February 5, 2022
20 mins read

ብልፅግና ሆይ ወይ ሥምህን ቀይር ። ወይም ደግሞ ድህነትን ማስፋፋትህን አቁም!! – ሲና ዘ ሙሴ

272762622 471319214552162 7545406059116084000 n  ሰሞኑንን የማፍረስ ዘመቻ በአዳማ አንዳንድ ቀበሌዎች እየተካሄደ ነው ። የማፍረስ ዘመቻውንም እያከናወነ ያለው የከተማው አሥተዳደር ነው ። አሥፈፃሚዎቹም ለፀጥታና መረጋጋት ይበጃሉ ተብለው ከየጎጡ የተመለመሉ እጅግ የበዙ ሥራ ፈቶች ናቸው።  በእርግጥ  አንዳንድ የመሥተዳድሩ አካላትም በብልፅግና ሥም ራሳቸውን የሚያበለፅጉ ቀምቶ በሎች እንጂ ሠርቶ በሎች እንዳልሆኑ ስለሚታወቅ በዚህ ተግባር ላይ ተሠማርተዋል  ።እናም  ይኽ የማፍረስ ዘመቻ   የሥራ ፈቶች ዘመቻ በመሆኑ አንድ ታታሪ ሰው ፣ ምን ያህል እንደሚለፋ እና ለኑሮዎ መቃናት እንደሚደክም ሥለማይረዱ በማፍረስ እና መልሰው ጉቦ በመቀበል በማሠራት እንደ ወያኔ ዘመን ልምዳቸው ማሥራተቸው ሳይታለም የተፈታ ነው ። ይኼ ፣ ትላንት ያሥተዋልነው ፤ ውሃ ቅዳ ፣ ውሃ መልስ ተግባር ነው  ። ይኽ የማፍረስ ዘመቻ በሥራ ለምናምን ብዙዎቻችን አሥከፊው ፀረ _ ብልፅግና  ዘመቻ እንለዋለን ።

ይኽ  ፀረ _ ብልፅግና   ዘመቻ ፤ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ያለው   ፣  በየመንገዱ ዳርና ዳር ፣ ከተከራዩበት ቤት ውጪ ፣ ጊዚያዊ  ጥላ ሰርተው ፣ ቤት ገንብተው ፣ የፀሐይ መጠለያ ሰርተው ሸቀጦቻቸውን   ዘርግተው ፣ እየሸጡ ባሉ ግለሰቦች እና እነሱን ከለላ አድርገው ፣ ሲኒ ደርድረው ቡና በመሸጥ ላይ የነበሩትን በእጅጉ የጎዳ ነው  ። በዋና መንገድ ላይ ወንበር ደርድረው ፣ ይኽንን ደሃ ህዝብ ሥጋ እየበሉ ና ውስኪ እየጠጡ  የሚያሥጎመጁትን ፣ “ ወደ ንግድ ቤቱ ግቡና ያሻችሁን ፈፅሙ ። ይኽ ነፃ ቦታ የእናንተ በረንዳ አይደለም  ።” በማለት ለውበት አሳማሪ _ ሊስትሮዎችና ለመንገድ ላይ ቡና አፍይዎች የተዋበ መጠለያ በጎዳና ላይ ወይም  ጥገ አላይም በፓርክ ውሥጥ ቦታ ሰጥቶ  ሥራ አጥነትን ፣ ሥራ በመፍጠር ፣ ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ የማይጥር ፤ የከተማ አሥተዳደር ፣ ለብልፅግና ቆሜያለሁ ማለት እንዴት ይችላል ?

በበኩሌ “ የከተማው መሥተዳድር ፣ ነገ ከተማው ሲለማ ፣ ፎቅ እየተሰራ ቅርፅ በሚይዘው ከተማ ፣ ምንም ዓይነት እግረኛ የማይጎዝበትን  ፣ በጭርቁስ ቤት የተሞላን የጎዳናንን ዳርና ዳር ፣ ዳስና በረንዳ ማፍረሱ ተገቢ ና ፍትሃዊም አይደለም ። “ እላለሁ ። ለዚህ ድህነትን የማሥፋፋት ፣ ድርጊትም የምንጃር ጎዳናንን በዋቢነት አቀርባለሁ   ።     “ በተለይም  08 እና 07  ቀበሌ ውሥጥ የሞሉት ጭርቁስ ቤቶች በጊዚያቸው በልማት የተነሳ መፍረስ ላይቀርላቸው ለምን ዛሬ ብዙ ሺ ሥራ አጦችን በውሥጣቸው አካተው ሣለ በዘመቻ መልክ የማፍረስ ተግባር ሊከናወንባቸው ቻለ ?  “ በማለትም እጠይቃለሁ ።

እነዚህ ሁለት ፣ ቀበሌዎች ያለሙና  እጅግ የበዛ ህገወጥ ግንባታ ያለባቸው ናቸው ። 08 ሙሉ ለሙሉ የህገወጥ ገብያ መናህሪያ ነው ። ሙሉ ለሙሉ ” ጉልት ነው ።” ማለት ይቻላል  ። ዜሮ ሰባትም ከ08 የማይሻል የምንዱባኖች የዕለት እንጀራ ማግኛ  ቀበሌ ነው ።

እነዚህ ሁለቱ ቀበሌዎች ፣ የሚለወጡት ፣ በአገሪቱ ሠላምና መረጋጋት ሰፍኖ ፣መንግሥትና ህዝብ ወደልማት ፊቱን ሲመልስ እንደሆነ ይታወቃል ።በወቅቱ  በልማት ፣ ሥለልማት ከተባለ ደግሞ ፣ ለጉልት ቸርቻሪዎች ፣ ሌላ ህገዊ ሆነው የሚሰሩበት ፣ እራሳቸውን ጠቅመው አገሪቱንም በግብር ክፍያ የሚጠቅሙበትን ፣ መንገድ በማመቻመች  ቸርቻሪዎቹን ወደ ሌላ የገብያ ማዕከል መጠለያ ( ሼድ ) ሰርቶ ማዛወር እንጂ ፤  ብት ፈልጉ ዲንጋይ ብሉ ብሎ ፣ ከየጉልቱ ጠራርጎ ማንሳት የሚፈጥረው የራሱ የማይቀለበስ ችግር እንደሚወልድ የታወቀ ነው ።  እናም  ተለዋጭ  ሥፍራ  ሳያዘጋጁ  መነካካት አላሥፈላጊ አይመሥለኝም ። ለራሱ ሰው ኑሮ ጭቅላቱን አዙሮታል ። ተጨማሪ ትንኮሳ ፣ ሆድ ለባሰው ጩቤ ማዋስ እንደሆነም መንግሥት አያውቅም ማለት አይቻልም ።

“ትላንት  ፣ በአማራና  አፋር የደረሰውን መፈናቀል እኛም እንደግመዋለን ! ” ነው እንዴ ነገሩ ? … ።በበኩሌ ፣ “ ይኽ የማፈናቀል ዘመቻ ፣ ህዘብን ለማስቀየም እና የብልፅግና መንግሥትን የድህነት መንግሥት አድርጎ ለመሣል የተወጠነ ነው ። ሌበነት ፣ ለማኝነት ፣ ጎዳና ተዳዳሪነትን  ለማበራከት እና እንደገና በሁከትና በብጥብጥ መንግሥት እንዲተረማመስ  ና ሀገር እንዲፈርስ ለማድረግም በህግ ማሥከበር ሥም የተተኮሰ የመጀመሪያው ሠላም አደፍራሽ ጥይት ነው ። “ ብዬ ለማመን እገደደለሁ ። ይኽ  ድርጊት  መወገዝ ያለበትና በአስቸኳይ መቆም ያለበት ውጉዝ ተግባር  እንደሆነም አሰምርበታለሁ ።

ይኽ ውጉዝ ተግባር ፣  በእግረኛ መንገድ ማፅዳት ሥም ፣  በመሐል ከተማ በጎርፍ መውረጃዎች ውሥጥ የተከማቸውን ግማት ፣ ማዘጋጃ ቤቱ  ሳያፀዳ ፤ በሥራ ፈትነት አልያም ለሥውር ጥቅም ፣ አልያም ለሥውር ሤራ  የገባባት የማፍረስ ተግባር  ከሆነ ደግሞ እጅግ አሣፋሪ ነው ።

( እኔ የለሁበትም የየቀበሌው ካድሬዎችና አጫፈሪዎቻቻቸው ናቸው ካለ ደግሞ ፤  በማዘጋጃ ቤቱ አንፈርድም ። )

እንዴ ! ሆን ብሎ ሠርቶ የሚበላውን ህዝብ ፣ የመሥሪያ ሥፍራውን እያፈራረሱ ፣ መሥለቀሥ ምን የሚሉት ህግና ደንብ ማሥከበር ነው ?  ለሚሰራ ሰው ቀድሞ ቦታ ሳያመቻምቹ   እነሱን ተገን አድርገው የዕለት እንጀራቸውን የሚያገኙትን የመንገድ ላይ ቡና አፍይ እህቶቻችንን እንጀራ መሣጣትሥ  የሚጨበጨብለት ተግባር ነውን ? ¡¡ ከምናፈናቅላቸው በፊት  ለሠራተኛ ዜጎች  ተገቢ መፍትሄ ማሥቀመጥ የአሥተዳደር ነኝ ባዩ ፤ የመንግሥት ሹም ኃላፊነት ነበር ። ይኽ አሥተዳደር የመንግሥት የታችኛው አካል መሆኑንም መዘንጋት አልነበረበትም ።

ዜጎች  ይህ  የታችኛው  የመንግሥት አካል ፣ ፖሊሥን እና ሥራ ፈት የጎጥና የቀበሌ ጭፍራዎቹን ይዞ ” ኃይ በለው ” በማለት በዘፈቀደ ፣ ከጎዳና ላይ ዜጎችን “ቢፈልጉ አፈር ይብሉ ። ምን አገባኝ ። አሥጨንቄ ኋላ ትርፍ አገኛለሁ ። …”በማለት መንቀሳቀሱን ያውቃሉና ፣ ቅሬታቸው አገርን በመምራት ላይ ባለው መንግሥት ላይ መሆኑንን ከፍተኛው የመንግሥት አካል ማወቅ አለበት ። ብዙ መልካም አማራጮችን እና ገቢዎችን ማግኛ መንገድ እያለ ፣ በደቀቀ ኢኮኖማ ፣ ዜጎችን በሥራ አጥነት ማድቀቅም ነውረኝነት ነው ። መሥተዳድሩ ድብቅ ሤራ ባይኖረው ፣ ወይም የዕውቀት ደሃ ባይሆን ኖሮ ፣ ዜጎች ፣ ባልተገነነ ኪራይ ፣ ሰርተው የሚለወጡበትን ፣ የመንገድ ጥግ  ፣ ቡና ማፍያ  ፣ በአማረ መልኩ ሠርቶ በማከራየት ፣ ማዘጋጃቤቱ ገቢ ማግኘት ይችል ነበረ እኮ ! !

ለምሳሌ ፣ ለጫማ ውበት ጠባቂዎች ፣ መንገዱን የሚያሥውብ የፀሐይ መከላከያ ና መቀመጫ ፣ በየመንገዱ በመሥታወቂያ አገልግሎት ፣   በየመቶ ሜትሩ በማሠራት ፣ ለማዘጋጃ አገልግሎት     ፣ በየወሩ በባንክ  እንዲከፍሉ በማድረግ ገቢውን ማሳደግ ይችል ነበር ። ህዝብን ዝቅ ብለው በማገልገል ፣  የዕለት እንጀራቸውን  በማግኘት  ላይ ያሉትን ፣ አገርን ጠቃሚ ማድረግ ሲገባ ፣ ማሳደድ ተገቢ ና ትክክል አይደለም ። በዚኽኛው ዳር መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሲሰራ ” የእኔ ወገን ነው ። ”  ብሎ መተው ፣ በወዲያ በኩል ተመሣሣይ ሥራ የሚሰራውን በነጋ በጠባ ” መጣሁብህ !  ንብረትህን እወርሳለሁ !! ” ብሎ ማሥፈራራት የሰው ተግባር አይደለም ና ሊወገዝና ባሥቸኳይ እንዲቆም ቀጭን ትዕዛዝ በሚመለከተው ባለሥልጣን ሊሠጥበትም  ይገባል ።  …

( በአዳማ ከተማ ፣ በዋናው ንግድ ባንክ ፊት ለፊት ፣ በፓርኩ  መሐል ፤ በኮብል እስቶን መንገዱ ጥጉን ይዘው የሚሰሩትን ሊስትሮዎች ፣ እንዳይሰሩ መከልከል በበኩሌ ፣ ዘርፋችሁ ፣ ሠርቃችሁ ፣ ለምናችሁ ወዘተ ። ብሉ እንጂ ሠርታችሁ አትብሎ ማለት ነው ።

ሥለ ህገ ወጥ አሠራር መወገድ ከተነሳ   ፣ ከወያኔ አገዛዝ ጀምሮ ህግን መጣሥ የተለመደ እና የሚበረታታ ሆኖ መገኘቱ እየታወቀ ። በዋነኝነት ይህን የህገ ወጥ መድረክም የከፈቱትና ለመላው ከተማ ኗዋሪ ያሥተማሩት  እነሱ መሆናቸው እየታወቀ ፣ ዛሬ ደርሶ ይህንን ውሥብሥብ ህገ ወጥ ድርጊት ፣ ህጋዊ ና ሁሉንም ያካተተ ባልሆነ የጉልበት መንገድ ፣ ቦታ እየለዩ  ማፍረስ ህገ ወጥ አሠራር ነው ። በቅድሚያ ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ ፣ ለእነዚህ ህገ ወጥ ድርጊቶች ፣ ምን ዓይነት ህጋዊ መፍትሄ በናቅድና ፣ይህንን እቅድ ለመተግበር የሚያሥችል ሀብት ከነማን እናገኛለን ብሎ ማሰብ ሊቀድም ይገባል ። ለሁሉም ነገር ፣ ለከተማ ፅዳቱም ቢሆን በቆሻሻ ለተሞላው አርጂን ዘላቂ መፍትሄ ለመሥጠት ፣ በችግሩና በችግሩ አፈታት ዙሪያ የሚመለከታቸውን ምሁራንን ያካተተ ውይይትና እቅድ እጅግ አሥፈላጊ ነው ።

የከተማ ውበትና ፅዳት የሚመለከታቸው ና የሚቆረቁራቸው ፣ የበኩላቸውን ለማዋጣት ዝግጁ የሆኑ ምሁራን ከተማዋ አላጣችም ።  ደግሞም መታወቅ ያለበት ፣  መላ አዳማ ፣ በአራቱም አቅጣጫ ፣  በጨረቃ ቪላ ቤቶችና ደሳሳ ጎጆዎች  የተሞላች ፣ እና የአካባቢውም ውበት ፣ በእጅጉ የቆሸሸበት ሥፍራ   መኖሩ እንግዳ አይደለም ። እናም  ህገ ወጦች ባለ ጨረቃ ቤቱች ፣  ቢያንስ ግብር የሚገብሩበትን መንገድ መመቻቸት ወይም ወደ ህጋዊ መንገድ ማምጣት እንዲቻል የመፍትሄ አቅጣጫ ሊያሥቀምጡ የሚችሉት እነዚህ ምሁራን እንደሆኑ መገንዘብ ያሥፈልጋል  ።  ቆሻሻ በሚከማችበት የጎርፍ መውረጃም ከአካባቢው ባለሀብት ጋር በመነጋገር ፣ የጎርፍ መውረጃው ፣ ቆሻሻ በማይደፋበት መልኩ ፣ በወጉ  የማገነባበትን መንገድ ሊቀይሱ የሚችሉት እነዚህ ምሁራን ናቸው  ።

ይኽን የከተማዋን ገፅታ ያበላሸ ፣ ማሀል ከተማ ውሥጥ የሚታይ አሥጠሊታ ቆሻሻ ለማሶገድ ፣ መላው የከተማን ህዝብ አሥተባብሮ ወደ መፍትሄ መግባትን ተቀዳሚ ሥራው ከማድረግ ይልቅ ነገ በልማት አሥገዳጅነት የሚሥተካከሉትን እና ከሥራቸው ጋር የብዙ  ሺ ሠርቶ በሌዎችን ጉሮሮ የሚያረጥቡ ፣ የሥራ መድረኮችን መዝጋት በአሁኑ ሰዓት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነውና የብልፅግና መንግሥት ድህነትን ከማሥፋፋት  ና በፀሐይና በቁር አቦራ ለብሰው ጎንበስ ብለው ጫማችንን በማሣመር የሚተዳደሩትን ሊስትሮዎች እና ትኩስ ቡና ለደሃው አዘጋጅተው በርካሽ ዋጋ ጀባ የሚሉንን ወደ ድህነት አረንቋ ተመለሠው እንዲገቡ ከመጫን እንዲቆጠብ በፅኑ እንመክራለን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop