February 5, 2022
11 mins read

ይድረስ፡ ያቶ ደመቀ ኦነጋዊነት ለማይታያችሁ ዓይነ ግንባሮች – መስፍን አረጋ

demekeአቶ ደመቀ መኮንን ወሎ የኦሮሞ ነው በሚለው በኦነጋዊው በዐብይ አሕመድ ስብከት ታውሮ ወደ ኦነጋዊነት ተቀይሮ፣ ከመምህሩ ደቀመዝሙሩ እንዲሉ ከራሱ ከዐብይ አሕመድ በላይ ጽንፈኛ ኦነጋዊ ሁኖ፣ የኦነጋውያንን ፀራማራ አጀንዳ ከዐብይ አሕመድ በበለጠ ጽንፈት እያራመደ እንደሆነ፣ ጉዳዩ በይበልጥ ለሚመለከተው ለአማራ ሕዝብ በተለያዩ ጦማሮች ለማሳሰብ የተቻለኝን ሞክሬያለሁ፡፡  የአማራ ሕዝብ እየተመራ ያለው የሕልውናው ቀንደኛ ጠላት በሆነ ኦነጋዊ ነው በማለቴ ደግሞ የተወሰኑ ሰወች መረጃህ ምንድን ነው ሲሉ ጠይቀውኛል፡፡

ከጠየቁኝ ሰወች ውስጥ አብዛኞቹ ዐብይ አሕመድ ጥቁሩን ነጭ ቢላቸው ምንም ሳያንገራግሩ አወ ነጭ ነው የሚሉ ዓይኔን ግንባር ያርገው ባዮች እንደሆኑ ባውቅም፣ ጥቂቶቹ ግን ቅና አሳቢወች ሊሆኑ ስለሚችሉ ጥያቄውን ማስተናገድ የግድ ነው፡፡  ጥያቄው ግን የመረጃን ምንነት በውል ካለመረዳት የመነጨ (እንደ ደራሲ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ብሽቅ ጥያቄ ባልልም) የዋህ ጥያቄ ነው፡፡

አብዛኛው ሰው መረጃ ሲባል የሚያስበው በድበቅ የወጣ ንግግር ወይም ቪዲዮ ነው፡፡  ከመረጃወች ሁሉ የሚበልጠው ትልቁ መረጃ ግን በዐይን በብረቱ የሚታይ፣ ማንም ሊክደው የማይችል የተግባር ውጤት ነው፡፡  ያቶ ደመቀ መኮንን የተግባር ውጤት ደግሞ ያለምንም ጥርጥር የሚመሰክረው ግለሰቡ የለየለት ፀራማራ ኦነጋዊ መሆኑን ነው፡፡  የአማራ ሐዝብ መሪ ነኝ እያለ፣ ይህ ሁሉ የኦነግና የወያኔ መርገምት በአማራ ሕዝብ ላይ ሲወርድበት ዝንብ የሞተ ሳይመስለው ድመጹን አጥፍቶ የተቀመጠው ፀራማራ ስለሆነ ብቻ ነው፡፡

ዐብይ አሕመድ የአማራን ሕዝብ ረክዞ ከወያኔ ጋር ካርታ የሚጫወት ቁማርተኛ ሲሆን፣ ጆከሩ ደግሞ ደመቀ መኮንን ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ ስልጣን ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ፣ በአማራ ሕዝብና መሪወች ላይ የፈጸማቸውንና ያስፈጸማቸውን ሁሉንም ወንጀሎች፣ አንዳቸውንም ሳይቀር ሊፈጽምና ሊያስፈጽም የቻለው ጆከሩን ደመቀ መኮንንን ስለያዘ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ዐብይ አሕመድ የአማራን ሕዝብ አይንቁ ንቀት ንቋል፡፡  ትልቁን የአማራን ሕዝብ የናቀውን ያህል እጅግ አናሳ ናቸው የሚባሉትን አኝዋኮችን ወይም ኔኡሮችን አልናቀም፡፡  የአማራን ሕዝብ በዚህ ደረጃ ሊንቅ የቻለው ደግሞ የአማራ መሪ ነው የሚባለው ግለሰብ፣ ሲጠራው አቤት፣ ሲልከው ወዴት የሚል አፋሽ አጎንባሹ፣ ንከስ የሚለውን የሚነክስ፣ ላስ የሚለውን የሚልስ ታዛዥ ውሻው እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ርግጠኛ ስለሆነ ነው፡፡

ዐብይ አሕመድ የደመቀ መኮንንን ሙሉ ድጋፍ ባያገኝ ኖሮ ከዲባቶ አምባቸው ህልፈት በኋላ ጃንደረባወቹን እነ ተመስገን ጡሩነህን በአማራ ክልል ላይ በመሾም ክልሉን የኦነጋውያን መሳቂያና መሳለቂያ ለማድረግ ባልቻለ ነበር፡፡  ዐብይ አሕመድ በደመቀ መኮንን ሙሉ በሙሉ ባይተማመን ኖሮ አማራወች በወለጋና በመተከል ባሰቃቂ ሁኔታ እስኪጨፈጨፉ እየጠበቀ፣ ምንም እንዳልተፈጠረ በመቁጠር በዕለቱ ወይም በማግስቱ እየወጣ ሕንጻ በመመረቅና አበባ በመትከል በአማራ ሕዝብ ቁስል ላይ እንጨት አይሰድም ነበር፡፡  ዐብይ አሕመድ የደመቀን እሽታ ባያገኝ ኖሮ፣ ወያኔና ኦነግ ድሽቃ በታጠቁበት ሰዓት የአማራን ጓንዴ ለመንጠቅ ባልዛተ ነበር፡፡

ዐብይ አሕመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከደመቀ መኮንን ጋር ሙሉ ስምምነት ባይኖረው ኖሮ፣ የአማራ ሕዝብ በወያኔ እሳት እየተለበለበ ባለበት ሰዓት፣ በጀርባ በኩል ከወያኔ ጋር ለመደራደር ባልደፈረ ነበር፡፡  አለበለዚያማ አቶ ደመቀ መኮንን እንደ ዐምዱላ (ኮሎኔል) ጎሹ ወልዴ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱን በፈቃዱ ለቆ ብአዴንን ከብልጽግና በማስወጣት የዐብይ አሕመድ መንግሥት እንዲንኮታኮት ማድረግ ይችል ነበር፡፡

እርግጥ ነው፣ ዐምዱላ ጉሹ ወልዴና አቶ ደመቀ መኮንን ሰማይና መሬት ናቸው፣ ዱባና ቅል እየቅል እንዲሉ፡፡  ደመቀ መኮንን፣ በእውቀቱ ብዙም ያልገፋ በዚያ ላይ ደግሞ የሚያውቃትን በደንብ መግለጽ የማይችል አንደበተ ግድር (challenged) ከመሆኑም በላይ በራስ መተማመን የሚባል ነገር ምናምኒትም እንደሌለው በግልጽ ያስታውቅበታል፡፡  በዚያ ላይ ደግሞ ኃላፊነትን እንደ ጦር የሚፈራ የጃግሬነት (የተከታይነት) ሰብዕና የተጠናወተው ሰው ነው፡፡  አንድ ታዋቂ ግለሰብ ‹‹ አቶ ደመቀ መኮንን ጠቅላይ ሚኒስትር ሁን ቢሉት፣ ምን አመጣችሁብኝ ብሎ የቤተ መንግስቱን አጥር ዘሎ ይጠፋል›› ሲል የተናገረው ንግግር የአቶ ደመቀን ሰብዕና ቁልጭ አድርጎ ይገልጻል፡፡  ያቶ ደመቀን ዓይነት ለጀሌነት የተፈጠረ ሰው በሐሰተኛ ትርክት አደንዝዞ ፍጹም ተከታዩ ለማድረግ ደግሞ በሐሳዊ ተዋኝነት (con artist) ወደር ለሌለው ላጭበርባሪው ዐብይ አሕመድ በጣም ቀላል ነው፡፡

የዐብይ አሕመድ ቋሚ መርሕ በሬ ሆይ ሞኙ ሆይ ነው፡፡  ዐብይ አሕመድ አያሌ አንቱወችን እንዲያምኑት እያደረገ በደንደሳቸው የጣለ ጮሌ ፈረስ ነው፡፡  በመሆኑም፣ እንኩቶውን ደመቀ መኮንን ባፍጢሙ ደፍቶ በኮቴው እየረጋገጠ ኦነጋዊነትን አምኖ ተቀብሎ፣ እሱን (ማለትም ዐብይ አሕመድን) ዋቆ እንደቀባው እንደ ሰባተኛው ሉባ ተመልክቶ ፍጹም ታዛዡ እንዲሆንለት ለማደረግ ምንም አያስቸግረውም፡፡

እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በተኛበት ይጨፈጨፍ የነበረው የአማራ ሕዝብ፣ ተጨፍጭፎ ከማለቁ በፊት መነሳሳት መጀመሩ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡  ሆ ብሎ ከተነሳና ትክክለኛ መሪ ካገኘ ደግሞ ወያኔና ኦነግ እድሜያቸው ከሳምንታት ቢበልጥ ከወራት እንደማይዘል እነሱ ራሳቸው ያውቁታል፡፡  የአማራ ሕዝብ የሕልውናው ቀንደኛ ጠላት በሆነ ኦነጋዊ መመራቱን እስከቀጠለ ድረስ ግን ሕልውናውን ማጣቱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ ለሕልውናው ሲል አስቀድሞ ማድረግ ያለበት ከዐብይ አሕመድ ወይም ከደመቀ መኮንን አንዱን ከጫንቃው ላይ ማውረድ ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ዐብይ አሕመድን ከጫንቃው ላይ ካወረደ፣ ደመቀ መኮንንና ብአዴኖች ድምጥማጣቸው ይጠፋል፣ ብአዴን ለጀሌነት እንጅ ለመሪነት አልተፈጠረምና፡፡  የአማራ ሕዝብ ደመቀ መኮንን ከጫንቃው ላይ ካወረደ ደግሞ ዐብይ አሕመድ ይንኮታኮታል፣ ዐብይ አሕመድን ሙሉ በመሉ ቀጥ አድርጎ የያዘው የደመቀ መኮንን ብአዴን ነውና፡፡

ዐብይ አሕመድ አማራን ቆረጣጥሞ እየበላ ያለ ኦነጋዊ አውሬ ቢሆንም ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ ብአዴኖች ናቸው፡፡  ከጥርሶቹ ውስጥ ደግሞ ክራንቻወቹ (ማለትም አማራን የሚዘነጣጥልባቸው በግራና በቀኝ ያገጠጡት ሁለቱ የፊት ጥርሶቹ) ደመቀ መኮንን እና ተመስገን ጥሩነህ ናቸው፡፡

 

መስፍን አረጋ

[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop