“በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽብርተኛውን ወራሪ ኃይል ማጥፋት አለብን” ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ

253840121 4533871670037329 2405478025300775148 nበተናበበ ሕዝባዊ ማዕበል በመዝመት፣ አካባቢን ከጠላት ተላላኪ ነቅቶ በመጠበቅ እና ለወገን ጦር የሚደረገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማጠናከር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሽብርተኛውን ወራሪ ኃይል ማጥፋት አለብን አሉ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ።
የአማራ ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ አሁን ላይ ሽብርተኛውና ወራሪው ህወሃት ራሱ በቀቢጸ ተስፋ በአማራ እና በአፋር ሕዝብ ላይ በከፈተው ወረራ በገባበት መንገድ መውጣት እንደማይችል አውቋል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ኃይል በተስፋ መቁረጥ እየወሰዳቸው ያሉት ርምጃዎች ይህንን አመላካች መሆናቸውን ጠቅሰው፥ ወራሪው ቡድን ድጋሜ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሕልውና ሥጋት በማይሆንበት ደረጃ ማጥፋት የግድ መሆኑን ነው የልዩ ኃይል አዛዡ የገለጹት፡፡
የሽብርተኛውን ወራሪ ኃይል እንቅስቃሴ ለመግታትና የወረራቸውን አካባቢዎች ነፃ ለማውጣት ከመደበኛው የመከላከያ ሠራዊት በተጨማሪ ሕዝባዊ ማዕበል ያስፈልጋል ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ፥ ለዚህም ሲባል በመንግሥት በኩል የክተት ጥሪ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
“ዛሬ የተረከብናትን እና የምንኖርባትን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የነፃነት ማማ የክብር ቦታ ላይ ያገኘናት ያለ ዋጋ አይደለም” ያሉት ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ፥ የአሁኑ ትውልድም የአባቶቹን ውርስ ማስጠበቅ እንደሚኖርበት አሳስበዋል።
በክተት ጥሪው መሠረት የሥራ ኃላፊዎች እና ሕዝቡ በቅንጅት እየሠሩ በመሆኑ ወራሪውን ኃይል በወረረው መሬት ላይ ሳንቀብር አንመለስም ነው ያሉት።
ሽብርተኛው የህወሃት ቡድን የያዘው ጭፍጨፋ፣ ዝርፊያ እና ውድመት የሚመከተው በተናበበ ሕዝባዊ ማዕበል መሆኑንም ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ገልጸዋል፡፡
ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

1 Comment

  1. ወራሪውን የምታጠፋው ያሰርከውን የቀድሞ ሰራዊት ስትለቅ ብአዴንን ጠቅላላ ስታባርር ለፋኖ ለሚሊሽያ ለልዩ ኃይል ያልተገደበ የመሳሪያ እገዛ ስታደርግ ነው። ዶር አብርሃም አረጋዊ አርከበን የመሳሰሉ ቀንደኛ ህወአቶች መሀል ውስጥ ቁጭ ብለው የማይሆን ነገር ብታወራ ውጤት አያመጣም በዚህ ላይ ለትግሬ ዋና ተከራካሪ ሁነሀል አማራን አትግደሉ የሚል ትግሬ ትነግረናለህ? ይሄን ሁሉ መአት ትግሬ አማራው ላይ አዝንቦ አማራ ክልል ምን ይሰራል? ወይስ በረከት ስንል ነው እኔንም መመሪያ የሚሰጥህ?

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.