November 2, 2021
26 mins read

የውጪና የውስጥ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ሤራ ፤ በተባበረ ክንዳችን ይከሽፋል ! – መኮንን ሻውል

ኢትዮጵያ በዜጎችዋ መስዋትነት ታፍራና ተከብራ ትኖራለች !!

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ዴሞክራሲ ወድደን በምንተገብረው ሥርዓት (Manifestation ) እና ተገድደን በምንተገብረው ሥርዓት መካከል፣ያለ የነፃነት ቀጭን ክር ነው እንጂ ፤ ቅኝ ገዢዎች  ና ባንዳዎች በጠመንጃ የሚለግሱን ፍርፋሪ አይደለም ። ለምሳሌ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በጠላት እጅ በተረሸኑበት ወቅት፣ቀደም ሲል በዛው በተረሸኑበት አደባባይ ላይ ጭምር ወጣት ኢትዮጵያዊያን ፣ምልምል ባሊላዎች (ካድሬዎች) በፕሮፓጋንዳ  ግፊት ኢትዮጵያችንንፋቺታ ኔረ!” (ኔግሮዋ ወጣት) በሚል መዝሙር እያሞካሹ የፋሺሥት ግዛት ተቀባይነቷን ሲዘምሩ ፣በገጠሯ ኢትዮጵያ ግን (በኤርትራ ጭምር) አባቶቻችንኢትዮጵያ ወይም ሞት!” እያሉ ለነፃነት መፋለማቸው፣በባህልና በታሪክ አነሳሽነት ወድደው በተገበሩት  አባቶችና ተገደው በተገበሩት ልጆቻቸው መካከል ያለው የነፃነትና የዴሞክራሲ ቀጭን ክር ፍንትው ብሎ ይውለበለብ ነበር። ዛሬም በልባችን ውሥጥ ይውለበለባል ።ለዘህ ነው ዛሬም በአፅኖት  ደጋግመንራሳችንን እንወቅእምንለው።

ቀይ ሕንድን  ከጠቅላላው  ሰሜን ደቡብ አሜሪካ ምድረ ገፅ ትላንት የደመሰሰ ፣የጥቁርን ዘር ከጠቅላላው  የአውስትራሊያ ክፍለ አህጉር ትላንት የገፋ ሤራ ፣ ዛሬ አፍሪካን ይለቅልናል ብለን ራሳችንን እንዳናሞኝ ና እርስ በእርሳችን በጭፍን እንዳንናቆር እንጠንቀቅ ውሃ ሙላት ሲወስድ እያሳሳቀ ነው።እንዲሉ፣ይኼ በባህል ካባ ሸፋፍነን፣ በምር የተያያዝነው ማዘናጊያ የጎሣ ፕሮፖጋንዳ በቁማችን እንቅልፍ እያሥወሰደን ነው ። ዛሬ ላይቤሪያ፣አልጄሪያ፣ሩዋንዳ፣ብሩንዲ፣የመጀመሪያዎቹ መረማመጃ  ክስተቶች ናቸው ። ናቸው እንጂ የመጨረሻዎቹ አይመሥሉኝም ። ሥለዚህ በቶሎራሳችንን ካላወቅንእግዛብሔር አይበለውና ገና የባሰ ጉድ እናይ ይሆናል ። ዛሬም ጥንትም ሕይወት የሚዘራብንን ፣ ካም አበው በጋራ ያወረሱንን ፣ለዓለም  ጥቁር ዘር ሁሉ የመሠረት ድንጋይ የሆነውን ራሳችንን የማወቅ ፣ሕዝብን እና ሀገርን ከልብ የመውደድ፣ ፅናታችንን ፣የሰብዓዊ ክብር ፍቅራችንን የማይናወጥ ኢትዮጵያዊነታችንን ፣እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ አንድነታችንን ፣በባዕዳን ሥውር ሴራ በተደገሰልን የጎሰኝነት መርዝ ታውረን እንዳንደመስሰው እጅጉን እንጠንቀቅ።

