February 10, 2022
14 mins read

ሃይማኖት የግል ነው ሃገር የጋራ ነው! ገለታው ዘለቀ

lion of judah

ማህበረሰብ የሚኖረው በተፃፈ ህግ ብቻ ሳይሆን ባልተፃፉ ቃል ኪዳኖች (Hidden Covenants) ጭምር ነው። ርእስ ያደረኩት አባባል በቀጥታ ቃል በቃል በህገ መንግስት ባይሰፍርም ነገር ግን በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ ሰፊ ቦታ አግኝቶ ዝንት አለም የሚኖር የመቻቻላችን ቃል ኪዳን ነው። ይህ አባባል በኢትዮጵያውያን ነገስታት ዘንድ እንደ መርህ ይነሳ የነበረ እንቁ ብሂል ነው። አፄ ምኒልክም አፄ ሃይለስላሴም ይከተሉት የነበረ ከዚያም በፊት የነበረ መርህ ነው። የሃይማኖታዊ መቻቻላችን መልህቅ ነው ማለት ነው።

ኢትዮጵያዊ የሆንን ሁሉ በዚህ ባህር በሆነ አለም ውስጥ ስንኖር በዘመናት መካከል ይህንን ብሂል ጠብቀን መኖር አለበን። በግድግዳዎቻችን ላይ የምንፅፈው ታላቅ አባባል ነው። እንግዲህ ታዲያ ተቻችለን መኖር እንዳለብን ትንሽ ካልኩ በኋላ በተለይ በቅርብ ጊዚያት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ግፍ በሚመለከት ትንሽ አስተያየት ልስጥ::

በብዙ አለማት ታሪክ እንደታየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖታዊ መንግስት መስርታ ሃገሪቱን ለዘመናት አስተዳድራለች። መሪዎችን አስተምራ፣ ቀብታ፣ ስታሰማራ ኖራለች ። ሁዋላም አዲሱ ትውልድ ወደ ሪፐብሊክ ልገባ ነው ሲል ጊዜ ኦርቶዶክስ ሞግዚት ሆና ያቆየችውን ስርዓተ መንግስትና የትምህርት ስርዓት ለዘመነኛው መንግስት ሙሉ በሙሉ አስረክባለች። ከዚያም ትምህርት ነፃ ሆኖ ቀጠለ……..። መንግስትና ሃይማኖት ተለዩ ተባለ……። የሚያሳዝነው ነገር ግን ይህቺን ፊደል ቀርጻ ያስተማረች ታላቅ ተቋም አዲስ የመጣው የትምህርት ስርዓት ወደ ላይ እያንጋጠጠ ያላግጥባት ጀመረ። መንግስት ደግሞ እኔና ሃይማኖት ተለያይተናል ማለቱ በጎ ቢሆንም ሃገርን እዚህ ያደረሰችውን ቤተ ክርስቲያን ማዋረድ ጀመረ። ኦርቶዶክስ ፊደል ያስቆጠረችው ሰው ኮሌጅ ሲበጥስ እሷን የሚነቅፍ መሆን አልነበረበትም። ስርዓተ መንግስት ሲቀየር ኦርቶዶክስን የሚያወግዝ ሆኖ መፈጠሩ በእውነት አሳፋሪ ታሪክ ነው። በመሰረቱ ወደ ሪፐብሊክ መሻገር ማለት የቀደመውን ስርዐት መሳደብ ማለት አይደለም። የሪፐብሊክ ሽግግር ዲሲፕሊን ይጠይቃል። እንግሊዞች ወደ ሪፐብሊክ ሲሻገሩ ዘውዳቸውን በድንጋይ ለመምታት አልሞከሩም። ባንዲራቸውን አልቀደዱም። ጨዋ ሆኖ የሪፐብሊክ ፓርላማ ማቋቋም እንደሚቻል የገባቸው በመሆናቸው እሴቶቻቸውን ጠብቀው ኖሩ። ንግስቲቱን ሳይነኩ፣ የጌቶች ቤት (The House of Lords) የሚባለውን ሳያፈርሱ ወደ ሪፐብሊክ ምዕራፍ ገብተዋል።

EWTvzCXXsAEBBC4

ብዙዎቹ በዴሞክራሲ በለፀጉ የሚባሉ ሃገራት ወደ ሪፐብሊክ ሲሻገሩ መነሻ ምልክቶቻቸውን አልሰበሩም። የስካንዲኒቪያን ሃገራትን ባንዲራ ብናይ መሃል ላይ መስቀል አለ። ዛሬ በነዚህ ሃገራት የተለያየ ሃይማኖት ቢበዛም ያንን መነሻ አሻራ ግን ካልቀደድን ሞተን እንገኛለን አላሉም። በነገራችን ላይ እንግሊዞች ባንዲራ ላይ የሚታየው መስቀል የሚወክለው ቅዱስ ጌዎርጊስን ነው። ዛሬ እንግሊዞች ዴሞክራሲ ገብቶናልና ይህንን አርማ ፍቀን እንጣል አላሉም። መነሻ ታሪክን ማክበር ተገቢ መሆኑን ተረድተዋል።

አሜሪካንን ጨምሮ ብዙ ሃገራት በህገ መንግስታቸው ፕሪአምብል ላይ ልኡል እግዚአብሔር ይመስገን የሚለውን አልሰረዙም። የምኖርበት ማሳቹሴትስ በስቴቱ ህገ መንግስት ላይ የዐለምን ጌታ እግዚአብሄርን እውቅና በመስጠት ይጀምራል። እንዲህ ይላል። “We, therefore, the people of Massachusetts, acknowledging, with grateful hearts, the goodness of the great Legislator of the universe……..” የጎረቤታችን ኬንያ

ህገ መንግስት መግቢያው ላይ ደግሞ እንዲህ ይላል “We, the people of Kenya –

ACKNOWLEDGING the supremacy of the Almighty God of all creation” እኛ ኬንያውያን የፍጥረት ሁሉ ጌታ ለሆነው ለሃያሉ እግዚአብሄር እውቅና እንሰጣለን ይላሉ።

እንድ ጊዜ አንድ ጥናት ሳይ ሃይማኖት ጠቃሚ ነው ብለው ከሚያምኑ የዐለም ሃገራት መካክል ኢትዮጵያ 98% ህዝቡዋ ሃይማኖት ዋና ጉዳዬ ነው ብሎ የሚያምን እንደሆነ ይናገራል። ይህ ህዝብ በዋናው ቃል ኪዳን ሰነዱ ወይም ህገ መንግስቱ ላይ እግዚአብሄር ሃገራችንን ይባርክ ብሎ ቢጀምር አይበዛበትም ነበር። ጎረቤት ኬንያ፣ ጋና፣ ናይጀሪያ ወዘተ በህገ መንግስታቸው መግቢያ ላይ እግዚአብሄር ይክበር ይመስገን ብለው ጀምረዋል። ይህ ማለት ሃይማኖትና መንግስት ተደባለቀ ማለት አይደለም። የህዝቡን መንፈሳዊ ፍላጎት ማክበር ነው።

ወደ ኢትዮጵያ ስንመጣ ግን እግዚአብሄር ይመስገን ማለታችን ቀርቶ የሃገር መሰረት የጣለችውን ቤተክርስቲያን የመምታት ነገር በሰፊው ይታያል። ምልክቶቻችንን፣ የሃገር አሻራዎች ሁሉ አንድ በአንድ የመምታት ነገር አለ።

ባለፈው ጊዜ “የዶክተር አብይ ፒኮክና የይሁዳ አንበሳ” በሚል ርእስ ስር ኢትኦጲስ ጋዜጣ ላይ አንድ ጦማር ፅፌ ብዙ ሰው መነጋገሪያ አድርጎት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ተቆጭቶ ለለውጥ የታገለ ብዙም አላየሁም። እኔ እንደ ዜጋ በቤተ መንግስት በኩል ሳልፍ እነዚያን ፒኮኮች ሳይ በጣም አዝናለሁ። የማዝነው ፒኮክ ከተባለች እንስሳ ጋር ፀብ ኖሮኝ አይደለም። ብዙ አመት በውጭ ሃገራት ብኖርም ፒኮክ ያየሁበት ጊዜ የለም። እኔን የሚያሳዝነኝ አንበሳ እኮ ብሄራዊ ምልክት ነበር። እንዴት በምን ሂሳብ ዛሬ በእኔ ትውልድ ይህ ይሞከራል በሚል ነው። ድሆች ብንሆንም አንበሶች ነን። ኢትዮጵያን እዚህ ያደረሰው የሰሎሞንን ስርወ መንግስት ታሪክ ማዋረድ ምን ይባላል? ሞአ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ የሚለው ታሪክ እኮ በታሪክነቱ መቀመጥ አለበት። እንዴት እንደዚህ ይሰራል? አንድ ጊዜ ለገሃር የነበረውን ሃውልት መጫወቻ አድርገውት ባየን ጊዜ ልናፀዳ ሄደን ነበር። ይሁን እንጂ ፖሊሶች ጠራርገው እስር ቤት አጎሩን። በዚህ ታሪካችን ላይ ያለው ጥላቻ በጣም አሳሳቢ እንደሆነና እዚህ ጫፍ እንደደረስን የሚያሳይ ክስተት ነበር።

ሁሉም እንደሚያውቀው ደርግ ሶሻሊስት ነኝ፣ ሃይማኖት ጠል ነኝ ብሎ ነው የተነሳው። ይሁን እንጂ መንግስቱ ሃይለማርያም ይኖርበት የነበረው ቤተ መንግስት አጥር ላይ የነበረው የንጉሱ ስም፣ የዳዊት ኮከብና የአንበሳውን ምልክት መንግስቱ ምክር ሰምቶ አልነካም ነበር። ዛሬ በዚያ አካባቢ ሳልፍ በነዚህ ታሪካዊ ምልክቶች ላይ አንዴ አሮጌ ቆርቆሮ ጭነውበት አንዴ ምናምን አልብሰውት ሳይ አፍራለሁ። ታሪካችንን ማክበር አለብን ጎበዝ።

በአሁኑ ጊዜ የባህልና ስፖርት ሚንስትር የሆኑት አቶ ቀጀላ መርዳሳ የሰጡትን ኢንተርቪው እያየሁ ነበር። እኚህ ሰው ሲናገሩ “እኔ የኢትዮጵያን የቀድሞውን (እረንጉዋዴ፣ ቢጫና ቀዩን) ባንዲራ የማልቀበለው ቢጫው መደብ የኦርቶዶክስ ምልክት ስለሆነ ነው” ይላሉ። ያሳፍራል። በእውነት እኔ ይህንን ታሪክ አላውቅም። ይሁንና ቢሆንም እኮ መነሻ ታሪክ፣ የሃገር ታሪክ እኮ ነው። ኦርቶዶክስ በታሪካችን ውስጥ ባላት አሻራ ልትመሰገን ይገባል እኮ። ሌላው ቢቀር ይህ ታሪካዊ ባንዲራ ዛሬ በየሰልፉ ሊከለከል አይገባም እኮ።

ዛሬ ዛሬ ኦርቶዶክስ ላይ ያነጣጠሩትን ጥቃቶች ሳጠና ጥቃቱ ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆን በዋናነት ለሃገር ያበረከተችውን አስተዋፃ የሚያቀል፣ ምልክቶችን የሚያጠፋ ሆኖ አያለሁ። የሃገርን መሰረቶች የመምታት ስራዎች ሲሰራ በሰፊው ይታያል። ይህ ደግሞ አደጋ አለው። ይህቺ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ሰአት ጥቃት በዝቶባታልና ሁላችን ከጎኗ ልንቆም ይገባል። ካህናቶቿ በነፃነት ያገልግሉ፣ ታሪካዊ አሻራዎቿ ይከበሩ፣ ምእመኗ በሰላም ያምልክ። በቅርብ የተነሳው የመስቀል አደባባይ ጥያቄም ይመለስ። የይዞታ ማረጋገጫዋ ይሰጣት። በየቦታው የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት ይታደሱ። ኦርቶዶክስ እሴቶቿን መጠበቅ፣ መንከባከብ መብቷ ነው። መንግስት ጥያቄዎችን በቅጡ ሳይፈታ ነገር እየጎተተ ባያመጣ መልካም ነው። በፕሮቴስታንቱና በኦርቶዶክስ መካከል ግጭት በመጥመቅ ደጋፊ አገኛለሁ የሚል ሴራ አይሰራም። ኦርቶዶክስ ስትጠቃ ፕሮቴስታንቱ ከጎኗ ሊቆም ይገባል። የዚህች ቤተ ክርስቲያን ጥቃት ጥቃቴ ነው ማለት አለበት። ሙስሊሙ ማህበረሰብም እንዲሁ በኦርቶዶክስ ላይ ግፎች ሲበዙ ድምፁን ማሰማት አለበት። ሃገር የጋራ ነው ሃይማኖት የግል ነው እንደምንለው ሃይማኖታዊ ልዩነታችን በአንድ ሃገር ልጅነታችን ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። ነገር ግን ኦርቶዶክስ እንደ ተቋም በትር ሲበዛባት ሁላችን ልንመክት ይገባል።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop