“ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደ አፋር ጎጆ ማፍረስ ቀላል አይደለም” ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

 የጉምሩክ ኮሚሽን በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን ወረራና ጥቃት ጉዳት ለደረሰባቸው የልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ አባላትና ሌሎችም ወገኖች ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን የተቀበሉት የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳደር አወል አርባ ኮሚሽኑ በኅልውና ዘመቻው እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ በአፋር ሕዝብ ልብ ውስጥ ለዘላለም ተከትቦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
“ኢትዮጵያን ማፍረስ እንደ አፋር ጎጆ ማፍረስ ቀላል አይደለም” ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ወራሪው የሕወሓት ቡድንን ጀግናው የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአፋር ሕዝብና ልዩ ኃይል መቆሚያ መቀመጫ እያሳጡት እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽር ደበሌ ቀበታ በበኩላቸው አፋር የሰው ልጅ መገኛ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያነቱ የማይደራደርና ሕዝቡንና ድንበሩን የማያስደፍር የጀግኖች መገኛ በመሆኑ ይህንን አገር ወዳድ ሕዝብ በችግሩ ጊዜ መቆም እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡
ኮሚሽኑ ከአሸባሪው ሕወሓት ቡድን ወረራ በተጨማሪ ሌሎችም ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት ላደረሱባቸው የፀጥታ አካላትና ሌሎችም ዜጎች በአጠቃላይ የ262 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ጥቅምት 29/2014 (ዋልታ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ መርሀፅድቅ መኮንን የአማራ ክልል ኘሬዝዳንት የህግ አማካሪ በዶክተር ይልቃል ከፋለ ከስራው መባረሩ ተሰማ

1 Comment

  1. አወል አርባ መልካም ሰው ሁነው ፎቷቸው ወንጀለኛው አረጋዊ በርሄን ስለሚመስለኝ ቅር ይለኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share