March 5, 2022
19 mins read

በአብይ አህመድ ዘመን ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ህይወቱን አጥቶል፣ አንድ ትሪሊዮን ብር ንብረት ወድሞል!!!

ፂዮን ዘማርያም ክፍል ሁለት (ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOM

ee2233144የህወሓት ጦር አበጋዞች ከኢትዮጵያ የዘረፉት ከባድ መሣሪያዎችና ተወንጫፊ ሮኬቶችና ሚሳኤሎች!!!

     በዶክተር አብይ አህመድ አራት አመታት የሥልጣን ዘመን  ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ በጦርነትና ግጭት በተለይ በአማራ፣ አፋርና በትግራይ ክልሎች  በህወሓት፣ ኦነግና ብልፅግና  ተዋናዬች ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ህይወቱን አጥቶል፣ ብዙ ሽህ ከብቶችና ግመሎች ታርደዋል፣ ተነድተዋል፤ አስራ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ቀየውን ለቆ ተፈናቅሎ እርዳታ ጠባቂ ዜጋ ሆኖል፡፡  አንድ ትሪሊዮን ብር ንብረትና ኃብት ተዘርፎል ወድሞል!!! የህወሓትና የኦነግ ሽብርተኞች ከህዝብ ግብር ይሰበስባሉ፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ15 ቢልም የህዝብ ህይወት እንደ ቅጠል በመርገፍ ላይ ይገኛል፡፡ በሃገሪቱ መንግሥት የለም!  የብልፅግና መንግሥት የጦር ግምጃ ቤቱን መሳሪያዎች ታንኮች፣ ሞርታለች፣ ቢኤሞች፣ ብሬኖች፣ ዲሽቃዎች ሚሳኤሎች፣ ሮኬቶች ፣አዘርፎል፡፡ የሃገሪቱን  ባንኮች፣ ፋብሪካዎች፣ ከባድ መኪኖች፣ አዘርፎል፡፡ በምድረ ኢትዮጵያ ዓየር በዓየር የጦርነት ንግድ ተጦጡፎል፣ አንድ ክላሽን አንድ መቶ ሃያ ሽህ ብር ይሸጣል፡፡ ዓየር በዓየር  ንግድ፣  ህገወጥ የጦር መሣሪዎች ዝውውርና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር  ከቁጥጥር ውጪ ሆኖል፡፡

የህወሓትና የኦነግ አሸባሪዎች ኢትዮጵያን የመዝረፍ ህብረት ፈጥረዋል፡፡ የሃገሪቱን  የጦር መሣሪያ ዘርፈዋል፣ ባንኮች ዘርፈዋል፣ መሬቱን ዘርፈዋል፣ መኪኖች ዘርፈዋል፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የቴሌኮሙኒኬሽን መገናኛዎች፣ የመብራት ኀይል ስብስተሸኖችና ትራንስፎርመሮች፣ ፋብሪካዎች ፈትተው  ዘርፈዋል፣ የአርሶ አደሮቹን ከብቶች ነድተው ዘርፈዋል፣ የአማራና የአፋር ክልሎች በዝርፍያው ተጠቂ ናቸው፡፡ ክልሎቹ በዝርዝር የዝርፊያውን መጠን በመረጃ አስደግፈው ለህዝብ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የህወሓት የጦር አበጋዞች በሃገር ክህደት ከኢትዮጵያ የዘረፉት ከባድ መሣሪያዎችና ተወንጫፊ ሮኬቶችና ሚሳኤሎች!!! The Tigray Defence Forces – Documenting Its Heavy Weaponry ህወሓት ‹‹የትግራይ መከላከያ ሠራዊት›› የከባድ መሳሪያዎች ዶሴ›› በስቲጂን ሚትዘረና ጆሰት ኦሊማንስ ወታደራዊ ዘገባ እንሆ፡፡……………..(1)

የህወሓት የጦር አበጋዞች በጦርነቱ ወቅት በስፋት ከባድ መሣሪያዎች ታንኮችን፣ መድፎችን፣ በእርቀት የሚወነጨፉ ሮኬቶች ተምዘግዛጊ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች አስወንጭፈዋል፡፡  የህወሓት ኃይል ከኢትዮጵያ በዘረፈው መሣሪያ ሦስት ባሊስቲክ ሚሳኤሎች ወደ ኤርትራ አስወንጭፎ የአስመራ ዋና ከተማን ደብድበዋል፡፡ ህወሓት አሸባሪዎች የቻይና ስሪት የሆነውን ኤም ትዊንቲ ኤስአርቢኤም (M20 SRBMs)   ሚሳኤሎች ወደ ባህር ዳር ዓየር ማረፍያና ጎንደር አስወንጭፎ ከተሞቹን መደብደቡ የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡   “ Perhaps contrary to popular expectation, Tigray forces operate a sizeable arsenal of tanks, artillery and even took possession of long-range guided rockets and ballistic missiles. ……………..Tigray forces fired at least three missiles at Eritrea’s capital Asmara hours after it warned Eritrea that such an attack may be imminent. [2] Around the same time, Tigray forces (meanwhile morphed into the Tigray Defences Forces) also fired Chinese M20 SRBMs against Ethiopian air bases in Bahir Dar and Gondar in retaliation for Ethiopian air strikes in Tigray. [3]”

የኢትዮጵያ ሠራዊት ከባድ መሳሪያዎች በሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት እጂ ላለፉት ሦስት አስርት ትግራይ ውስጥ ድንበር በመጠበቅ ግዳጂ ላይ የነበረ ሠራዊት ሲሆን በህወሓት የሀገር ክህደት የሠራዊቱን አባሎች በመግደልና በማሰር ከባድ መሣሪያዎቹን በሙሉ በህወሓት ቁጥጥር ስር ወድቀው ነበር፡፡    የኢትዮጵያ ሠራዊት ባደረገው ከባድ ውጊያ ወር ባልሞላ ጊዜት ውስጥ የተዘረፉትን ከፊል ከባድ መሣሪያዎች ከወያኔ መማረክ ችለው ነበር፡፡ “Tigray was home to a significant portion of the Ethiopian Army’s heavy weaponry, much of which fell in the hands of Tigray forces in November 2020.Large numbers were subsequently recaptured by Ethiopia however, and therefore could not be included in the list. Not all heavy weaponry is operated by the TDF at the same time, with some entries already lost in action. Small arms, mortars, ATGMs and trucks are not included in this list.”

{1} ህወሓት የዘረፈው ሰማንያ ስድት ታንኮች (Tanks )  ሲኖሩት ከዚህ ውሰጥ ሃያ ዘጠኙ T-55: ታንኮች  ሲሆኑ አንዱ ደግሞ  T-55(A)MV ታንክ: ሠላሳ ሦስቱ ደግሞ  T-62 ታንኮች: ሃያ ሁለቱ T-72B ታንኮች:  አንዱ T-72UA1: ታንክ መሆናቸው ታውቆል፡፡

{2} ህወሓት አንድ አርሞርድ ሪከቨሪ ቭኒክል (Armoured recovery vehicles ) ዘርፎል፡፡

{3} ህወሓት ሠላሣ  አርሞርድ ፐርሶኔል ኬሪየርስ  (Armoured personnel carriers ) አለው፡፡ ከዚህ ውስጥ ሃያ ስድስቱ Type 89A APC: ሲሆኑ፣ አራቱ WZ-551 APC:  ናቸው፡፡

{4} ህወሓት  ስልሣ አምስት ቶውድ አርቲለሪ (Towed artillery )ሲዘርፍ ከዚህ ውስጥ  አንዱ 85mm D-44 divisional gun:፣ አርባ ስምንቱ 122mm D-30 howitzer 2A18: ሲሀኑ፣ ዘጠኙ  130mm M-46 field-gun:ሲሆኑ ቀሪው ሰባቱ ደግሞ  155mm AH-1 howitzer: ዓይነቶች ናቸው፡፡

{5} ህወሓት  አስራስድስት መልቲፕል ሮኬት ላውንቸርስ (Multiple rocket launchers ) ሲዘርፍ ከዚህ ውስጥ ስድስቱ 107mm Type-63: ዓይነት፣ ስምንቱ  122mm BM-21 ‘Grad’:ዓይነት፣ አንዱ 300mm AR2:ዓይነት፣ ሲሆን ቀሪው አንድ ደግሞ 300mm A200/M20 TEL: ናቸው፡፡

{6} ህወሓት አንድ M20/A200 TEL: ባሊስቲክ ሚሳኤል ላውንቸር (Ballistic missile launcher) ዘርፎ የነበረው ሲሆን በኖቨምበር 2020 በባህር ዳር ዓየር ማረፍያ ላይ አስወንጭፎ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፡፡  M20/A200 TEL:  (Used in the missile strike on Bahir Dar airbase in November 2020)

{7} ህወሓት አራት ሮኬትና ሚሳኤል ሰፖርት ቬኒክል ( Rocket and Missile support vehicles ) ሲዘርፍ  ከዚህ ውስጥ አንዱ AR2 loader: ሲሆን ሦስቱ ደግሞ M20/A200 loader: ናቸው፡፡

{8} ህወሓት አስራ ሁለት ማን ፖረብል ኤር ዲፊንስ ሲስተም (Man-Portable Air Defence Systems ) ሲዘርፍ 9K310 Igla-1: ዓይነት ናቸው፡፡

{9} ህወሓት ሃያ ሰባት ፀረ አይሮፕላን (Anti-aircraft guns (27) ሲዘርፍ ከዚህ ውስጥ ሃያ አንዱ  23mm ZU-23: ሲሆኑ ስድስቱ  37mm Type-65/74: ዓይነት ናቸው፡፡

{10} ህወሓት ከምድር ወደ ዓየር ተወንጫፊ ሚሳኤል (13 ላውንቸር በ 4 ሳይትስ)  Surface-to-air missile systems (13 launchers in 4 sites) ሲኖረው ከዚህ ውስጥ አንዱ  S-75 ”SA-2” site:  ሲሆኑ ሦስቱ S-125 ”SA-3” sites:

{11} ህወሓት ሰባት ራዳሮች  (Radars ) ሲዘርፍ ከዚህ ውስጥ አንዱ P-18 ‘Spoon Rest D’: ፤ሁለቱ ST86U/36D6 ‘Tin Shield’: አንዱ SNR-75 ‘Fan Song’ (for S-75): ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ SNR-125 ‘Low Blow’ (for S-125): መሆናቸውን መረጃው ያሳያል፡፡

 

የአማራና አፋር ክልል የጦርነቱ ሠለባዎች

የአማራ ክልላዊ መንግሥት መረጃ መሠረት በአማራ ልልል 380 ቢሊዮን ብር ንብረት መዘረፉንና መውደሙን ዳግም ለመገንባትም ብዙ አመታት እንደሚፈጅ በተደጋጋሚ አሳስበው ከፌዴራል መንግሥቱ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጠይቀው ነበር፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በህወኃት አሸባሪ ድርጅት በአማራ ክልል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 100 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ለፓርላማ አባላት ገልፀዋል፡፡ ከወደሙት ትምህርት ቤቶች ውስጥ 1200 ትምህርት ቤቶች በጦርነትና በሌሎች ምክንያት የወደሙ፣ 5000 ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፣ ሶሰት ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል፣ መቶ ሃምሳ ሽህ መምህራን ከመማር ማስተማር አገልግሎት ውጪ ሆነዋል፣ ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች በከፊልና በሙሉ ወድመዋል በማለት የደረሰውን ጉዳት ገልጸዋል፡፡ በአማራ ክልል ብዙ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ብዙ 11.6 ሚሊዮን ህዝብ በጦርነቱ ተፈናቅለው እርዳታ ጠባቂ ዜጎች ሆነዋል፡፡ በሌላ በኩል የብአዴን/አዴፓ ብልጽግና ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች 60 ሚሊዮን ብር ተከፋፍለው ለመጥፋት በዝግጅት ላይ እንደነበሩና መቶ ሚሊዮን ብር እንደተዘረፈ ተገልፆል፡፡

የጤና ሚኒስትሮ ዶክተር ሊያ ታደሰ በአማራና በአፋር ክልሎች ለተዘረፉና ለወደሙ 36 ቢሊዮን ብር መልሶ ለማቆቆም እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል በህወኃት የተዘረፉ የጤና ተቆማት ተፈታትተው የተዘረፉ የህክምና መሣሪያዎችና የላብራቶሪ እቃዎች ግምት 36 ቢሊዮን ብር እንደሚገመት ታውቆል፡፡በአፍር ክልል እስከ አምስት መቶ ሽህ ህዝብ በጦርነቱ ተፈናቅሎ ይገኛል፡፡

 

የኦነግ ሸኔ  የአማራ የዘር ፍጅት፣የንብረት ዘረፋና ውድመት  

የኦህዴድ ብልፅግና መር ሽብርተኛነትና የአማራ የዘር ፍጅት፣በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ በሁሩ ጉድሩና በምስራቅ ወለጋ  በኦነግ ሸኔ የሚከወን የአማራ የዘር ፍጅት በፌዴራሉ መንግሥትና በኦሮሚያ ክልል የሚመራ ሽብርተኛነት የደህንነት ኃላፊ የነበሩት በጊዜው አጋልጠው ነበር፡፡  በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የሚኖሩ አማራዎችን በማጥፋት የዘር ፍጅት በማከናወን የኦሮሞ የበላይነትን ማንገስ ቀጣይ እኩይ መርሃ ግብር በተግባር ከዋለ ሦስት አመታት አስቆጥሮል፡፡ ኦነግ ሸኔ  የአማራ ክልልና የኦሮሚያ ክልል የሚያገናኘውን የቡሬ ነቀምቴ መንገድን በመዝጋት አምስት ሚሊዩን አማራዎችን በመጨፍጨፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ በኦነግ ሸኔ በሁሩ ጉድሩና በምስራቅ ወለጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2563፣ የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር 68፣ የተዘረፉ የቀንድ ከብቶች 145000፣ የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያኖች 68፣ የተቃጠሉ መስጊዶች 46፣ የተቃጠሉ ወፍጮዎች 84፣ የተቃጠሉና የተዘረፉ መኪኖች 18 መሆናቸው ተገልጾል፡፡

የኢትዮጵያ ሠብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሠመኮ)የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን የከረዩ አባ ገዳ አስራ አራት ሰዎችን ሜዳ ላይ አስተኝቶ የኦሮሚያ ፖሊስ እንደገደላቸው ኢሠመኮ አጋልጦል፡፡ በኢትዮጵያ ዜና ማሰራጫዎች የከረዩ አባ ገዳዎችን ኦነግ ሸኔ ግድያውን እንደፈፀመ ገልጸው ነበር፡፡

ኦነግ ሸኔ በቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሜ ወረዳ 168 ንጹሃን ሰዎች መግደሉ ተገልፆል፡፡ በኦነግ ሸኔ በቄለም ዞን 30 የመንግሥት ተቆማቶች ወድመዋል፣ 45 አንደኛ ደረጃ ተምህርት ቤቶች፣ 4 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ 6 ጤና ተቆማት፣ ሃያ ሽህ ሃምሳ አራት የመንግሥት ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ተገልለዋል፣የቄለም ዞን ወደ መደበኛ የመንግሥት ተቆማት ለማደራጀት 15 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተብሎል፡፡

በሌላ በኩል የኦነግ ሸኔ ጥቃት በምዕራብ ሸዋ ዞን 647 ንፁሃን ዜጎችን መግደሉ ተገላፆል፡፡ 1252 (እንድ ሽህ ሁለት መቶ ሃምሳ ሁለት) ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ታውቆል፡፡ 85000 (ሰማንያ አምስት) ሽህ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ ኦነግ 26.7 (ሃያ ስድስት ነጥብ ሰባት) ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረና ኃብት ዘርፎል፣ አውድሞል፡፡ ባለፈው ጊዜ ኦነግ የዘረፈው የሻሸመኔ ከተማ፣ አርሲ፣ አጣዬ፣ ጂማ፣ ዘረፋና ውድመት ልብ ሊሉ ይገባል፡

 

ኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ/ ወታደራዊ ወጪዋ  502 ሚሊዮን ዶላር ወይም ሃያ አምስት ቢሊዮን ብር

ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ የዓለም የማክሮ ሞዴሎችና ትንተና ግምቶች መሠረት ኢትዮጵያ በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ  በ2021 እኤአ መጨረሻ ድረስ ወታደራዊ ወጪዋ  502 (አምስት መቶ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር ወይም ሃያ አምስት ቢሊዮን ብር እንደሚደርስ ተተንብዬል፡፡ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ወጪ ከ2011 እስከ 2022 እኤአ ከ466 ወደ 502 ሚሊዮን ዶላር እንዳደገ ይስተዋላል፡፡ በዚህም መሠረት እድገቱ  በ2011 (466) ሚሊዮን ዶላር፣በ2012 (437) ሚሊዮን ዶላር፣በ2013 (438) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2014 (477) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2015 (489) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2016 (537) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2017 (545) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2018 (560) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2019 (545) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2020 (460) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2021 (502) ሚሊዮን ዶላር፣ በ2022 (475) ሚሊዮን ዶላር፣ እንደሚሆን የመረጃው ምንጭ ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ ዶት ኮም ዘግቦል፡፡

Military Expenditure in Ethiopia is expected to reach 502.00 USD Million by the end of 2021, according to Trading Economics global macro models and analysts expectations. In the long-term, the Ethiopia Military Expenditure is projected to trend around 475.00 USD Million in 2022, according to our econometric models………..{4}

 

ምንጭ

(1)The Tigray Defence Forces – Documenting Its Heavy Weaponry

Oryx  Wednesday, September 01, 2021  Ethiopia , By Stijn Mitzer and Joost Oliemans

[2] Ethiopia’s Tigray leader confirms firing missiles at Eritrea https://apnews.com/article/international-news-eritrea-ethiopia-asmara-kenya-33b9aea59b4c984562eaa86d8547c6dd

[3] Two missiles target Ethiopian airports as Tigray conflict widens https://edition.cnn.com/2020/11/14/africa/ethiopia-airport-tigray-intl/index.html

{4} Ethiopia Military Expenditure – Forecast (tradingeconomics.com)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop