”—-መስማማት ካቃታችሁ በቃ ይገደል!—” ፊልጶስ

ከወለጋ፣ አዲስ አበባ፤ ከአዲስ አበባ ደብረ-ብርሃን፤ ከደብረ-ብርሃን አዲስ አበባ፤ ከአዲስ አበባ አርሲ፤ ከአርሲ መርሲ——- ይቀጥላል።
እቃ ወይም ኮንትሮባንድ እየተጓጓዘ አንዳይመስልን፤ ወይም የሰላም ተጓዥ፤ አንዳይመስለን። ትላንት ቤት ንብራት፣ ቤተሰብ የነበራቸው፣ አሁን ግን የሌላቸው፤ ሰርትው፣ ጥርው -ግረው ለመንግሥት ግብር እየከፈሉ የሚያድሩ፤ ከመታረድና ከመታገት የተረፋ ሰላማዊ ዜጋ ናቸው፤ የሰው ልጅ ናቸው። ግን አሁን እንደ ሰውም ሆነ እንደ ዜጋ የሚቆጥራቸውም ሆነ የሚያቸው የለም። አንድም የሃይማኖት ተቋም ወይም ስብዕና ያለው አካል ሊረዳቸው ቀርቶ መንፈሳዊ መፅናናን እንዲያገኙ ሊያናግራቸው የፈቀደ የለም።
ትላንት እንደ እኛ ሁሉም ነገር ነበራቸው። አሁን ግን አገር እንኳን የላቸውም።

ጣሊያን አገር በሮም ከተማ ውስጥ በሚገኝ የአንድ መቃብር ቦታ መግቢያ በር ላይ ” ትላንት እኛም እንደ እናንተ ነበርን።”. የሚል መልዕክት በትልቁ ተፅፎ ይታያል። የወለጋ ተፈናቃዮችም ሆኑ በአገራችን የሚታረዱትና የሚሳደዱት ትላንት እንደ እኔ ፣ እንደ አንችና እንደ አንተ ነበሩ። ‘ርግጣኛ መሆን የሚቻለው በዚህ ከቀጠልን የግዜ ጉዳይ እንጅ ፤ ነገ ቢቀር ከነገ ወዲያ ሁላችንም በየተራ የወለጋ ተሳዳጅና ተፈናቃዮች እድልም በእኛ ላይ ይፈፀማል።

አገርና መንግሥት ስሌላቸው ለምን ገዥዎቻችን የተባበሩት መንግሥታት ፈቃደኛ ከሆነ ለእነሱ አያስረክቧቸውም? ወይም በአንድ ስብሰባ ላይ አንድ አባት ሲናገሩ የሰማሁት አይፈፀምባቸውም? እኒህ አባት በአንድ ስብሰባ ላይ ለታዳሚ የተናገሩት የሚከተለው ነው፤
”ድሮ በደርግ ዘመን በአዲስ አበባ በአንዱ የቀበሌ አዳራሽ ውስጥ ነው። ስብሰባው እንድ ዳንኤል (እውነተኛ ስሙ አይደለም) ስለተባለ ወጣት፤ በወቅቱ በየቀበሌው የሚኖሩ ወጣቶች ተደራጅተው የማርክስዚም ሌኒንዝም የፓለቲካ ንቃተ-ትምህርት ይሰጣቸው ነበር። ዕድሜው የደረስ ወጣት ደግሞ የማርክስዚም-ሌኒንዝም የፓለቲካ ንቃተ ትምህርት መከታተል ግዴታ አለበት። ዳንኤል ግን በተደጋጋሚ በዚህ የንቃት ትምህርት አልተገኘምና ክስ ቀርቦበት የቀበሌው ኗሪ ህዝብ ተስብስቦ ”ምን ዓይነት ርምጃ የወሰድበት” በሚል መውያየት ተጀመረና፤ ተሰብሳቢው እየተነሳ በቅጣቱ ላይ ሃስቡን መስጠት ጀመረ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  እንደ ተከበሩና እንደ ኮሩ መሞት  - ጠገናው ጎሹ

አንደኛው ተሰብሳብ” ዳንኤል ጥሩ ልጅ ስለሆነ ምህረት ይደረግለት።” ሁለተኛው ድግሞ ”ምህረትማ አየደረግለትም አብዮቱን እየተፈታተነ ስለሆነ ሌላው ቢቀር በእስር ይቀጣ።” ሶስተኛው ቀጥለ ”እሱን አስሮ ማን ይቀልባል?
ሊላው ደግሞ ” በገንዘብ ይቀጣ።” ብሎ ሲል፤ ሌላው ” የቅጣቱን ገንዘብ የሚከፍሉት ወላጆች ናቸው፣ በዚህ የኑሮ ውድነት የት አምጥተው ሊከፍሉት ነው?”
ብዙ የቅጣት ዕይንቶች ቢቀርቡም በዳንኤል ቅጣት ላይ መስማማት ስላልተቻለ ተሰብሳቢው ማጉረምረም ሲጀምር፤ አንድ በሰል ያለ ሰውየ ጉረሮን ሞርዶ ተሰብሳቢውን ጸጥ ካደረገ በኋላ ፤
” ያላችሁትን ሁሉ በደንብ ተከታትያለሁ። በተሰጠው የቅጣት ሃሳብ ሁሉ በእንዱ እንኳ መስማማት ካቃታችሁ በቃ ዳንኤል ”ይገደል!” አለና ተቀመጠ።

እንግዲህ ለእኛዎቹ ከርታታ ዜጎች ገዥዎቻችን ምን እንደምታደርጓቸው መስማማት ካቃታችሁ፤ የደርጉ ዘመን የቀበሌ ተሰብሳቢ እንዳአሉት እነዚህ የወለጋ ተፋናቃዮች ” ይገደሉ” ፤ ከመገደል ተርፈው የመጡ አይደሉ? ምን አልባትም እኮ እነሱ በአሁኑ ሰዓት እንደ ከብት ታርደውን እንደ አውሬ ታድነው በተገደሉት ወገኖቻቸው ይቀኑ ይሆናል?

በ’ርግጥ እኛ ኢትዮጵያዊ ነን የምንል ከሚታረዱትም ሆነ ከሚንከራተቱ በባሰ በቁማችን ሞተናል። ሰው በመሆናቸው ብቻ፣ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ብቻ፣ የምድርን ፍዳ ሁሉ ሲከፍሉ እያየን የምንኖር፤ ባለሃብትም ሆነ ባለዝና ነን ብለን ልንመፃደቅ እንችላለን። በእውነቱ የጓድ መንግሥቱን ኃ/ማርያም አባባል ልዋስና፤ “ወደድንም ጠላንም በቁማችን ሞተናል።” ሞታችብ ደግሞ በየሰዓቱ፣ በየደቂቃውና በየቀኑ ነው።

በተለይም ላለፋት አራት ዓመታት ሳያቋርጥ የዘር ማጽዳት ዘመቻ ሲካሄድ፤ እንዴት እንድም የሃይማኖት ተቋም፣ ድርጅት ወይም ዜጋ ወይም የሰባአዊ መብት ታጋይ ነኝ የሚል ማስቆም ያቅተዋል? ማስቆም አይደልም ገዥዎቻችንን ቁጭ አድርጎ ”ምን እየተደርገነው’? ” ብሎ መጠየቅና፤ በዚች አገር ላይ የሚካሄደውን የዘር ማፅዳት ሊላው ቢቀር ለዓለም ህብረተሰብ ማሳወቅ ይሳናል? በእውንቱ ኢትዮጵያኖች እንደዚህ ረክሰናል? እንዲህስ አንሰናል? ነፍሳቸውን ይማረውና ጸጋየ ገ/መድህን ”እናታለም ጠኑ ” በተሰኘው ተውኔቱ ውስጥ ”አሁንስ አንሰን! አንሰን! አይጥ አከልን።” የሚል መነባንብ አለ። ግን ያኔው ዘመን የተሻለ ነበር ማለት ነው፤ አይጦች ርስ-በ’ርስ አይበላሉም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የአንዳርጋቸው አማራ የለምና የወያኔ ቤታማራን መቆጣጠር - መስፍን አረጋ

የህዳሴው ግድብ ተገደበ ተባለ። አዎ! ለኢትዮጵያዊ ከዚህ የበለጠ የሚያስደሰተው ነገር የለም። በተመሳሳይ ለኢትዮጵያዊ የአንድ ዜጋ መገደል የበለጠ የሚያሳዝነን ሊኖር ባለተገባ ነበር። አሁንማ መታረዱንም ሆነ መሳደዱን ተለማምደነው የኢትዮጵያዊነታችን መለያ አድርገነው በተገቢው መንገድ መዘገብና ዜና መሆኑ ቀርቷል።
ግድያውንም ሆነ መፈናቀሉንና መሳደዱን እንቅልፍ ነስቶን ወሬያችንም ሆነ ትግላችን በአገራችን ላይ በተሰነዘረው ሰይፍ ላይ በሆነ ነበር። ይሁን እንጅ በተለይ በዚህ ሰሞን የዮክሪንና የሩሲያ ጉዳይ በልጦብናል። በየቀኑ ግን ዮኪሪን ከሚሞተውና ከሚፈናቀለው በመቶ እጅ በበለጠ በአገራችን ላይ የሰው ልጅ ይገደላል። ይፈናቀላል። ታዲያ ”የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች” ሆኖ፤ በማያገባን ገብተን በየዩቲየቡና ድህረ-ገፁ የጦርነትና የዓለም ፓለቲካ ተንታኝ በመሆን ” የሰው ሊጥ ” እናቦካለን።

ለመሆኑ ግድብ ተግንብቶ መብራት እንዲኖረን የምንፈልገው፣ መንገድ እንዲሰራ የምናፈልገው ፣ በአጠቃላይ ብልጽግና የምንፈልገው ለማን ነው? ዜጎች የመኖር መብት ከሌላቸውና ”አገራቸው፣ አገራችሁ አይደለም” ከተባሉ እኮ፤ ነገ -ከነገ ወዲያ ያፈርሱታል። ምክንያቱም የኔ የሚሉትን ማንነታቸውንና መብታቸውን አይደለም ህይወታቸውን በጉልበተኞችና በጎሰኞች ተነጥቀዋል፤ እየተነጠቁም ነው። ዛሬ ደካማ ሆነው ፣ በገዛ አገራቸው ምጻተኛና ተቅበዝባዥ ቢሆኑም፤ በአገራቸው አገር አልባ እንደተድረጉና በማንነታቸው መታረዳቸው የማይቆም ከሆነ፤ ነገ -ከነገ ወዲያ ራሳቸውን አደራጅተው ለራሳቸው መብት እንደሚፋለሙ የሚያጠያይቅ እየደልም።
እያልን ያለነውና ሌት ተቀን የምንቃትተው ግን ይህ ለማንም አይበጅም፤ ተያይዘን እናልቃለን ነው።
የሰው ልጅ በማንኛውም መንገድ ቢሆን መገደሉና መሳደዱ መቆም አለበት። አሁንም መንግሥት ነኝ የሚለው አካል ሃላፊነቱን ወስዶ ነገ ዛሬ ሳይል የዜጎቹን መብት ያስከብር ።
ለእያንዳዱ ዜጋ መታረድም ሆነ መፈናቀል፤ ተፈናቅሎም ደግሞ መጠለያ በማሳጣት ማከራትት ኃላፊነቱ የገዥዎቻችን መሆኑን ለአንዳፍታም አትዘንጉት። ኢትዮጵያዊንም፣ ሃይማኖት አለን የምትሉ ተቋማትም ለዜጎቻችን ድምጽና ኃይል በመሆን የዜግነታችን ድርሻ እንወጣ። ገዥዎቻችን ፊት ለፊት ”በቃ” እንበላቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ ህልውና አደጋዎች

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!
———//—ፊልጶስ
የካቲት -2014

3 Comments

  1. አትልፋ ነገሩ ሁሉ የእብደት ሆኗል። ሰው ዘሩን ቆጥሮ እንባ የሚያፈስባት፤ እጅን የሚዘረጋባት ሃገር ጦቢያ ብቻ ናት። የኦሮሞ ፓለቲከኞች ሽገር ላይ እንደፈለጉ እየሆኑ አንድም ቀን በወለጋም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች የሚደረገው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ልክ አይደለም መቆም አለበት በማለት ድምጻቸውን አላሰሙም። በመሰረቱ በዘራቸው የተሰለፉ ምንም አይነት ፓለቲከኛም ሆነ የሃይማኖት ሰው ሰው አይደለም። አውሬ እንጂ። የሰው ልጅ ሰውነቱ የሚለካው ህብረ ብሄራዊ በሆኑ መልኩ ሰልፉን አስተካክሎ ሲገኝ ብቻ ነው። ያኔ ያለምንም አድሎ ለተገፉት ያነባል፤ ድምጽ ያሰማል፤ ታግሎ ያታግላል። ከዚያ ውጭ ያለው ሁሉ ፉርሽና አርዪሳዊ እይታ ነው።
    ከዘመናት በፊት አሳምነው ገ/ወልድ ደመቀ “የብካይ ነበልባል – ላልተወለደው ልጄ ማስታወሻ” ካስነበበን መጽሃፍ ላይ ልጥቀስ፡
    ” ከአባት ቆይቶ ወደ ልጅ በቃል ሲተላለፍ ቆይቶ ከእኔ የደረሰውን፤ በትምህርትም ዓለም የተገነዘብኩትን ገድለ ጦቢያ በህሊናዬ ባገላብጥ ከሰቆቃ፤ ከዋይታና ከሮሮ፤ ከጦርነትና ከጠኔ እልቂት በቀር ሌላ ምዕራፍ አላገኘሁም” ይለናል። መጽሃፉ ታትሞ ከወጣ 30 ዓመታት አልፎታል። ይህ አሁን ያለንበትን የሃገራችን ሁኔታ አይመስልም? ካለፈው ሰቆቃና መከራ የከፋ አይደለም? ሃገር ሁሉ አዲስ አበባ ብቻ ለሚመስላችሁ ወስላቶች ምን አልባት የመሸታውና የጮቤ ረገጣው ሁኔታ አደንዝዧቹሁ ካልሆነ በጦቢያ ምድር ዋይታው ብዙ ነው። የትግራይን ህዝብን ቀፍድዶ የያዘው ወያኔ ሃርነት (ባርነት) ትግራይ ልክ እንደ ጥንቱ ዛሬም እናቶችን ያስለቅሳል። ያለ እኛ ማን አለ እኛን ብቻ ስሙ ይላል። ሬዲዪ፤ ቴሌቪዥን በምንም ሂሳብ ከወያኔ የፈጠራ ታሪክ ውጭ ማውራትም አይፈቀድለትም። በአዲስ አበባ ጠ/ሚሩ ይህንም ያንም እያሉ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባ ሆኗል። ቁርጠኝነት ሁሌ በሃሳብ ከማዝገም ይመረጣል። በከተማ በገጠር ሰው ተፈራርቶና ተጠባብቆ ያለው ህግ በምድሪቱ ባለመኖሩ ነው። ለዚህም በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ከሚፈጸመው የቀንና የማታ ዝርፊያ ውጭ ሌላ ማስረጃ አላቀርብም። በዚህ ላይ በኦጋዴን፤ በሱማሊያና በሌሎች አካባቢዎች ድርቁ ከወያኔና የኦነግ ሸኔ ጋር አብሮ ሰውን ሰንጎ ይዞታል፡፤ እኮ እናንተ አሁን ጾም ጽሙ የምትሉን ፈጣሪን የት ነህ ይህ ሁሉ ግፍና መከራ ሲደርስ ብላችሁት ታውቃላችሁ? የአማራው ደም እንደ ውሃ ሲፈስ ጠ/ሚሩ ደንዝዟል፡፤ ለንገሩ ከወያኔ ጋር ሆኖ ለ 27 ዓመት ስንቶች ከእነ ህይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ ሲቀበሩ፤ ሲሰወሩ፤ ጥፍራቸው ሲነቀል፤ ብልታቸው ላይ ውሃ ሲንጠለጠልና እንጨትና መሳይ ነገር ሲገባባቸው አብሮ አይደለ የሰራው? አሁን ታዲያ ማን ይሙት የሰው ሞትና መፈናቀል ደንታ ይሰጠዋል? አይመስለኝም። አውቃለሁ ጠ/ሚሩ ክንፍ አውጥተው ይበራሉ የምትሉ እንዳላችሁ። ይሁንላችሁ። አብራችሁ ብረሩ። እኔ ግን እልፍ ጥያቄ አለኝ። እንዴት ታምራት ነገራ ሽመልስ አብዲሳን ተሳደበ ተብሎ ሃበሳውን ያያል? ሰድቦት ከሆነ ባይሰድበው ይመረጣል። ከሆነ ግን ጉዳዪ እንኳን ለእስርና ለእንግልት ለግልምጫም አያበቃም። ግን የታምራት ነገራንና የመሰሎቹን ጋዜጠኞች አቋም የጠላው የኦሮሚያ ፓሊስና ፍ/ቤት ታሳሪዎቹ የሚሉት እውነት ስለሆነ ብቻ ነው። እውነትን ደግሞ ይጠላሉ። ተው ካለፈው ደንበር ገተር ተማሩ፤ ህዝባችን ይዛችሁት ወደ ገደል አትግቡ። ይናገሩ፤ ይጻፉ፤ የክልል ፓለቲካውን አፍርሱ። ያ እስካልሆነ ድረስ ዛሬ አማራው እንደ ጫካ እንስሳ እየታደነ ቢገደልና ቢፈናቀል ነገ በሌላው ላይ እንደሚመጣ ጥርጥር የለውም። ግፍ ግፍን ይወልዳል። በሰው ደም መነገድ የበሉትን ያስታውካል። ግን ከመግቢያው ላይ ደራሲ አሳምነው እንዳለው መከራው፤ ጠኔው፤ በገዥዎች መገፋቱ አብሮን የኖረና የሚኖር እንደሆነ ነው። አይጣል። አታርድስ ነው የሚያሰኝ። ሰው መሆን እንዲህ ሆነ? የእናቶች እንባ፤ የህጻናት ለቅሶ ሰሚ አጣ? ዋ የሰማዪ ምላሽ እንኳን ቢዘገይ ምድራዊ ገሃነምም እንዳለና ድርቡሻዊ እይታ ያላቸውን ሁሉን በቀናቸው እንደሚያጋይ መታወቅ አለበት። ሰው እንሁን። የዘር ፓለቲካ ገደል ይግባ። ያኔ ሁሉም ባይሆን ይበልጡ ነገር ይስተካከላልና! በቃኝ!

  2. ፊልጶስ እናመሰግናለን ህግም ሰብአዊ መብትም ሀይማኖትም መንግስትም የሉንም። ሁሉም እንዳለፈው ሁሉ በኦሮሙማ ቅኝት ተቃኝቶ ስራውን እየሰራ ነው ጠቅላይ ሚኒስተር ሽመልስ አብዲሳ በነገሩን መሰሩት ይቀጥላል። ሰው ከየት ይምጣ ምሁር የምትለው ሽራፊ ስልጣን ስጠው ከካድሬ በላይ ጭራውን ቆልፎ ለኦሮሙማ ይዘፍናል። የበረከት በድኖች (ብአዴኖች ተሳስቼ ነው) ለገዛ ህዝባቸው የምድር መርገምት ሁነውበታል። ህግ በሌለበት ታራጅ ህዝብ ያለው ምርጫ አጥፍቶ መጥፋት መጀመር ነው። ነገሩ ቀድሞ የገባቸው ታላቁ ምሁር ፕሮፌሰር አስራት አማራውን ዝም ብትል ትገደላለህ ብትታገልም ትገደላለህ መገደልህን ለመቀነስ ገዳዮችህን ቀንድ ብለው አልፈዋል። እንግዲህ አማራው እንደ ዳይኖሰር ነበር ብለህ ልትታሰብ የቀረህ ጥቂት በመሆኑ ምርጫችን ውሰድ።

  3. ክርስቶስ የእኝህን እናት እንባ አይቶ ፍርዱን ይስጥ ጥጋባችሁን ማስተንፈሱ አይቀርም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share