ትላንት ተደስቼ እስቲ ይሁን ብዬ በምስጋና ዜማ
በ ሐሴት ጨፍሬ
ዛሬ ደግሞ ከፋኝ በሚሆነው ሁሉ ህልም እየመሰለኝ
አንገቴን ሰብሬ
ሰማይ ተደፋብኝ እውነት እርቃብኝ እራሴን ጠላሁት
እስከመፈጠሬ
እንቆቅልሽ ሆኖብኝ ቋንቋው ተለየብኝ የገጠመኝ ነገር
ቅኔው ያልተፈታ
ይኽው ዘመን ገፋሁ በሐገሬ ጉዳይ ላይ ነገር ሥተበትብ
ስቋጥር ስፈታ
እራሳችን ዞረ አረ በቃ በለን የአለም ሁሉ ገዢ እውነተኛ ዳኛ
የሰራዊት ጌታ
ወንድሜን ቀብሬ አባቴን አጥቼ ሐገር ጉድ እስኪለን
ከሀዘን ሳንወጣ
ሰርጎ አገባኝ የወንድሜ ገዳይ የተገላቢጦሽ
የአባቴ ባላንጣ
እስቲ ምን ይባላል ለሰሚው ግራ ነው በእኛ የደረስው
የዘንድሮው ጣጣ
ጠላትና ወዳጅ በአንድ መአድ ቀርበው በስመእብ ብለው ባርከው
ገበታ እየበሉ
አስመስሎ ማድርን ደም እየተቃቡ በጥርስ እየሳቁ
እንዴት ይችላሉ
ሌባውና ዳኛው እኩል ተቀምጠው እንዴት ሊገፋ ነው
ህዝብ እየበደሉ
እድላችን ሆኖ ዘመን ተፈራርቆ አንዴ ስንደሰት ደግሞ እንደገና
በሐዘን ስንከፋ
ለሐገር ክብር ብሎ ጀግና ለወገኑ አንድ ነፍሱን ሰጥቶ
በጥይት ሲደፋ
ደግሞ መከራችን የራሳችን ዳፋ ግዙፍ ገበናችን ይኽው አሳቀቀን
አንገት እያስደፋ