ጄፍሪ ፌልትማን ከሶስት ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን በትላንትናው ዕለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከሶስት ከፍተኛ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር መወያየታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቃባይ ገለጹ። ልዩ መልዕክተኛው በዛሬው ዕለትም ከሌሎች የኢትዮጵያ ባለስልጣናትን አግኝተው እንደሚነጋገሩ ገልጸዋል።
ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ልዩ መልዕከተኛ ጋር ትላንት ተገናኝተው ከተወያዩ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት መካከል፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን አንዱ እንደሆኑ ኔድ ፕራይስ ተናግረዋል። ፌልትማን ባለፈው ነሐሴ ወር ወደ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸው ይታወሳል።
አሜሪካዊው ዲፕሎማት፤ ከአቶ ደመቀ በተጨማሪ ከመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ እና ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ጋር ተገናኝተው መወያየታቸውን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቃባይ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።
የሽዋስ አለምነህ ወንድም
ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio : ኦብነግ በከፈተው ጥቃት አንድ ቻይናዊ ኢንጂነርን ጨምሮ የወያኔ አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት ሰነዘርኩ አለ፣ኢ/ር ይልቃል በድጋሚ መመረጡና በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ክፍፍል የለም መባሉ ፣ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች በወንድ አሰልጣኖቻቸው የወሲብ ጥቃት እንደሚፈጸምባቸው ተዘገበ፣ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለፖለቲካ ስልጠና ተጠሩ፣የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ማሻቀብ የፈጠረው ዓለም አቀፍ ስጋት፣ ቃለ መጠይቅ ከሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ ጋር እና ሌሎችም

2 Comments

  1. የፌልትማን (የአሜሪካ ዓላማ) ህወሓትን ማዳን ነው። ስለዚህ ነው፣ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት በሳምንታት ሳይሆን በቀናት አቅጣጫ መቀየር አለበት ያለው። ቢቆይ ለህወሓት አይበጅምና ነው። የህወሓት ስልቱ ዛሬም አሜሪካኖች አዲስ አበባ እንዳስገቡት እንደ 1983 ዓ.ም. ነው። ያኔ ቶሎ ከ80 በላይ ፓርቲ በየቋንቋው አቋቊሞ ዲሞክራሲ እንካችሁ አለ። አሜሪካኖችም ዲሞክራሲ እያጠናከርክ ስለ ሆነ ብለው ብዙ ዶላር ሰጡት። ከዚያ ቆይቶ “አል ሸባብ” የተሰኘ ኩባንያ መሠረተ። የማያቋርጥ የዶላር ምንጭ አገኘ (በነገራችን ላይ ህወሓት ከተባረረ በኋላ አልሸባብ የገባበት ጠፍቷል!)።

    ህወሓት ወደ አዲስ አበባ እየገሠገሥኩ ነው የሚለውና አሜሪካኖች የሚያስተጋቡለት የፍርሓት ፕሮፓጋንዳ ለመንዛት ነው። ዛሬ ግን ዘመኑ እንደ 1983 ዓ.ም. አይደለም። ቴክኖሎጂ ብዙውን ምሥጢር ይፋ አድርጎታል። ወጣቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነቅቷል፤ ከዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር ተሠልፏል። የህወሓት ተመልሶ ሥልጣን መያዝ በአማራው ይሁን በኦሮሞው በወላይታው ወዘተ ተቀባይነት የለውም። ክተት አዋጅ ሲታወጅ ጦሩን ለመቀላቀል የተመዘገበው ወጣት ቊጥር እጅግ ከፍተኛ የሆነው ለዚህ ነው። ትልውዱ የአሜሪካኖችን ሤራ በደንብ አውቆታል፤ አገሩን ለመታደግ አንድነቱን እየገለጸ ይገኛል።

    ህወሓት ተመልሶ ሥልጣን መያዝ ቀርቶ ቀድሞም በማስፈራራት እንጂ እንደማይዘልቃት አውቆታል። ህወሓት የሚፈልገው ምንድነው? ብቻዬን አይደለሁም፤ የአርጎባ የቤንች የጒሙዝ የአፋር የኦሮሞ ሕዝብም ከፋኝ ብሏል በሚል ሰበብ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተከፍቷል፤ ድርድር ማድረግ ይፈልጋል ብሎ በሰበቡ ራሱን ተበዳይ ተደራዳሪ አድርጎ ለማቅረብ ነው። ችግሩ ግን እንዲህ ነው፦ የአርጎባ የቤንች የሺናሻ ወዘተ የሚላቸው ፓርቲዎች አብረውት የሉም! ፈጠራ ነው።

    ህወሓት እንደ ለመደበት፣ ከዶ/ር ዐቢይ መንግሥት ጋር መግጠም የፈለግሁት ወደ ሥልጣን ለመመለስ አይደለም፤ የትግራይ ሕዝብ መጨፍጨፍ እንዲቆም ብቻ ነው እያለ ነው! የትግራይ ሕዝብ በረፈረንደም የራሱን እድል ይወስን ለማለት ነው። ልክ ለኤርትራ እንዳደረገው! የትግራይ ሕዝብ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ በእቅዴ ውስጥ አያገባቸውም ነው!

    አሜሪካኖች ኢራቅ አፍጋኒስታን ሊብያ የመን ላይ ሲያደርጉ የነበረውን ግፍ ለመፈጸመ አኮብኩበዋል። ሕዝብ የመረጠውን የቬኔዙዌላውን ማዱሮን ተናነቁት፤ ሥልጣን ልቀቅ አሉት፤ ምክንያቱስ? ትልቅ የዘይት ሃብት አለው፤ ከቻይና ከኩባ ጋር ወዳጅ ነው። ማዱሮ ወጊዱ አላቸው። አሜሪካኖች ከቬኔዙዌላ ተቃዋሚ ነን የሚሉ የሥልጣን ጥመኞችን ወደ አጎራባች አገር አሰባስበው ማሠልጠን ጀመሩ። ሲኤን ኤን ቪኦኤ ሌት ተቀን ማዱሮን እንደ ወንጀለኛ ማጠልሸት ጀመሩ። በመጨረሻ፣ የአሜሪካ መንግሥት አንድ ካናዳዊ ኮማንዶ ከሦስት መቶ ቅጥረኞች ጋር በአንድ ሚሊዮን ተኲል ዶላር ቀብድ ተኮናተረ። ማዱሮን ካስገደሉ በኋላ አሜሪካኖች በኢራቅ በሊብያ እንዳደረጉት የቬኔዙዌላን ዘይት ከእጅ ስለሚያስገቡ ከዘይቱ ሽያጭ $200 ሚሊዮን ያህል ለካናዳዊው እና ለአበሮቹ ሊሰጡ ቃል ገቡ። እንደ ታቀደው ግን አልሆነም። ምክንያቱ አንድ ነው። ሕዝቡ ከማዱሮ ጋር ቆሞ ስለ ነበር፣ ባእዳን ቅጥረኞቹ ተያዙ፤ ኮንትራት የተቀበለው ካናዳዊ በመሆኑ አሜሪካኖች እጃችን የለበትም ብለው ለመካድ አመቻቸው!

    ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከህወሓት ጋር የተሠለፉ ነጮች እና ጥቊሮች (ባእዳን) ተዋጊዎች ተገኝተዋል ብለውን ነበር። በድናቸውን ይሁን በቊማቸው እነዚህን አደባባይ ማውጣት እጅግ አስፈላጊ ነው።

    ባጭሩ፣ ኢትዮጵያውያን አንድ ምርጫ ብቻ አለን። አንድነት መቆም ነው። አንድነት እስከ ቆምን ድረስ
    ከእግዚአብሔር ጋራ ኃያል የተባለች አሜሪካ እንኳ ምንም ልታደርግ አትችልም። ሃያ ዓመት በኢራቅ እና በአፍጋኒስታን ብዙ እልቂት አድርሳ፣ ብዙ ዘርፋ በመጨረሻ ግን በውርደት ተባርራለች! ይህን አንርሳ! ጣልያን በወቅቱ ኃያል ጦር ያላት ነበረች። አውሮፕላን ቀርቶ ታንክ አልነበረንም። ግን ውርደት ተከናንባ ተመለሰች! አንድነት እንቊም። እንቊም ማለት እጅ አጣምረን አይደለም። ቴክኖሎጂ ችሎታ ያላቸው በዚያ ብቃታቸው፤ ጽሑፍ መጻፍ የሚችሉ በጽሑፍ፤ አካባቢን በመሰለል እርስ በእርስ በመግባባት አንድነታችንን ማሳየት አለብን። ውጭ አገር ያሉ በቨርጂንያ ምርጫ እንዳደረጉት የባይደን አስተዳደር ሳይወድ በሚገባው ስልት ማስረዳቱን መቀጠል አለባቸው፤ በአሜሪካኖች ጥበብ የተካኑ ለአገራቸው መቆም የሚችሉት አሁን ነው፤ ታሪካችንን ዘመኑ እየመዘገበ ነው። ሌላ ሌላውን ወደ ጎን ማድረግ ግድ ነው! አገራችን እና ሕዝባችን አንዴ እንኳ እንዳያልፈለት የፈለጉ ጠላቶች ተከማችተውበታል። የየፊናችንን ከያለንበት፣ በግል ይሁን በማህበር እንወጣ።

    ሌላው የኤርትራ ድርሻ ጒዳይ ነው። የኤርትራ መንግሥት ሁኔታዎች የሚያስከትሉትን በጽኑ ተረድቶታል። ህወሓት የአሜሪካኖች እርዳታ እንደማያስጥለው ገብቶታል። አሜሪካኖች የአፍሪቃን ቀንድ ከቻይና ከራሽያ እና ከቱርክ ጋር ለመቀራመት በሚያደርጒት ግብግብ ህወሓት ታስፈልጋቸዋለች። ኢትዮጵያ ብትበታተን አሜሪካ ዓላማዋ ይበልጥ ይሳካልና ደንታ የላትም። ባለፈው ወር የሱዳኑን መንፈቅለ መንግሥት ያፈጣጠሙት አሜሪካኖች ናቸው፤ ሳማንታ ፓወር የመጣች ጊዜ ያለቀ ጒዳይ ነው።

    ኢትዮጵያውያን ያለን ምርጫ ሁለት አይደለም፤ አንድ ብቻ ነው፤ ከዶ/ር ዐቢይ ጋር መቆም ነው።

  2. እንዲህ አይነት መሱሪ ከአብረሀም በላይ ጋር በግል እንዲነጋገር እድል መሰጠት ነበረበት? ከጳጳሱ ጋር እንደተደረገው ስብሰባ አይነት መሆኑ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share