የኦሮሞ ህዝብ አዲስ የፖለቲካ ትግል ምዕራፍ!

271626476 468996638087991 2651423884159750237 n 11ኛ/ በመጀመሪያ በህገ ወጥ ሴራ እና ሸፍጥ በእስር ቤት ላላፉት አንድ አመት ከስድስት ወራት በላይ በግፍ ለተጉላላችሁ እነ ጀዋር መሃመድና በቀለ ገርባን ጨምሮ፣ ለሁሉም የኦሮሞ የፖለቲካ መሪዎች እንኳን በሰላምና በጤና ከአሰቃዮቻችሁ እጅ ወጣችሁ ማለት እንወዳለን። የታሳሪዎች ቤተሰብ፣ ወዳጅና ዘመድ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።
2ኛ/ አሁንም የኦነግ የፖለቲካ አመራሮች ስላልተፋቱ፣ እነዚህ የፖለቲካ ታሳሪዎች እንዲፋቱ ሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ግፊት ማድረጉን እንዲቀጥል ጥሪ እናቀርባለን!
3ኛ/ የፖለቲካ አመራር ያልሆኑ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኦሮሞዎች በፖለቲካ ምክንያት ብቻ ታስረው በመላው አገርቷ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።አሁንም ደግመን ሁሉም የኦሮሞ ፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥሪ እናቀርባለን!
4ኛ/ ከእስር የተፈቱትም ሆነ በውጭ ያሉት የኦሮሞ ፖለቲካ መሪዎች፣ ይህ አዲስ የፖለቲካ ትግል ምዕራፍ መሆኑን አውቃችሁ፣ ለድርጅታችው ወይም ለምትወክሉት ቡድን፣ ወይም ለፖለቲካ ስልጣን ሳይሆን፣ በአደጋ ላይ የወደቀውን ኦሮሞ ህዝብን ህልውና ለመታደግ የተቀናጀና በህዝባችን ብሄራዊ ጥቅም ላይ ብቻ የተመሰረተ ወጥ የጋራ አመራር ወደ መስጠት እንድትሸጋገሩ አጥብቀን እናሳስባለን!
5ኛ/ መላው የኦሮሞ ህዝብ በፊቱ የተደቀነው ትግል የህልውና ትግል ፣ ወይም እንደ ህዝብ የመኖርና ያለመኖር ትግል መሆኑን ተገንዝቦ፣ በፖለቲካ ድርጅት፣ በሃይማኖት ወይም በአከባቢ ሳይከፋፈል፣ በአንድነት እንደ ህዝብ፣ በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ፣ እራስን የማዳን የህልውና ትግሉን እንዲመራ ጥሪ እናቀርባለን!

Birhanemeskel Abebe Segni

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.