February 21, 2022
3 mins read

የከሸፈውን የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽን ምስረታ ህዝብ እንዲቃወም የቀረበ ጥሪ

bALDERAS H አገራችን እየደረሱባት ላሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች እና ጦርነት ዋነኛ ምክንያቶች ህገ-መንግሥቱ፣ ህወሓት እና ብልጽግና ፓርቲ እንደየደረጃቸው መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ከገባንበት ጦርነት እና ምስቅልቅል ችግሮች ለመውጣት እንድንችል ብሔራዊ ምክክር አስፈላጊ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ ስለሆነም፣ ሀገሪቱ በታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም ሂደት ላይ ትገኛለች፡፡

ምክክር ኮሚሽኑ ስኬታማ አገራዊ ሰላም እንዲያመጣ እና የአገር አንድነታችንን ለማስጠበቅ እንዲያግዝ ሂደቱ ቢቻል በገለልተኛ አካል እንዲመራ፣ ካልሆነም ደግሞ፣ የሚመለከታቸው ዋና ዋና አካላት በሙሉ ተሳትፈውበት አካታች በሆነ መልኩ እንዲመራ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ ባልደራስ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

እንደሚታወቀው፣ ችግርን የፈጠረ አካል የመፍትሄው አካል ሊሆን ቢችልም፣ የሂደቱ ዋና መሪ ሊሆን ግን በፍፁም አይገባም፡፡ ሆኖም ግን፣ ብልጽግና ፓርቲ (መንግሥት) ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ዋና ዋና አካሎች፣ ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪክ ተቋማትን እና የሃይማኖት ተቋማት አግልሎ ሂደቱን ብቻውን በማን አለብኝነት ሲያስኬድ ቆይቷል፡፡ ባካሄደው ሂደትም እጩ ኮሚሽነሮችን ለማንም ዜጋ ግልጽ የሆኑ የመምረጫ መስፈርቶች ሳያስቀምጥ ለራሱ በሚመቸው መንገድ፣ በመጀመሪያ ከ632 እጬዎች 43ቱን ለይቶ በማውጣት፣ ቀጥሎም ከ43ቱ 11 እጩዎችን አውጥቶ በማውጣት በዛሬው እለት በተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸውን አፀድቋል፡፡ ይህ ሁኔታም አገራችንን ለተጨማሪ ውስብስብ ችግሮች የሚዳርጋት እንደሆነ እሙን ነው፡፡

ለመላው የአገራችን ሕዝብ ግልጽ መሆን የሚገባው ብልጽግና (መንግሥት) ይህንን ታሪካዊ የሠላም እና የአገራችን የግዛት አንድነት ለማስጠበቅ በእጅጉ ይጠቅማል ተብሎ ተስፋ የተጣለበትን የምክክር ኮሚሽን የምስረታ ሂደት አሳታፊ ባለማድረግ፣ ኮሚሽኑ ገና ሳይመሰረት እንዲመክን ማድረጉ ነው፡፡
ስለሆነም፣ መላው የአገራችን ዜጎች ይህንን የብልጽግና (መንግሥት) በሴራ የተሞላ መንገድ በመቃወም የተበላሸውን የምስረታ ሂደት ከጎናችን በመሆን እንድትቃወሙ ታሪካዊ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ
የካቲት 14/2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop