February 21, 2022
2 mins read

ከጉባኤ እስከ ጉባኤ – ፀጋ ዓራጌ ትኩየ

ከዛሬ ሶስት አመት ተኩል በፊት የተካሄደው የብአዴን/አዴፓ 12ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ እንደ ድርጅታችን ስም ምግባርና ግብራችን እንቀይራለን ብለን አስበን፣ የአማራን ህዝብ ጥያቄዎች ቆጥረን አንስተን፣ የጉባኤ ውሣኔ አድርገን፣ ለአማራ ህዝብ ተስፋ ሰጭ ፖለቲካዊ አቋም ይዘን ብቅ ብለን ነበር።

ማዕበል ጋላቢeee

በድርጅታዊ ጉባኤው አቋም የተወሠደባቸው የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች፦

  1. የወልቃይትና የራያ የወሠንና የማንነት ጥያቄን እንዲፈታ ማድረግ
  2. ከክልሉ ውጭ የሚኖረውን የአማራ ህዝብ መብቱ ተከብሮ በሠላም እንዲኖር፣ ተመጣጣኝ የሆነ የፖለቲካ ስልጣን ውክልና እንድኖረው ማድረግ
  3. በአማራ ህዝብ ላይ የተዘራው የጥላቻና የሀሠት ትርክትን እንዲለወጥ የሚያደርግ ስራ መስራት
  4. በሃገሪቱ ከሚካሄድ ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ከአድሎ በፀዳና በግልፅ በሚታወቅ መርህና በሚዘጋጅ የህግ ማቀፍና የአሠራር ቀመር መሠረት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
  5. አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚባል የሽግግር ጊዜ ፖለቲካዊ ፕሮግራም በማንኛውም አግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል እንድደረግ
  6. ለአማራ ህዝብ ይሁን ለኢትዮጵያ ህዝብ የችግሮች ሁሉ መነሻ የሆነው ህገ መንግስት እንዲሻሻል እንታገላለን ብለን የአቋም መግለጫ አውጥተን የጉባኤ ውሳኔ መሆኑ ግልፅ እውነታ ነበር።

ከእነዚህ የጉባኤ ውሳኔዎች ውስጥ አንዱን እንኳን ሳንተገብር ለ13ኛው ወይም ለብልፅግና መስራች ጉባኤ ዝግጅት እየተደረገ ነው። የብልፅግና መስራች ጉባኤ ለአማራ ህዝብ ምን ይዞለት ይመጣ ይሆን? አብረን የምናዬው ይሆናል።

የአማራ ህዝብ አሁን ቢያንስ ቢያንስ በቋንቋውና በደሙ ምክንያት ሞትና መፈናቀል ሊቆምለት ይገባል !!

1 Comment

  1. አቶ ጸጋ ብዙ መልእክቶች ይኖሩሀል መቼም ብአዴን ሳይበላህ ያሉህን ሰነዶች ለህብር ራዲዮና ለዘሀበሻ እንዲሁም ታማኝነት ላላቸው ወዳጆችህ ልከህ እየቆጠቡ ያውጡት ማስፈራሪያም ይሆንሀል። ስለ በረከት ስምኦን ስለ አሳምነው ጽጌ ዘርዘር አድርገህ ጻፍልን የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ነው ጉዳዩ ካሁን በሗላ ወደ ሗላ የለም። አገኘሁ ተሻገር ፣ተመስገን ጥሩነህ ጥርሳቸውን እየነከሱብህ ነው ህዝብ ላይ ተንጠላጠል። ከብአዴን ክብር ያሳምነው ጽጌ በስንት ጣእሙ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

artworks 000098629696 fezu93
Previous Story

፹፭ ኛዉ ዝክረ አደዋ ድል ታሪክ ወይስ ንትርክ? – ማላጂ

bALDERAS H
Next Story

የከሸፈውን የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ምስረታ ህዝብ እንዲቃወም የቀረበ ጥሪ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop