የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሉዓላዊነት ባለቤት ማን ነዉ ? – ማላጂ

ዓለም ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ ምድር እና ህዝብ እንደነበር የስነ ፍጥረት እና የስነ መለኮት ድርሳናት ያስረዳሉ ፡፡

የኢትዮጵያ ዘመናዊ የግዛት አንድነት እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ መንግስት ምስረታ ከዘመነ መሳፍንት እና ከተበታተነ የሕዝብ አስተዳደር እንዲወጣ በማድረግ በዐፄ ቴወድሮስ ተጀምሮ በዐፄ ሚኒሊክ የዘመናዊት ታላቋ ኢትዮጵያ መስራች እና የጥቁር ህዝቦች የነፃነት አባት ዕዉን ሆኗል፡፡

ይህ እንዳለ ኢትዮጵያ ከ፭ ሽ ፭፻ ዘመን በላይ ያላት ምድረ ቀደምት ኢትዮጵያን እና ታላቁን ህዝበ ኢትዮጵያዊ ሲፈልጉ የአንድ መቶ ዓመት ዕድሜ  ያለዉ ዕልፍ ሲል እነርሱ ከኃዲዎች በእጃቸዉ የሰሯት አገር እና የፈጠሩት ህዝብ አስኪመስል እንደ አገለገለ ዕቃ መሸጥ መለወጥ ችለዋል፡፡

አበዉ  “ይመስላል ካሉ ፤ይወለዳል አይገድም ” እንዲሉ የኢትዮጵያን ዕዉነተኛ መሰረት እና የህዝቧን ማንነት ለመናድ በምድር ላይ የሚቻለዉን አፍራሽ ድርጊት በኢትዮጵያ ምድር እና ህዝብ ላይ የሆነዉን ከመጥቀስ ያልሆነዉን ማየት ሳይቀል አይቀርም፡፡

ከሶስት አስርተ ዓመታት በላይ ለዜጎች ጅምላ ሞት ፣ መፈናቀል እና ስደት መንስዔ  ከ1983 ዓ.ም. አስካለንበት ጊዜ ድረስ ምንጩ የት.ህ.ነ.ግ መተዳደሪያ (Manifesto) እና ህገ መንግስት መሰረት እና እንዲሁም ከዚህ ቀደም በሆነዉ አገራዊ ክህደት እና ዉርደት በግፍ እና ማንአለብኝነት ተፈፅሟል፡፡

ከህገ ኢህዴግ /ትህነግ መንግስት 1987.ዓ.ም. ጀምሮ ስራ ላይ ከመዋል በፊት ፡-

፩) በህገ – ትሓህት/ ኢህአዴግ አንቀፅ ፪ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር የሚወሰነዉ በዓለም ዓቀፍ የግዛት እና ወሰን ስምምነት መሠረት ይሆናል ፡፡ይህም የቅኝ ግዛት ዘመን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እና ህዝቦች ክብር ለመስበር የታቀደዉን የጠላት ፍላጎት ለማሳካት የታቀደዉን ሴራ ለማስፈፀም የነበር ሲሆን በዚህም፡-

  • የኢትዮጵያ አስኳል እና ማዕከል የሆኑት የኢትዮጵያ ግዛቶችን ከጎጃም መተከል ፤ ከጎንደር ወልቃይት ጠገዴ ፤ከወሎ ራያ እና አካባቢዉ ፣ እንዲሁም በሸዋ የተለያዩ አካባቢዎችን፣ በአፋር የቀይ ባህር መዉጫ ….በማሰብ እና ታላቋን ትግራይ ለመመስረት የተደረገ ክህደት ነበር ፡፡
  • ይህም ማዕከላዊ ኢትዮጵያን የማክሰም እና ኢትዮጵያዊነትን ከማንነት  ማደብዘዝ ሴራ ጥንስስ ነበር ፤ ነዉ፣
  • በኢትዮጵያዊነት እና በሉዓላዊነት ጉዳይ የማይደራደረዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በተለይ በዓማራ ህዝብ ላይ ሁሉን አቀፍ መከራ በማግለል፣ በመግደል ፣ በድህነት እና በአገራዊ ጉዳይ የበይ ተመልካች ሆነዉ ኖረዋል፣
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሞራል ዝቅጠት እና የአድርባይነት ልክፍት ፡ ጣምራ ደዌዎቻችን! - ጠገናው ጐሹ

ከዚህ ጋር ሳይጠቀስ የማያልፈዉ ነገር ኢትዮጵያ ከዓለም ቀደምት  አገር  ሆና ሳለ እና ጀግኖች ኢትዮጵያዉያን በአጥንት ክስካሽ እና በደም ፍሳሽ መስርተዉ እና ሠርተዉ ባስረከቡን አንዲት አገር ላይ ህዝቦችን  በወዳጂ እና ጠላት መፈረጂ እንደ ዋና የፖለቲካ ስልጣን ማስከበሪያ እና ማስጠበቂያ ሆኗል፡፡

በአገር ዳር ድንበር ጉዳይ በማንነት እና ወሰን ጉዳይ በግንባር ቀደም የሚጠቀስ  ጎንደር ነዉ ፡፡ ጎንደር የኢትዮጵያ አንድ የግዛት አካል ሆኖ ሳለ በኃይል እና በዝረፊያ ወልቃይት ጠገዴን በዕብሪት እና ምቀኝነት ትግራይ (ትግሬ) ወርሷል ፤ወስዷል ፡፡

ይህም በትህነግ/ ኢህአዴግ  በጎ ፈቃድ የመኃል አገር ግዛት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ እና ሱዳን ዳር ድንበር ፤ የኤርትራ ወሰን ፣ የባህር በር…የነበረዉ እና ያለው ደባ ሁሉ የሆነዉ ፡፡

ይህን ሁሉ ታሪካዊ ክህደት እና ዉርደት በህዝብ እና አገር ላይ ሲደርስ መሪ እና አስተባባሪ የሆነዉ ትህነግ/ ኢህአዴግ አሳልፎ የሠጠዉን የዜጎች መብት ፣ነፃነት እና ማንነት እና የወሰን ዳር ፤ድንበር እንዲያስከብር መጠበቅ  አጉልነት ነዉ ፡፡

ይሁን በአሁኑ ጊዜ የአገሪቷን እና ህዝብ ለዓመታት በይፋ የተካሄደዉን የማንነት ላይ ጥቃት እና የዳር ድንበር ጉዳይ ከኢኃዴግ /ትህነግ መፍትሄ ሲጠበቅ ይስተዋላል፡፡

ለአብነት ከጎንደር  -ወልቃይት ፤ ከወሎ -ራያ  አስቀድሞ ያለህዝብ ይሁንታ እና አመኔታ ባልነበረበት ለትግራይ አሳልፎ የተሰጡት በዓማራ ህዝብ ልጆች ተጋድሎ ወደ ቀደመዉ ይዞታ እና ማንነት ወደ ዕናት ምድር ኢትዮጵያ የግዛት ቋት( ጎንደር እና ወሎ) ምስጋና ለጀግኖች ኢትዮጵያዉያን ለ ፴ ዓመት የተዘረፉ እና የተለዩት ወልቃይት እና ራያ እንዲቀላቀሉ/እንዲመለሱ  ሆኗል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  "ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም' - ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ምላሽ ሰጠ

ሆኖም የኢትዮጵያ የግዛት አካል የሆነዉ ሁሉ ባለቤቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ሲሆን ለአንድ አካል ወይም ለተወሰነ የፖለቲካ ድርጂት እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡

ይሁንና የህዝብን ሉዓላዊነት ክብር እና የአገር ዳር ድንበር የህዝብ እንጂ የአንድ ዘመን የፖለቲካ ስርዓት ድርጂት ፍላጎት ማስጠበቂያ ሊሆን አይገባም፤ ህዝብም ራሱን እና አገሩን ከጥቃት እና ዳግም ሞት ለመታደግ በራሱ መደራጀት እና ህብረት መፍጠር እንጂ የጥፋት እና ክህደት መናጆ ሆኖ በሬ ካራጁ መቆም አለበት ፡፡

ኢትዮጵያዉያንን የፈጠረ ዓምላክ ፤ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያዉያን ጀግኖች አባቶቻችን ፤ቅድመ አያቶች እና መሪዎች ነበሩ ናቸዉ ፡፡

ነገር ግን በኢትዮጵያ ምድር ላይ ከቀድሞ መንግስት 1983. ዓ.ም. መገለል በኋላ ኢትዮጵያዉያን አስተማሪ ፤ ኢትዮጵያ መሪ ካጣች ድፍን ሶስት አስርተ ዓመት ባስቆጠረችበት  ዛሬም ስለ አገር እና ስለ ህዝብ የሚያስብ እና ኃላፊነት የሚወስድ  ለማግኘት መፈለግ ሞኝነት ነዉ ፡፡

የቀደሙትን የኢትዮጵያዉያን ማንነት ፣ ነፃነት እና ድንበር የሚያስከብር ራሱ ህዝብ ብቻ ነዉ ፡፡

ይህም ሲባል በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል በቅኝ ግዛት አስተሳሰብ እና በፀረ ኢትዮጵያዉያን የተከለሉት እና በአገራቸዉ የተገለሉት የጎጃም ፤ የወሎ እና ጎንደር አካባቢዎች የመመለስ ፣ የማልማት እና የኢትዮጵያን አንድነት ማስጠበቅ እና ማስቀጠል የህዝብ እንጂ የመጣ ፤የሄደዉ የየትኛዉም አካል ወይም ድርጅት ችሮታ ሊሆን አይገባም፡፡

የአንድ አካባቢ ሆነ አገር የሀብት ምንጭ ህዝብ እንጂ ፓርቲም ሆነ መንግስት ሊሆን አይችልም ፡፡ ለዚህ ነዉ የወልቃይት የሀብት ምንጭ ለማግኘት  መንግስትን ወይም ድርጅትን ብቻ ሳይሆን ዋናዉን የአገር እና የዕድገት መሰረት የሆነዉን ህዝብ ማሳተፍ ብቸኛ እና ዘላቂ መፍትሄ ነዉ ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ገንዳው - በእውቀቱ ሥዩም (አሜሪካ እንደመጣ የፃፈው)

እንኳንስ የዓማራ ህዝብ ቀርቶ በዞኑ የወልቃይት ጠገዴ የግብርና እና ሌሎች ልማቶችን እንዲሰሩእና የስራ ዕድል እና የገቢ ምንጭ በማድረግ ከዞኑ አልፎ ለክልሉ እና ለመላ ኢትዮጵያ ተስፋ መሆን ይችላል፡፡

ከዚህ ዉጭ የሠረቀን ሌባ አፋልገኝ ማለት ዘበት ነዉ ፡፡”

ከዚህ ዉጭ ባለቤት ያልሆነዉን እንዲሰጥ ፤ እንዲነሳ መጠበቅ እያዩ ከማለቅ ሌላ ፋይዳ የለዉም፡፡

 

ማላጂ

“ ዕዉነተኛ  ህልዉና  እና ነፃነት የሚረጋገጠዉ  በመተባበር እና አንድነት ብቻ ነዉ  ፡፡ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share