ቀጥሎ እና የዐማራም ህዝብ በከፍተኛ ስጋት ላይ እያለ፣ አገዛዙ ሰላም ያለ ለማስመሰል በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ተጠምዷል። ይህ ህዝብ ማዘናጋትና ትጥቅ ማስፈታት ፀረ ኢትዮጵያዊነት ተግባር እንጅ አገር የሚያስተዳድር መንግሥት ተግባር ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ተረድቶ ከእውነት ጎን ቆሞ አገሩን እንዲያተርፍ እንጠይቃለን።

 

  1. ጦርነቱ ባልተቋጨበት ሁኔታ የትግራይ ህዝብ ተርቦና ተቸግሮ፣ በጦርነት በደቀቀውና ወያኔ ዶሮና የተቦካ ሊጥ ሳይቀር ወደዘረፈውና የተራቆተው የዐማራ ምድር ወሎ እየፈለሰ መሆኑን መስማት በጣም ያሳዝናል። ርሀብ ቀን አይሰጥምና የትግራይ ወገኖቻችን የሚላስ የሚቀመስ አጥተው ከመጡ መቀበሉ መልካም ነው። ነገር ግን ወደወሎ ከሚገቡት ውስጥ በጦርነቱ ላይ የተሳተፉ፣ አስነዋሪ ወንጀልን የፈፅሙ እንዳሉበት የመከራው ገፋት ቀማሽ የሆነው የአካባቢው ህዝብ ምስክርነት እየሰጠ ይገኛል። እነዚህ የዘረኝነት እሳቤ ያላቸው ወንጀለኞች በርሀብ ስም ተቀላቅለው ገብተው በጦርነት ያልተሳካላቸውን ግብና ድል ለመፈፀም እንደሚሰሩም መዘንጋት የለበትምና ከፍተኛ ጥንቃቄና ምርመራ ተደርጎ ርሀቡ ፀንቶባቸው የመጡ የእድሜ በለፀጋዎች፣ ህፃናትና አቅመ ደካማዎችን ማስተናገድ የሚቻልበት መንገድ እንዲፈጠር እንመክራለን።

 

አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፤ ሁሉም ዐማራ ለዐንድ ዐማራ!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
www.moreshwegenie.org
InfoAndPR@moreshwegenie.org

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop