ሁሉን በምግባሩ እና ተግባሩ እንጥራዉ ! – ማላጂ

ጥንትም ሆነ ዛሬ አገራችንን እየጎዳ የሚገኘዉ ፊት ለፊት የሚገኝ ጠላት ሳይሆን ሁሉን አሜን አድርባይ የወዳጂ ጠላት ነዉ ፡፡

በየትኛዉም አገር እና ታሪክ ህዝብ እና ብዙኃን ፊት ለፊት ከመጣ ጠላት ጋር ተጋፍጦ የተሸነፈ የለም ከዉስጥ ድክመት እና ሽንፈት ዉጭ ሆኖ አያዉቅም ፡፡

አበዉ ከንግግር ይፈረዳል ፤ ከአለባበስ ይቀደዳል እንዲሉ ከንግግሮቻችን እንደ አገር እና ብሄራዊ ጥቅም እና ክብር የሚመጥን መሆን ነበረበት ፤መሆን አለበት ፡፡

ለአብነት ህግ ማስከበር ከሚል የአገር አንድነት እና ህዝብ ደህንነት ለማስቀጠል አገርን ከፍረሰት ህዝብን ከፍልሰት መታደግ የሚያስችል አገራዊ ብሄራዊ ነፃነት ትግል ( አብነት) ሊባል ይገባ ነበር ነዉ ፡፡

እናም ፡-

ከህግ ማስከበር አገር እና ህዝብ ለማሻገር …..የአብነት ትግል እና ጥሪ፣

የቡድን ወረራ እና ምዝበራ ( የትህነግ ቡድን) ከማለት የትግሬ እና ተባባሪ የጥፋት መንጋ የትግሬ ወራሪ እና መዝባሪ መንጋ ከታሪካዊ ጠላቶች የዉስጥ እና ዉጭ ፣ ከሩቅ እና ቅርብ ጠላቶች ጋር ድር እና ማግ ሆኖ አገር ለመፍረስ ፤ህዝብ ለማፍለስ የሚሰራ በመሆኑ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ሁነኛ ጠላቶች መሆናቸዉን በተለይም ሳይቃወም ፤ሳይደግፍ በህቡ በህዝብ ግፍ የሚደሰት እና የሚፅናና ቢኖር እርሱ ነዉ የቅርብ ወዳጂ ጠላት ፡፡

ለብሄራዊ እና ታሪካዊ ጠላቶች የሚዘረጋ የመንግስት እና የህዝብ እጂ እንዴት ከትናንት አስከ ዛሬ ለህዝብ እና አገር ህልዉና ሊነፈግ ይችላል፣

በማንኛዉም ሁኔታ እና ቦታ መጣኝ መረጃ እና ዕርዳታ ሊኖር ይገባል፣

ለማንኛዉም ህዝብ ከራሱ በላይ ማንም ሊታደግ የሚችል ኃይል ስለማይኖር ለራስ ነጻነት እና ክብር የሚመኝ ራሱን ያዳነ ራሱን ያድናል እንዲሉ ራስን እና አገርን ለማዳን ህብረት እና አንድነት ምንጊዜም ያስፈልጋል፣

በየትኛዉም አገሪቷ ክፍል የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ራሱን ፣ ቤተሰቡን ፣ አካባቢዉን እና አገሩን እንደ ንስር በትኩረት ሊጠብቁ ይገባል፣

ጀግኖች ዕረኞች የያዙትን እና የሚጠብቁ ትን በጎች መንጋ ለቀበሮ ትተዉ የጠፉትን በጎች ፍለጋ በመንጋ አይባዝኑም እና ሁሉም በተቀናጀ እና በተደራጀ መልክ ተገቢዉ ጥበቃ ሊደረግ ይገባል ፡፡

የአገር አንድነት እና የህዝብ ደህንነት ሊጠበቅ የሚችለዉ የያዙትን በመልቀቅ በትኖ ከመልቅም ይዞ መጠበቅ ያስፈልጋል ፣

በተለይም በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ (ሰም-ኢትዮጵያ) -ዓማራ ክልል የሚደረገዉ ኢትዮጵያን የማክሰም የጥፋት ትንቅንቅ ሴራ በቀላሉ ሊታይ ስለማይገባ በየትኛዉም የዓማራ ክልል የአስተዳደር ግዛት ይዞታ እና ድንበር ከማንኛዉም ጊዜ በላይ በጥብቅ እና በተጠንቀቅ ሊጠበቅ ይገባል፣

ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን ማዳን አፍሪካን መታደግ እንጅ የአካባቢዉ ህዝብ እና ግዛት ችግር ብቻ አለመሆኑንን በተጨባጭ ማረጋገጥ እና ዕዉነቱን መርገጥ ያስፈልጋል ፡፡

የዓማራ ብሄራዊ መስተዳደር( ሠም-ኢትዮጵያ መስተዳደር) መንግስት እና ህዝብ ለአካባቢዉ እና ኢትዮጵያ አንድነት እና ደህንነት ለሚዋደቁ የዓማራ ህዝባዊ እና ልዩ ኃይል ተገቢዉ የጥቅማጥቅም እና ዕዉቅና ድጋፍ ማለትም የስራ ድጋፍ ፣ ቤተሰቦችን የመጠበቅ እና የመንከባከብ ፣ በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸዉም ሆነ ለሚሳተፉ ኃይሎች እና ቤተሰቦች የተለያዩ አገልግሎቶች ይኸዉም ህክምና ፣ ትምህርት እና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚያገኙበት አሰራር ሊታቀፍ ይገባል ፡፡

ለዓመታት የኢትዮጵያ ህዝብ እና ብሄራዊ ጥቃት የሚያሳስባቸዉ ዜጎች የግል፣ የቤተሰብ ፣የማህበረሰብ እና የህዝብ ደህንነት በማስጠበቅ እና ነጻነት ለማስከበር ህብረት ፣ አንድነት ፣ እና ሙሉ ዝግጂት ( ትጥቅ ጭምር ) ለማድረግ ከህዝብ እና መንግስት አስፈላጊዉ ትብብር ፣ ድጋፍ እና ማዕቀፍ እንዲደረግ በተለያ ጊዜ ህዝባዊ ጥያቄ መቅረቡን እናስታዉሳለን ፡፡

ለዚህም በ2013 ዓ.ም. በተለይም የጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ ፣ሸዋ እና ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ህዝባዊ ኃይሎች / ወጣቶች በነቂስ ወጥተዉ ጠይቀዋል ፡፡

የዓማራ ወጣቶች ወይም የነጻነት ኃይሎች ለ27 ዓመት የነበረዉን ብሄራዊ ጭቆና ግፍ፣ በደል፣ ዘር ፍጅት እና ኢፍትሃዊ ፤ኢሰባዊ ጥፋት በቃ ሞት፣ በቃ ዉርደት ሲል አሁንም ለዚህ ዓይነት ብሄራዊ እና ወቅታዊ የአራስ እና አገር አድን የአደረጃጀት እና ዝግጅት ጥያቄ ዕዉቅና እና ዋጋ አለመስጠት ለዛሬ ብሄራዊ ዉርደት እና ጥቃት ዳርጓል፡፡

ሁላችንም ለራሳችን ፣ ለቤተሰባችን ፣ ለህዝባችን ደህንነት እና ለአገር አንድነት ፤ሉዓላዊነት ለመዘጋጀት የሚቀርብ ጥያቄ አይደለም የግለሰብ ሀሳብ እና አስተያየት የግል፣ ቡድን ፣ ህዝብ እና አገር ከሚኖረዉ ፋይዳ አኳያ ሊወሰድ ይገባል ፡፡ ህዝብን እና አገርን ከሞት ለማዳን የአንድን አካል ይሁንታ እና አለኝታ መጠበቅ ሊበቃ እና በቃ ሊባል ይገባል፡፡

ወዲያ ማዶ የትግሬ ሠራዊት እያለ የህዋት ቡድን እያሉ መግተልተል ራስን ከማዘናጋት ዉጭ ጠብ የሚል የቃላት ቀንብብር ካልሆነ በቀር ሌላ እንደማይኖር ከአስካሁን ( ከ1983- አስከ) የታዩት የመከራ ዘመናት የሚታወቅ ዕዉነት ነዉ ፡፡

የሆነዉ እና እየሆነ ያለዉ የዘመናት እና የክፍለ ዘመኑ መከራ የዓማራ እና የአፋር ህዝብ ብቻ አድርጎ የሚያስብ፣ የሚያሳስብ እና የሚገድብ ፀረ ኢትዮጵያዉነት ካላቸዉ ታሪካዊ ጠላቶች የሚመነጭ እና የሚረጭ መርዝ ነዉ ፡፡

በህዝብ እና በመንግስትም ቢሆን ዕዉነቱን እና መሪሩን ሀቅ ለህዝብ እና ለዓለም ለማሳወቅ ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል ፡፡

ለዚህ እንደአብነት የትግራይ ህዝባዊ ነጻ አዉጭ ግንባር /ኃይል ያካሄደዉ እና እያካሄደ ያለዉን ኢትዮጵያን የማዳከም ስልት ( ዓማራ እና አፋር መዉረር ፤ መመዝበር……..) ሕዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር የትግራይ ህዝብ ሠራዊት ሲሉ መንግስትም ሆነ መገናኛ ብዙሃን የህወኃት ቡድን / ኃይል ማለትን ሲያዞትሩ ይህም በህግ የታገደ ድርጅት ዕዉቅና እንደመስጠት ነዉ ፡፡ ሁለትም አሸባሪ ኃይልን ( ህዝባዊ ወረረራ እና ምዝበራ) ቡድን ማለት ችግሩን የማሳነስ እና ህዝባዊ መረጃን ማዛባት ይሆናል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለህዝብ እና ለአገር አንድነት ደረታቸዉን ለጦር ዕግራቸዉን ለጠጠር እየሰጡ ላሉት ህዝባዊ ነፃነት ኃይሎች በተለምዶ ፋኖ በትክክል ምግባር እና ተግባር ለመመስከር እና ዕዉቅና ለመስጠት የሚቸገሩ እና ዕዉነት የሚመራቸዉ መኖራቸዉ ታዉቆ ሊስተካከል ይገባል፡፡

የኢትዮጵያ ጠላቶች ጠላትነታቸዉ ለዓማራ እና ለአፋር ብቻ አድርጎ የአንድ ክ/ዘመን የጠላት ሴራ አይነት እና ልክ ማሳነስ እና ኢትዮጵያን ከዓለም ምስል ፤ህዝቧን በተለይም ኢትዮጵያዉያንን (ዓማራ….) ከምድርረ ገጽ ለማጥፋት የሚደረግ ትንቅንቅ የብሄራዊ ጥፋት ትልም አካል መሆኑን ለአፍታ ኢትዮጵያዉያን በተለይም ዓማራ ፣ አፋር ፣ ሶማሊያ ……መዘናጋት ሞት እና ሞት ነዉ ፡፡

የዓላማ አንድነት እና ግልፅነት ከቁርጠኛ አቋም እና ከፊት ሆኖ የሚገኝ መሪ ፣አስተማሪ እና አስተባባሪ በእጅጉ የሚፈለግበት ታሪካዊ አጋጣሚ ላይ እንገኛለን ፡፡

የሞኝ ለቅሶ ማልቀስ ህዝብን ከማልቀስ፤ከመፍለስ እና ሀገር ከመፍረስ አይታደግም ፡፡ ስለ ጠላት እና የጥፋት መንጋ ማዉራት እና ማስወራት ቆሞ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ማንነት በተግባር ማስመስከር እንጂ የ100 ዓመት የጠላት የወጥመድ ሴራ መደጋገም ይቁም ፤ ጠላት ጠላት ነዉ በማንኛዉም መንገድ የተለያየ ታብ

ጠላት ህዝባዊ ሠራዊት በሚል አገር እና ህዝብ በመዉረር እና በመመዝበር የሞት ሽረት የጥፋት ትግል ሲግተለተል ከሁለት አሰርት ዓመታት አስቀድሞ መደራጀት እና ህብረት በአንድነት ጠይቋል ፡፡

ጥንትም ሆነ ዛሬ የኢትዮጵያዉን እና የኢትዮጵያ የክፉ ቀን ቁርጥ ቀን ልጆች ጥቂቶች እና የታወቁት በህዝብ እና ዓለም የተመሰከረላቸዉ አነዚህ ዋኖች ናቸዉ፡፡

ሆኖም የዓማራ ክልል መስተዳደር ቢዘገይም በቅርቡ ለዓማራ ህዝብ የዓመታት የመደራጀት ፣ የመተባበር እና አንድነት ጥሪ እና ጥያቄ ምላሽ መስጠቱ ይበል የሚባል ነዉ ፡፡

የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ አስተዳደር ለዓማራ ህዝባዊ ሠራዊት አደረጃጀት ህልዉና ዕዉቅና መስጠት ለሚመለከታቸዉ የክልሉ አመራሮች አገርን ለማዳን የሚደረገዉን የመኖር ፤አለመኖር ትግል የሚያፋፍም በመሆኑ ለብሄራዊ አንድነት እና ህብረት ህዝባዊነት በማስከበር አስካሁን ላሳዩት ቸልተኝነት እና ምንቸገረኝነት ኃላፊነት ወስደዉ ህዝቡን ለመታደግ እና ደሙን ለመመለስ መዘጋጀታቸዉን አሳይተዉናል፡፡

እናም ለዉሸት እና አድር ባይነት ዕምቢ ባይ ትዉልድ መፍጠር ሁሉን በምግባሩ እና ተግባሩ መጥራት እና በዕዉነተኛ የዓላማ ፅናት ለራስ እና ለአገር ዘብ መቆም ያስፈልጋል፡፡

እናመሰግናለን ፤እናከብራችኋለን ……..ኢትዮጵያ ወይም ሞት…… ዓማራ የኢትዮጵያ ዋልታ እና መከታ ነዉ ፡፡

ዓማራ የሞተዉ እና የሚሞተዉ ለኢትዮጵያዊነት እና አንድነት እንጂ …..ለዓማራዊነት አልነበረም አይደለም ፡፡

ማይጨዉ ፣ አደዋ፣ ካራ ማራ……..ኮንጎ……ኮሪያ…… የሞተዉ ወይም መስዋዕት የሆነዉ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ክብር እንጂ ለአንድ ማህበረሰብ ብቻ እንዳልነበር ጠላት የሚናገረዉ ዕዉነት ነዉ ፡፡

ለአገር እና ህዝብ ዋጋ የከፈሉ ነገር ግን በተለያየ ጊዜ የተገፉ ሁሉ ከዚህ በፊት ክህደት የተፈፀመባቸዉ ሁሉ ይቅር ተብለዉ ለራስ፣ ለህዝብ እና አገር ክብር እና ነጻነት እንዲታደሙ ጥሪ ሊደረግ ይገባል ፡፡

ያለምን ቅድመ ሁኔታ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፤ህዝባዊ ሠራዊት (ከ1983 ዓ.ም በፊት ) የአየር ኃይል፣ ባህር ኃይል እና ምድርጦር ጥሪ ሊደረግ ይገባል ፡፡

የቀድሞ ጦር የደረግ ሳይሆን የኢትዮጵያ እንደነበር ጠላት ትህነግ እና ኢምፔራሊስቶች የሚመሰክሩት ዕዉነት ነዉ ፡፡ የኢትዮጵያን ጦር …..በፓርቲ ጦር የቀየረዉን አሰላለፍ ማክሸፍ የድል ምዕራፍ መጀመሪያ ነዉ ፡፡

 

 

ማላጂ

 

“ኢትዮጵያዊነት ተግባር እንጅ ንግግር አይሆንም ፡፡”

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

 

 

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.