April 2, 2013
4 mins read

ሱዳንም ቀደመችን?! ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ሜሪ አርምዴ፡-

ዕድሌ ነው እንጂ ሀብት መች አነሰኝ፤
ብርቱካን ሲታደል ሎሚ የደረሰኝ፡፡

ብላ መዝፈኗ የዕድልን መጥመም ለማመልከት ነው፡፡

የዛሬ 24 ዓመት ገደማ 81ዓ.ም ክረምት ላይ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ ላይ ሲካሄድ በመንግሥት ለሥራ ተመድቤ በጉባኤ አዳራሹ ውስጥ ነበርኩ፡፡ ያኔ ሣተናው አልበሽር የሱዳንን መንግሥት በጉልበቱ ከገለበጠ ገና ሦስት ቀናትን እንኳ አላስቆጠረም፡፡ ነገር ግን ስብሰባውን ለመካፈል ሰተት ብሎ ወደ አዲስ አበባ መጣ፡፡ ያልተገረመ ሰው አልነበረም፡፡ እኔም ያን ሁኔታ ባሰብኩት ቁጥር ሁልጊዜ ይገርመኛል፡፡ ጓደኞቹን እንዴት ቢተማመን ነበር ሥልጣኑን ሳያረጋጋ ሊመጣ የቻለው? ነው የሡዳኑ እንትን ገትሮ ያዘለት?

ዕድሜ ደጉ ዛሬ ደግሞ ልብ ገዝቶ ሀገሩን ሱዳንን ከቀውስ ሊያድን ጉዞውን ‹ሀ› ብሎ እንደጀመረ በታወቁ ሚዲያዎች እየሰማን ነው፡፡ ‹የቆዬ ሰው ከሚስቱ ይወልዳል› ይባል የለም? እንደ አንድ ለዓለም የሚጨነቅ ተራ ዜጋ የሱዳንም ጉዳይ ያሳስበኝ ነበርና ይህን ዜና ስሰማ በጣም ነው የተደሰትኩት፡፡ ‹ሰላም እንድታድር ጎረቤትህን ሰላም ያሳድርልህ› መባሉን መዘንጋት አይገባም፡፡ በዚያ ላይ ሁላችንም – እንጥቆር፣ እንቅላ ወይ እንንጣ እንጂ ሁላችንም የአዳምና የሔዋን ዘሮች ነን፡፡ የሶርያውያኝ ሠቖቓ የማይሰማው ሰው ቢኖር ሰው ሳይሆን ሣር ባይበላም ከብት ነው፡፡ በዘርና በሃይማት ጥላ ሥር ተጠልሎ ‹የኔ ወገን ካልሆነ የራሱ ጉዳይ› ማለትም ከመጥፎ ከብትነት ተራ የሚያስመድብ የክፋት ምንጭ እንጂ ሰው አያሰኝም፡፡

‹የፖለቲካ እሥረኞችን እፈታለሁ፤ ዱር ቤቴ ያሉ ብረት ያነገቡ አማፂያንን ጨምሮ ሁሉንም ተቃዋሚዎች ለሰላም ድርድር ጠርቼ እነጋገራለሁ፤ ለሀገሬ ሱዳን ለውጥ ለማምጣት ቆርጫለሁ› ባለ ማግሥት ዛሬ ጧት     ስድስት የፖለቲካ እሥሮችን በነጻ ለቀቀ – ቃሉንም በተግባር አስመሰከረ፡፡ ግሩም ነው፡፡ የንቃተ ኅሊና ዕድገትና የልቦና መከፈት ማለት እንደዚህ ነው፡፡ ለሱዳን ጽዋችንን እናንሳ!

የኞቹ ሕወሓቶችስ ከሱዳኑ መሪ ከኦማር አልበሽር የሚማሩት ነገር ይኖር ይሆን? አንዳች መንፈሳዊ ቅናት ወረር አያደርጋቸው ይሆን? ማሙሽ ከነሽበቱ መሆንን ዕርም የሚሉበት ዘመን እንደተሸሸገ ይቀር ይሆን? የኛ ያስፈራል፤ ግን ለሁሉም ጊዜ አለ፡፡

ከሃሌ ኩሉ ቸሩ መድሓኔ ዓለም ለሱዳኑ መሪ የላከውን የዕርቅና የስምምነት መንፈስ ለኢትዮጵያም እንዲልክ ሱባኤ እንግባ፤ ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም፡፡ በቃኝ፡፡ (እነዚህን ጨምሮ በ297 ቃላት ያለቀ የመጀመሪያው አጭር ደብዳቤየ እንደሆነ ይመዝገብልኝ! ‹እስከመቼ›ዎች ባላችሁበት ይመቻችሁ፤ ምክራችሁ መሬት አልወደቀም ፡፡)

1 Comment

  1. we are lucky enough to talk, write or read ,when it comes to weyanes they plan how to live their life,because no body lives for ever.they knew they are going to die one day but till then they kill, put us in jail, lie about anything and everything as long as they make it to the next day.I am not suggesting what they are doing is right,but at least why can’t we be united and do something fruitfull.

Comments are closed.

Previous Story

አማረኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ማፈናቀል የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው (ሸንጎ)

Ryot Alemu
Next Story

ርዕዮት አለሙ በወህኒቤቱ አስተዳደር ክስ ቀረበባት

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop