ከዚህ የእሥር መቋረጥ በሥተጀርባ የተጠነሰሰ ታልቅ ሤራ እንደነበረ ወደፊት ገለፅ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ። ወደፊት እነ ጃሥ የራሳቸው ኃይለኛ ሤራ እንደሚኖራቸውም ይገመታል ።
ክሳቸው የተቋረጠላቸው እነ ጃሥ ( ጃዋርና ሥብሐት ) ቆጥሮ ለመጨረሥ ዓመታትን የሚያሥቆጥር ረብጣ ብር እንዳላቸው የታወቀ ነው ና የሤራ ፖለቲካቸውን እሥር ቤት አቅደው ዛሬ ከእሥር ውጪ ለመተግበር ክሳቸው ተቋርጦላቸዋል ። እናም ፣ በሤራ ፖለቲካ ፈረሥ እየጋለቡ ፣ እነዚህ የቢሊዮን ዶላር ባለቤቶች በታላቅ ጥንቃቄ ና ምሥጢር ሥራ አጡን ፣ በንቃተ ህሊናው ዝቅተኝነት ተጠቅመው ለጥፋት ዓላማቸው ሊጋልቡት ና ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ የአገር አውዳሚነት ተግባር ሊያሠልፉት ይችላሉ ። ምናልባትም የ1969/70 ዓ/ም ቀይ ና ነጭ ሽብርን በሌላ መልኩ ሲደገም እናይ ይሆናል ። ይኽ ከሆነ ደግሞ ። ” ኢትዮጵያ ወይም ሞት ! ” የምንል ይኽ አገር አጥፊ ድርገት ሲከሰት እንደ ቀደመው ጊዜ ፣ እጃችንን አጣምረን አንቀመጥም ።
ጉዳዪ የሞት የሽረት ትግል በመሆኑ በተጋድሎ ለመሰዋት ዝግጁ እንሆናልን እንጂ፣ እንደ ቀድሞው የገዛ እጃችንን አሥረን በማጅራታችን አንታረድም ።
ይኽ የጥቂት የመንግሥት ከፍተኛ አመራር ሥህተት ብዙዎቻችን በማጅራታችን እንድንታረድ ለጠላቶቻችን አሣልፎ እንደሰጠን እናውቃለን ። እንዲህ አይነቱ የህፃን ድርጊት ይፈፀማል ብለን ከቶም አላሰብንም ። እኛ ተናንቀን ለመሞት የምንችለውን ብቻ ሣይሆን የወለዱንን አያሌ እናቶች የኽ መብረቃዊ ውሳኔ አሥደንግጧቸዋል ። ከተረጋጉ በኋላም አብይን እንደወደድንህ ጠላንህ ።
ልባችን ውሥጥ ነበርክ ከልባችን ወጥታሃል ሲሉ በጆሮዬ ሠምቻለሁ ። እናት ሠላምን አጥብቃ እንደመሻቷ ፍትህም በአገር እንዲነግሥ በብርቱ ትፈልጋለች ። እናም በፍርድ ቤት ደረጃ ፣ በችሎት ተከራክረው ፣ በወንጀል የተጠረጠሩት “ እነ ጃ – ሥ “ ( ጃዋርና ሥብሐት ) ከተመሠረታቸው ክስ ነፃ ናቸው ። ” ተብለው ቢፈቱ ኖሮ እንዲህ ልባቸው አይሰበርም ነበር ። የፍርድ ቤት ውሳኔ በመሆኑ እና በግልፅ ጥፋተኛ አይደለንም ብለውየሚከራከሩበትን ጭብጥ ህዝብ ሥለሚያቅ ። የሁን እንጂ ፣ የፍርድ ሂደቱን ፣ ብልፅግናን ለመሪነት ያበቃው ህዝብ በአንክሮ እየተከታተለ ሣለ ና የጀግኖች ልጆቻችን ደም ሣይደርቅ ፣ በቀጥታ ከጦርነት አውድማ ላይ የተማረኩትን ነፍሰ ገዳዮች ክስ ና በአማራ ደም የተጨማለቀ እጅ ያላቸውን የሰው ጭራቆች ክሥ ማቋረጥ ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንድ ና ሴትን የወለዱ እናቶችን ልብ መሥበር ነው ። ዛሬም ሰው መሆንን በካዱ የእንስሳ ጭንቅላት ባላቸው ፣ ደንቆረዎች አያሌ ንፁሐን ዜጎች እንደ በረሮ እየተቆጠሩ እየሞቱ ነው ። ጠ/ሚ አብይ አህመድ የሰጡት ምላሽም የጲላጦስን ያህል አያረካም ።
በነገራችን ላይ ጲላጦስ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመልቀቅ ይፈልግ ነበር ። ህዝቡ ግን “ ሥቀሎ ! ሥቀሎ ! ይሳቀል ! ይሰቀል ! “ ብሎ በመጮሁና ወንበዴውን ፣ ጨካኙን ባርባን እንዲፈታ በመጠየቁ ባርባንን ፈቶ ኢየሱስን ለእነሱ ለማሥረከብ ወሰነ ። ሆኖም እኔ ከደሙ ንፁነኝ ። ለማለት እጁን በአደባባይ ታጠበ። እናም እንዲሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው ። ይኽ እውነት የሚያሥተምረን መሪ ምንጊዜም የህዝብን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ዝግጁ ካልሆነ ፣ ህዝብ ቢሳሳት እንኳን ከጎኑ ከልቆመ አወዳደቁ የከፋ እንደሚሆን ነው ። ህዝብ ከጫፍ እሥከጫፍ ግልብጥ ብሎ ከሥልጣን ውረድ ቢልህ ምን ታደርጋለህ ? ከሥልጣን ከመውረድ በሥተቀር ። ይልቁኑስ ማረኝ ፣ በድዬሃለሁ ። እምነትህን በልቻለው ። ብሎ በአደባባይ ይቅርታ መለሠን ያዋጣል ። እንደ እውነቱ ከሆነ ፣ ጠለ/ሚ ክስ ማቋረጥ ብቻ ሳይሆን በፍፁም ምህረት ከእሥር ቤት መፍታት ያለበት ፣ ለሰዎች ሰብአዊ መብተ ና ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ተሞጋቺ ጋዜጠኛ እሥክንድር ነጋ ብቻ ነበር ። ከእርሱ ጋር በርባኖችን ደባልቆ መፍታቱ ጠ/ሚ አብይን ጲላጦስ አያሰኘውም ። …
ከዚህ አንፃር ክስ የተቋረጠላቸው የተፈቱበት ግልፅና አሳማኝ አይደለም ። ይላል ህዝብ ። ጠ/ሚሩም የሰጡት ምላሽ እጅግ የተምታታ ነው ። ወንጀለኛ በዕድሜው ና በጤና ችግር የተነሳ ይፈታ ከተባለ በሺ የሚቆጠሩ እሥረኞች ከኦቦይ ጋር መፈታት ነበረባቸው ። …
ደሞም አንዳንድ የምናከብራቸው ምሁራን እንደሚሉት ፣ ይኽ የንግድ ወይም የፖለቲካ ቢዝነስ ጉዳይ አይደለም ። “ እናተርፋለን ። እንከሥራለን ። “ የሚባል ጉዳይ እዚህ ላይ አይሰራም ። ወዳጄ በህይወት ጉዳይ ውሥጥ ቃላት ሥንጠቃ ና አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁም ቦታ የላቸውም ። ጉዳዩ እኮ ፣ ህይወታቸውን ገብረው የአፋርና የአማራን ህዝብ ነፃ ያወጡ ፣ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጉዳይ ነው ። የጥቃቱ ሰለባዎች የአፋርና የአማራ ልዩ ኃይል ጉዳይ ነው ። የአማራ ፋኖ ና የአፋር ወጣት አርበኞች ጉዳይ ነው ።ይኽ ጉዳይ የኢትዮጵያ ፍቅር የሚያንገበግባቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ የእሸቴ ሞገሶች ጉዳይ ነው ። ይኽ ጉዳይ የጥቂት ተሸላሚ ጀግኖች ጉዳይ ብቻም አይደለም ። ጉዳዩ ልጥቂት ከሞት የተረፉ ጓዶቻቸው የጦር ሜዳ ጀብዷቸውን የሚመሠክሩላቸው በይፋ ያልተሸለሙ ፤ በይፋ ሥማቸው ያልተጠራ ፤ የአያሌ የጦር አመራሮች ፣ የአያሌ መሠረታዊ ወታደሮች ደም ና አጥንት ጉዳይ ነው ። ይኽንን መሠዋትነት ያቃለለ መሪ ለአንድ ቀንም ቢሆን ሥልጣን ላይ መቆየት የለበትም ። ማንም ከኢትዮጵያ በላይ አይደለምና !!!!!!!!!! )
በነገራችን ላይ ኦቦይ በግል አብይን ይቅርታ መጠየቅ አለባቸው ። ዶክተሩም ፣ ይቅር ለእግዜር ሊሏቸው ይችላሉ ። ዶ/ር አብይ በኦቦይ ሥብሐት በግልፅ ተሰድበዋል ። የጨዋነታችን ሥነ ምግባር ሥለማይፈቅድልኝ የኦቦይን ሥድብ አልደግመውም ። በዚህ ሣቢያ ግን ዶ/ር አብይ በኢትዮጵያ ጠ/ ሚኒሥተርነታቸው ፣ የአውሬ ና የጭራቅ ድርጅትን ደግፈው ፣ ዘግናኝ ድርጊት በመከላከያ ላይ ” ሀ ” ተብሎ የፈፀም ዘንድ አባሪ ና ተባባሪ ሆነው መቀሌ ከተማ ሰዘባነኑ እና ውሥኪ ሲራጩ የነበሩትን ፣ ሰውነትና የሰው ክብር ምን እንደሆነ የማይገነዘቡ ደናቁርታት ክስ እንዲቋረጥ ማድረግ ግን አይችሉም ።
” አይ ! ነገሩ ወዲህ ነው ። አሜሪካ በምላሹ ፣ ኢትዮጵያን ወደ አገዋ ( AGWA ) መልሳ በማሥገባት እንደ መንግሥት ከተደቀነባት ዘርፈ ብዙ ችግር አንዱ ና ዋንኛውን እቀርፍላቸዋለሁ ፣ ብላ ቃል በመግባቷ ነው ። ” ከተባለም ፣ እርሱ ሱሚ ነው ። አሜሪካ የደርግ ጀነራሎችን በፎርጅድ ዶላር ሣይቀር ገዝታቸው እንደነበር አሥታውሥ ። ሲአይ ኤ እንደ ኬጂቢ በራሱ ሰው አይቀሳቀሥም ። እንቅሥቃሴው በራሳችን ሆዳም ምሁራኖች ፊት አውራሪነት የሚታገዝ ነው ። ይኽም ከቅኝ ገዢነት ና ተገዢነት ልምድ የተወሰደ አሠራር ነው ። ቅጥረኞችም ዶላር ና ምቾት አምላካቸው የሆነ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ናቸው ። የልጆቻቸውና የሚስቶቻቸው የእረፍት ጊዜ ፣ አሜሪካና ዱባይ እንዲሆን የሚሹ ።በጥቂት ወራት ቢሊዮነር ለመሆን የሚፈልጉ የሲአይኤ ልጆች ናቸው የአሜሪካ መንግሥትን ግብ የሚያቁት ።
የሲአይኤ ቲያትር ዛሬ ነው ግልፅ ሆኗል ። ይኽንን ቲያትር አሣምረው የሚያውቁት እነሥብሐት በአሜሪካ ሚሥጢራዊ ሠራተኞች ( ተላላኪዎች ) በታላቅ ምሥጢር በመጠቀም ከእሥር ተፈተዋል ።
እንደምታውቁት ከአሸባሪ ድርጅት ጋር አሜሪካ አትደራደርም ። ይሁን እንጂ የእኛን ህግ ና የፍትህ መንገድ ፈፅሞ አትቀበልም ። አሜሪካ ሁሌም የምታየው ጥቅሟን ሥለሆነ ሆዳም ና ደንቆሮ በለሥልጣናትን ( ከጥበብ የራቁ ለማለት ነው ።) በገንዘብ ና በጥቅማ ጥቅም በመግዛት ፣ የብዝበዛ መንገድ ለማግኘት ብርቱ ጥረት ታደርጋለች ። ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ ። የሚለውን ጥቅሥ እዚህ ላይ አምጣው ። ከመጣኸው ዘንድ የነሥብሐትም እሥር ከጅምሩ ድራማዊ ነበር ። ሾ ነበር ። እንዴት ብትል ፣ ለሽብር ተሠልፈው ፣ ለጥፋት ሠራዊቱ ለትህነግ ወታደራዊ ክንፍ ፣ የሞራል ሥንቅ በመሆን ፣ በአፋርና በአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጥፋት ካደረሱ በኋላ ፣ ለዘላለም ለመኖር አቅደው እኮ ነው ፤ ከገቡበት ዋሻ ለመውጣት የፈለጉት ። ከቢሊዮን ያላነሰ ብር እያለኝ እዚህ ዋሻ ውሥጥ በችግር ና በችጋር ለምን እሞታለሁ ብለው ፤ የነገ መውጫቸውን በማሥላት እኮ ነው ፣ እጃቸውን የሰጡት ። በብር ወደ ጥልቁ ታዝለው ገቡ በዘዴ ከጥልቁ ወጥተው በቂሊንጦ ሆቴል በታላቅ እንክብካቤ ኗረው ፣ ዛሬ፣ ወደ ተደላቀቀ ቪላቸው በክብር ተሸጋገሩ ። …
በሚገረም መልኩ ፣ ከምቾትና ከመድሃኒት አቅርቦት አንፃር ፣ ህይወታቸው አደጋ ላይ በመውደቁ ፣ ራሳቸው ያሉበትን ቦታ እንዲጠቆም በመፍቀድ መልክተኛ ልከው ፣ በታላቅ ጥንቃቄ በመከላከያ ሠራዊታችን ፣ ” ከጥልቁ ምሽግ ” ታዝለው በመውጣት ፣ ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ፣ ድራማዊ በሆነ መልኩ ፣ እጃቸው በሰንሰለት ታሥሮ ካየን በኋላ ፣ ወዲያው ደግሞ ቁጭ ብለው እየሳቁ ቁርጥ ሥጋ ሲበሉ በኢቲቪ ያየነው እውነታ እዚህ ላይ አክለህ ፣ እውነቱን ተረዳ ። ተረዳህ ? ግባልኝ !!
እናም የኢትዮጵያ መሪዎች እራሳችሁ ተሞኝታችሁ እኛን አታሞኙ ። የአሜሪካ መንግሥት የሚፈልገው ፣ በእፍኝ ሰጥቶ በቁና መቀበልን ነው ። እናም በሰፊው ለመበዝበዝ ፍቃደኛ ሁኑ ። ቻይናንን ፊት ንሱ ። የአሜሪካ ካምፓኒዎችን በከርሰ ምድርህ ሀብታችን ላይ አሰማሩ ። ለ1% ቱጃሮች ቢዝነሥ ዋሥትና ሥጡ ። በመንግሥት ሁሉም ፖሊስ ላይ ፣ ፈላጭ ቆራጮቹ እነሱ እንዲሆኑ አድርጉ ። ይኽንን ካደረጋችሁ ዓለም በጎናችሁ ታልፋለች ። ( ጥቂቶቻችሁ አሜሪካና አውሮፓ ለዘር ማንዘራችሁ የሚሆን የግል ትውልዳችሁ ሳይለፋ ፣ ሳይጥር ና ሳይግር ተደላቆ የሚኖርበት ቢሊዮን ዶላር ይኖራችኋል ።) ሲአይ ኤ ለራሱ ከምፓኒዎች ጥቅም ሲል መከላከያን ያዘምናል ። በአፍሪካ ከግብፅ ቀጥሎ ፈርጣማ ጡንቻ ያለን ተከባሪ ና ተፈሪ ጦር እንድንገነባ ያግዛል ። ከኤርትራ ጋርም በኮንፊደሬሽን ማዋሃድ ለእርሱ ቀላል ነው ። ሁሉን በነሱ ቁጥጥር ካደረግህ ፣ ሁሉን እንደሚሰጡህ ዕወቅ ። እነሱ ናቸውና የባህር በር ያሳጡህ ፤ መልሰው ራሳቸው የሚቆጣጠሩት የባህር በር ያሰጡሃል ። በአፍሪካ ውሥጥ የትኛውም የባህር በር የእንግሊዝ ፣ የፈረንሳይ የአሜሪካ ና የጀርመን ጥቅም ማግኛ መሣሪያ ነው ። ደግሞም በሤራ ቲዎሪ ራሻና ቻይና ጫፋቸው አይደርሱም ።
የአሜሪካ ሤራ ደግሞ ከሁሉም የላቀ ነው ። በቢሊዮን ዶላር የሚታገዝ ከመሆኑም በላይ እጅግ የረቀቀ ነው ። ሤራው ከላይ ባነሳሁት ” የቢሆናል ሃሳብ ” ብቻ የሚቋጭ አይምሰልህ ። ሌላም የቢሆን ሃሳብ አለኝ ።
አሜሪካኖቹ በሲአይኤ አማካኝነት አንድ ሺ አማራጭ ፣ የሤራ ረቂቅ ይዘው ነው የሚደራደሩት ። የሤራ ረቂቅ ንድፉም ፣ በየጊዜው የሚከለሥ ነው ። እቅዱም ራሱን የቻለ ቡድን ና አሥፈላጊ የሆነ የሎጀሥቲክ ድጋፍ ያለው ነው ። ዋና መሪው ደግሞ ሲአይኤ ነው ። ( መአከላዊው የአሜሪካ የስለላ ድርጅት ) እንበልና ፣ ከሲአይኤ ከአንድ ሺ አንድ እቅዱ አንደኛው ዕቅድ ደግሞ ጠ/ሚር አብይ አህመድን በቅጥር ነፍሰ ገዳይ ማሥገደል ና ፣ ሁነኛ የአሜሪካ መንግሥት ሎሌ ወይም በሪሞት ኮንትሮል የሚያንቀሳቅሱት አሻንጉሊት መንግሥት በመንበሩ ማሥቀመጥ ቢሆን እና ይህንን የነፍስ ግድያ እቅድን ሲተገብሩ የሚያሳይ ረቂቅ የአኒሜሽን ቪዲዮ ለጠቅላዩ ቢያሳዮቸው ፣ ጠቅላዩ ይኽንን እውነት ከተረዱ ” የት ድረሥ መሄድ እንደምትችሉ በቪዲዮ ምሥል ተደግፋችሁ ካሳያችሁኝማ ፣ ቻይናም ሆነች ሩሲያ እኔን ማዳን እንደማይችሉ በበቂ ሁናቴ ተገንዝቤያለሁ ። ትዕዛዛችሁን ለመፈፀምም ዝግጁ ነኝ ። ” ቢሉ ምን ይገርማል ።