የአንቶኒ ብሊንከን መግለጫ ዋና ጭብጥና የዐብይ አሕመድ ሚና

Antony Blinkenበአቶ ብሊንከን (Anthony Blinken) የሚመራው ያሜሪቃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ‹‹የኢትዮጵያን ግጭት ባስቸኳይ የማቆም አስፈላጊነት›› (The Urgent Need to End the Conflict in Ethiopia) በሚል ርዕስ ጥቅምት 18፣ 2014 ዓ.ም (November 4, 2021) ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡

የመግለጫው ጭብጥ አንድና አንድ ብቻ ስትሆን፣ እሷም መግለጽ በማያስፈልጋቸው ግልጽ ሐቆች መካከል የተሰነቀረችው ‹‹የኢትዮጵያ መንግስት ዘር ተኮር ሚሊሻወችን ክተት ማለቱን እንዲያቆም›› (We call on the Government of Ethiopia to halt its … mobilization of ethnic militias) የምትለው ናት፡፡

ወያኔ አማራን ለማጥፋት ከከተተና ከዘመተ ወራቶች እንዳለፉት ላቶ ብሊንከን መንገር አያስፈልግም፡፡ የኦሮሞ ክልልም እንደዚሁ ባያሌ ዙሮች ያስመረቀውን ከፍተኛ ሠራዊቱን እስካፍንጫው አስታጥቆ፣ ዝግጅቱን ሙሉ በሙሉ አጠናቆ፣ በተጠንቀቅ መጠባበቅ ከጀመረ ወራቶችን ማስቆጠሩን አቶ ብሊንክን አሳምሮ ያውቃል፡፡ ስለዚህም የአቶ ብሊንከን መግለጫ የሚመለከተው አማራንና አማራን ብቻ ነው ማለት ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ እስካፍንጫቸው በታጠቁት በወያኔና በኦነግ የሕልውና አደጋ ስለተጋረጠበት፣ አደጋውን ለመቀለበስ መክተት፣ መዝመት ጀምሯል፡፡ አቶ ብሊንከን ደግሞ ክተት፣ ዝመት ማለትህን አቁመህ እጅህን አጣጥፈህ ተቀመጥና አስቀድመው በከተቱትና በዘመቱት በወያኔና በኦነግ ተጨፍጨፍ ይለዋል፡፡

የአቶ አንቶኒ ብሊንከን መግለጫ ዋና ጭብጥ ይሄውና ይሄው ብቻ ነው፡፡ የዚህ መግለጫ ፍሬ ሐሳብ ሊመነጭ የሚችለው ደግሞ ከሌላ ከማንም ሳይሆን ወያኔና ኦነግ እስካፍንጫቸው እስኪታጠቁና አማራን ለማጥፋት በወለጋና በወሎ አቅጣጫ እስኪዘምቱ ድረስ ድምጹን ካጠፋ በኋላ፣ አማራ ራሱን ለመከላከል መነሳሳት ሲጀምር፣ ባደባባይ ወጥቶ አትክተት፣ አትዝመት ካለው ከኦነጋዊው ከዐብይ አሕመድ ነው፡፡

ደጋግሜ ለማሳሰብ እንደሞከርኩት፣ አቶ ብሊንከን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የተመለከተን ማናቸውንም መግለጫ የሚያወጣው ከዐብይ አሕመድ ጋር ከተመካከረና ቢያነስ በተወሰነ ደረጃ የሐሳብ ስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ ብቻ ነው፡፡ የአቶ ብሊንከን መልዕከተኞች ሳመንታ ፓወርና ጀፈሪ ፌልትማን አዲስ አበባ ሲመጡ፣ ዐብይ አሕመድ በአካል አግኝቶ የማያነጋግራቸው፣ በስልክ የጨረሰውን ሻጥር ለማስተባበልና የአማራን ሕዝብ ለማታለል ሲል ብቻ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ከያኒ ታሪኩ ጋንኪሲ (ድሽታጊና) አትክተቱ፣ አትዝመቱ ብሎ ባደባባይ እንዲቀሰቅስ ያሳመነውና ያመቻቸለት ራሱ ዐብይ አሕመድ ቢሆን እንጅ ባይሆን አይገርመኝም፡፡ የዐብይ አሕመድን ያጭበርባሪነት ክሂሎት አለማድነቅ አይቻልም፡፡ ዘመቻን የሚቃወም መልዕክት በታዋቂ ከያኔ ለማስተላለፍ ሲል፣ ለዘመቻ የሚያነሳሳ አስመስሎ ሰልፍ በመጥራት፣ ብዙ ሺ ወጣቶችን ባደባባይ የመሰብሰብ ሐሳብ ሊመጣለት የሚችለው ሰይጣን ወይም የሰይጣን ቁራጭ ብቻ ነው፡፡

ዐብይ አሕመደ ከመቀሌ ለቆ የወጣብትን ምክኒያት በተጠየቀ ቁጥር ርስበርሳቸው የሚቃረኑ የተለያዩ መልሶችን እየሰጠ የሚዘበራርቀው፣ እየዋሸ ስለሆነ ነው፡፡ የሁኔታወች ሂደት በግልጽ የሚያመላክተው ደግሞ፣ ከመቀሌ ለቆ የወጣው፣ ወያኔ እስከ ደብረብርሃን ድረስ ዘልቆ የአማራን ክልል በሻሻ እንዲያደርግ ከወያኔ ጋር ተስማምቶ እንደሆነ ነው፡፡ አሁን ላይ ደግሞ በከያኒወች አማካኝነት ስለ ድርድር የሚሰብከው፣ ወያኔ ደብረብርሃንን ሊቆጣጠርና ሊዘርፍ ስለተቃረበ፣ ዘርፎ እንደጨረሰ ወዲያዉኑ ድርድሩን ይፋ ለማድረግ የአማራን ሕዝብ ስነልቦና ለማዘጋጀት ነው፡፡

አበው እንደሚሉት እጅግም ስለት አፎት ይቀዳል፡፡ ዐብይ አሕመድ እጅግ የተዋጣለት አጭበርባሪ ቢሆንም፣ አጭበርብሮ እንደኖረ ተጭበርብሮ ይሞታል፣ ወያኔም ከሱ ያላነሰ አጭበርባሪ ነውና፡፡ ዐብይ አሕመድ አማራን ለማጥፋት የሚከተለው መንገድ ባላሰበው አቅጣጫ ወስዶት እሱን ራሱን እንደሚያጠፋው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ መሠረታዊው ጥያቄ ግን ዐብይ አሕመድ የሚጠፋው አማራን ካጠፋ በኋላ ነው ወይስ ሳያጠፋ በፊት የሚለው ነው፡፡ ይህን ጥያቄ መመለስ የሚችለው ደግሞ ሌላ ማንም ሳይሆን የአማራ ሕዝብ ብቻ ነው፡፡

የአማራ ሕዝብ ትልቁ ጠላት ወያኔም፣ ኦነግም ሳይሆን፣ ባጭበርባሪነት እጅጉን የተካነው፣ በወያኔ ጉያ ውስጥ በማደግ በአማራ ጥላቻ ጥርሱን የነቀለው፣ በጨካኝነቱ ወደር የሌለው፣ ሰይጣናዊው ዐብይ አሕመድ ነው፡፡ ይህ ኦነጋዊ ሰይጣን እስካልተወገደ ድረስ፣ የአማራ ሕዝብ መቸም ቢሆን እፎይታ አያገኝም፡፡

በመጨረሻም ምክር ቢጤ ለብአዴናውያን፡፡ ዐብይ አሕመድ አማራን አዳክማለሁ ብሎ ራሱን አዳክሟል፡፡ እስኪሞት ከማይለየው ከማጭበርበር ችሎታው ውጭ አሁን ላይ ይህ ነው የሚባል አቅም የለውም፡፡ በተለይም ደግሞ በማጭበርበርና በማሳመን (convince and confuse) ካልሆነ በስተቀር በነ ዶክተር አምባቸውና ጀነራል አሳምነው ላይ የፈጸመውን ዳግመኛ የመፈጸም ችሎታ የለውም፡፡ ስለዚህም እንደስካሁኑ አትፍሩት፡፡ ቆፍጠን ብላችሁ እምቢ አሻፈረኝ ብትሉት፣ አምቅ አቅሙ ወደር የሌለው ሰፊው የአማራ ሕዝብ በነቂስ እንደሚደግፋችሁ ስለሚያውቅ፣ ወያኔን ከሚለማመጠው ይበልጥ ይለማጣችኋል እንጅ ዝንባችሁን እሽ አይልም፡፡ ቢያንስ፣ ቢያንስ ግን አንመራዋለን ለምትሉት ለአማራ ሕዝብ ብላችሁ ሳይሆን ለገዛ ቆዳችሁ ብላችሁ የሚከተለውን ባጽንኦት ንገሩት፡፡ ወያኔ የፌደራል መንግሥትን ጣልቃ ሳይስገባ ትግራይን ወክሎ እስከተደራደረ ድረስ፣ በአማራ በኩል የምንደራደረው እኛ የአማራ ክልል አመራሮች እንጅ አንተን ፌደራለኛውን ምንም አያገባህም በሉት፡፡ አለበለዚያ ግን ድርድሩ ባለቀ ማግስት እያንዳዳቸሁ እየተለቃቀማችሁ፣ ባልሰራችሁት ወንጀል የጦር ወንጀለኞች ተብላቸሁ እንደሚፈረድባችሁና የተወሰናችሁት በስቅላት እንደምትቀጡ ቅንጣት አትጠራጠሩ፡፡

Mesfin Arega

[email protected]

5 Comments

 1. አለም ገልብጠህ አንብበህ ተሳደብ እስክንድር ላይ ምስክር የሆንክ እዚህ ብትሳደብ ምን ይገርማል።

 2. መስፍኔ፣
  “ደጋግሜ ለማሳሰብ እንደሞከርኩት፣ አቶ ብሊንከን የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ የተመለከተን ማናቸውንም መግለጫ የሚያወጣው ከዐብይ አሕመድ ጋር ከተመካከረና ቢያነስ በተወሰነ ደረጃ የሐሳብ ስምምነት ላይ ከደረሰ በኋላ ብቻ ነው፡፡ የአቶ ብሊንከን መልዕከተኞች ሳመንታ ፓወርና ጀፈሪ ፌልትማን አዲስ አበባ ሲመጡ፣ ዐብይ አሕመድ በአካል አግኝቶ የማያነጋግራቸው፣ በስልክ የጨረሰውን ሻጥር ለማስተባበልና የአማራን ሕዝብ ለማታለል ሲል ብቻ ነው፡፡”

  ይኸ ያንተ ግምት ነው። ደፍረህ እርግጠኛ ነኝ የምትል አይመስለኝም! ወይ እነ “አቶ ብሊንከን፣ ወ/ሮ ሳመንታ ፓወር እና ቀኛዝማች ፌልትማን” አዲስ አበባ ደርሰው ሲመለሱ በስልክ ሹክ ብለውህ እንዳይሆን! ወይም በፊዝክስ ስልት የስልክ ጭውውታቸውን ጠልፈህም ይሆናል፣ ማ ያውቃል?!

  የሚገርመው ይህ ነው፤ ወድቀህ ተነሥተህ የማትደብቃት ጥላቻ መገለጧ አልቀረም። ሌላ ሕዝብ ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለ ወይም መኖር የለበትም ማለት እስኪመስልብህ፣ “አማራ፣ አማራ” ነው። ዛሬ ደግሞ ያገር ልጅ “አሳሜን” ጨምረኸዋል። በቁርጠኝነት፣ ዐቢይ “ጀነራል አሳምነው ላይ የፈጸመውን ዳግመኛ የመፈጸም ችሎታ የለውም” ብለሃል። አሳሜ ለትንሽ ሥልጣን አመለጠው እንጂ ቢቀናው ኖሮ በዐቢይ ቦታ ጠ/ሚ አድርጎ ይሾምህ ነበር?

  በነገራችን ላይ፣ ዐቢይ መወገድ መጥፋት አለበት የምትለዋ አንቀጽህ ሁሌ ትደጋገማለች! በሕዝብ ድምፅ ሳይሆን በጥይት መሆኑ ነው! አካሄድህ ጥሩ አይመስለኝም። እንዲህ ዓይነቱን አሳብ በአደባባይ መናገርህ ይገባል ትላለህ? ብትናገረውም፣ በልብህ ብትሠውረውም አንተን ነው እረፍት የሚነሳ፣ የሚያጠፋ!

  የዐቢይ ደጋፊው አይደለሁም፤ ሆኜም አላውቅም። በዐቢይ አመራር ላይ እኔም ጥያቄ አለኝ። ነገር ግን ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ መርጦታልና የሕዝቡን ድምፅ ማክበር ግዴታዬ ነው ብዬ አምናለሁ። በዚህ ቀውጢ ሰዓት ማ ይተካዋል ስል ማንንም ማሰብ አልቻልኩም። ምናልባት አንተ ትሻል ይሆን? ወይም አንተ ለአገሪቷ የምትመርጥላትን ብትጠቊመኝ አስብበታለሁ፤ ግራ የተጋባን ስላለን እባክህ እርዳን!

 3. አዎን መስፍን አርጋ ( መስፈርት አይረጋ) ሁል ጊዜ ዶ/ር ዐቢይ መወገድ መጥፋት አለበትን የምትለዋን አንቀጽ ሁልጊዜ የሚጠቅሰው ልፍስፍስና ደካማ በመሆኑ ከሰዎች የደረስኩ መስሎት አርቲፊሻል ጥይት መተኮሱ ሲሆን ዶ/ር አቢይን አስወግዶ ማን መተካት እናዳለበት የመፍትሄ ሃሳብ እንኳን ማቅረብ አይችልም ያው መወገድ አለበት ከማለት በስተቀር።ሳምንት ደግሞ አደግድጎ ያገለግለው የነበረውን ጌታቸው ረዳ አገር ይምራ ማለቱ ስለማይቀር የሚለውን እንጠበቅ። ያው እንደታወቀው መስፈርት አይርጋ ሥጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያውን ነውና እንዲህ መከራውን የሚያይ የደብረ ጽዮን ፍርፋሪ ስለቀረበት ነው።

  • አምባው ምን ችግር አለው አንተ መሆን ይከብድሀል እንዴ? ነው ተከታይ ብቻ ነህ ?ሞክረው ሊሆንልህ ይችል ይሆናል ከካድሬነትም ትገላገላለህ ስራም ትቀይራለህ።

 4. አይ አለምና አምባው አሁንስ ከካድሬም ተራ ካድሬ ሆናችሁብኝ እንደ ጠረጠርኩትም አዲስ ሀሳብ ማመንጨት የማትችሉ ድኩማን ናችሁ ማለቱ ሳይቀል አልቀረም። ኢትዮጵያን ለማፍረስ አጥብቃችሁ የምትሰሩ ካድሬዎች ናችሁ እውነቱን ጨምሮ።
  ፕሮፍ እነዚህ የአስተሳሰብ ድኩማን ባይገባቸውም አንተ ግን ማስተማስተማርህን ቀጥልበት ተፈጥሯዊ ድርሻ ነውና።

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.