ለአሸባሪው ሕወሓት ፅንፍ የወጣ ድጋፍ እያሳዩ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአግዋ ዕድል ተጠቃሚነት የሰረዙበት ውሳኔ ተችትን እያስተናገደ ነው

blinken biden rt jt 201123 1606166992688 hpembed 23x15 992
blinken biden rt jt 201123 1606166992688 hpembed 23×15 992
የእንግሊዙ ክላንፊልድ ዩኒቨርሲቲ የዓለም ዐቀፍ ፀጥታ ፕሮፌሰሯና የመንግሥት አስተዳደር ተመራማሪዋ አን ፊትዝ ገራልድ የባይደን አስተዳደር አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ክልል 100 ንፁሃንን ገድሏል የሚለው ሪፖርት በወጣ ማግስት የሽብር ቡድኑን ከማውገዝ ይልቅ በሕዝብ የተመረጠን መንግሥት ጫና ውስጥ ለማስገባት ከአግዋ መሰረዙን ጠቅሰቀው ድርጊቱን ተቃውመዋል፡፡ መሰል የአሜሪካ አካሄድ ጥፋትን ከማባባስ የዘለለ ፋይዳ እንደሌለውም አስምረውበታል፡፡
በእንግሊዙ አቢርደን ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊና ፖለቲካ ሳይንስ የሦስተኛ ዲግሪ ምሩቁ ብስራት ለሜሳ (ዶ/ር) በቲውተር ገፃቸው የባይደን ውሳኔ አዲስ እንዳልሆነ ገልፀዋል፡፡
አሜሪካና አጋሮቿ ምዕራባዊያን የሽብር ቡድኑን ሕወሓት ለመደገፍ የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነውም ብለዋል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስተዳደር አግዋ በምጣኔ ሃብት ሽፋን የፖለቲከ መሳሪያ ስለመሆኑ በቂ ትምህርት አግኝቷል ብለው እንደሚያምኑ የጠቀሱት ብስራት ለሜሳ (ዶ/ር) ትኩረቱን ሁሉ የኢትዮጵያን ፍላጎትና ብሔራዊ ጥቅም አስጠብቆ መጓዝ ላይ እንዲያደርግ መክረዋል፡፡
የማኅበራዊና ፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ አያይዘውም ‹‹ከተረጋጋን፣ በአንድነት ከቆምን እና የምንችለዉን ሁሉ ለኅልውናችን ካበረከትን ወደፊት የሚንደረደረዉን የጥፋት ኃይል ማስቆም ብቻ ሳይሆን ማክሰም እንችላለን›› ብለዋል።
ኢትዮጵያዊያን የባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያን ለዓመታት ተጠቃሚ ከነበረችበት የአሜሪካ የቀረጥና ኮታ ነፃ ገበያ (አግዋ) የሰረዘበትን አካሄድ በማኅበራዊ ትስስር ገፆች በኩል እየተቃወሙት ነው፡፡ አግዋ የምጣኔ ሃብት ማበረታቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፍላጎት ማስፈፀሚያ መሆኑንም እየገለፁ ይገኛል፡፡
የባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያን የሰረዘው ከሰብኣዊ መብቶች ጥሰት ጋር ተያይዞ መሆኑንም ኋይት ሃውስ አስታውቋል።
ይሁንና ኢትዮጵያ በአሸባሪው የሕወሓት አገዛዝ ዘመን ከፍተኛ የሰብኣዊ መብቶች ጥሰትና መንግሥታዊ ሽብር እየተፈፀመባት ከነፃ ገበያ ዕድሉ ያልሰረዘችው አሜሪካ አሁን ላይ ይህን ጥያቄ ማንሳቷ ፍላጎቷ ሌላ መሆኑን አመላካች ነው።
የባይደን አስተዳደር ግልፅ ድጋፍ እያደረገለት የሚገኘው አሸባሪው ሕወሓት ዛሬም እየፈፀመ የሚገኘውን የሰብኣዊ ቀውስ ከመቃወም ይልቅ የዜጎቹን ኑሮ ለማሻሻል እየጣረ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና ማሳደርን መርጧል።
ሽብርተኝነትን እዋጋለሁ የምትለው አሜሪካ በሽብር የፈረጀቻቸውን አካላት ለማጥፋት የአገራት የአየር ክልልን ጥሳም ጭምር የአየር ድብደባ ስትፈፅም ትክክል ነው ያለችው አካሄዷ ኢትዮጵያ ሽብርተኛ ያለችው ሕወሓት የከፈተባትን ጦርነት ስትከላከል ስህተት እንደሆነ ትገልፃለች።
በኢትዮጵያ ተላላኪ መንግሥት በመፍጠር ቀጣናውን እንዳሻው መዘወር የሚፈልገው የጆ ባይደን አስተዳደር ከአግዋ መሰረዝን ጨምሮ በማዕቀቦች ጫና ማሳደርን ስልቱ አድርጓል።
በዚህም ከአምራች ባለሃብቶች ባሻገር በኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ1 ሚሊዮን በላይ በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ከሥራ የሚያናጥብ ውሳኔን አሳልፏል።
አገራቱ ይህ የተወሰነባቸው የአሜሪካን ፍላጎቶች ማሟላት ባለመቻላቸው መሆኑን ያሳወቀው የባይደን አስተዳደር በእርግጥ በሰብኣዊ መብትና ዴሞክራሲ ስም ተሸፍኖ የሚቀርበው ፍላጎቱ ምንድነው የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው።
አሜሪካ ከኢትዮጵያ በተጨማሪም ጊኒ እና ማሊንም ከአግዋ አግዳለች።
ጥቅምት 23/2014 (ዋልታ)
ተጨማሪ ያንብቡ:  በቤኒሻንጉል ጉሙዝና አካባቢው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ፣ | ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል

1 Comment

  1. Yih nechachiba shimagle yefelegewun beyaderg Ethiopian liyashemakikat aychilm Ethiopia wede tinsaewa tigesegisalech America na gibreabrecha wede mekemek yewerdalu dil le Ethiopia ena hizbochua

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share