አሸባሪው፣ የአማራ ቄስ ብልጽግና ነው በሚል ካህናቱን ማረዱን የደብረጸሐይ ሐሙሲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርቲያን ካህናት ገለጹ

በሰሜን ወሎ ዞን ኮን ወረዳ ሐሙሲት ከተማ በምትገኘው በደብረጸሐይ ሐሙሲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑ ሁለት ካህናት ብልጽግና ናችሁ በሚል ብቻ በግፈኛው አሸባሪ ቡድን እንደታረዱ ካህናት ተናገሩ።
የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ የሆኑት ዲያቆን ዳዊት መኮንን፣ መሪ ጌታ ተፈራ ጉባይ እና ቄስ ጌጤ ያለው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች እንደተናገሩት፤ መንግሥት በመንግሥትነቱ ያስተዳድራል፤ ገበሬውም ምርቱን ያመርታል። ቄሱም እንዲሁ በቅስናው በማገልገል ምዕመኑን ከክፉ እንዲመለስ ያደርጋል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ዛሬ ቀሳውስቱ በአደባባይ ይታረድ ይዟል። በስፍራው ለበርካታ ጊዜ ሲያሰቃያቸው የነበረው ግፈኛውና ወራሪው ቡድን፣ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋይ የሆኑት ቄስ ደጀኔ ወልዴና ቄስ ወዳጄ ጌታ ተገድለዋል።
ዲያቆን ዳዊት እንደተናገሩት ከሆነ፤ ወራሪው ጁንታ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሞርታር የተባለውን መሳሪያ አጥምዶ እንዳትቀድሱ በማለት ሲያስፈራሯቸው ቆይተዋል። ይባስ በብሎም በቤተክርስቲያን ውስጥም ተጸዳድተዋል። ቅርሶችን አውድመዋል። የአማራ ቄስ በሙሉ ብልጽግና ነው በሚል ካህናትን.
….

(ኢ ፕ ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  የናቁትን «አረዳ» ሊጎበኙ መጥተው  «አረዳ ጠባቂ» ብሎ ጠባቂውን መናቅ ምን ይሉት እውቀት ነው?

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share