ከወልድያ ወደ ቆቦ የሚወስደው የአላውኃ ድልድይ በአሸባሪው ወራሪ ቡድን ወድሟል

አሸባሪ ቡድኑ በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ መሰረተ ልማቶችን አውድሟል፤ የሕዝብ መገልገያዎችን ዘርፏል፤ የሽብር ቡድኑ ዕኩይ ዓላማውን ለማሳካትና ከወገን ጦር የደረሰበትን በትር መቋቋም ሲሳነዉ ድልድዩን አውድሟል።
አሸባሪው የሕወሓት ወራሪ ቡድን የአለዋ ድልድይን ጨምሮ በርካታ መሰረተ ልማቶችን እያወደመ ሄዷል፡፡
ወራሪው ኃይል በአለዋ ድልድይ ላይ ያደረሰውን ጉዳት በዘላቂነት ለመጠገንና የጉዳት ደረጃውን ለመመልከት ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣንና ከአማራ ክልል የመንገድ ፈንድ የሥራ ኃላፊዎች ተጎብኝቷል፡፡
በአማራ ክልል ከሐይቅ ወደ ውጫሌ መግቢያ ያለን ድልድይ በስካፋተር ቆፍሮ ንዲወድም አድርጓል። ከወልዲያ ከፈረጠጠ በኋላም የአለዋ ድልድይን በከባድ መሳሪያና ፈንጅ በመታገዝ አውድሟል።
ድልድዩን ቶሎ ወደስራ ለማስገባት የሚያስችል ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ሲሆን፤ ድልድዩ አፋጣኝ ጥገና እስኪደረግለትም አማራጭ መንገድ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ የኢፕድ ዘጋቢዎች ተመልክተዋል።
(ኢ ፕ ድ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  አዲሱ አረጋ ከለገጣፎ መልስ የጻፉት ጽሁፍ

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share