እንደነሶቅራጥስ ያሉ ፈላሥፎች የጥበብ ሰዎች፣የመርዝ ፅዋ ጠጥተው ያተረፉልንን ዴሞክራሲ፣ እንደነ ፑሽኪን ያሉ የጥበብ ሰዎች በቅጥረኛ ጥይት ተገድለው ያተረፉልንን ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት (Freedom of Expression ) እኛ በራሥ ወዳድነት ተቆልምመን፣ በፍርሃት አጎብድደን በጎሰኝነት ብናስገድላት  የነገው ታራክ  ምሥክሮች፣ እኛ ሳንሆን ህዝብና ትውልድ መሆናቸውን ከቶም አለመዘንጋት የሚያሥፈልግበት ጊዜው አሁን ነው።

ባለቅኔ ሎሬት ፀጋዬ /መድህን

ጦቢያ መፅሔት ቅፅ 6 ቁጥር 1   1990 /

………………………………………………………..
ራሥን ማወቅ ማለት ከድንቁርና ነፃ መሆን ነው።አኛ ኢትዮጵያዊያን ለሺ ዓመት የተገነባ ድንቅ ባህል ያለን ህዝቦች ነን ። እነዚህ ድንቅ በህሎቻችን በቋንቋ ፣ ባለባበሥ ፣ በእደ ጥበብ፣በልዩ ልዩ የቤት ውሥጥ ቁሳቁሶች ፣ በአመጋገብ ፣ በህንፃ ሥራ ፣ በኪነት ወዘተ ። ይገለፃሉ ። ባህላችን በራሱ መደበላለቃችንን ይመሠክራል ። የአንዳችን ባህል ከሌላኛው ባህል ጋር ድርና ማግ ነው ። ባህላችን በዘመናት ሂደት ውሥጥ በወጉ ተፈትሎ የተሸመ ነው ።

ይህንን አኩሪ ፣ ቱባ ባህላችንን፣ወደ ገደል ለመጨመር ለዘመናት በውጪ ፀረ – ኢትዮጵያ ኃይሎች በተደጋጋሚ ጊዜ ኢትዮጵያንን ና ህዝቧን የሚጠፋ  ሤራ ተጎንጉኗል ፡፡ የዛሬውም ወያኔ የትላንቱ ሤራ ቀጣይ ገቢር ፈፃሚ  ፀረ ኢትዮጵያ ኃይል ነው ፡፡  ከጫካ ጀምሮ ለብዝበዛ እንዲያመቸው ሥሙን እየቀያየረ ቢመጣም  ነጣጣይ ፣ እና በዓለም ላይ የሌለ ” ” የአራዊት  ርእዮተ ዓለምን “ በላያችን ላይ በግድ ለመጫን ሃያሰባት ዓመት ሙሉ የባዘነ ፀረ -ኢትዮጵያና ህዝቧ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ ወያኔ ትህነግ   ከውጪ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች ጋራ በግልጽና በኅቡ በማበር ታላለቅ አገር አክሳሪ ሤራወችን   ኪሱን ሲያሳብጥ ለ47 ዓመት መሰንበቱ ይታወቃል ፡፡ ዛሬም እጅግ በሚቀፍ ፣ በሚዘገንን እና እወክለዋለው የሚለውን ህዝብ በሚሸማቅቅ መልኩ አገር አጥፊና አክሳሪ ሴራውን ቀጥሏል ፡፡ የሚከተለው ህግም የአራዊት መሆኑ በደሴና በኮንቦልቻ ዳግም ተረጋግጧል ፡፡ ጭካኔውን በሳተላይቷ የምትከታተለው አሜሪካም ሰቅጣጭ ድርጊቱን ለማውገዝ አልደፈረችም ፡፡ ፈረሷን ምን ብላ ታወግዛለች ? ከወሎ ውጣ ስትል ” አትውጣ ፤ አጥበቀህ ያዝ ፤ እኔ አለሁልህ ፤ አደራድርህ ና ለስልጣን ትበቃለህ ፡፡ ” ማለቷ እንደሆነ ስንቶቻችን እንገነዘባለን  ፡፡ ” ይኽ ግን ከቶም አይሆንም ፡፡ ኢትዮጵያውን ከቶም አይቀበሉትም ፡፡ ከማይካድራ ጀምሮ ፤ በአፋርና በወሎ ፤ የፈሰሰው የዜጎች ደም እየጮኸ ድርድር ብሎ ነገር የለም ፡፡ የዘረኝነትን ሥም ለራሱ የሰጠውና በመላው ኢትዮጵያ ተጋብተውና ተዋልደው የሚኖሩትን ትሁትና ፈርሃ እግዚአብሔር ያላቸውን የትግራይ ክፍለ አገር ተወላጆችን እጅግ ያሸበረና  ያሰቀቀ ድርጊት  ትህነግ ወያኔ በገዛ የአገሩ ሰዎች ላይ በመፈፀም እኛን ልክ እንደሶርያ ለማድረግ ከጨካኙ ከሲአይ ኤ ጋር በመተባበበር የ20 ዓመት አገራዊ መገዳደል አቅዶልናል ፡፡ ( ፊልትማን ያወራው ይኽንኑ ነው ፡፡ ) ያም ሆነ ይህ  በአውሬነት የጨፈጨፋቸው ንፁሓን ደም እየጨኸ የሚደራደር መንግስት እንደሌለን እኛ ኢትዮጵያዊን ስለምናውቅ የፊልት ማን ሤራ ይከሽፋል ፡፡ ኢትዮጵያዊያንም ኢትዮጵያን በመሰዋትነታቸው ታፍራና ተከብራ እንድትኖር ያደርጋሉ ፡፡ ›››የውጪና የውስጥ ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ሤራም ይከሽፋል ፡፡

ሤራ 1

ወያናዊ ሤራ

ወያኔ በሤራ ፤ አኩሪ የመተሳሰብ ፣ የመከባበር እና የመፋቀር ባህላችንን በመሸርሸር ፡፡   ሰውን በቋንቋው በመለየት አንደኛ ፣ሁለተኛ፣ ሦሥተኛ ወዘተ ዜጋ በማድረግ ፤ የመተሳሰብ ባህሉ እጅግ የገዘፈውን የኢትዮጵያን ሰው ፤ ራሱን ከሌላ ሰው የተለየ አድርጎ እንዲያይ ና ሰውን በቡድን እንጂ በግለሰብ ደረጃ እንዳያስብ አድርጓል ፡፡ ያውም በሆዱ ብቻ እንዲያስብ በማድርግ ፡፡ አንድ ትሪ ላይ ያለውን እንጀራ አንዱ ቋንቋ ብቻ ጠቅልሎ የመጉረስ መብት እንዳለው በህገመንግስት ና በክልሎች የክልል ህግ ውስጥ  ሳይቀር በማፀደቅ ፡፡ ላብና ደም ሳያወጣ የሚበላ ወሬኛ ካድሬ እንደ አሸን እንዲፈላና እንዲበለፅግም አድርጓል ፡፡ ብልጽግናም ከሞላ ጎደል ይህንኑ ካድሬ ይዞ መጓዙን ማስተባበል አይቻልም ፡፡

እውነቶችን በየፈርጁ ማቅረብ ቢቻልም ፣ ” ሳይደወል ቅዱስ ”  ወይም ” ሱሪ በአንገት  አውልቅ ፡፡ “እንዳይሆን ነገሩ ፤ ለብልጽግና ፓርቲ የቤትስራውን የሚሰራበትን በቂ  ጊዜ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ ፤ ጉዳዩን በይደር አቆይቸዋለሁ ፡፡ደግሞም ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀበሌን እና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ፤ ለምሳሌ  የኬሚካል ኮርፖሬሽንን ወርደው ይቆጣጠሩ ወይም ተቆጣጣሪ ሰው ራሳቸው ይመድቡ አይባልም ፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስተር ምን ይሰራል ?! ሆኖም በሚታዩ ጥፋቶች ” አብይ … ፤ አብይ… ነው ፡፡ እሱም …” እንደሚባሉ ፤ ጠቅላዩ አያውቁም አልልም ፡፡ በሁኔታው ግን  አዝናለሁ ፡፡ አሀን እና ዛሬ ግን ይኽቺ አገር ከወሬ ይልቅ ድርጊት ትፈልጋለች እላሉሁ ፡፡ ወሬ ና ከወያኔ የፕሮፖጋንዳ ማሽን የተቀዳ የፓርቲ ቅስቀሳ ምን ይፈይድላታል ? አዲስ ወይን አለን ካልን ዘንዳስ ለምን በአሮጌ አቁማዳ እንጨምራለን ፡፡ ዛሬ ከጅምሩ ብልጽግና ፓርቲ የጠመቀው ወይን አዲስ መሆኑን በቅጡ ይፈትሽ፡፡ …ወደማያስመስለው እውነተኛው ህዝብ ተጠግቶ የልቡን ትርታ ያዳምጥ  ፡፡ የአዲሱ ወይን አዲሱ አቁማዳ ኢትዮጵዊ አስተሳሰብ ያለው ዜጋ ነው  ፡፡ይኽንን ጠንካራ እና ለአገሩ ዳርድንበር ፤ ለህልውናዋ ሲል ህይወቱን የሚሰዋ ዜጋ ፣ በቋንቋ ፌደራሊዝም ከፋፍሎ   በሁሉም ከተሞች ኗሪዎችን እያገለሉ እንደ ጅብ ተጠራርተው የሚበሉ የወሬ አበጋዞች ወያኔ ፈጥራ ብዝበዛዋን ለ27 ዓመት ስታጧጡፍ ነበር ፡፡ ይኽ የወያኔ ሤራ ለዛሬው የከተማ ጊዚያዊ ሽንፈት አጋልጦናል ፡፡

እናም ዛሬና አሁን ግልጽና እውነተኛ ውይይት ፣ በገለልተኛ አካል ህዝቡ ማድረግ አለበት  ፡፡ እነሱ እንዳይወቀሱ ና ከወንበራቸው እንዳይነሱ ፤ የህዝብን አፍ ለጉመው  መንግስት መስማት ይገባዋል የሚሉትን ብቻ በማቅረብ በሐሰተና ሪፖርት መንግስት በማጅራቱ እንዲታረድ ከወያኔ እና በስግብግብነታቸው ልክ የለሽነት የተነሳ ሰው መሆናቸውን ከረሱ ዘረኞች ጋራ በህቡ የሚሰሩ በውል መገንዘብ አለበት ፡፡የራሱን ጋዜጠኞችም በየሚድያው ህዝቡ የሚፈልገውን እውነት ይናገሩ ዘንድም ነፃ ሊያደርጋቸው ይገባል ፡፡ ባለማወቅ ሆነ አውቀው በዜና ዘገባ ጭምር የወያኔን ዓላማ የሚያራምዱ አሉ ፡፡ ለምሳሌ ተቆርጦ መቅረት ያለበት ህዝብን የሚሰድብ ንግግር በዜና ሰምቼ ደንግጫለሁ ፡፡

ሕዝብ እንደ ህዝብ በጠላትነት አይፈራረጅም  ፡፡ህዝብ ሁሉ ሰው ነው ፡፡ለሰው ፣ መግብ ፤ መጠለያ እና ልብስ ዋነኛ ፍላጎቱ ነው ፡፡ እነዚህን የሚያሟለ ሁኔታ መንግስት እንዲያመቻምችለትም ይፈልጋል ፡፡ ሰርቶ ይበላ ና ይጠጣ ሀብትም አፍርቶ ተደላድሎ ይኖር ዘንድ ፡፡ ይኽ ካልተሳካለትና ምንዱባን ከሆነ ግን ፤ በቀላሉ የአንድ ቡድን ሃሰተኛ ትርክት ሰለባ በመሆን ለድህነቱ ሰበብ ያልሆነውን በቋንቋ ብቻ የተለየን ሰው ለማጥቃት እንዲነሳ ለማድረግ ይችላል ፡፡…  የራሳቸውን እኩይ አላማ በህዝብ ልብ ውስጥ ለማስረጽ የሚችሉ ፤ በተንኮል፤በመሰሪነት፤በማስመሰል፤በአስብቶ አራጅነት ያታወቁ ፤  ቁም ነገሩን ሁሉ ዳዋ በማልበስ አርቲ ቡርቲውን ሁላ የሚያገዝፉ የዘላቂ ሰላም እና የሰው ተስፋ ጠላቶች እንደሆኑ በማሳወቅ  ፡፡ ለተሻለ ኑሮ አብሮነት እጅግ እንደሚመረጥ በመገናኛ ብዙሀን ተደጋግሞ መሰበክ አለበት ፡፡ በየከተሞችም ህዝብ አብሮነቱን የሚጠናክር መድረክ መፈጠር ይኖርበታል ፡፡ ግልጽ ውይይት ሰዎች እርስ በእርሳቸው እንዲተዋወቁ ያድርጋቸዋልና ፡፡ ጅምላዊ የሆነ ፍረጃና በቋንቋ ና በትውልዱ ብቻ ሰውን መጥላትም በየቀበሌው በሚደርግ  ግልፅ ውይይትም ይወገዳል ፡፡ ለህሊናው ሳይሆን ለገንዘብ ያደረውን በጥባጩንም ለመለየት በማስቻል የወያኔን ከውጪ ኃይሎች ጋር የተናበበ ሤራ ያከሽፋል ብዬ አስባለሁ ፡፡

ሤራ 2

የውጪ ኃይሎች ሤራ

ስለ ውጪ ኃይሎች ሤራ ሲነሳ ዛሬ ና አሁን የወያኔ ሤራ ፤ በውጪ ኃይሎች ታግዞ መቀጠሉን ልብ ማለት ያስፈልጋል ፡፡ በተለይም በአሜሪካ ፡፡ ያውም በውሸታሙ ፊልትማን ታግዞ ፡፡ ከ1983 ዓ/ም በፊት  ወያኔንን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ሲያደራድር የቆየውና መንግስቱ ኃይለማርያምን ወደ ዝንቧብዌ ሸኝቷ ወያኔን ወደ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት ማነው ያስገባው ? ( ሰለነ ኸርማን ኮሆን የሤራ ፖለቲካ ብዙ የተጻፉ ሰነዶች እንዳሉም መታወቅ አለበት ፡፡ በህይወት ያሉ የዛን ጊዜ የመንግስት ተደራደሪዎችም እኮ አሉ ፡፡ የዶ/ር አሻግሬ ይግለጡንም ቃለ ምልልስ ከኢሳት ቴሌቪዢን ማግነት ይቻላል ፡፡በዩቲዩብ በኩል ፡፡

ዛሬም የኢትዮጵያ መንግስት እጁን እንዲሰጥና ከአሜሪካን በዝባዥ ኃይሎች ጋር በወያኔ አማካኝነት  እንዲደራደር የተከበሩ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ጆን ባይደን ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የአግዋን ነጻ የንግድ ቀጠና እንቅስቃሴ ፣ ከፈንረጆች አዲስ ዓመት ጀምሮ አቆመዋለሁ ብለዋል ፡፡ በዚህ እኩይ ድርጊታቸውም ወደ 3 ሚሊዮን የሚጠጋ ኢትዮጵያዊያንን ስራ ለማሳጣት አቅደዋል ፡፡ ብራቮ ¡¡ ባይደን ፡፡ እንላለን ፡፡ በመቅላት እና በመጥቆር ወይም በቆዳ ቀለም የህሊና እና የሞራል ምጥቀት አይለካምና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትዎን ታዝበናል ፡፡ ከዚህ በላይ እኩይ ሊባል የሚበቃ ድርጊት የለም ፡፡ እናም በዕድሜዎት ምክንያት አንድ እግርዎት ጉድጓድ ውስጥ መሆኑን ተገንዝበው በንስሃ ይኽንን ከአንድ የሠለጠና መንግስት የማይጠበቅ ውሳኔ ቆም ብለው በማሰብ ውሳኔዎ እንዳይተገበር ያደርጉ ዘንድ በትህትና እጠይቅዎታለሁ ፡፡ …

የውጪዎቹ ኃይሎች ሴራ ፤ ኢትዮጵያውያንን በጎሣ ከመከፋፈል ውጪ በጦርነት ድል አድርገን በምድሪቱ ውስጥ ያለውን ሀብት ለመበዝበዝ አንችልም በሚል የሥግብግብነት ቅኝት የተቃኘ መሆኑን እንደምናውቅም እወቁልን ፡፡ ነጮች ፣ በአድዋ ላይ ድል መደረጋቸውና አድዋ በየዓመቱ የበለጠ ገዝፎ መከበሩ  እጅግ አናዷቸዋልና ሽንፈታቸው ዘላለማዊ ታሪክ ሆኖ ፣ አድዋም ታላቅ ቱሪዝም ከተማ ሆና ማየትን አለወደዱምና ፣ ጥቂት ዘረኞች ፤ ይኽ ሆኖ ከማየት ኢትዮጵያ የምትባል አገር ፈጽሞ ከዓለም ካርታ ላይ እንድትጠፋ ፍላጎታቸው ነው ፡፡  ይህንን ብርቱ ፍላጎታቸውንም የሚያሳካላቸው በስግብግብነቱ የታወቀውና ለገንዘብ ሲል ወንድሙን ከመግደል የማይመለሰው ከጥንት የሚውቁት ወያኔ መሆኑን ተገንዝበዋል ፡፡ ይኽ ቡድን ለገንዘብ ሲል የማይፈፅመው ሴጣናዊ ድርጊት እንደሌለ በእጅጉ በመረዳታቸው እና  አልጠግብ ባይነቱንም አብሯቸው የኢትዮጵን ሀብት ሲዘርፍ ና በአሜሪካ ባንኮች ሲያከማች በማየታቸው ፈረሳቸው አድርገውታል ፡፡

ዐይናቸውን በኢትዮጵያ ማዕድነትና የተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚንከላወስ ፣  የአሜሪካ ቱጃሮችም ሆኑ ለተጨማሪ ዘረፋ የሚሯሯጡት ወያኔዎች ፣ ዛሬም እንደትላንቱ የሚታያቸው የሚዘርፉት ሀብት እና የሚያፈሩት ንብረት እንጂ የሚጠፋው የሰው ህይወት  ያሳደጉትን ውሻ ያህል እንኳ ፈጽሞ  አያሳዝናቸውም  ፡፡

እኛ ኢትዮጵያዊያን እነዚህን አገር አውዳሜ ሴረኞች ቁጭ ብለን ማየት አለብን ብዬ በበኩሌ አላምንም። ለዚህም ነው ፣በየአቅጣጫው  መንግሥት ለአሸባሪነት፣ለለየለት የአውሬ ድርጊት  ዘላቂ መፍትሄ እንዲያበጅለት ስንወተውት የባጀነው ፡፡

በዚህ የሞት ና የሽረት ወቅት ፣ ኢትዮጵያ  ታሸንፍ ዘንድ ፣መንግስት ፣ በተሠጠው ህዝባዊ አደራ መሠረት የኢትዮጵያን ህዝብ በወጉ አደራጅቶ ፣ አንቅቶና አስታጥቆ በወያኔ እና በግብራበሮቹ ላይ   የማያዳግም ፣ ተግባራዊ እርምጃ በመውሰድ ፣ እዚህም ቤት እሳት መኖሩን ከዘረፋ ፣እና ከሌብነት ውጪ ሙያ የሌላቸው ሁሉ እንዲገነዘቡ ማድረግ አለበት ፡፡ እግረ መንገዱንም ፣ የህዝብን የፍትህ፣ የሠላምና የሰብአዊ መብት ጥያቄ  በተገቢው መንገድ መመለሥ አለበት ብሎ ይኽ ፀሓፊ ያምናል ።  ይህንን ጥያቄ በአግባቡ መመለሥ የሚቻለውም ፣በመንግሥት ከፍተኛ አመራር ውሥጥም ሆነ በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ፣የኢትዮጵያን ህዝብ ታሪክ ፣ ባህልና ሥነ ልቡና በውል የሚያውቁ  ዜጎች ተገቢ ሥፍራ እንዲኖራቸው  በማድርግ ነው ፡፡

ሀገር፣ዛሬና አሁን ፣ በጥበብ የደረጁ፣ የህዝቡን ባህላዊ እሴት በውል የሚውቁ ፤ እውቀት የዘለቃቸው ፣ ከልባቸው ሰውን የሚያከብሩ ፣ አመዛዛኝ ህሊናን ገንዘባቸው ያደረጉ፣”ከራሥ በላይ ነፋሥ” የማይሉ፣ የሞራል ልእልና ያላቸው ፣ሰው አፍቃሪ ና ትሁት የሆኑ ፣ሰውን በቋንቋው ሳይለዩ ከልብ የሚመወዱ፣ሰውን ለሥራ፣ለእድገትና ለብልፅግና አነሳሽ፣ ተገልጋይ ሳይሆኑ አገልጋይ የሆኑ ፤እጃቸውን ከግፍ የሚያርቁ የመንግሥት ባለሥልጣናት ከላይ እሥከታች ያሥፈልጓታል ።

 ( ፈጣሪዬ ሆይ ! እኔ ሐጥያተኛው ፍጥረትህ ፤ በከንቱ ሥምህን አላነሳምና ፤ ለአንተ የሚሳንህ የለምና ሐጥያታችንን ይቅር ብለህ ፣ እስከ ዕለተ ሞታችን ፣ እንደፈቃድህ እንድንኖር የሤጣንን ዘግናኝ ሥራ ከኢትዮጵያ ምድር ታጠፋልን ዘንድ እለምንሃለሁ ፡፡አሜን ፡፡ )

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop