ኢህአዴግ 42 ዓመት መግዛትን አስቧል?

ሳሙኤል ተወልደ በርሔ/ሃርስታድ ኖርዌይ/
ሳሙኤል ተወልደ በርሔ/ሃርስታድ ኖርዌይ
ዛሬ በዓለማችን ላይ በርካታ የሆኑ ለውጦች ተፈጥረዋል፡፡ ህዝብ ይመረጣል፣ ህዝብ ያወርዳል፡፡ ሥልጣን እርስት አይደለም፡፡ የዚህ አይነቱነገር ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ እየሰላ መጥቷል፡፡ ልክ እንደዚህ አይነቱ ሁኔታ በሚታይበት ሁኔታ ደግሞ በተቀራኒው ሥልጣንን የሙጥኝ ብለው ዘላለማዊ አገዛዝን ለመግዛት የሚያስቡ መኖራቸው አልቀረም፡፡ የጠ/ሚ/ር ኃ/ማርያም ደሳለኝ አማካሪ በመሆን የተሾሙ አቶ በረከት ስምኦን ባለፈው ሰሞን “ኢህአዴግ የጀመረውን የልማት ሥራ ለመጀመር በቀጣይነት 42 ወይም 45 ዓመታት ያፈጅበታል” ሲሉ ገለጹ፡፡ ይህ የአቶ በረከት ስምኦን ንግግር ምናልባትም በምርጫ ዋዜማ ሠሞን የተነገረ ከመሆኑ አንፃር ብዙ ነገር እንዲታሰብ ያደርጋል፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን ምርጫ በደረሰ ቁጥር በኢህአዴግ ውስጥ ስልት አለ፡፡ የአሸናፊነት መንፈስን በማሰብ ሳይሆን፣ ሁልጊዜም ቢሆን ተሸናፊነትን እያሰበ ይወጣል፡፡ በዚህ ወቅት ደግሞ የተለያዩ ሕጐችንና ደንቦችን በማውጣት ምርጫው ሕጋዊ ወይም ተገቢ ያልሆነ መንፈስ እንዳይኖረው ያደርጋል፡፡ ታዲያ አቶ በረከት ስምኦን እንደሚሉት ሆነ ወይም በቀጥታ ትርጓሜው ሳይሆን፣ በኢህአዴግኛው ትርጓሜው ‹‹በቀጣይም እቺን አገር የምንስተናገደው እኛ ነን›› የሚል መንፈስ ያለው ነው፡፡

ኢህአዴግ በሃገሪቱ በሶስት አይነት ዘርፍ የልማት ሥራ ጀምሯል፡፡ የህዳሴው ግድብ፣ የባቡር ሃዲድ ዝርጋታ እና በንግድ፡፡ እነዚህ ሶስት ሥራዎች ግን ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቁ ከመሆናቸው አንፃር በተፈለገው መንገድ ተፋጥነው ሊያልቁ የሚችሉ አይደሉም፡፡ ይህ አለመሆኑ ደግሞ ምናልባትም ኢህአዴግ እንደ አቶ በረከት ስምኦን አባባል በፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ለመጠቀም ያስቀመጠውም የሚመስልበት ሁኔታ አለ፡፡ የኢህአዴግ ያለፉት 22 ዓመታት ጉዞ ምናልባትም እርሱ ‹‹ዕድገት›› ይበለው እንጂ፣ በብዙ መልኩ ውድቀቶችና ድህነቶች የበዙበት ነው፡፡

የ11 በመቶ ዕድገት ለሌሎች ሳይሆን፣ ለኢህአዴግ ብቻ የሚገለጽ ነው፡፡ የህንጻ መብዛት ‹‹የሃገር ዕድገት ነው›› የሚለው ኢህአዴግ እንጂ፣ ከሚሠሩት ፎቆች ስር በርካታዎች ማደሪያ አልባ መኝታ ማድረጋቸውን በየቀኑ የሚታይ አሣዛኝ ገልጻ ነው፡፡ የሃገር ለውጥ የህዝብ ለውጥ ነው፡፡ ማንም ሰው ቢሆን፣ የደሞዝ ጭማሪ በሚደረግበት ጊዜ በራሱ ላይ የተወሰነ ለውጥ ይታይበታል፡፡ የሃገር ዕድገትም 11 በመቶ ከደረሰ፣ ህዝቡ በራሱ ላይ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል ወይም አንዱ በአንዱ ላይ የሚመለከተውም ለውጥ ይኖራል ማለት ነው፡፡ በነዚህ 22 ዓመታት ግን የዚህ አይነቱን ነገር ለማየት አልተቻለም፡፡ ያ ማለት ዕድገቱ የስም ነው ማለት ነው፡፡ የፎቅ ግንባታዎች እና መንገዶች ተሰርተዋል፡፡ ያ ማለት ግን ሃገራዊ ለመፍጠር አንድ ምሣሌ ልንገራችሁ፡፡ ለልጅቱ 14 ዓመቷ ነው፡፡ የሰውነትዋ ግዝፈት ደግሞ 20 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ ያለች አስመስሏታል፡፡ አንድ ሰው ደግሞ ልጇቷን ለጋብቻ ጠየቀ፡፡ የ14 ዓመት ልጅ መሆኑዋን የሚያውቀው አባት፣ ‹‹አይ ማግባት አትችልም›› አለ፡፡ ምክንያቱም ገና 14 ዓመቷ ስለሆነ ለጋብቻ የፈለጓት ወገኖች 14 ዓመት የሚለውን ነገር ፈጽሞ ሊቀበሉ አልፈቀዱም፤ አልተዋጠላቸውምም፡፡ የልጅቱዋን የሰውነት ግዝፈት በመመልከት “ኢህአዴግ እየነገረን ያለው ዕድገትም ቢሆን የዚህ አይነት ምሳሌ ያለው ነው፡፡ እንደሚታወቀው ዛሬ ሙስና የስርዓቱ መለያ ሆኗል፡፡ በርካቶች በአንድ ጀምበር የፀሐይ ፍጥነት በሚያስደንቅ መልኩ ተቀይረው ሃብታም ሲሆኑ ይታያል፡፡ የዚህ የሃብት ምንጭ ግን አይታወቅም፤ ምክንያቱም ሥራው ሙስና ነው፡፡
አቶ በረከት
ይህ የሙስና ተግባር ደግሞ በተለይ በአሁን ሰዓት ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት ውስጥ ሳይቀር የገባበት ሁኔታ ታይቷል፡፡ ስርዓቱ ለይምሰል ብቻ እንደ ህዝብ ገፀ-በረከት ከዝቅተኞቻችን ተሿሚዎች መካከል ሙሰኞች እያለ ለህዝብ ቢያጋልጥም ዋናዎቹን ግን ለመንካት ታስቦ አይደለም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ምንም ሳይሆን አንዱ ከተነካ ሌሎችንም ይዞት የሚሄድበት የተሳሰረ የሙስና ሰንሰለት ስላለ ነው፡፡ ሌላው ነገር እንዳይነካው ሲጥር የሙስና ተግባር እየተስፋፋና አሁን አሁን ይበልጥ ወደ ሕጋዊነት እየተቀየረ የመጣበት ሁኔታ በመሰማት ላይ ይገኛል፡፡ በአንድ ሃገር ላይ ትልቁ ችግር የመንግስት ሹማምንት ሙሰኛ መሆን ነው፡፡ የሙሰኞች ቁጥር እየሰፋ በመጣ ቁጥር ተጐጂ የሚሆነውና አደጋ ላይ የሚወድቀው ማንም ሳይሆን ህዝቡ ነው፡፡ ኢህአዴግ ይህንን የሙስና ተግባር ፈጽሞ ሊያጠፋው አልቻለም፡፡ ሲታይም እንዲጠፋ የሚፈልግም አይመስልም፡፡ ባለፉት ዓመታት ‹‹የባለሥልጣናት ሃብት ምዝገባ›› በሚል አንድ ምዝገባ ተከናውኖ ነበር፡፡ ይህ ምዝገባ በቅርቡ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ቢገለጽም፣ አቶ መለስ ከመሞቱ አስቀድሞ የተደረገው ምዝገባ ለህዝብ ይፋ ሊደረግ አልተቻለም፡፡ ምክንያቱም ህዝቡ የሚያየው ሃብትና የሚገለጸው ነገር ፈጽሞ አይገናኝም፡፡ ህዝቡ የቱ ድርጅት የየትኛው ባለሥልጣን እንደሆነ አብጠርጥሮ ያውቃል፡፡ ስለዚህ የዛኔም ቢሆን ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ከዓለም ባንክ የተቸረውን ገንዘብ ለማግኘት ሲል ይህንና ድራማ ይተውን እንጂ፣ የባለሥልጣናቱን ሃብት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ግን አይጠበቅም፡፡ ከዛ ባለፈ ደግሞ በሃገሪቱ የትምህርት ጥራትና የተማረ ኃይልን የምንመለከተው ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡ የትምህርቱ ጥራት ከመውረዱ የተነሳ ዲግሪው የከበዳቸው ወይም በ‹‹በዲግሪው›› የሚያምኑ ተማሪዎች በዝተዋል፡፡ ኢህአዴግ የትምህርት ጊዜውን ዓመት ከመቀነሱም በላይ በገፍ ተማሪዎች ያስመርቃል፣ ወደ ስር ሲገባ ግን ፈጽሞ የማይመጣጠን እየሆነ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትውልዱን እየገደለና እያወረደው መጥቷል፡፡ ተስፋና ለሃገርና ለወገን የሚጠቅም ተግባር የሚፈጽም ወጣት ሳይሆን፣ቀድሞተስፋ የቆረጠ ሲመረቅ ለድንጋይ ጠረባ /ኮብልስቶን/ የተዘጋጀ መሆኑን አውቆ ሃሞቱ የፈሰሰ ትውልድ ለዚህች ሃገር እያስረከበ ይገኛል፡፡
ይህ ብቻም አይደለም፡፡ በእውነቱ ከሆነ የየትኛው ባለሥልጣን ልጅ ነው በሃገር ውስጥ ወይም እነርሱ በወጣ ፖሊሲ የሚማረው? የእነርሱ ልጆቻች በአውሮፓና በአሜሪካ እያስተማሩ ሌላውን እዚህ ሃገር ውስጥ እየታሸ ለአራትና አምስት ዓመት ተምሮ ዕውቀቱን በድንጋይ ጠረባ ላይ እንዲያፈሰው እየተደረገ እንዴት የተማረ ኃይል በዚህች ሃገር ውስጥ ለራሱ ይቻላል፡፡ የህዝቡ እና የጤና ላይም ቢሆን ይበልጥ የወረደ የተለየ ለውጥ የታየበት አይደለም፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ለሴረኞች እየመሸ ይመስለኛል በኢትዮጵያ እየሆነ ያለው  ሁሉ ይገለጥ ዘንድ ነው - ሰርፀ ደስታ

ኢህአዴግ ባለፉት 22 ዓመታት ቆይታው የመራው ነገር ብዙም ሚዛናዊ የሆነ ነገር አይደለም፡፡ ፖሊሲው በፈጠረው ችግር በርካቶች ከሃገር እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡ ዛሬ በርካታዎች የሚሰደዱት የሃገሪቱ ኢኮኖሚ በመውረዱ፣ ሥራ አጥነት፣ ከዛ ባለፈ ደግሞ ፖለቲካው የሚፈጥረው ጫና ከሚፈጥርባቸው አደጋ ጋር ተያይዞ ነው፡፡ በዚህ ስርዓት የመጣ ለውጥ የለም፡፡ እስቲ ሌሎችም ጐልተው ዕድሉን በማግኘት ይሰሩ ቢባል፣ ምርጫው ግን ፈጽሞ ነፃ ሊሆን አልቻለም፡፡ “እኛ ታግለን ነው የገባነው፤ እኛ ብቻ ልንመራ ይገባል” የሚለው አካሄድ የኢህአዴግ መለያው ሆኗል፡፡ ትግል ለሕዝቦች ነፃነት እኩልነት እንጂ፣ ለአንድ ወገን ብቻ ዘላለማዊ ሥልጣን የሚሰጥ አይደለም፡፡ በፈሰሰው ደምና በተከፈለው መስዋዕትነት ሃገር ስታድግ፣ ህዝቡ ዲሞክራሲያዊ መብቱ ሲከበር ደስ ይላል፡፡ ይሄ ግን ኢህአዴግ ጋ አይሰራም፡፡ ቢቻል ዘላለማዊ አገዛዝን በመያዝ ወይም ‹‹ልንመራ የሚገባን እኛ ነን›› የሚል ፖሊስ ይዟል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን የሚችል አይደለም፡፡ ዛሬ ዓለም ተቀይሯል፤ ምናልባት ኢትዮጵያን ጨምሮ ውስን የአፍሪካ ሃገራት ላይ የአንድ ፓርቲና ወገን በበላይነት ሰፍኖ ሊታይ ይቻላል፡፡ ከዛ ባለው ግን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ለማድረግ የሥልጣን ሽግግር እያየን ነው፡፡ አቶ በረከት ባለፈው ሰሞን የነገሩን “የዘፈንዳር ዳሩ ነው” እንደሚለው፣ ተረት አሁንም በሥልጣን ላይ ለመቆየት እንደሚፈልጉና ይህንን ለማድረግ ደግሞ የተጀመሩትን የልማት ሥራዎች ‹‹በቀብድነት›› በማስገባት እንደው ነገሩን ለማስመሰል ጥረዋል፡፡ ኢህአዴግ ይህን አያደርግም አይባልም፡፡ ባቀጣይነት የሃገሪቱ ውድቀት እንደሚቀጥል መዘንጋት የለበትም፡፡

1 Comment

Comments are closed.

Share