አትሌት ሽህ አለቃ ደራርቱ ቱሉ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላለፈች

271768136 467583928065275 4460507138807850360 n
ጀግናዋ አትሌት ሽህ አለቃ ደራርቱ ቱሉ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት ታህሳስ 29/2014 ዓ.ም ከእስር ለተፈቱት እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣ቀለብ ስዮም እና አስካለ ደምሌ” እንኳን ደስ ያላችሁ፤እንኳን ለቤታችሁ አበቃችሁ” በማለት መልካም ምኞቷን ገልፃለች። አትሌቷ ከእስር ለተፈቱት አመራሮች መጭው ጊዜአቸው የተቃና እንዲሆን እና ኢትዮጵያም ሰላሟ፣አንድነቷ እና ክብሯ እንዲመለስ ያላትን ምኞት ገልፃለች።
የባልደራስ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ በበኩሉ አትሌት ሽህ አለቃ ደራርቱ የፓርቲው ፅ/ቤት ድረስ ቃሏን አክብራ በመልካም መንፈስ በመገኘት ይህንን እውቅና በመስጠቷ ከልብ አመስግኗል። በተጨማሪም “በቀጣይ በኢትዮጰያ ሰላምና ልማት ይሁን። ሲል መልካም ምኞቱን ገልጿል። ሌሎች ከእስር የተፈቱ የፓርቲው አመራሮች አትሌቷ ቃሏን አክብራ በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በመገኘት “የእንኳን ደስ ያላችሁ”መልዕክት በማስተላለፏ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል።
Source Balderas

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.